Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.75K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 12

2023-05-01 11:11:14
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው::

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ተወካዮች በቀጣይ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ከ22ኛው ሳምንት ጀምሮ የሚያስተናግደውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለአራተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ረፋድ ላይ ተመልክተዋል።

ቀደም ባሉ ምልከታዎቻቸው የሊጉ የበላይ አካል በሜዳውና ከሜዳው ውጪ ያሉ መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ መሆናቸውን ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ሊጉ በቀጣይ ሀዋሳ ላይ እንደሚደረግ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ፕሪምየር ሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታውን በአዳማ ከጀመረ በኋላ ከመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ እስከ 27ኛው ሳምንት ድረስ ሀዋሳ የሊጉን ውድድር ታስተናግዳለች::

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.3K views08:11
Open / Comment
2023-05-01 11:02:58
A+ Tutorial Class ለ2015 የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማስተማሩን ጀመረ

የመጀመሪያ አመት የ ዩኒቨርሲቲ ና የኮሌጅ ተማሪዎች በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሰረት የሚወስዱትን freshman course ለመረዳት ምቹ ÷ ግልፅ የሆኑ ኖቶችን እና ማብራሪያዎችን ከ ምስል እና ከ PDF ፋይል ጋር አቀናጅቶ በማስተማር የሚታወቀው ፤ ብዙ ሺህ ተማሪዎች ለከፍተኛ ውጤት እንዲበቁ አስተዋዕፆ ያደረገው ÷

በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች A+ በማምጣት የከፍተኛ ውጤት ባለቤት በመሆን ወደሚፈልጉት ዲፓርትመንት እንዲቀላቀሉ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋዕፆ ያደረገው A+ tutorial class  ለዘንድሮ ለ 2015 አዲስ ገቢ የ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ ናቹራል፤ በሶሻል ሳይንስ እንዲሁም A/ASTU ለተመደቡ ተማሪዎች ማስተማር በይፋ ጀምሯል።

ከላይ ለናሙና የቀረቡት ፎቶዎች በ 2013 ና 2014 ዓ.ም በ A+ tutorial Class የተሰጠውን የ freshman course ቲቶርያል በመከታተል በግቢ ትምህርታቸው የከፍተኛ ውጤት ባለቤት ከሆኑት በ ሺህ ከሚቆጠሩት የ A+ tutorial class አባላት መካከል የ ጥቂቶቹ ምስክርነት ለ ናሙና የቀረቡ ናቸው።

ይመዝገቡ ወደ ሚፈልጉት ዲፓርትመንት ለመቀላቀል የሚጠብቅዎትን ትግል ያቃሉ።

ለመመዝገብ እና ለተጨመሪ መረጃ
@AplusTutorialbot

ለጥያቄና አስተያይት
@Ucan_Scorebot

ለበለጠ ከአምና ከ 2014 ተማሪዎች ጋ በነበረን ቆይታ ከተሰጡ ብዙ ምስክርነቶች መካከል ለናሙና የቀረቡትን ምስክርነቶች ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ

https://t.me/+b1zKh1uFuytlZWI0

ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
Your Sucess is guaranteed with A+ Tutorial Class!

A+ Tutorial Class.
419 views08:02
Open / Comment
2023-05-01 08:00:03 ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን አዲስ አዋጅ ፀደቀ

የተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት አዋጅ አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን አዲስ አዋጅ አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ መንግስት አዘጋጅቶ ያቀረበውን የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ኖህ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ መከላከያ ሰራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ሃይል አባል የሚሆኑ ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠብቁላቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡

በመንግስት ተዘጋጅቶ የቀረበው የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የተጣለበትን ሀገርን የመጠበቅ ተልክኮ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመወጣት እንዲችል ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በመንግስት የተሻሻለውና ከትናንት በስቲያ በምክር ቤቱ የፀደቀው ይህው አዋጅ የሰራዊቱ አባላት የጡረታ መውጫ የእድሜ ጣሪያ አወሳሰን እንዲሁም የአገር ህልውና ከባድ አደጋ ላይ በሚወድቅ ጊዜ ከሰራዊቱ የተገለሉ አባላት መቀጠር የሚችሉበትን ሁኔታ ሁሉ አካቶ መያዙም ተገልጿል፡፡

አዲስ አድማስ


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.6K viewsedited  05:00
Open / Comment
2023-04-29 13:38:00
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ አንድ ተቋም እና 18 ኮሌጆች የተሟላ መረጃ መላካቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) #ETA

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
4.6K viewsedited  10:38
Open / Comment
2023-04-29 13:27:31
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ #tikvah

