Get Mystery Box with random crypto!

Corporate Lawyer

Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer C
Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer
Channel address: @henoktayelawoffice
Categories: Loans, Taxes and Laws
Language: English
Subscribers: 461
Description from channel

⌚️10-11
⚖️" "⚖️

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 6

2022-04-10 21:15:41 ሕጋዊ መከላከል
• የራስን ወይም የሌላውን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገወጥ ጥቃት ለማዳን ጥቃቱ እንዳይደርስ ለማድረግ ሌላ መንገድ ሳይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈጸመ ድርጊት::
ህጋዊ መከላከል በወንጀል የማያስቀጣው የራስን ወይም የሌላውን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገወጥ ጥቃት ለማዳን ጥቃቱ እንዳይደርስ ለማድረግ ሌላ መንገድ ሳይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈጸመ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ. ሪብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 78 ይዘትና መንፈስ የምንረዳው ጉዳይ ነው፡፡ ሕጋዊ መከላከል የወንጀል ተጠያቂነትን የማያስከትለው ተመጣጣኝ የሆነ ዘዴ ወይም መሳሪያ በመጠቀም በቅርብ መድረሱ የማይቀረውን ህገ ወጥ የሆነ ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊ የሆነ ድርጊት መፈፀም ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ. ሪብሊክ የወንጀል ህግ አንቀፅ 78 እነ 79 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ በግልጽ ያሳያል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86570 ቅጽ 15፣ ወ/ህ/ቁ. 78፣ 79
ህጋዊ መከላከልን ከመጠን ማሳለፍ የወንጀሉ ማቋቋሚያ በሆነ ጊዜ እንደ ቅጣት ማቅለያ ምክንያት አይወሰድም፡፡ ህጋዊ መከላከል የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ስለመሆኑ የወ/ሕጉ አንቀጽ 79/1/ ይገልፃል፡፡ በወ/ሕጉ አንቀጽ 541/ሀ/ ሥር ከተመለከቱት የድንጌጋው ማቋቋምያ ምክንያቶች አንዱ ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የነፍስ ግድያ ወንጀል እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ የወ/ሕጉ አንቀጽ 79/1/ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አድርጎ በገለፀው አኳኋን አንቀጽ 541/ሀ/ ሁለተኛው ሀረግ ደግሞ ወንጀሉን ለማቋቋም እንደሚችል ደንግጓል፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ በወ/ሕጉ አንቀጽ 82/2/ እንደተደነገገው ድርጊቱን ለማቋቋም የተደነገገው ልዩ ክፍል ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57446 ቅጽ 12፣ ወ/ህ/ቁ. 79፣ 82(2)፣ 84(2)
Source :-Amharic Legal Glossary,




@Henoktayelawoffice
3.5K viewsedited  18:15
Open / Comment
2022-04-10 07:06:30 ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?

ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡

እነዝህም

አንደኛው የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን

ሁለተኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡

እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡-

አንደኛው:- ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡

ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

ሦስተኛው ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ ተግባራዊ መሆን የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች

* በዘርፉ በመረጃ አያያዝ ጉድለት የነበረውን ችግር ተጠቅመው ጥቂቶች አላግባብ የሚበለፅጉበትንና ህጋዊ ባለይዞታዎችን ለተለያዩ ጉዳቶች ይዳርግ የነበረውን የአሰራር ችግር ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይታመናል።

* የከተማ አስተዳደሮች የሚያስተዳድሩትን መሬት ቆጥረው እንዲያውቁ፣ የትኛውን መሬት ለየትኛው አገልግሎት ማዋል እንዳለባቸው አቅደው እንዲሰሩና በተገቢው መንገድ እንዲያስተዳድሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርግላቸዋል።

* ከተሞች ከመሬት ሃብታቸው መሰብሰብ የሚገባቸውን ግብር እና ኪራይ በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ ለከተማው የመሰረተ-ልማት ግንባታ በማዋል ከተሞች በስርአቱ ያድጋሉ፣ የከተማው ነዋሪም የልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል።

