Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.92K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 304

2021-02-08 15:52:28
በሑመራ ከተማ ትምህርት ተጀመረ

በሑመራ ከተማ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር መጀመሩን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በሕግ ማስከበር ሂደቱ ከተማዋ ከጥፋት ኃይሎች ነፃ ከወጣች በኋላ ማኅበረሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ በሪሁን እያሱ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም በከተማዋ ትምህርት ለማስጀመር ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ በሪሁን እንዳሉት በትምህርት ቤቶች የነበሩ ችግሮችን በመለዬት ቁሳቁስ እንዲሟሉ ተደርጓል፤ መምሕራንን በማሟላትም ደመወዝ እስከመክፈል ተደርሷል፡፡ በመሆኑም ዛሬ በአምስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም ባለሙያዎችን በመመደብ፣ መምሕራንን በማሟላትና ማኅበረሰቡን በማወያዬት ትምህርት ቤቶችን መልሶ በማደራጀት ሥራው ስኬታማ እንዲሆን ደግፏል ብለዋል፡፡ አሁንም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው አቶ በሪሁን ያስታወቁት፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
10.8K viewsedited  12:52
Open / Comment
2021-02-06 21:33:32
ማስታወቂያ
ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

እንደምታወቁት የ2012 ተመራቂ የሆናችሁ ለጊቢያችን ተማሪዎች የምረቃት ቀን የካቲት 20/2013 እንደሁነ የታወቅ ስሆን፣ በአሁን ጊዜ አሉባልታ የሆነ መረጃዎች በተማሪው ዘንድ እየተሰራጨ መሆኑን እና በሀሰተኛ ወሬ ቀኑ ተቀንሰው በ13/06/2013 ሆነዋል ተብለው እየተነገረ ያለ ስለሆን፣ የተባለ ያለው መረጃ ሀሰት መሆኑን ተገንዝባችሁ እና ምንም አይነት የቀን ለውጥ እንደለሌ እንድታወቁ እናሳውቃለን።

Barattoota Universiti Haramaya Hundaaf!!!

guyyaan eebbaa gaafa guyyaa 20/6/2013 tahu isin yaadachifna.

Barattoonni odeefanno sobaa gidduu barattoota oofa jirtan oduu sobaa kanarraa akka of-qusattan isiniin janna.
Odeefannoo sirrii hordafuuf page gamtaa barattoota UH akka hordaftan isiniin janna.

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
13.5K viewsedited  18:33
Open / Comment
2021-02-06 18:43:42
CAUTION

"ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል አለ" - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጋቸው ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል መኖሩን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ትምህርት ቢሮው ይህን ያሳወቀው በባህር ዳር ከተማ "እንድናገለግሎ ማስክዎን ያድርጉ" የሚል ንቅናቄ በተጀመረበት ወቅት ነው።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ ትምህርት እንዲቀጠሎ ተደርጎ መከፈታቸው ይታወሳል።

ምንም እንኳን ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱም በኮሮና ቫይረስ መከላከያ ላይ ያለው አተገባበር በታሰበው መልኩ እየሄደ አይደለም ተብሏል።

ተማሪዎች ትምህርት ቤት ዳግም የተከፈተ ሰሞን ጥሩ ጥንቃቄ ያደረጉ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ትኩረት እያጡ መከላከያውም እየተረሳ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ ፥ አሁን እየታየ ያለው መዘናጋት እና ግዴለሽነቱ ካልቆመ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሊዘጉ እንደሚችሉ አሳስበዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለው ፥ በክልሉ ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያን ተግባራዊ በማድረግ ሊመጣ እና ሊያጋጥም ከሚችለው አደጋ እራስን መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

AMMA/EPA/ENA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
12.5K viewsedited  15:43
Open / Comment
2021-02-06 15:41:14
ብዙዎችን ያስገረመው የዛሬው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ምርቃት ፕሮግራም ክስተት።

ዛሬ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ በነበረበት ወቅት እና የምርቃት ስርአቱ በቀጥታ ስርጭት በአማራ ቴሌቪዥን እየተላለፈ በነበረበት ወቅት ተመራቂ ተማሪ ዮሴፍ በመድረኩ ላይ ተንበረከከ። ታዳሚዎች ምን ሆኒ ይሆን እያሉ ግራ ሲጋቡ ለተመራቂ ተማሪ የምስራች ታገቢኛለሽ ወይ ሲል የጋብቻ ጥያቄ አቀረበ። እርሷም አዎ ብላ እሺታዋን የገለጸችለት ሲሆን ቀለበት አስሮላታል፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
11.3K views12:41
Open / Comment
2021-02-01 20:29:50
ትምህርት ሚኒስቴር አሁንም ዝግጁ ነኝ እያለ ነው

ሚኒስቴሩ በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ገለጸ
----------
የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡

በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር ተግባር በጸረ-ሰላም ሃይሎች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የትምህርት መሻሻል ዳይሬክተር ጀነራል ዮሐንስ ወጋሶ በተለይ ለዋልታ እንደገለጹት፣ የትመህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ በቅርቡ ትምህርት የሚጀመርባቸው አካባቢዎች እንደሚኖሩም አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችንም ለመፈተን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራም እየተሰራ ስለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም በቤኒሻንጉል ክልል በመተከል ዞን በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተነሱ ተማሪዎች መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ ዮሐንስ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር ትምህርት ማስጀመር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

የተለያዩ አጋር አካላትን ጭምር በማስተባበር የዝግጅት ምዕራፉ በፍጥነት ተጠናቆ በአካባቢው የመማር ማስተማር ሂደቱ በሚፈለገው ፍጥነት እንዲጀመር ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡
(በሜሮን መስፍን)

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
4.3K viewsedited  17:29
Open / Comment
2021-02-01 20:05:24 ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥር 28 እና 29 ቀን 2013 አ/ም በግቢው በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ የወጣው ማስታወቂያ ያመለክታል።

ተማሪዎች በፊት በነበራችሁበት ካምፖስ በተጠቀሰው ቀን በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እና የዲፓርትመንት ምደባችሁን ደግሞ ከጥር 26 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የኦንላይን አድራሻ estudent.ambou.edu.et ማየት ምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

ይህንንም ተከትሎ ከተቀመጠው ቀን ዘግይቶም ይሁን ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርቲው እንደማይቀበል ያሳስባል።

ተማሪዎች በኮሮና ወረርሺኝ ሳቢያ ለረጅም ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ዳግም መንግስት ባስቀመጠው የመከላከል መርህ ተማሪዎች በጥንቃቄ የመከላከል መርሆችን እየተከተሉ ትምህርታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ መወሰኑን ተከትሎ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ተመራቂ ተማሪዎችን ቀጥሎም ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎችን ጥሪ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን እያስቀጠለ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መስፈርት ጥር 22 ቀን 2013 አ/ም ለማስመረቅ ዝግጅቱን አጠናቋል፤ይህንንም በማስመልከት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከመቀነስ አንፃር ዩኒቨርሲቲው ባስቀመጠው የመከላከል መርህ ተመራቂ ተማሪዎች ግቢውን ከለቀቁ በኃላ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን በመቀበል ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በመወሰኑ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ከላይ በተቀመጠላችሁ ጊዜ መሰረት በግቢው በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል።

Via AUSUE

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
4.5K viewsedited  17:05
Open / Comment
2021-02-01 15:55:38 ትምህርት ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሳምንት ዝግጅት ጨርሰናል ማለቱ አይዘነጋም!
ትምህርት ሚኒስቴር በቃሉ የሚገኘው መች ይሆን?

@NATIONALEXAMSRESULT
5.7K views12:55
Open / Comment
2021-02-01 15:51:13
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ #ከሕዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት_ማሳሰቢያ_ተሰጠው!!!

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸው "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ 'ታብሌቶች' ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

ENA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.5K viewsedited  12:51
Open / Comment
2021-02-01 15:51:05
ለልደት፣ ለምርቃት እና ለማንኛውም አይነት ስጦታ #ሰዓቶችን_በሚፈልጉት_ሰው_ፎቶ ወይም በድርጅት ሎጎ እንሰራለን በብዛት ለሚያዝ እና ለማከፋፈል ለሚፈልጉ ቅናሽ እናደርጋለን።
#ባለ_ቆዳ 300
#ባለ_ብረት 400

#በተጨማሪም_የተለያዩ_ለስጦታ_የሚሆኑ ኩባያዎች ፣ ትራስ ፣ ቲሸርት ፣ የግድግዳ ሠዓቶችን እና ሌሎችንም በፈለጉት ፎቶ አሳምረን እንሠራለን፡፡

Order us via Telegram @habeshagifts1
or Call 0935199954
አድራሻ፡- አውቶቡስ_ተራ_መሳለሚያ ወይም ጀሙ mina mall ህንፃ ወይም ሜክሲኮ
ወደ ክልል ከተሞች በፖስታና በሹፌር በታማኝነት እንልካለን።

For more products
#JOIN_OUR_CHANNEL
https://t.me/joinchat/AAAAAE_-T4p_QITNQ151fA
5.0K views12:51
Open / Comment
2021-02-01 13:01:30
ወደሌላ ዩኒቨርሲቲ መዘዋወር ተከልክሏል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ የተማሪ ከተቋም ተቋም ዝውውር እንዳይፈጸም አሳስቧል።

አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተማሪዎች የሚያቀርቡትን የዝውውር ጥያቄ ተቀብለው እያስተናገዱ ነው ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቀን 21/05/2013 ቀን ጀምሮ ዝውውር እንዳይፈጸም አግዷል።

በዚህ የትምህርት ዘመን ዝውውር የሚፈጸመውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ታይቶ ሲፈቀድ ብቻ እንደሆነ አሳስቧል።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
6.0K viewsedited  10:01
Open / Comment