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.9K viewsedited  10:27
Open / Comment
2023-04-29 09:37:06
ለትምህርት ቤቶች አስተዳደር ሠራተኞች የተላለ መልዕክት ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
3.0K viewsedited  06:37
Open / Comment
2023-04-29 07:25:35
የኢንተርኔት አገልግሎት ላለፉት ሁለት ሳምንታት መቋረጡ በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን የቤት ሥራም ሆነ በግላቸው የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከየካቲት ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በአላማጣ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.3K viewsedited  04:25
Open / Comment
2023-04-29 07:24:17
ትምህርት ቤቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሳደግ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው
-----------------------------
ሚያዚያ 20,2015ዓ.ም ( የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከክልልና ከተማ መስተዳደር ለተውጣጡ የትምህርት ባለሙዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኔስኮ-ሁዋዊ (UNESCO - Huawei) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ነው የተሰጠው።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የዩኔስኮ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ሪታ ቢሶናዝ (ዶ/ር) ስልጠናው ለትምህርት ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ክፍተት ለመሙላት አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።

በትምህርት ቴክኖሎጂ በቂ እውቀት ያላቸውን የትምህርት ባለሙያዎችን በማፍራት እና ት/ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ርብርብ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ከድር ኡርጂ በበኩላቸው የትምህርት ስርአቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በተጠናከረ መልኩ ለመደገፍ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያከናወናቸው ካሉ የለውጥ ስራዎች መካከል አንዱ ዲጂታላይዜሽን ሲሆን በዘርፉም በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2.9K views04:24
Open / Comment
2023-04-26 10:24:49
A+ Tutorial Class

የመጀመሪያ አመት የ ዩኒቨርሲቲ ና የኮሌጅ ተማሪዎች በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሰረት የሚወስዱትን freshman course ለመረዳት ምቹ ÷ ግልፅ የሆኑ ኖቶችን እና ማብራሪያዎችን ከ ምስል እና ከ PDF ፋይል ጋር አቀናጅቶ በማስተማር ብዙ ሺህ ተማሪዎች ለከፍተኛ ውጤት እንዲበቁ አስተዋዕፆ ያደረገው ÷

በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት  በማምጣት የከፍተኛ ውጤት ባለቤት በመሆን ወደሚፈልጉት ዲፓርትመንት እንዲቀላቀሉ በማድረግ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እና ተከታይነትን ያተረፈው A+ Tutorial Class ለዘንድሮ ለ 2015 አዲስ ገቢ የ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማስተማር ለ ፈተና በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የበኩሉን አስተዋዕፆ በመወጣት ላይ ይገኛል።

ከላይ ለናሙና የቀረቡት ፎቶዎች በ ዘንድሮ በ A+ Tutorial Class እየተሰጠ ያለውን የ freshman course ቲቶርያል በ Natural Science ፤ በ Social Science እንዲሁም በ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተመደቡ ተማሪዎች ሲከታተሉ የሚያሳይ ነው።

ይመዝገቡ ወደ ሚፈልጉት ዲፓርትመንት ለመቀላቀል የሚጠብቅዎትን ትግል ያቃሉ።

ለመመዝገብ
@AplusTutorialbot

ለጥያቄ ና ሀሳብ
@ucan_scorebot

ለበለጠ ከአምና ከ 2014 ተማሪዎች ጋ በነበረን ቆይታ ከተሰጡ ብዙ ምስክርነቶች መካከል ለናሙና የቀረቡትን ምስክርነቶች ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ

https://t.me/+b1zKh1uFuytlZWI0

ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
Your Sucess is guaranteed with A+ Tutorial Class!

A+ Tutorial Class.
251 views07:24
Open / Comment
2023-04-25 22:01:59
መልካም ዜና Highschool ተማሪዎች በሙሉ!
የ2015 የ12ኛ ክፍል ተማሪ ከሆንክ እባክህ ይህ መልካም እድል ላንተ የተዘጋጀ ነው እንዳያመልጥህ
የ2015 ተፈታኝ  ለሆነ ወዳጅ ወይን ጓደኛዎ ይህን መልእክት share አድርጉለት
ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች  ይህን  እድል እንዲጠቀሙበት ይጋብዙኝ
ለሀገራችን የተማሪዎች የተስፋ ወጋገን የሆነ Entrance Hub የሚባል ተቋምን የምታውቁት ለሌሎች አሳውቁ፣ ለማታውቁ ከታች link አስቀምጣለሁ እሱን ለሌሎችም አድርሱ!!!
እኔ የበኩሌን ተወጥቻለሁ ተራው የእናንተ ነው
@ENTRANCEHUBETHIOPIA
2.5K views19:01
Open / Comment