Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.92K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 7

2023-06-12 12:55:04 " የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር ሳይጋጭ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ፣ ከመውጫና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲከናወን የሚረዳ ዕቅድ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ አስታውሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ኤባ ፤ በዘንድሮው ዓመት 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸው ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱን አመላክተዋል።

ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በማዕከል ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና ሥርዓት ለመሞከር እንደ አገር ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቀው፤ በዚህም ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከልና ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደራጀ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለመውጫ ፈተናው የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ጄኔሬተሮች ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
6.0K viewsedited  09:55
Open / Comment
2023-06-12 12:26:12
#ተቃውሞ #Exit_Exam #ምርቃት

ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ ለምርቃት አይቀመጥም የሚለውን ውሳኔ ዳግም እንዲያጤነው በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች እየጠየቁ ይገኛሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
6.8K viewsedited  09:26
Open / Comment
2023-06-12 11:26:43 #Defense #Exit_Exam #2015EC

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ( ሶሻል ሳይንስ ፋካሊቲ) ፣ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ( Biology Department) ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ (FBE) ተመራቂ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ዝግጅት እንዲያደርጉ በማሰብ ዲፌንስ እንዲቀርላቸው ተደርጓል።

ሌሎቻችሁስ ጋር ምን አይነት የተለየ እንቅስቃሴ አለ?

እርማት
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ FBE ዲፌንስ እንዳልቀረ አረጋግጠናል። ይቅርታ እንጠይቃለን።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.1K viewsedited  08:26
Open / Comment
2023-06-11 22:58:19 በወቀታዊ ጉዳይ ላይ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ መግለጫ

በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም በሀገር ደረጃ ተግባራዊ ለሚደረገው የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጥሩ ውጤት እንዲያልፉ ለማስቻል ከፍተኛ የሆነ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በተያያዘ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና የሚያደርገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጣ ግብረ ኃይል የመስክ ምልከታ አድርጎ የመፈተኛ ክፍሎች በአግባቡ መዘጋጀታቸውን፣ ክፍተቶችን በተቋሙ አለማየታቸውን ፣ የአይሲቲ መሠረተ ልማት ዝግጅት... ወዘተ ዩኒቨርሲቲው የተሻለ ዝግጅት ማድረጉንና ለሌሎችም መልካም ተሞክሮ እንዳለውና በዩኒቨርሲቲው የበለጠ ተበረታቶ መስራት እንዳለበት በግምገማው ተመላክቶዋል።

ይሁን እንጂ ከዩኒቨሲቲው እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ በቀን 03/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2ዐ15 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) አንፈተንም በሚል በዋናው ግቢ በዉስን ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ እንዳለ ዩኒቨርሲቲው ለመገንዘብ ችሏል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ዜና ግነት የበዛበት ሲሆን የተፈጠረውን መጠነኛ ያለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው ደህንነት ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀዲያ ዞን ፖሊስ፣ ከሌሞ ወረዳ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሉች ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሠላማዊ የሆነ የመማር ማስተማር ሥራ ማስቀጠል ተችሉዋል።

በዚህ ሁኔታ በዩኒቨርሲቲው የተማሪ ረብሻ፣ የንብረት ዉድመት እንዲሁም የጎላ የፀጥታ ችግር በሌለበት አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች የሰላም አምባሳደር የሆነውን የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም ሆነ ብሎ ለማጠልሸት ጥረት ማድረጋቸው ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ማስገንዘብ ይወዳል።

በመጨረሻም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በነበረው መጠነኛ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ያለመድረሱንና ዩኒቨርሲቲው ወደተለመደው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መመለሱን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7.3K viewsedited  19:58
Open / Comment
2023-06-11 22:33:34
#0 Year Experience Jobs

#Accounting Jobs for #Junior Accounting Professionals on typicalethiopian.com

Click on the Job you are interested to apply before the applications are closed:-

Dashen Bank S.C Vacancy Announcement

Position: Customer Service Officer (Maker)
Location: Addis Ababa, Hawassa, Adama, Jimma, Bahir Dar, Dire Dawa, Wolaita and Dessie Districts
Deadline: June 15, 2023
Click here to Read Details & Apply

Berhan International Bank Vacancy Announcement

Position:
Junior Customer Service Officer For West District
Location: Addis Ababa
Deadline: June 15, 2023
Click here to Read Details & Apply

Armauer Hansen Research Inistitute(AHRI) Vacancy Announcement

Position:
Project Admin Officer
Location: Adama, Oromia
Deadline: June 11, 2023
Click here to Read Details & Apply

