Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.75K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 13

2023-04-25 13:01:01
በፒራሚድ ንግድ ስልት ላይ የተሰማሩ ሁለት ኩባንያዎች በህግ ሊጠየቁ ነው ተባለ።

በአቋራጭ ትከብራላችሁ የሚል አደናጋሪ መልዕክትን በማስተላለፍ ህገወጡን የንግድ ስልት ተግብረው ብዙዎችን ከጎዱ ድርጅቶች መሀል ሁለት ኩባንያዎችን በህግ ለመጠየቅ ሂደቶች መጀመራቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ የትኞቹ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃው ሊወሰድ እንደሆነ ስም ባይጠበቅም ቀጥተኛ ንግድ የሚመራበት መመሪያ አለመኖሩና በፒራሚዳዊ ስልት የተሰማሩ ድርጅቶች ሲደረስባቸው የህግ ክፍተቱን እንደሽፋን መጠቀማቸው ለስራዬ እንቅፋት ሆኖብኛል ብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.5K viewsedited  10:01
Open / Comment
2023-04-25 10:07:44
ምርት እና አገልግሎትዎን ዘመነኛ ደንበኛን የመሳቢያ አማራጭ ሆነው በመጡት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማስተዋወቅ አስበው መድረኩን ለማግኘት ተቸግረዋል ?

እንግዲያዎስ.........

➪ አዲስ የከፈታቹትን ቻናል ማስታወቂያ

➪የእቃ ሽያጭ ማስታወቂያ

➪የኮንሰርት ማስታወቂያ

➪የድርጅት ምርት ማስታወቂያ

➪የዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ

➪ለሴልስ ስራዎች ማስታወቂያ

➪የድረገፆች ማስታወቂያ እና ሌሎችንም...

በተጨማሪም በምንሰራቸው ስራዎች ላይ ስፖንሰር በመሆን ከእኛ ጋር መስራት የምትፈልጉ ካላቹ በልዩ ልዩ ጥቅሎች ከተመጣጣኝ ዋጋ ጋር በ ተወዳጁ ቻናላችን በኩል ለብዙሃን ተደራሽ ማድረግ ትችላላቹ !

ይፍጠኑ ምርቶን ለማስተዋወቅ ከታች ባለዉ  አካዉንታችን ይጠቀሙ አሁኑኑ ያናግሩን
@studentsnewsadv35bot
3.1K views07:07
Open / Comment
2023-04-24 09:55:52 #MekelleUniversity

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/77964

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

ሙሉ ስም
የመታወቅያ ቁጥር
ትምህርት ክፍል
የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.9K views06:55
Open / Comment
2023-04-24 09:55:07
3.2K viewsedited  06:55
Open / Comment
2023-04-24 07:14:13
ማስታወቂያ
የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

1/የ2015 ት/ት ዘመን ፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ ይካሄዳል።
2/ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። ምክንያቱም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋማችን የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው።
3/ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን።
4/ፈተናው የምሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሲሆን የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ የምንገልጽ ይሆናል። እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም።

ስለሆነም ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ እያሳሰብን መልካም ውጤት እንዲያስመዘግቡ እንመኛለን።

የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በጋራ እንከላከል!!

የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
4.1K views04:14
Open / Comment
2023-04-23 15:41:52 የመምህራኑ ጥያቄ ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን ማኅበር በሥሩ ከሚገኙት አባላት መካከል የ29,500 አባላቱ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታለት ከንቲባ አዳነች አቤቤን በደብዳቤ ጠይቋል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ለሪፖርተር ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር። በዚህ ቃለምልልስ ምን አሉ ?

- ማህበሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ለከንቲባዋ በጻፈው ደብዳቤ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ መምህራን የቤት ጥያቄ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡

- የመምህራን ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ ከንቲባዋ ከመምህራን ጋር በ2013 ዓ.ም. በነበራቸው ስብሳሰባ፣ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየ አይደለም።

- ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ለመምህራን የኑሮ ውድነትን የሚያረግቡ ድጎማዎች እንዲደረጉ፣ ከንቲባዋ በመድረክ ላይ የገቡት ቃል ወደ ታች ወርዶ እንዲፈጸምና በከተማ አስተዳደሩ በተጀመሩ ልማቶች የመምህራን ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ተጠይቋል።

- የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከተቻለ በልዩ ትኩረት በከተማው ደረጃ ውሳኔ ሰጥቶበት እንዲፈታ፣ ካልሆነም ደግሞ የሚመለከተው የፌዴራል ተቋም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እልባት መስጠት እንዲቻል እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

- የኑሮ ውድነት ማረጋጊያ ድጎማ 3,000 ብር የሚሰጥ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ከችግሩ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ቢያንስ በእጥፍ እንዲያድግ መምህራኑ ይፈልጋሉ።

በተጨማሪ ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ....