* የካዳስተር ስርዓቱ በሚፈጥረው የመረጃ ምልዑነት በከተማ መሬት ይዞታ የሚስተዋለውን በዜጎች መካከል የሚፈጠረውን ክርክር ይቀንሳል፣ በዚህ ምክንያት የሚያጠፋውን ገንዝብ፣ ጊዜ እና የፍትህ መጓደል ይቀንሳል።

* ማንኛውም ዜጋ በከተማ መሬት ይዞታ ዘርፍ ማግኘት የሚፈልገውን መረጃ ብዙ ውጣ ውረድ ሳይገጥመው በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል።
ጽሁፍ:- የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር
3.2K views04:06
Open / Comment
2022-04-09 18:03:17 ስለ ጣልቃ ገብ

በፍትሃ ብሔር ክርክር ተካፋይ ያልነበረ ሰው የክርክሩ ተካፋይ የሚሆንበትና መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር ተገቢውን ክርክር እንዲያቀርብ በህጉ የተዘረጋ ስርዓት

ጣልቃ ገብ ወደ ክርከሩ የሚገባው በተከሳሽ ጠያቂነት ወይም በራሱ አነሳሽነት ሊሆን እንደሚችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል፡፡ በዚህ ድንጋጌ እንደተመለከተው ሌሎች ወገኖች በሚከራከሩበት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሶስተኛ ወገን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር እንዲፈቀድለት ሊከራከር ይችላል፡፡ ሆኖም የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብ ለመሆን ሌሎች ሰዎች በሚከራከሩበት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የሚነካ መሆኑን የማስረዳት ግዴታውን መወጣት አለበት፡፡ በሌላ አገላለፅ ጣልቃ ልግባ ጥያቄ ተቀባይነት እንዲኖረው ውሳኔው የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ሰው መብትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ በቀጥታ የሚፈጸም መሆኑንና ሌላ አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላል፡፡

ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ጣልቃ ገብ ልሁን በሚል ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው ውሳኔው በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የማይጎዳ ከሆነ እና አዲስ ክስ በማቅረብ ማስቀረት የሚቻልበት ሁኔታ ያለው ከሆነ ጥያቄው በህግ ፊት ተቀባይነት የሚያገኝበት ሁኔታ የሌለ መሆኑን ነው፡፡

ጣልቃ ልግባ የሚለው ወገን በተከራካሪ ወገኖች መካከል ባለው ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ መብቱን በምን አግባብና መልኩ ሊነካ እንደሚችል ማሳየት እንደአለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41(2) ድንጋጌ ያሳያል፡፡ በመሆኑም አመልካቹ ዝርዝር ምክንያቱን በማስፈር ይህንኑ የማስረዳት ግዴታ አለበት፡፡ የጣልቃ ገብነቱ አቤቱታ ሊቀርብ የሚገባውም ጊዜ ለማራዘም፣ ክርክሩን ለማጓተት ሊሆን እንደማይገባው ከተጠቃሹ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ከፍትሃ ብሔር ስነ ስርዓት ህጉ መሰረታዊ አላማ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ.95934 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41

በአንድ ክስ ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች በክርክር ላይ ባሉበት ጊዜ ማናቸውም ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ያገባኛል የሚል ሲሆን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብ ሆኖ ለመከራከር እንደሚችል እና የጣልቃ ገብነት ማመልከቻው በክሱ ውስጥ ያገባኛል የሚልበትን ምክንያት የሚዘረዝርና በተለይም የመብቱን ሁኔታ የሚገልጽ መሆን እንዳለበት፣ እንዲሁም የጣልቃ ገብነት ጥያቄ አቅራቢው በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር የሚያስችል መብት ያለው መሆን አለመሆኑ በቅድሚያ ሊወሰን እንደሚገባው፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል መብት የለውም በተባለ ጊዜ መሰናበት እንደሚገባው እና መብት አለው በተባለ ጊዜ ግን የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን ከተደረገ በኃላ ከጣልቃ ገቡ መብት አንፃር ጭምር አጠቃላይ ክርክሩ ተመርምሮ ተገቢ ነው የሚባል ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ከፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 41 (1)፣ (2) እና (3) ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡

