🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.40K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 16

2023-04-15 08:21:01
2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ "ሴቭ ዘ ችልድረን" የተባለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ተቋም ገለጸ፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ባለመጀመራቸው ምክንያት 2.3 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ተማሪዎች አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

የመማሪያ ክፍሎች እንደገና ተከፍተው ተማሪዎችን ያስተናግዱ ዘንድ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል ተቋሙ።

በመላ ሀገሪቱ ከ 3.5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት (ከ16 ህጻናት አንድ) ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።

ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑት ህጻናቱ፤ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለጾታዊ ጥቃት እና ላልተፈለገ ጋብቻ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል።

በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውድመት አስተናግደዋል።

በትግራይ ክልል 85 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተጎዱ ሲሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ መሆናቸውን የድርጅቱ መረጃ ያሳያል።

22, ሺህ 500 መምህራን ከሁለት ዓመት በላይ ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንደቆዩም ድርጅቱ አስታውሷል።

ምንጭ፦ Save the Children

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-15 08:21:01
ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ሊሰጥ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት ማቆሙ ይታወቃል።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የተሻሻሉት መመሪያዎቹ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ፈቃድ የነበራቸውን ጨምሮ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ እንደ አዲስ ምዝገባ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ምዝገባው በዘንድሮ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን በ2016 ዓ.ም አዲስ ፍቃድና የእድሳት አገልግሎት መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 360 የሚጠጉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መረጃ ያሳያል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-15 08:21:01
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ የሰራተኞች የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ሠራተኞች በተቋሙ እንቅስቃሴ እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ተወያይተዋል።

አክሱም፣ መቐለ፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-15 08:21:01
ወደፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ" የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የውይይት መድረክ የትምህርት ሚኒስትር
ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የማድረጉ ሂደት በተያዘው ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሮ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ በስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።

“መስፈርቱን አሟልተው የሚፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲኖሩ"፤ አዋጁ ወደፊት የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎችንም የሚመለከት መሆኑን ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል።

ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከፍለው የሚማሩ መሆን እንዳለባቸውም ዶ/ር ሳሙኤል አመልክተዋል።

“ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ አይመደብላቸውም” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፤ ፍትሃዊነትን ለማምጣት ሙሉ እና ከፊል-ነጻ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

ረቂቁ “ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት” ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከሚያበቁ መስፈርቶች መካከል እንደሚካተቱ ይጠቅሳል።

ለዚህም “ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኳቸው ውጤታማ ለመሆን ሀብት ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው።

ሀብት ለማመንጨት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎቹ “የንግድ ድርጅት ሲያቋቁሙ፤ ሌላ ነጋዴ መስራት የሚችለውን ሳይሆን ከተልዕኳቸው ጋር የሚመጋገብ” መሆን እንዳለበት ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-15 08:21:01
"በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል።"

የትምህርት ሚ/ር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በአገር አቀፍ ደረጃ ከ47 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አዲስ ወግ በተሰኘ የውይይት መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን መስፈርት ባሟላ መልኩ የተገነቡ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ዘመቻ ለማከናወን ዕቅድ መዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዘመቻው በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት እንደሚሰራም ሚኒስትሩ መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-15 08:21:01
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉትን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው "ራስ ገዝ" ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ገልጸዋል፡፡

በዚህም የፋይናንስና የሰው ኃይል አደረጃጀት መመሪያ ተዘጋጀቶ ከሰራተኞች ጋር ውይይት መደረጉንና መመሪያው በቀጣይ ለቦርድ ውሳኔ የሚቀርብ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውይይት እየተደረገበት ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የአዋጁን መጽደቅ እየጠበቀ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆን የአካዳሚ፣ የአስተዳደር፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የምርምር ተልዕኮ የተሰጣቸውና የመጀመሪያው ትውልድ ተብለው የተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ" እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2.0K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-15 08:21:01
የትርጉም እና አስተርጓሚነት ሙያ ስልጠና ስርዓተ ትምህርት ረቂቅ ተዘጋጅቷል፡፡

ረቂቅ ስርዓተ ትምህርቱ በአዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

ረቂቁ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት 3ኛው ሀገር አቀፍ የትርጉም ጉባኤ ላይ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በኢትዮጵያ የትርጉም እና አስተርጓሚነት ሙያን ማሳደግና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ላይ ትኩረት ያደረገ የቋንቋ ፖሊሲ፤ በ2012 ዓ.ም ወደ ሥራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2.6K viewsedited  05:21
Open / Comment
2023-04-14 19:20:02
የዛሬው ዕለት:—

በእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን ወር የመጨረሻው ጁሙዓ ነው።

በክርስትና እምነት ተከታዮችም የአብይ ፆም የመጨረሻዎቹ ቀናት ስቅለት የሚከበርበትና ስግደት የሚፈፀምበት ዕለት ነው።
ሁላችንም ለፈጣሪ የቀረቡ ተግባራት በመፈፀም በየቤተ እምነቶቻችን አናሳልፋለን።ሀገራችንንና ህዝባችንን በዱዓ/ፆለታችን እናስብ

Team: @NATIONALEXAMSRESULT
4.2K viewsedited  16:20
Open / Comment
2023-04-14 13:39:53
የ1 GB የኢንተርኔት ዳታ ስጦታ ከኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም የስቅለት በአልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ ቀን የሚቆይ የ1 GB የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ስጦታ ለደንበኞቹ አበርክቷል።

ይሁንና እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራምና ዩትዩብ የመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛዎች ላይ የተጣለው ክልከላ ዛሬም ባለመነሳቱ ደንበኞች ስጦታውን መጠቀም የሚችሉት "በቪፒኤን" በመግባት ብቻ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
4.9K viewsedited  10:39
Open / Comment
2023-04-14 13:39:53
ATM ስትጠቀሙ ተጠንቀቁ

ከአንድ ATM ተጣቃሚ ቤተሰባችን ሁለት/ሦስት ሆነው ተሰላፊ መስለው በመምጣት አንደኛው ሚስጥር ቁጥሩን በማየት አንደኛው እየቀለደ "የእኔ ATM እምቢ ብሎኝ ነው" በማለት አደናግሮዎት የእርሶን ልሞክር ብሎ ATM card በመቀየር ይሰወራሉ። እንዲህ አይነት ነገር ሲፈጠር እጅዎት ላይ ያለው card የእርሶ መሆኑን ያረጋግጡ። የእርሶ ካልሆነ በፍጥነት ደውለው ያዘጉት።

ሲጠቀሙ ከኃላዎት ያለው ሰው ቢያንስ 1 ሜትር ርቀት ካልቆመ እንዲጠጋ ይንገሩት ተሳስቶ ከሆነ ለእርሱም እንዲህ አይነት የሌብነት ዘዴ እንዳለ ያስረዱት።

ሚስጥር ቁጥር ሲያስገቡ በአንድ እጆት ይሸፍኑ በተጨማሪም ሲፅፉ ፈጣን ይሁኑ። ተከታትለው የኪስ ቦርሳዎትንም እንዳይሰርቆት ብር ካወጡ በኃላ ከዋላዎት የነበሩ ሰዎች አለመከተላቸውን ይቃኙ።

ሼር አድርጉት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
4.3K viewsedited  10:39
Open / Comment