ለመምህራን ሁለተኛ መ/ ቤታቸው የሆነው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ፣ ግንቦት 2013 ዓ.ም. መምህራንን ባወያዩበት ወቅት መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ የተገለጸ ቢሆንም፣ ነገር ግን እስካሁን በተፈለገው ርቀት ወደ ሥራ አለመገባቱን ያትታል፡፡

በዚህ የተነሳ ባለፉት ወራት ምንም ዓይነት ለውጥ አለመኖሩ መምህራንን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ፣ ጉዳዩን በተቃራኒ በጥርጣሬ እንዲያዩት አነሳሽ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ተስፋ አስቆራጭነቱ እየሰፋ የመጣ ስለመሆኑ ይገልጻል።

ይህ ጉዳይ መምህራን ቃል የገቡልንን አልተገበሩልንም (አላስተገበሩልንም) የሚል ስሜት ፈጥሮ የመምህራንን ሞራል ያላሸቀ ፣ ቤት ባላቸውና በሌላቸው መምህራን መካከል የፍትሐዊነት ጥያቄ ያስነሳ መሆኑም በደብዳቤው ተመላክቷል፡፡

መምህራን የሚያገኙት የደመወዝ መጠንና በአሁኑ ወቅት ያለው ፦ የቤት ኪራይ ዋጋ፣ በተጨማሪም የኑሮ ውድነት መምህራንን ተረጋግተው እንዳያስተምሩ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ ከንቲባዋ ለመምህራኑ በገቡት ቃል መሠረት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ " አጥብቀን እንጠይቃለን " ብሏል።

በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መምህራኑ ከሚያገኙት ደመወዝና የኑሮ መደጎሚያ ጋር ተቋቁሞ መኖር ከባድ መሆኑን የሚያስረዳው ደብዳቤው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ባደረገው የኑሮ መደጎሚያ ላይ ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ ፦ https://telegra.ph/Reporter-04-23

#ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
4.9K viewsedited  12:41
Open / Comment
2023-04-22 21:22:32
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል የ"ኦንላይን" ፈተና አስተዳደር ስርዓት አበለጽጓል።

ስርዓቱ በዩኒቨርሲቲው የኮምፒውተር ሳይንስ መምህራን መበልጸጉ ተገልጿል።

የ"ኦንላይን" ፈተና አሰተዳደር ስርአቱ ከበላይ አመራሮች ጀምሮ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች በተፈቀደላቸው ልክ እንዲከውኑበት ተደርጎ የበለጸገ ነው ተብሏል። #ዲዩ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K viewsedited  18:22
Open / Comment
2023-04-22 15:10:58
One Young World Summit 2023 in Belfast (Fully Funded)

The OYW Summit will bring 2000+ Participant's from all countries for a 4 Day Summit (2-5 Oct 2023)

Open to anyone. No IELTS. No Fee

The Program Covers Airfare Tickets, Accommodation, Health, Visa Fee, Meals and everything.

Visit: https://opportunitiescorners.com/one-young-world-summit/

Deadline: 30th April 2023

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.1K viewsedited  12:10
Open / Comment
2023-04-22 15:10:58 #እንድታውቁት

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

በመሆኑም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ #የማይገኙ ሁሉም የዲግሪ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን፣ ክረምት) እንዲሁም የማስተርስ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን ፣ ክረምት) ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ሊንክ ፦ http://196.190.28.50

ምዝገባው የሚያበቃበት ቀን ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ ዘውትር በየስራ ሰአት በሚከተሉት ቁጥሮች መወደወል ይቻላል ፦ 0914485592 / 0921990158

ከኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ #የራያ_ዩኒቨርሲቲም በጦርነት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል።

በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት በራያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የመማር እድል ያላገኙ ተማሪዎች ከ09/08/2015 ዓ/ም እስከ 13/08/2015 ዓ/ም ባሉ የስራ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎች የሚመዘገቡት ለዩኒቨርስቲው ረጅስትራር እየደሉ ሲሆን የስልክ ቁጥሮቹ 0970140000፣ 0970240000 ፣ 0970230000 ናቸው። ተማሪዎች ዘውትር በስራ ሰዓት ብቻ እንዲደውሉ ጥሪ ቀርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2.8K viewsedited  12:10
Open / Comment
2023-04-22 15:10:58
2.3K views12:10
Open / Comment