2021-03-22 18:49:20
“የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድርሻ እና አስተዋፅኦ ለሀገራዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች በዘርፉ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
==================================================
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የልማት ፖሊሲ፤ የፖሊሲው ማስተግበሪያ ፕሮግራሞች እና የቀጣይ 10 ዓመታት የልማት መሪ እቅድ እና ቁልፍ የውጤት አመልካች / KPI / ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ፖሊሲና ስትራቴጂው ለሀገሪቱ የብልጽግና ጉዞ ሚናው የላቀ መሆኑን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲገነዘቡና የየራሳቸውን ድርሻ እንድወጡ ታሳቢ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ፖሊሲው ከሀገራዊ የአስር አመቱ እቅድ መነሻ ያደረገ በመሆኑ የጋራ በማድረግ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግበር አስፋላጊ በመሆኑ ከአመራሮች ጋር ውይይት ማድረግ እንዳስፈለገ ፕሮፌሰር ሚኒስቴር ዴኤታዉ አክለዋል፡፡
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው በፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና መሪ እቅዱ ዙሪያ ሥልጠና ተዘጋጅቶ እንዲወያዩበት መደረጉ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል፡፡
በሥልጠና ፕሮግራሙ የሁሉም የግል ከፍተኛ ተቋማት፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር፣ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ ፣ የተጠሪ ተቋማት እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀዉ ሥልጠና በአዋጅ 1097/2011 እና አዋጅ 1152/2011 የተቀመጡ ቁልፍ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተልዕኮዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከመጋቢት 13-14/7/2013ዓ.ም ለሁለት ቀናት ይሰጣል
ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
3.4K viewsedited 15:49