Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.75K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 306

2021-01-29 21:20:39
የሲዳማ ክልል የ8ኛ ክፍል ውጤት እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ይፋ ይደረጋል።

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የ2012 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል የፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ገልጿል።

ፈተናው የሲዳማ ህዝብ በክልልነት ከተደራጀ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠጠ ነው።

በአሁኑ ወቅት ፈተናው ታርሞ የተጠናቀቀ ሲሆን እስከሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና መማ/ማስ/ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታፈስ ገ/ማርያም አሳውቀዋል።


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.2K viewsedited  18:20
Open / Comment
2021-01-29 19:55:33 ለመላው ኢትዮጵያውያን የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቀረበ ጥሪ

አንድ እሽግ ቆሎ(1kg) ለወገኔ

ውድ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አንጋፋው ዩኒቨርሲቲያችን በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል በቅ ዝግጅት አድርጎ መጥራቱ በጣም የሚያስደስት ነው ደግሞም እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን ።

ሁላችንም እንደምናውቀው በትግራይ ክልል እንደኛ ተምረው ለመለወጥ አላማ ያላቸው ብዙ እህት ወንድሞች ተሰደዋል ፤ ለረሃብም ተዳርገዋል።

እኛም ወደ ግቢ ስንሄድ ለወገኔ 1kg ቆሎ በሚል የቻልነውን ያህል፦ ቆሎ፣ ሞኮሮኒ፣ ሩዝ፣ ፖስታ፣ ኩኪስ ...ወዘተ ቶሎ የማይበላሽ ማንኛውንም ምግብ ሆነ መጠጥ እና የሚቻል ከሆነ የሴቶች እና ህፃናት የንፅህና መጠበቂያዎች እንደ (ሞዴስ፣ዳይፐር፣ሳሙና፣ኦሞ....የመሳሰሉ) ይዘን ብንሄድ፤

ሁሉም ካምፓስ በር ላይ የሚረከብ አካል አመቻችተናል፤ ወይም የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት እየሄዳችሁ መስጠት ትችላላችሁ ።
       ዋና ግቢ
1. Titina Tedros 0913133678
.Teacher Eyuel 0914768256
.Teacher Betelhem 0914857638
2. Eyerusalem - 0960706053
        ዓይደር ግቢ
1.Abraham Awoke 0935212853
2.Gedam  090 984 9699
          ኲሓ ግቢ
1.Temesgen Bayu 0966034877
2.-Tsion tadelle 0932000884
               MIT ግቢ
1. Goitom 096 685 2127
          ዓዲ ሓቂ ግቢ
1.091 493 8723 Aredom
        Veterinary Campus
1. 092 672 8579 Gere

ከ መቐለ ዩኒቨርስቲ በጎ አድራጎት
አስተባባሪዎች

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.7K viewsedited  16:55
Open / Comment
2021-01-29 13:24:37 በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ለነበሩና በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጪ ለሆኑ ሕፃናት የአስቸኳይ ጊዜ የተከታታይ ዓመት ትምህርት መርኃግብር ይፋ ሆነ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)፣ ጄኔቫ ግሎባል እና ኢጁኬሽን ካንኖት ዌት ይፋ ያደረጉት ፕሮግራም፣ በምሥራቅ ሐረርጌ አራት ዞንና በምሥራቅ ወለጋ ዞን አንድ ወረዳ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተሰምቷል፡፡

ኤጁኬሽን ካንኖት ዌይት የተባለው ተቋም ለመርኃግብሩ ማስጀመሪያ 82 ነጥብ 14 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ጄኔቫ ግሎቫል 6 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በመመደብ በዓመት 8 ሺ 274 ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውንም ተሰምቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በነበረው ሁከት ምክንያት ከትምህርት ገበታ የተፈናቀሉ ሕፃናትና ቀደም ሲል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጪ የነበሩ እድሜቸው ከ9 እስከ 14 የሆናቸው ሕጻናት ያባከኑትን የትምህርት ጊዜ በተፋጠነ የትምህርት አሰጣጥ መርኃግብር በመደገፍ ከዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር በክፍል እንዲስተካከሉ ማድረግ የመርኃግብሩ ዓላማ ነው ተብሏል፡፡

አካል ጉዳተኛ እና ሴት ሕጻናትን በበለጠ ይጠቅማል በተባለው የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት መርኃግብር በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ30 ሺህ የሚበልጡ ሕፃናትን በትምህርት፣ እንዲሁም ከ30 ሺ የሚበልጡ እናቶቻቸውን ደግሞ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በግጭቱ ምክንያት ከምሥራቅ ሐረርጌና ከኦሮሚያ ዞኖች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩና ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ሕፃናት የአስቸኳይ ትምህርቱን ከጀኔቫ ግሎባልና ከኢጁኬሽን ካንኖት ዌት ጋር በመተባበር ተግባራዊ የሚያደርጉ አምስት ግብረሰናይ ድርጅቶች በውድድር መመረጣቸውንም የጄኔቫ ግሎባል ዓለምአቀፍ ተቋም የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ሳሙኤል አስናቀ ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በ2018 ሰራሁ ባለው ጥናቱ መሠረት ዕድሜአቸው ለትምህርት የደረሱና ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው ከትምህርት ቤት ውጪ የሆኑ ሕፃናት ቁጥር በኢትዮጵያ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ነው ብሏል፡፡

[Sheger FM]


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
9.8K viewsedited  10:24
Open / Comment
2021-01-28 20:37:48
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
10.3K viewsedited  17:37
Open / Comment
2021-01-28 20:06:11
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
10.1K viewsedited  17:06
Open / Comment