Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.92K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 305

2021-01-31 13:49:59
የጥሪ ማስታወቂያ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.0K viewsedited  10:49
Open / Comment
2021-01-31 10:20:05
ለልደት፣ ለምርቃት እና ለማንኛውም አይነት ስጦታ #ሰዓቶችን_በሚፈልጉት_ሰው_ፎቶ ወይም በድርጅት ሎጎ እንሰራለን በብዛት ለሚያዝ እና ለማከፋፈል ለሚፈልጉ ቅናሽ እናደርጋለን።
#ባለ_ቆዳ 300
#ባለ_ብረት 400

#በተጨማሪም_የተለያዩ_ለስጦታ_የሚሆኑ ኩባያዎች ፣ ትራስ ፣ ቲሸርት ፣ የግድግዳ ሠዓቶችን እና ሌሎችንም በፈለጉት ፎቶ አሳምረን እንሠራለን፡፡

Order us via Telegram @habeshagifts1
or Call 0935199954
አድራሻ፡- አውቶቡስ_ተራ_መሳለሚያ ወይም ጀሙ mina mall ህንፃ ወይም ሜክሲኮ
ወደ ክልል ከተሞች በፖስታና በሹፌር በታማኝነት እንልካለን።

For more products
#JOIN_OUR_CHANNEL
https://t.me/joinchat/AAAAAE_-T4p_QITNQ151fA
8.4K views07:20
Open / Comment
2021-01-30 15:33:35
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ
-----------------------------------------
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 6ኛ ዓመት ድረስ የሚማሩ እንደሆነ ተመልክቷል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ከሰተ ለገሰ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው 13 ሺህ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ተማሪዎችን ከአውቶቡስ መነኸሪያ እና መቀሌ ከተማ ተቀብለው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማስገባት የተማሪዎች ህብረት አመራሮች ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ያለምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የምግብ ፣ መኝታ ፣ መማሪያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ መብራት እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መሰናዳታቸውን ዶክተር ከሰተ አስታውቀዋል።

የጊቢው የማፅዳት ስራ መጠናቀቁን አመልክተው የመማር ማስተማር ስራው የሚካሄደው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያስችል መንገድ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ለሚመጡ ተማሪዎች ከጥር 28 እስከ 30፣ 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሀ አቀባበል ይደረጋል ብለዋል።

ከአቀባበሉ በኋላ የመማር ማስተማሩ ሥራ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የመማሪ ማስተማር ስራ ሲጀመር በመልካም ሥነ-ምግባር ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል።
(ምንጭ፦ኢዜአ)

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
9.0K viewsedited  12:33
Open / Comment
2021-01-30 10:55:22
አምቦ እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

አምቦ ፣ ቦንጋ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠኗቸውን ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቁ ነው፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ እያሰመረቃቸው ያሉት ተማሪዎች ከ5 ሺህ 73 ናቸው። ከተመራቂዎቹ መካከል 1ሺህ 810 ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።

የምረቃው ሥነ-ሥርዓት በዩኒቨርሲቲው ሥር ባሉት ሃጫሉ፣ ጉደር ማሞ መዘምር፣ ወሊሶ ካምፓስና ዋናው ግቢ የሚያጠቃልል ነው። (ENA)

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.5K viewsedited  07:55
Open / Comment
2021-01-30 10:54:37
መቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያየ የትምህርት መስክ ትምህርታቸውን የተከታተሉ 2,896 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.3K viewsedited  07:54
Open / Comment
2021-01-30 09:56:49
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተመራቂ ተማሪዎች ከተዘጋጀው መድረክ ውጪ የተመራቂ ወላጆች እና ወዳጅ ዘመዶች በተለመደዉ መንገድ በመመረቂያ አዳራሽም ሆነ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተገኝተው ምርቃቱን መታደም አልቻሉም።

