Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.75K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 300

2021-03-11 13:42:43
በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የቴሌግራም አገልግሎት አሁን መስራት ጀምሯል!

ኢትዮጵያ ቼክ ማረጋገጥ እንደቻለው የቴሌግራም መተግበርያ በመላው ኢትዮጵያ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ መስራት አቁሞ ነበር።

በበርካቶች ዘንድ መልእክት ለመለዋወጫ ተመራጭ እየሆነ የመጣው ቴሌግራም ለምን መስራት እንዳቆመ በግልፅ ባይታወቅም ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያያዞ አንዳንድ የቴሌግራም ግሩፖች ላይ ህገወጥ ፅሁፎች ሲንሸራሸሩ እንደነበር ቅሬታዎች ሲቀርቡ ነበር።

ከሚመለከተው አካል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ እያረግን የነበረ ሲሆን መልስ ማግኘት አልቻልንም። ዛሬ ቀትር ላይ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ቴሌግራም ዳግም መስራት ጀምሯል።

Via Ethiopia check

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.1K viewsedited  10:42
Open / Comment
2021-03-11 13:08:38 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እና በቅርቡ እንደሚገለጽ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ከየካቲት 29 - መጋቢት 02 ,2013ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የሁሉም ድርሻ ከፍተኛ እንደነበረ ገልፀው ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት፣ ተማሪዎች እና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እንደ ሀገር የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ የትምህርት ጊዜ ወደ ኋላ እንዳይቀር እና የተማሪዎች የትምህርት ዘመን እንዳይራዘም መደረጉንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በዘንድሮው የፈተና አሰጣጥ ስርቆትን ለማስቀረት 8 ፈተናዎችን በ 32 ስብጥር በማድረግ ኩረጃ እንዳይኖር መደረጉም በመግለጫው ተነስቷል።


የፀጥታ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ፈተናውን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉንም ሚኒስትሩ በመግለጫው አንስተዋል።

የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤቱም በቅርብ ጊዜ እንደሚገለፅ እና ተፈታኞችም በዚሁ አመት ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተገልጿል።

የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናውን ከ 358 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውስዳቸው ተነግሯል

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.7K viewsedited  10:08
Open / Comment
2021-03-11 13:04:38
ለትግራይ ክልል እና መተከል ዞን አካባቢ ተፈታኞች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ አስተያየት ይደረጋል ተባለ !

በትግራይ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አካባቢ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ወደ ከፍተኛ ትምርት ተቋማት በሚያስገባው የማለፊያ ነጥብ ላይ አስተያየት እንደሚደረግ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ በሰጡት መግለጫ፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና በትግራይ ክልልና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ በአካባቢያቸው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ስነበሩ በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ላይ አስተያየት እንደሚደረግላቸው ጠቅሰዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ፈተናው በሰላም መከናወኑን አመልክተዋል።

ለዚህም የመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ አስነብቧል።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.9K viewsedited  10:04
Open / Comment
2021-03-11 13:03:54 ለ3 ተከታታይ የፈተና ቀናት ያለምንም እርምጃ ተቆይቶ የፈተናው የመጨረሻ ቀን ላይ የቴሌግራም አገልግሎት [ በሞባይል ዳታ በኩል ] እንዲቋረጥ ተደርጎ የነበረ ሲሆን አሁን ቴሌግራም ዳግም መስራት ጀምሯል!

