Get Mystery Box with random crypto!

Corporate Lawyer

Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer C
Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer
Channel address: @henoktayelawoffice
Categories: Loans, Taxes and Laws
Language: English
Subscribers: 461
Description from channel

⌚️10-11
⚖️" "⚖️

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 4

2022-05-27 08:32:50
1/የቀበሌ ቤት ለሶስተኛ ወገን በምን አግባብ ይተላለፋል?
2/የቀበሌ ቤት መሸጥ ይቻላል ?
3/የቀበሌ ቤት በውርስ ማግኘት ይቻላል?
የሚሉትና መሠል ጥያቄዋች በጠበቃ በቂ ማብራሪያና ምላሽ ስለተሰጠባቸው ይህን ሊንክ በመጫን መስማት ትችላላቹ
https://youtube.com/channel/UCFRKg_th2M2xAIiN6s9W7rg
1.1K views05:32
Open / Comment
2022-05-26 21:05:20
ግንቦት 16/2014 የተሰጠ የሰበር ትርጉም

በወንጀል ክርክር ጉዳይ ፍርድ ቤት መዝገብ ሲዘጋ የተከሳሽ አቆያየት በተመለከተ ትእዛዝ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ - ማረሚያ ቤት እና አቃቤ ህግም አቆያየቱ በተመለከተ ምንም በፍርድ ቤት ትእዛዝ ያልተሰጠበት ታሳሪ ሲገጥማቸው እርስ በእርስ ተናበው አቆያየቱ በተመለከተ ትእዛዝ እንዲሰጥ በመጠየቅ ያለባቸው ስለመሆኑ
1.7K views18:05
Open / Comment
2022-05-23 19:23:18

1.7K views16:23
Open / Comment
2022-05-18 17:30:38
2.0K viewsedited  14:30
Open / Comment
2022-05-11 08:11:37 ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
#የድምፅ ብክለት


የድምፅ ብክለት ክልከላ ባለቤቱ ስራውን የሚፈፅመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም ድርጊቱ ሌላውን ጎረቤት እንዳይረብሽ፣ እንዳያውክ፣ ወይም ችግር እንዳያስከትል በማድረግ መብቱን ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን አድማስ የሚወስን ስርዓት መሆኑን ከአንቀፅ 1226 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
0953758395
Henok Taye/ሄኖክ ታዬ
በማንኛውም ፍ/ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም ያግኙ


#HenokTayeLawOffice
#Ethiopia
#AddisAbaba
https://t.me/HenokTayelawoffice
2.9K views05:11
Open / Comment
2022-05-11 08:11:37 በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች

ተጨማሪ የሕግ መረጃ በቴሌግራም
https://t.me/HenokTayeLawoffice

የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።

ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦
https://t.me/HenokTayeLawoffice

#የመፋለም ክስ ( petitory action)


ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡

ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡

ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)

N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
#ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat)


እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው።

አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል......
ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገዱ አይደሉም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 43226)
https://t.me/HenokTayeLawoffice
N.B= ይህ ሲባል ግን የህጉን መስፈርት ያላሟሉ ውሎች (illegal contract) ከህገ ወጥ ውል በተለየ ሁኔታ ታይተው የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆንባቸው መሆኑን መረዳት ይገባል።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
#የመንግስትን መሬት የማስመለስ ክስ


ግለሰቦች በፌደራሉ እና በክልሉ መንግስት በወጡ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ በሚደነግጉት መሰረት በህጋዊ መንገድ ሳይሰጣቸው ከህግ ውጪ የወል ወይም የመንግስትን መሬት ይዘው መቆየታቸው እና የመሬቱ ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታቸው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ሊያደርጋቸው አይችልም። በወረራ የተያዘ የመንግስት መሬትም ይርጋ የሌለው መሆኑን የአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 በግልፅ ያስቀምጣል።

በመሆኑም ከህግ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን መኖራቸውን ሲረዳ መሬት አስተዳደርም ሆነ የመንግስት ወኪል የሆነ አካል መሬቶቹን ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ)https://t.me/HenokTayeLawoffice

#በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ የግለሰብ ይዞ መሬት


ከላይ እንደተመለከትነው ህገ ወጥ ውልን መሰረት አድርጎ የግለሰብን መሬት በያዘ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 መሰረት ህጉ በማይፈቅድበት መንገድ በሀይልም ሆነ በህገ ወጥ አግባብ የገጠር መሬትን ይዞ የተገኘ ግለሰብ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የለውም።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
N.B= በህገ ወጥ መንገድ የሚለው ሀሳብ በህግ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን የያዘን በሚመለከት እንጂ የህጉን መስፈርት ባላሟላ ውል ወይም ተግባር (illegal contrat) አማካኝነት የተያዘን መሬት የሚመለከት አይደለም። ምክንያቱም መሬቱን የያዘው በህጉ በተፈቀደ የውል ተግባር ሆኖ የሚፈለገውን ፎርማሊቲ ወይም መስፈርት አለማለቱ ብቻ አያያዙ ህገ ወጥ ነው የሚያስብል ስላልሆነ ነው።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
#የአደራ ውል


አደራ ተቀባይ በአደራ የሚጠብቀውን ዕቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውል ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ ዕቃውን መመለስ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2781(1) የተመለከተ ሲሆን በውል ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከሌለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዲያውኑ እንደሚመለስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2989(1) ስር ተመላክቷል።

ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው አደራ ተቀባይ ዕቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዲቀመጥ የሰጠው ዕቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን ነው።
https://t.me/HenokTayeLawoffice
#የውርስ ሀብት ክፍፍል
2.3K views05:11
Open / Comment
2022-05-07 07:44:52 አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ
3.7K views04:44
Open / Comment
2022-05-05 17:58:21
4.0K views14:58
Open / Comment
2022-05-04 12:44:33
#Ads
ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ ዙሪያ የሚሰሩ ሦስት ትላልቅ የሕግ ቻናሎችን አሁኑኑ ይቀላቀሉ
ለመቀላቀል ከታች የሚገኙትን ማስፈንጠሪዎች ይጠቀሙ
1.8K views09:44
Open / Comment
2022-04-30 13:53:11 በንግድ ሕግ ቁ. 674/1/ ድንጋጌ መሰረት በኢንሹራንስ ውል ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ማንኛውም ክስ ጥያቄውን ለማቅረብ የሚያስችለው ምክንያት በተከሰተ ወይም ጥቅም ያላቸው ወገኖች ጉዳዩን ካወቁበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜውስጥ መቅረብ አለበት፡፡ የይርጋ ጊዜውን ለመወሰን የፍትሐብሔር ሕግ ቁ. 1677 እና 1845 በኢንሹራንስ ጉዳይ ላይ አግባብነት የላቸውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 46778 ቅጽ 10፣ ን/ህ/ቁ. 674/1/፣ ፍ/ህ/ቁ. 1677፣ 1845

ጉዳት የደረሰው በመድን ዋስትና ውል ባልተሸፈነ ሁኔታ ነው በሚል ምክንያት የኢንሹራንስ ድርጅት የከፈለው ካሳ እንዲመለስለት የሚያቀርበው ክስ ሁኔታውን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ይታገዳል፡፡

በተሸሸገ ወይም በሐሰት ቃል የቀረበ ጉዳይ ያጋጠመ ሲሆን የይርጋው ዘመን የሚታሰበው ኢንሹራንስ ሰጪው የተሸሸገውን ወይም በሐሰት የቀረበውን ቃል ካወቀበት ቀን ጀምሮ

እንደሆነ በንግድ ሕግ ቁ. 674(2) ተደንግጓል፡፡ የይርጋው ዘመን ሁለት ዓመት እንደሆነም በዚሁ ቁጥር ንኡስ ቁ (1) ተመልክቷል፡፡

ሰ/መ/ቁ 42309 ቅጽ 9፣[11] ን/ህ/ቁ. 674/1/

6. የመድን ጥቅም

የመድን ጥቅም /insurable interest/ ያለው ሰው ሲባል በደረሰው አደጋ ወይም ጉዳት በትክክል የተጎዳ ወይም ሊጎዳ የሚችል ሰው ማለት ነው፡፡

መድን ሰጪው ካሣ የሚቀበለው ጉዳት በደረሰበት ወቅት ጉዳት በደረሰበት ንብረት ወይም እቃ ላይ የመድን ጥቅም ያለው ሰው ሲሆን የመድን ጥቅም የሌለው ሰው ካሣ ለመጠየቅ የሚያስችለው የሕግ መሰረት የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 47004 ቅጽ 13[12] Abrham Yohannes
1.7K views10:53
Open / Comment