ቤትና ይዞታን በሚመለከት በሚደረግ ክርክር አንድ ጣልቃ ገብ አመልካች ክርክር በሚደረግበት ቤትና ይዞታ ላይ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር መብት አለኝ በማለት መብቱን የሚያሳዩ ሰነዶችን አቅርቦ እያለ የባለይዞታነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አላቀረብክም ተብሎ ከወዲሁ ጣልቃ ገብተህ ልትከራከር አትችልም ተብሎ አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ አግባብነት የለውም፡፡

የሕግ መረጃ ለማግኘት
#Ethiopia #Law

#Join #Invite ሊንኩን ይጫኑ
ኢትዮ-ሕግ Ethio-Law

@Henoktayelawoffice
ሰ/መ/ቁ. 90713 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41
2.9K views15:03
Open / Comment
2022-04-09 17:56:05 የስራ ማስታወቂያ
NGOs Platform Manager (local title HINGO Forum Director)
#danish_refugee_council
#legal_services
#political_science
#program_manager
Addis Ababa
Postgraduate qualifications in international relations, political science, development, or other relevant fields with progressive international experience working with UN, NGOs, and/or Donor agencies preferably with experience in fragile and post-conflict contexts at the senior leadership/management level
Quanitity Required: 1
Minimum Years Of Experience: #7_years
Deadline: April 15, 2022
How To Apply: Register using the following link https://www.drc.ngo/about-us/careers/vacancies/job/?p=163915
2.4K views14:56
Open / Comment
2022-04-09 17:55:09 አዋጅ ቁጥር 1267/2014 አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ
2.4K views14:55
Open / Comment
2022-04-09 17:54:53 የስራ ማስታወቂያ
Information Counselling and Legal Assistance (ICLA) Officer
#the_norwegian_refugee_council_nrc
#legal_services
#law
#legal_counsel
Assosa
University degree in Law with relevant work experience. Fluency in English, both written and verbal
Quanitity Required: 1
Minimum Years Of Experience: #3_years
Deadline: April 15, 2022
How To Apply: Register using the following link https://ekum.fa.em2.oraclecloud.com/hcmUI/CandidateExperience/en/sites/CX_1001/requisitions/preview/5742/?location=Ethiopia&locationId=300000000306687&locationLevel=country
Note: Female Candidates are highly encouraged to apply and will be given a priority for the position.
2.8K views14:54
Open / Comment
2022-03-31 17:12:18 የወንጀል ክስን ክዶ መከራከር፣ተበዳይ ጋር ታርቆ አለመካስ እና የፍርድ ቤትን ወጪ መሸፈን የወንጀል ቅጣት ገደብ ቅድመ ሁኔታወች አይደሉም!!!!!
~~~~~
የሰ/መ/ቁ 1857ዐዐ፡- የወንጀል ቅጣት ውሳኔ ሊገደብ የማይቻልባቸው ልዩ ሁኔታዎች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 194 ስር በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ በዚህ አንቀፅ ስር ቅጣት እንዳይገደብ የተቀመጠው ክልከላ ፡-