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢ.ቲ.ቪ ቋንቋዎች እና በኢ.ቲ.ቪ መዝናኛ ቻናሎች በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ይገኛል።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.2K viewsedited  06:56
Open / Comment
2021-01-30 09:30:56 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተመራቂ ተማሪዎች በጠዋቱ ደምቋል።
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ በ39 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 518 ተማሪዎችን ለ7ኛ ጊዜ ዛሬ ያስመርቃል፡፡ ከተመራቂዎች ውስጥም 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
የ7ኛ ዙር ተመራቂዎችም በመጀመሪያ ዲግሪ 2 ሺህ 486 (በመደበኛውና በኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ)፤ በሁለተኛ ዲግሪ 32 ተማሪዎች እንደሆኑ ከዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ዳዊት ብርሃኑ በተለይ ለአብመድ እንደገለጹት የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የምረቃ ጊዜያቸው የተራዘመባቸው ናቸው።
እንደ አቶ ዳዊት ማብራሪያ ዩኒቨርሲቲው በ2012 ዓ.ም በሁለተኛው ግማሽ ዓመት በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች የሚማሩ 12 ሺህ 874 ተማሪዎች ነበሩት፡፡ ከነዚህ ውስጥም 4 ሺህ 690 ሴቶች ናቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በሚያከናውነው የምረቃ መርሃ ግብርም በመደበኛው 1 ሺህ 905 (ወንድ- 1 ሺህ 207 ሴት-698) እንዲሁም በተከታታይ ትምህርት 581 (ወንድ-274 ሴት-305) ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ይመረቃሉ፡፡
በኀይድሮሊክስ፣ በደቨሎፕመንታል ኢኮኖሚክስ፣ በአካውንቲንግ፣ በጆግራፊና ቴፍል ቀደም ሲል ሳይመረቁ የቀሩ 32 የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችም በዚህ የምረቃ መርሃ ግብር ተካተዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው 47 ትምህርት ክፍሎች አሉት፡፡ ለዛሬ ምረቃ ያበቃቸው ተማሪዎችም በ39 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ነው፡፡
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ሰብአዊ ፣ በተፈጥሮ ቀመርና ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ፋኩሊቲዎች፤ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በሜዲስን ትምህርት ቤት የተዋቀረ የሶስተኛው ትውልድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው፡፡
የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በ2022 ዓ.ም በምርምር ሥራዎች፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በማሕበረሰብ አገልግሎቶችና በሌሎችም ተግባራት ከኢትዮጵያ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ለመሆን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡

Via AMMA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.5K viewsedited  06:30
Open / Comment
2021-01-30 01:43:26 በተደጋጋሚ ለተጠየቅነው ጥያቄ ምላሽ:-

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ይፋ አልተደረገም።

@NATIONALEXAMSRESULT
8.0K viewsedited  22:43
Open / Comment
2021-01-29 22:57:58
ለኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ #ለማታና_እረፍት_ቀናት ተማሪዎች በሙሉ

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 ዓ.ም ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት የገፅ ለገፅ መማር ማስተማር ቆሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን የማታና እረፍት ቀናት የዲፕሎማና ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በ26/05/2013 ዓ.ም እንዲጀምሩ ወስኗል፡፡
በመሆኑም የሚወጣላችሁን ሳምንታዊ የትምህርት ፕሮግራም በመመልከት በትምህርት ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
• ወደ ክፍል ስትመጡ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እና ሳኒታይዘር መያዝ ግዴታ ነው፡፡

ከኮሌጅ/ፋኩልቲ/አካዳሚ የማታና እረፍት ቀናት ትምህርት አስተባባሪዎች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል!

የኮ.ሜ.ዩ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት

ምንጭ፦ የዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.4K viewsedited  19:57
Open / Comment
2021-01-29 21:20:39
የሲዳማ ክልል የ8ኛ ክፍል ውጤት እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ይፋ ይደረጋል።

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የ2012 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል የፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ገልጿል።

ፈተናው የሲዳማ ህዝብ በክልልነት ከተደራጀ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠጠ ነው።

በአሁኑ ወቅት ፈተናው ታርሞ የተጠናቀቀ ሲሆን እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና መማ/ማስ/ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታፈስ ገ/ማርያም አሳውቀዋል።


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.2K viewsedited  18:20
Open / Comment