🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.40K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 295

2021-03-25 20:58:32
ትግራይ፡ የአክሱም ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከጥቃት ተረፉ

መጋቢት 16፤ 2013 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ ትግራይ) በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት አካባቢ የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ድንገቴ ጥቃቱ በተደረገበት በቅርብ ርቀት ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ የሚጓዙ ተማሪዎች ከጥቃቱ ተርፈዋል፡፡

የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች እንደተረዳው፡- ከአዲግራት አቅጣጫ በመምጣት ላይ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ላይ የሕወሓት ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተዋል፡፡ በታጣቂዎቹ ጥቃት ወታደሮቹን ጨምሮ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ዓድዋ በማምራት ላይ የነበሩ ሲቪል ተጓዦችም ይገኙበታል፡፡ 8 የአካባቢው ገበሬዎችን ጨምሮ የ17 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ እንደ ዓይን እማኞች ምስክርነት በጥቃቱ 25 የሚጠጉ ወታደሮች፣ ገበሬዎችና ሲቪሎች ሞተዋል፡፡ ቤቶችም ተቃጥለዋል፡፡ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል፡፡

ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ በመጓዝ ላይ የነበሩት ተማሪዎችም ተኩስና ግርግሩን በመሸሽ ወደመጡበት መመለሳቸውን ሰምተናል፡፡

Via Adiss zeyebe

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
2.3K viewsedited  17:58
Open / Comment
2021-03-25 20:32:27
በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የዳግማዊ ምኒልክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

ውድ የኮሌጃችን የ2012 ተመራቂ የነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦
በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ለነገ ጠዋት 2:00 አስቸኳይ የውይይት መድረክ የያዝን ስለሆነ መምጣት የምትችሉ ተማሪዎች ሁሉ በሆስፒታሉ ግቢ እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን።

የህብረቱ ዋና ፀሀፊ
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
2.5K viewsedited  17:32
Open / Comment
2021-03-25 18:00:43
#ማስታወቂያ

በFacebook ላይ ታዋቂነትን ያተረፈው የጊቢ meme አዝናኝ ሜሞች በቴሌግራም!

SHARE & JOIN US

@GIBIMEMES
3.8K views15:00
Open / Comment
2021-03-25 16:17:13
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት 30 ይሰጣል

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ በወረቀት ይሰጥ የነበረበትን ስርዐት በዚህ አመት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፈተናውን ግንቦት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል ማምሻውን በነበራቸው መግለጫ አስታውቀዋል።

በonline ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው የአምናው ፈተና በወረቀት መሰጠቱንም አስታውሰው በዚህ አመት ለሚፈተኑት ወደ 700ሺ የሚጠጉ ተፈታኞች ታብሌቶች ገብተው ዝግጁ መሆናቸውንና የማጓጓዝ ስራ በመጀመር ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

ከሚያዚያ 3 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ታብሌቶቹ እና የፈታኝ አስተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ገልጸው ለተማሪዎች የ አንድ ወር የመለማመጃ ጊዜ እንደሚሰጣቸውም አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የ2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ይሰጣል ተብሏል።

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.5K viewsedited  13:17
Open / Comment
2021-03-24 20:25:43
ማስታወቂያ ለኮተቤ ዩንቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በሀገራችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ በሚገኘው የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ምልልሶችን ለመቀነስ ሲባል ከግቢ የመውጫና የመግቢያ ሰዓት ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።

የመግቢያና የመውጫ ሰዓት

ጠዋት ከ1፡00 እስከ 3፡00
ቀትር ከ5፡45 እስከ 8፡00
ከሰዓት ከ10፡00 እስከ 1፡30

የግቢው ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሰው የመግቢያና የመውጫ ሰዓት መሰረት ፕሮግራማችሁን በማስተካከል ጉዳዮቻችሁን ከጥንቃቄ ጋር እንድታከናውኑ ተብላቹሃል ።

