Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.92K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 9

2023-05-11 21:18:35 በመጪው ሐምሌ ከሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስቀድሞ፤ ሞዴል የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰኔ መጨረሻ በአማራ ክልል እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ሞዴል ፈተናው ተማሪዎቹ የሚያደርጉትን ዝግጅት እንደሚያግዝ የቢሮው ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር) ለአሚኮ ተናግረዋል።

በክልሉ 215,590 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸው ይታወቃል።

በባለፈው ፈተና የታዩ የሥነ ምግባር ችግሮች በዚህ ዓመት እንዳይደገሙ ተከታታይ የሆኑ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል።


     የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K views18:18
Open / Comment
2023-05-11 20:23:23 በተጋነነ የክፍያ ጭማሪ ምክንያት ትምህርትቤቶችና ወላጆች ለሁለት ተከፈሉ!

የግል ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የጠየቁት ከፍተኛ የክፍያ ጭማሪ ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ለሁለት ተከፍለዋል።

በአዲስ አበባ ካሉ 1558 የግል ትምህርት ቤቶች፣ ጭማሪውን ለማድረግ ፍላጎት ያሳዩት  1253 ትምህርት ቤቶች ቢሆኑም፣  1031 ትምህርት ቤቶች ብቻ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ  ቢደርሱም 226ቱ መስማማት እንዳልቻሉ፣  የትምህርት ስልጠናና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደገለፁት፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት 1558 የግል ትምህርት ቤቶች 1253 የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ፍላጎት አሳይተዋል።226 ትምህርት ቤቶች ጋር  መግባባት ላይ መድረስ ያልተቻለ ቢሆንም፣  በቀጣይ መግባባት እንዲፈጠር ባለስልጣኑ ውይይት የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ከ2016 ዓም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከወርሃዊ ክፍያ ውጭ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ አክለው ገልፀዋል።በአሁኑ ወቅት ጭማሪ ለማድረግ መግባባት ላይ የደረሱት ትምህርት ቤቶች፣ ከ20 በመቶ ጀምሮ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን አቶ ዳኘው ተናግረዋል።

Vi Reporter


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
2.3K viewsedited  17:23
Open / Comment
2023-05-11 20:06:37
እስከሚቀጥለው እሁድ ግንቦት 6 ድረስ ልንቀበላቸው የምንችለው ውስን ተማሪዎችን ብቻ ነው።
በዚህ በመጨረሻ ሳምንት መመዝገብ የሚችሉት ከሁለቱም የትምህርት ዘርፍ እንደሚከተለው ይሆናል
ከተፈጥሮ ሳይንስ(natural) 89 አዲስ ተማሪዎችን
ከማህበራዊ ሳይንስ(social) 76 አዲስ ተማሪዎችን እስከ ግንቦት 6 2015 ደረስ ብቻ መቀላቀል ትችላላችሁ
ከግንቦት 6 በኃላ ሙሉበሙሉ የአዲስ ተመዝጋቢ ቅበላ ዝግ ስለምሆን የተወሰነው ኮታ ከመሙላቱ  በፊት  በቅድምያ እንዲትመዘገቡ ልናሳስባችሁ እንወዳለን።
ለመመዝገብ ይህን ቦት ይጠቀሙ
@EntranceHubBot
ለበለጠ መረጃ
▣ @EntranceHubEthiopia
Entrance Hub Ethiopia
507 views17:06
Open / Comment
2023-05-11 19:22:03
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ቀን እንዲስተካከል ጠየቀ!!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት "የ2015 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 19-20/2015 ለመስጠት ማቀዱን ለመረዳት ችለናል ብሏል።

ም/ቤቱ "በካላንደር ዝግ የሆኑ የህዝብ በዓላትን ባገናዘበ መልኩ እቅድ ማዘጋጀት የቢሮው ሃላፊነት ቢሆንም ሰኔ 21 እና 22/2015 የአረፋና የዒድ አልአድሀ በዓል ቀን እና ዋዜማ ፈተና ለመስጠት ማቀድ አግባብነት የሌለው እና ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተና ላይ እንዳይቀመጡ የሚያደርግ ተግባር ነው" ያለ ሲሆን የፈተናው ቀን ከዒድ አልአድሐ በዓል ከ3 ቀናት በፊት ወይም ከ3 ቀናት በኃላ እንዲሆን ይህም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ እናሳስባለን ብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2.4K viewsedited  16:22
Open / Comment
2023-05-11 15:57:02
የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ መጠየቅ አይችሉም - የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን
********

የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ ከተማሪ ወላጆች መጠየቅ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በከተማዋ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ 1ሺህ253 የግል ት/ቤቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ገብሩ ገልጸዋል።

የግል ትምህርት ቤቶች ዋጋ የሚጨምሩባቸው ምክንያቶች ግብዓቶችን ለማሟላት፣ ለአስተዳደራዊ ወጭዎች እና የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለማስቀጠል ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውም ተገልጿል።

የዋጋ ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ተወያይተው ሲስማሙ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል። የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2.9K viewsedited  12:57
Open / Comment
2023-05-11 11:11:29 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የት/ት ቢሮ እንዳስታወቀዉ ፤ 1,940 ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቢጀምሩም በአሁኑ ወቅት 552 ት/ት ቤቶች ስራ አልጀመሩም።የቢሮዉ ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ለዚህ ምክኒያቱ በትምህርት ቤቶቹ የተፈናቃዮች መጠለያ መሆናቸዉ እንደሆነ ገልጸዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.2K viewsedited  08:11
Open / Comment
2023-05-11 11:10:49
ቀን 3/9/2015 ዓ.ም

ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለስልጣን መስራቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጠው አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር ይገባል፡፡

የግል ት/ቤቶች ያደረጉትን ከፍተኛ ጭማሪ በማስመልከት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለግል ት/ቤቶች ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለስልጣን መስራቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጠው አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን አሳውቃል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2016 ዓ.ም የግል የትምህርት ተቋማት የዋጋ ጭማሪ ላይ ውይይት መደረጉን የጠቀሰ ሲሆን ነገርግን በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ በወረደው ሰርኩላር መሰረት ተግባራዊ እንዲደረግ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.1K viewsedited  08:10
Open / Comment
2023-05-11 06:29:12 በአዲስ አበባ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ለማድረግ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረባቸውን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ግን፣ የትኛውም ትምህርት ቤት ከተማሪ ወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደርስ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችል ማስጠንቀቁን ዘገባው ጠቅሷል። በከተማዋ ከሚገኙት 1 ሺህ 558 ትምህርት ቤቶች መካከል፣ በቀጣዩ ዓመት የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን ለባለሥልጣኑ ያሳወቁት፣ 1 ሺህ 257 ትምህርት ቤቶች እንደኾኑ ባለሥልጣኑ መናገሩን ዜና ምንጩ አመልክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.3K views03:29
Open / Comment
2023-05-11 06:29:01
የማላዊ ፍርድ ቤት ተማሪዎች ጸጉራቸዉን ድሬድ ማድረግ እንዲችሉ ፈቀደ

በማላዊ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የትምህርት ባለስልጣናት በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጸጉራቸዉን ድሬድ ያደረጉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ በ2016 እና 2010 ዓመት ወደ ህዝብ ትምህርት ቤት ለመግባት የተከለከሉ ሁለት የራስተፈሪያን ልጆች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ በዞምባ ከተማ ባስቻለዉ ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የሁለቱ ተማሪዎች ጉዳይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካገኙ በኋላ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።በማላዊ የሚገኘው የራስተፈሪያን ማህበረሰብ እና የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመፍታት የተካሄደው ውይይት ባለመሳካቱ የተራዘመ የህግ ክስ ቀርቦ ውሳኔው ሰኞ እለት ተላልፏል።

ዳኛ ንታባ ድሬድ ያደረጉ ህጻናት ትምህርት ቤት እንዳይማሩ መከልከል የመማር መብታቸውን መጣስ ነው ሲሉ ውሳኔ አስተላልፈዋል።"የትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የራስተፋሪያን ማህበረሰብ ልጆች ድሬድ አድርገዉ በክፍል ውስጥ እንዲገቡ ለመፍቀድ መግለጫ ማውጣት አለበት ይህንኑ የሚገልጽ መመሪያ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማሳወቅ እንደሚኖርበት" ዳኛ ንታባ አዘዋል፡፡

ይህዉ ጉዳይ በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የራስተፈሪያን ማህበረሰብ ስም በሶስት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አማካይነት ወደ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ችሏል፡፡

Via ዳጉ ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.3K viewsedited  03:29
Open / Comment
2023-05-10 21:31:35
ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ስምምነት ሳይደረስ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ!

ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከወላጆች ጋር በነበረ ውይይት ስምምነት ላይ መድረስ ያልተቻሉባቸው መድረኮችን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡

የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ አቅጣጫ ብቻ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
3.7K viewsedited  18:31
Open / Comment