More Accounting Vaccancies on https://t.me/ethiopianaccountingjobs

Accounting ስራ ፔጁን ለ አካውንታንት ጓደኛዎ ወይም ዘመድዎ Share ያድርጉ ::
Telegram
Facebook
Visit Our Website
6.1K views19:33
Open / Comment
2023-05-21 12:42:57
በድሬደዋ የተስተዋለውን ከፍተኛ የሙቀት ተከትሎ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ።

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን መስተዋሉን አስመልክቶ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።

ቢሮው በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው(ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣የልብ ህመም፣የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፤

2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፤

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፤

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፤

5. አመጋገብዎን ማስተካከል(ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፤

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፤

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፤

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፤

9.የተለያየ ህመም  ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ማድረግ፣ የታዘዘውን መድኃኒት በትዕዛዙ መሰረት በመውሰድ ጤናዎን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።



የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
121 viewsedited  09:42
Open / Comment
2023-05-21 11:40:28 Ads

ለማትሪክ, Grade 12 National Exam (ESSLCE)ዝግጅት መለማመጃ ፈተና ከሙሉ ማብራሪያ መልሶች፣

ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዝግጅት መለማመጃ ፈተና ከሙሉ ማብራሪያ መልሶች፣
እንዲሁም ጠቃሚ መፅሃፍትና አጫጭር ኖቶች ተዘጋጅቶ እየቀረበ ስለሆነ join  በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ።

Join For documented Tutorials
https://t.me/tutorialpointeth
Join for video tutorials

https://www.youtube.com/@Tutorialpointeth
674 views08:40
Open / Comment
2023-05-21 11:12:03
#Update

ለመምህራኑ የአስክሬን ሽኝት ተደረገ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ባገኘው መረጃ ራቅ ካሉ አካባቢዎች መጥተው በተቋሙ ሲያስተምሩ ለነበሩና በትላንትናው አሰቃቂ አደጋው ህይወታቸው ላለፈ መምህራን የአስክሬን ሽኝት አደርጓል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
957 viewsedited  08:12
Open / Comment
2023-05-21 11:09:46 #Update

መላው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትላንት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከባድ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ከሊል ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አደጋው ትላንት 1 ሰዓት ከ20 ላይ በዶዶላ ማዕከል ለማስተማር መምህራንን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ " ሰብስቤ ዋሻ " የሚባል አካባቢ ገደል ውስጥ ገብቶ መድረሱን ያብራራቱ ፕሬዜዳንቱ " አደጋው እጅግ በጣም አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።

አደጋው እንዴት ሊደርስ ቻለ በሚለው ጉዳይ ላይ ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተጠየቁት ዶ/ር ኢብራሂም " መኪናው ገደል ውስጥ የገባበት ቦታ በተደጋጋሚ መሰል አደጋዎች የሚደርሱበት ቦታ ነው ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከአደጋው የተረፉና ህክምና ላይ ያሉ መምህራኖቻችን ናቸው እንዴት የተፈጠረ የሚለውን መረጃውን መስጠት የሚችሉት " ብለዋል።

" በአካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ግን መኪናው አደገኛ ኩርባ አለች እሱን ጨርሶ እንደወረደ ቀጥታ እንደገባ ነው የነገሩን " ሲሉ አክለዋል።

በአደጋው እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን የገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከጉዳት የተረፉ በዶዶላ፣ ሻሸመኔ፣ ሀዋሳ ሆስፒታሎች ህክምና ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተዋል። በህክምና ላይ ካሉት ቀላል ጉዳት እንዲሁም ከባድ ጉዳት የደረደባቸው ያሉ ሲሆን ተቋሙ እነሱን እየተከታተለ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ህይወታቸው ያለፈውን ወደ ጎባ ሆስፒታል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው " በብዛት የባሌ አካባቢ ተወላጆች ስለሆኑ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተሟልተው ቤተሰቦቻቸው ወስደወል፤ ራቅ ራው ካሉ አካባቢዎች የመጡ መምህራኖቻችንን ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሽኝት እንዳረጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ለማስተማር ወደ ዶዶላ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ የዩኒቨርስቲው #መምህራን፣ #ሠራተኞች እና #ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

28 የሚሆኑ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው አደጋው ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ አብረውት ለነበሩት የምዕራብ አርሲና የባሌ ዞኖች፣ የሻሸመኔ፣ አዳባ፣ ዶዶላና ሮቤ ከተሞች ነዋሪዎችና አመራሮች ዩኒቨርስቲው አመራርና ሠራተኞች በተለይ አደጋው የተፈጠረበት አከባቢ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
877 views08:09
Open / Comment
2023-05-21 11:09:18
767 viewsedited  08:09
Open / Comment