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
6.2K viewsedited  17:25
Open / Comment
2021-03-24 11:37:45 የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የውሃ እጥረት ችግር እንዳማረራቸው በተደጋጋሚ እየገለጹልን ይገኛል፡፡ በተለይም በሴቶች ዶርም ጊቢ ውስጥ ውሃ ከጠፋ ቀናት እንዳለፉ ገልጸውልናል። በጣም ያስገረመን ደግሞ የተማሪዎች ካፍቴሪያ ጭምር ውሃ እንደሌለ እና ውሃ ከውጭ ገዝተው የሚመጡ አንዳንድ ተማሪዎች በራሳቸው እንደሚጠቀሙም ገልጸውልናል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን የያዘ ዩኒቨርሲቲ እንዲህ አይነት…
6.8K views08:37
Open / Comment
2021-03-24 09:09:14 የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የውሃ እጥረት ችግር እንዳማረራቸው በተደጋጋሚ እየገለጹልን ይገኛል፡፡

በተለይም በሴቶች ዶርም ጊቢ ውስጥ ውሃ ከጠፋ ቀናት እንዳለፉ ገልጸውልናል። በጣም ያስገረመን ደግሞ የተማሪዎች ካፍቴሪያ ጭምር ውሃ እንደሌለ እና ውሃ ከውጭ ገዝተው የሚመጡ አንዳንድ ተማሪዎች በራሳቸው እንደሚጠቀሙም ገልጸውልናል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን የያዘ ዩኒቨርሲቲ እንዲህ አይነት ችግር ለቀናት ሲዘልቅ መፍትሔ አለመስጠቱ የሚያሳፍር ነገር መሆኑንም ተማሪዎቹ አክለው ገልጸውልናል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ደውለን የሚሰጡንን ምላሽ እናሳውቃችኋለን።

@NATIONALEXAMSRESULT
6.9K views06:09
Open / Comment
2021-03-23 17:54:10 ይደመጥ| አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ተማሪዎች መጋቢት 28,29 እና 30 ወደ ዩንቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተወስኗል

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ነው ።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.7K viewsedited  14:54
Open / Comment
2021-03-23 16:05:52
ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ የሚያመላክት ሰነድ ይፋ ሊደረግ ነው።
---------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ የሚያመላክት የ2ኛ ዙር ግኝትን ያካተተ ሰነድ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ሰነዱን ይፋ እንደሚያደርግ ያስታወቀው የ2013 ዓ.ም የ6 ወር የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አፈጻፀም ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ነው።

ሰነዱ ትምህርት ቤቶች በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት ያሉበትን ደረጃ የሚያመላክት ነው።

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት አማካሪ አቶ አላምረው አክሊሉ ሰነዱ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ከመፈረጅም ባሻገር በእቅድ አፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች ለይቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ የሚጠቅም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ በቀረበው ሪፖርት አንዳንድ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ ዝግጅት ላይ ክፍተት እንዳለባቸው ተነስቷል።

በመድረኩ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.8K viewsedited  13:05
Open / Comment
2021-03-23 15:03:09
"የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ የሚደረግበት ጊዜ ታውቋል እንዲሁም በዚብ ወር መጨረሻ ይፋ ያደረጋል በመባል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነታው የራቀ ነው"

2012 ዓ.ም ላይ መሰጠት የነበረበት እና ዘንድሮ የካቲት ወር መጨረሻ ላይ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት በተለይም "በዚህ ወር መጨረሻ ይፋ ይደረጋል" የሚለውን መረጃ በተመለከተ ከብዙ ሙከራዎች በኋላ ተሳክቶልን በስልክ ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን " በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይወጣል አልያም በዚህ በዚህ ቀን … ይፋ ይደረጋል የሚል መረጃ የሰጠ የትኛውም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካል የለም " የሚል ምላሽ የተሰጠን ሲሆን " ከሌላው ጊዜ በፈጠነ መልኩ በጥራት እና በደኅንነት ፈተናው ታርሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል የዩኒቨርሲቲ ምደባም በዚያው ልክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል " ብለውናል።

ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች ፈተናውን በተመለከተ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከመንግስት ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲዎች የሚመጡ መረጃዎችን ብቻ እንዲከታተልም አሳስቧል።

TEAM: STUDENTS NEWS CHANNEL

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.9K viewsedited  12:03
Open / Comment