ከመጀመሪያው የፈተና ቀን አንስቶ እስከ ትናንት ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ስብሰባ ላይ ሆኖ ነው ወይስ ስልጠና

@NATIONALEXAMSRESULT
5.9K views10:03
Open / Comment
2021-03-10 20:59:07 የተማሪዎች መልዕክት

" ሰላም ኪራ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋንቅው ካምፓስ ነው የምጽፍልህ

እንደሚታወቀው ወደጊቢ ተመልሰናል። የሚገርመው ግን በጣም ትንሽ ተማሪ ነው የተመለሰው። አብዛኛው ተማሪ አምና የነበረውን ረብሻ እና ችግር ፍራቻ ነው ወደ ጊቢ ያልተመለሰው። ዘንድሮም ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ፈርተው በጣም ብዙ ተማሪዎች ቀርተዋል። ዶርም ውስጥም በጣን ትንሽ ነን። ወደ ጊቢ የተመሰውም አጠቃላይ ተማሪ በሚያሳዝን ሁኔታ በጣም ትንሽ ነው። "


ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
3.1K viewsedited  17:59
Open / Comment
2021-03-09 22:09:02
እንወያይ!

ስልክ ተይዞ እንዳይገባ ፥ ፈታኞችም ሆኑ ተፈታኞች በሕጉ መሰረት ፈተናውን እንዲያየጠናቅቁ መከታተል እንጂ ግሩፕ ማሳደድ ነው ወይ የሚያዋጣው? ለ4 ቀናት የቴሌግራም እና የFB አገልሎትን መያዝስ ቀላል ከጉዳቱ ጥቅሙ አያመዝንም፡ ነበር ወይ? ነው።

የእርስዎ ሐሳብ ምንድን ነው? ከታች ባለው comment መስጫ ላይ ያስፍሩ እንወያይ!

#SHARE
Team : @NATIONALEXAMSRESULT
1.7K viewsedited  19:09
Open / Comment
2021-03-09 22:05:34 " ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቅሬታ እየቀረበ ነው። ይህንን ተከትሎ ግን " ፈተናው ይሰረዛል ፥ ወደሌላ ቀን ይዘዋወራል …" የሚሉ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ መረጃዎች ተማሪዎችን ግራ እያጋቡ ነው፡፡ እንዲህ ያለ ውሳኔ አልተወሰነም፡፡ ለመወሰንም አልታሰብም። ስለዚህ ተፈታኝ ተማሪዎች የቀሩትን 2 የፈተና ቀኖች በእርጋታ ሆነው ሳይረበሹ ሊጨርሱ ይገባል። ምናልባትም አሁን ላይ በተጋነነ ደረጃ ሆነ እንጂ በስልክ የፈተና መልስ መሰጣጠት ከዚህም በፊት የነበረ ነው። ከዚህ በፊትም እንዲህ ሲያደርጉ የተያዙ ተማሪዎች አሉ። አሁንም ቴሌግራም በሚባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ አንድ ግሩፕ እንደተዘጋ መረጃው አለን። ስለዚህ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ተረጋግተው ሊፈተኑ ይገባል። ትናንትና እንደነገርኩሽ በኛ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በተቻለን አቅም ይህ አይነት ጉዳይ እንዳይከሰት እየጣርን ነው። "

ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር አድሚናችን ( admin 4) ለሁለተኛ ቀን በስልክ ከነበራት ቆይታ የተወሰደ።



የኛ ሀሳብ:

ኢትዮጲያ ቼክ ለትምህርት ሚኒስቴር "ኢንተርኔት ይዘጋል ወይ" ብሎ በጠየቀበት ወቅት " ይህ አይነት አሰራር የድሮ አሰራር ነው" አይነት ምላሽ የሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር እንዲህ አይነት በጠራራ ፀሐይ የሚፈጸም የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ለ2 ተከታታይ ቀናት ሲፈጸሙ ዝምታን መርጧል፡፡

በእርግጥም መልስ ሲዘዋወርባቸው ከነበሩ የቴሌግራም ግሩፖች ውስጥ አንዱ ተዘግቷል፡፡ ጥያቄው ግን ስልክ ተይዞ እንዳይገባ ፥ ፈታኞችም ሆኑ ተፈታኞችም በሕጉ መሰረት ፈተናውን እንዲያየጠናቅቁ መከታተል እንጂ ግሩፕ ማሳደድ ነው ወይ የሚያዋጣው? ለ4 ቀናት የቴሌግራም እና የFB አገልሎትን መያዝስ ቀላል ከጉዳቱ ጥቅሙ አያመዝንም፡ ነበር ወይ? ነው።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
1.8K viewsedited  19:05
Open / Comment
2021-03-09 13:48:50
ትምህርት ሚኒስቴር በክልሎች ያለውን የፈተና አሰጣጥ ትኩረት ይስጠው

ትምህርት ሚኒስቴርን የበላ ጅብ አልጮህም አለ!

