Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.75K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 298

2021-03-17 13:00:42
ዩኒቨርሲቲዎች በ2013 የመጀመሪያ አመት መቀበል የሚችሉትን የተማሪ ቁጥር ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቃቸዉን ገለጹ፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 አ.ም የ12ኛ ክፍል ትምህርት በመቋረጡ አጠቃላይ ሀገራዊ ፈተና ባሳለፍነዉ ሳምንት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርም የፈተናዉን ዉጤት በአጭር ጊዜ እንደሚያወጣ አሳዉቋል፡፡ ሀገር አቀፍ የፈተና ዉጤት ይፋ ሲደረግ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ መደበኛ የትምህርት መርሃግብር የተለየ ይሆናል፡፡

ዩንቨርስቲዎች ነባር ተማሪዎችን በቅርቡ ከመቀበላቸዉ አንጻር የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን ለመቀበል ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ ሲል አሀዱ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎችን ጠይቋል፡፡

የአዳማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የትምህርት መርሀ ግብሩን አዛብቶታል ብለዋል፡፡

ቢሆንም የ2013 አ.ም የመጀመሪያ አመት 2 ሺ 200 ተማሪዎችን ለመቀበል የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች አድርገን ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም አሳዉቀናል ብለዋል፡፡

የ2013 አ.ም የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅታችንን አጠናቀን ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ከ4 ሺ 500 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ያስታወቁት ደግሞ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ የወላይታ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በሶስት ካምፓሶች 4ሺ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

አሐዱ ቴቪ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
6.6K viewsedited  10:00
Open / Comment
2021-03-17 13:00:32
#ማስታወቂያ

#ጊቢ Meme
በዩኒቨርሲቲ life ላይ ብቻ የተሰሩ አዝናኝ እና አስቂኝ ሜሞችን ለማግኘት የጊቢ meme የቴሌግራም ቻናልን ተቀላቀሉ

JOIN US

@gibimemes
6.2K views10:00
Open / Comment
2021-03-16 17:37:54 AASTU NEW CALENDER

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.4K viewsedited  14:37
Open / Comment
2021-03-16 12:30:09 "ዩንቨርሲቲው የሚያስፈልጉትን ነገሮች ግዢ ላይ ነው እስከ መጋቢት 20 ድረስ ተማሪዎች ሊገቡ ይችላሉ ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ።"

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት መልዕክት

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.8K viewsedited  09:30
Open / Comment
2021-03-16 11:45:49 የቻናል ጥቆማ

ንባብ የምትወዱ ከሆን ምን አልባት የሚጠቅሞትን FILEs በ PDFs መልኩ ከእኛ ሊያገኙ ይችላሉ።

በእርግጠኛነት ቻናሉን ይወዱታል፤ ቤተሰብ ይሁኑን

ይሄው ሊንኩ

https://t.me/joinchat/0btKCYSJmxgxYTFk
7.6K views08:45
Open / Comment
2021-03-16 11:45:14 ጅማ ዩኒቨርሲቲ

DYNAMICS And HYDROLICS1 ያል ወስዳችሁ (ኣድ) ምታደርጉ ተማሪዎች ዛሬ ከ 7:00 ጀምሮ እስከ 12:00 ድረስ በ ተማሪዎች ህብረት ቢሮ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

DYNAMICS &HAYDROLICS 1
BARATTOONNI DYNAMICS FI HYDROLICS 1 HIN FUDHANNE YKN ADD GOOTAN BIIROO GAMTAA BARATTOOTAATTI SA'AA 7:00- 12:00 DHUFTANII AKKA GALMOOFTAN ISIN BEEKSIFNA.