1ኛ/ ጥፋተኛው ከዚህ በፊት የፅኑ እስራት ቅጣት ወይም ከ3(ሶስት) ዓመት በሚበልጥ ቀላል እስራት ቅጣት ተፈርዶበት ከሆነ እና አሁን ጥፋተኛ በተባለበት ወንጀልም ከእነዚሁ ቅጣቶች አንዱ የሚወሰንበት ከሆነ፤
2ኛ/ ከዚህ በፊት ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ ፅኑ እስራት የሚፈረድበት ከሆነ፤
3ኛ/ የቅጣት አፈፃፀሙ ከመታገዱ በፊት ጥፋተኛው በተራ ቁጥር 1 እና 2 ስር ከተመለከቱት ቅጣቶች ውስጥ በአንዱ ሊያስቀጣው የሚችል ሌላ ወንጀል ስለመፈፀሙ የተደረሰበት ከሆነ፤
4ኛ/ ወንጀለኛው ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተና በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 200 ስር በተመለከተው አኳኋን አስቦ አንድን ወንጀል የፈፀመ ከሆነ ወይም
5ኛ/ የቅጣት አፈፃፀሙ በታገደለት ጉዳይ የተሰጠው የፈተና ጊዜ መልካም ፍሬ የሚያስገኝ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ሲረዳው የሚሉት ናቸው፡፡ እናም ፍርድ ቤት አንድን የወንጀል ቅጣት ከመገደቡ በፊት የቅጣት ውሳኔው እንዳይገደብ ከእነዚህ መመዘኛዎች ውስጥ በአንዱ ክልከላ ያልተደረገበት መሆኑን በቅድሚያ ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡
ተከሳሹ ክሱን ክዶ መከራከሩ፣ ከተበዳይ ጋር ታርቆ አለመካሱ እና የፍርድ ቤቱን ወጪ ለመሸፈን የሰጠው ማረጋገጫ የመኖር የአለመኖር መመዘኛዎች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 197 መሰረት ጥፋኛው በተሰጠው የፈተና ጊዜ ውስጥ በመልካም ጠባይ እንዲመራ እና የፈተና ጊዜው ተገቢውን ፍሬ እንዲያፈራ በሚል ለመልካም ጠባይ አመራር ዋስትና የሚሰጡ ትዕዛዛት እንጂ ቅጣትን ለመገደብ ቅድመ ሁኔታዎች አይደሉም፡፡
በሰ/መ/ቁ/172111 ላይ የተሰጠው ውሳኔ በወንጀል ጥፋተኛ ከተባሉት ግለሰብ የግል ሁኔታ አንፃር የፈተና ጊዜ ቢሰጣቸው በመልካም ጠባይ የሚመሩ ለመሆኑ አሳይተዋል የሚያስብል ነገር አልተገኘም በሚል አቋም የተያዘበት ጉዳይ እንጂ ሁሌም ቢሆን የወንጀል ክስ ክዶ የተከራከረ ወይም ከተበዳዩ ጋር ታርቆ ተገቢውን ካሳ ላልከፈለ የወንጀል አጥፊ ቅጣት ሊገደብ አይገባም የሚል ግልፅ ትርጉም አይደለም፡፡
በመሆኑም የወንጀል ክስን ክዶ መከራከር በራስ ላይ ማስረጃ ካለመሆን እና የወንጀል ጥፋተኝነቱ በማስረጃ እስኪረጋገጥ ድረስ ንፁህ ሆኖ ከመገመት ህገ መንግስታዊ መብት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የወንጀል ክስ ያላመነ ሰው የቅጣት ውሳኔ ሊገደብለት አይገባም በሚል ትርጉም ሊሰጥበት የሚቻል ጉዳይም አይደለም፡፡የካቲት 3ዐ/2ዐ13 ዓ.ም

.......?..........................
በሌሎች ሰበር ውሳኔዎች ለምሳሌ በቅፅ 24 ሰ/መ/ቁ 177216 እና 171403 ላይ እንደ አማራጭ ቅድመ ሁኔታዎች ሆነዋል ፡፡

telegram.me/henoktayelawoffice
5.4K viewsedited  14:12
Open / Comment
2022-03-29 20:11:08
ከ100የአሜሪካን ዶላር በታች ይዘው በመገኘታቸው የተፈረደባቸው ወይም የተከሰሱ ሰዎች ቅጣታቸው በይቅርታ እንዲታይ ወይም ክሳቸው እንዲቋረጥ የፍትህ ሚኒስትሩ ወስነዋል! ከዚህ መጠን በታች ይዞ የተገኘ ሰው ገንዘቡ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ የወንጀል ክስ እንዳይመሰረትበትም ተወስኗል።
5.4K views17:11
Open / Comment
2022-03-29 12:07:03 አዲሱ የንግድ ሕግ ( በአማርኛ )
telegram.me/henoktayelawoffice
@ethiolawblog
4.8K viewsedited  09:07
Open / Comment
2022-03-28 19:34:54
telegram.me/henoktayelawoffice
4.7K views16:34
Open / Comment