ጭራሽ ሰልፊ

ፎቶ:- ATC

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.7K viewsedited  10:48
Open / Comment
2021-03-09 09:33:00
በ "Other Natural science" ውስጥ የተመደባችሁ ተማሪዎች መካከል ወደ Engineering & computing መግባት የምትፈልጉ ዛሬ የካቲት 30/2013 ዓ.ም እስለ ቀኑ 6:00 ሰዓት ብቻ በጥሪ ኢንጂነሪንግ ማስተባበሪያ ቢሮ ቁጥር 10 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከምትመዘገቡት ውስጥ የተሻለ CGPA ያላችሁ 57 ተማሪዎች ብቻ ወደ Engineering & computing መግባት የምትችሉ መሆንህን እንገልጻለን፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.3K viewsedited  06:33
Open / Comment
2021-03-09 09:26:54 ትምህርት ሚኒስቴር በክልሎች ያለውን የፈተና አሰጣጥ ትኩረት ይስጠው


Admin 4:
" ትናንትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ ስልክ ይዘው በገቡ ተማሪዎች አማካይነት ከፈተና ጣቢያ ውጪ ካሉ ልጆች ጋር መልስ እየተላላኩ ነበር። ይህንን ጉዳይ እኛም አንዳንድ ግሩፖች ላይ አይተናል። ቁጥጥራችሁ እስከምን ድረስ ነው? ስልክ ይዘው የሚገቡ ተማሪዎችንስ በዚህ ልክ ፈር የለቀቀ ስራ መስራት ይገባል ወይ? "

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ :
" እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፈተናው ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው መመሪያ መሰረት በጥንቃቄ እንዲሰጥ እና ከኩረጃ እና ከመሳሰሉት ነገሮች ነጻ እንዲሆን በተቻለን አቅም ሁላ እየሰራን ነው። ምናልባት ከከተማዋ ውጪ ባሉ የክልል ፈተና ጣቢያዎች አሁን አንቺ ያልሺኝ ጉዳይ ተከስቶ ይሆናል እንጂ ስልክ ወደ ፈተና ጣቢያ ይዘው እንስኪገቡ የሚያስችል አሰራር በየትኛውም የአዲስ አበባ ከተማ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች እንደሌለ ግን በጣም እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን። "



ትናንትና የጠዋት ፈተና ከተጠናቀቀ በኋ ጀምሮ ከተፈታኝ ተማሪዎች ከላይ የተባለውን ጉዳይ አስመልክቶ በጣም ተሰጋጋሚ ቅሬታ ሲላክልን ነበር፡፡ ይሁንና የሌሎችን ተማሪዎች የፈተና ሳይኮሎጂ ላለመረበሽ ቅሬታቸውን አልለጠፍነውም ነበር።

ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በአንድ አድሚናችን አማካኝነት ደውለን የተሰጠን ምላሽም ከላይ ያለው ነው። ይሁንና በአንዳንድ ክልሎች ዘንድ ያለው የፈተና አሰጣጥ ሂደት ግን ካቻምና ከነበረው ያልተለየ እንደሆነ ከምናየው አንጻር ታዝበናል።

የፈተናው አሰጣጥ ፍትሐዊ መሆን አለበትና ስለተማሪ የምትጨነቁ ከሆነ በተገቢው መንገድ ይሰጥ ዘንድ የኛም ጥያቄ ነው

Team: @NATIONALEXAMSRESULT
5.2K viewsedited  06:26
Open / Comment