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.0K viewsedited  08:45
Open / Comment
2021-03-15 21:03:03
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚክስ ት/ክፍል የ2013 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ የሆነችዉ መኪያ ደገፉ በኢትዮጲያ የፊዚክስ ባለሙያዎች ማህበር የሚዘጋጀዉን “Askok-Shobhana Gholap Award” በአገር አቀፍ ደረጃ ለሴት ተማሪዎች የተዘጋጀዉን ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡

ሽልማቱንም የት/ክፍሉ ኃላፊ እና መምህራን በተገኙበት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ19/06/2013 ዓ.ም. በተከናወነዉ 15ኛዉ ዓመታዊ የኢትዮጲያ የፊዚክስ ባለሙያዎች ማህበር ጉባዔ ላይ ተቀብላለች፡፡
ት/ክፍሉም የተሰማዉን ታላቅ ደስታ በመግለጽ መኪያ ደገፉን እንኳን ደስ አለሽ ለማለት ይወዳል፡፡

ቀሪው ጊዜም የስኬት እንዲሆንላት በመመኘት የመኪያ ስኬት በሌሎች የትምህርት ክፍሉ ሴት ተማሪዎች እንደሚደገም በመተማመን ነው፡፡

B.D.U.S.U

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.1K viewsedited  18:03
Open / Comment
2021-03-15 10:13:20
የአስትራዜንካ ክትባት ጥቅም ላይ እንዳይውል ያገዱ ሀገራት 7 ደረሱ!

ኔዘርላንድ የደም መርጋት የጤና ችግር ያስከትላል ስትል የአስትራዜኒካ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዳለች፡፡ የኔዘርላንድ መንግስት ለቀጣዮቹ 15 ቀናት የክትባት መድሃኒት እንደማይሰጥም አስታውቋል፡፡ከኔዘርላንድ አስቀድማ አየርላንድ ፣ በኖርዌይ በአንድ ጎልማሳ ላይ የክትባት መድሃኒቱ የደም መርጋት የጤና እክል በማስከተሉ የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ ወስናለች፡፡ከኔዘርላንድ እና አየርላንድ በተጨማሪ ዴንማርክ ፣ ኖርዌይ ፣ ቡልጋሪያ ፣ አይስላንድ እና ታይላንድ የአስትራዜኒካ ክትባት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አግደዋል፡፡

አስትራዜኒካ በበኩሉ ደም ያረጋል የሚለው መረጃ ምንም ማረጋገጫ የሌለው ሲል አስተባብሏል፡፡በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እና በእንግሊዝ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜኒካን ክትባት መውሰዳቸው ተሰምቷል፡፡የአስትራዜኒካ የህክምና ዋና ሓላፊ 17ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ወስደው ከ 100 ያነሱ ሰዎች ላይ ብቻ የደም መርጋት ተከስቷል መባሉን ተከትሎ የቫይረሱ ባህሪ እንደ ግለሰቡ የጤና ሁኔታ ሊለያይ ይችላል፡፡

Bisrat FM

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.8K viewsedited  07:13
Open / Comment
2021-03-14 20:56:41
የጥሪ ማስታወቂያ ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ኤክስቴንሽን ተማሪዎች

ለኣክሱም ዪኒቨርስቲ ኤክስቴንሽን /ኢ- መደበኛ/ እንዲሁም መደበኛ የሁለተኛ ድግሪ (ማስተርስ) ተማሪዎች ት/ት የሚጀሙሩበት ቀን ጥሪ አቀረበ።

- ለነባር ወይም ስንየር የኤክስተንሽን(ኢ-መደበኛ) ድግሪ ተማሪዎች ከመጋቢት 11/2013ዓ/ም ጀምሮ እንዲገቡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤

- ከመጋቢት 15 -16/2013ዓ/ም ባለው ጊዜ ለሁሉም #መደበኛ# የሁለተኛ ዲግሪ(ማስተርስ) ተማሪዎች የአንደኛ ሴሚስተር ኖርማል ምዝገባ ይካሄዳል።

- ለሁሉም የኤክስተንሽን (ኢ-መደበኛ) ማስተርስ ተማሪዎች ከመጋቢት 18-19/2013ዓ/ም ባለው ጊዜ የአንደኛ ሴሚስተር ኖርማል ምዝገባ ያደርጋሉ።

(ጌታቸው ካሕሱ /የአክሱም ዩኒቨርስቲ አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት ሃላፊ)

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.5K viewsedited  17:56
Open / Comment
2021-03-14 15:53:51
ከላይ የቀረበው ጥያቄ ላይ ( https://t.me/nationalexamsresult/7560 ) ለመለሱት መልስ ከስር Comment መስጫው ስር ምክንያትዎን መግለጽ ይችላሉ።

ESHU &
Team: @NATIONALEXAMSRESULT
9.0K views12:53
Open / Comment