Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.92K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 3

2023-08-27 12:21:49
የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው። በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

#MoE

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
13.1K viewsedited  09:21
Open / Comment
2023-08-25 21:39:45
የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
12.6K viewsedited  18:39
Open / Comment
2023-07-25 08:30:51
በቅድሚያ ለ 2015 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች   እንኳን ደስ አላቹ እያልን ለተመራቂዎች ፣ ለልደት ፣ ለ Anniversary እና ለማንኛውም ዝግጅት  ምርጥ ስጦታ ከዚህ በፊት ያልተለመደ ማንኛውንም አይነት ፎቶ ወይም ምስል ባማረ ሁኔታ እንጨት ላይ በ#MDF Colour ስራዎቻችን  በተመጣጣኝ ዋጋ በሚፈልጉት Size ለወዳጅ ዘመድዎ ያበርክቱ 


ይዘዙን ያሉበት ቦታ በነፃ  እናደርሳለን!

Contact:   @Henak_21
                  0924848164

#For_More_Gifts_Package
@Habesha_Gift
2.5K views05:30
Open / Comment
2023-07-24 22:55:36 የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ የRemedial ውጤት


በመጀመሪያ ፋይሉን ክፈቱ ከዚያም በተዘጋጀው ቦታ ላይ ሙሉ መታወቂያ ቁጥራችሁን (ID NO) በተዘጋጀው ቦታ ላይ ብቻ ጻፉ እንደ DTU16R1245:: ከዚያ ENTER ወይም NEXT ተጫኑ። ሁሉንም ውጤት እና መረጃ ማግኘት ትችላለችሁ፡፡ በገጹ ላይ የሚታየው ስም የእናንተ መሆኑን አረጋግጡ።

First open the file then Type Your full ID NO on the space provided. like DTU16R1245 . Then press enter or next. You can get all result and information. Make sure that the name displayed in the interface is yours.

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.8K views19:55
Open / Comment
2023-07-24 22:55:22 Jigjiga University #Remedial Program Students Results #NaturalScience


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.5K views19:55
Open / Comment
2023-07-24 15:55:26 ለድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ ት/ቤት ባሉት የተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛው እና በተከታታይ መረሃ-ግብሮች በ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

ሙሉ የማስታወቂያውን ይዘት እና የትምህርት አይነቶቹን ከዩኒቨርሲቲው ኦፊሲያል ቴሌግራም ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.8K viewsedited  12:55
Open / Comment
2023-07-24 15:28:19
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ


ማስተርስ ተመራቂ መሆኑን ልብ ይሏል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.9K views12:28
Open / Comment
2023-07-24 14:07:42
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመለከቱ ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና  ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ ያለውን የተማሪ አቀባበል፣የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አበረታተዋል ።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሀምሌ 19 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.8K views11:07
Open / Comment
2023-07-24 12:09:56
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ተሰርዘ

በክልሉ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል መሰረዙን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

የምረቃ በዓሉን ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የምረቃ ፕሮግራሙ መሰረዙን የተቋሙ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ከተማ ጥላሁን (ዶ/ር) ገልፀዋል።

"ተማሪዎቻችንን ለማስመረቅ ተዘጋጅተን ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰው እየሞተ የምረቃ በዓል ማድረግ ትርጉም አይኖረውም" ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ።

የተቋሙ አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት ዶ/ር ከተማ፤ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የምረቃ በዓሉን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቁመዋል።

659 የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እና ሁለት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ አሁን ላይ ጊዚያዊ ዲግሪ (Temporary) እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን ከ6 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከትላንት ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል።

ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.8K views09:09
Open / Comment
2023-07-24 11:31:22
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ከስርቆት ነጻ የሆነ ፈተና ለመስጠት የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከየሚማሩበት ትምህርት ቤት ወጣ ብሎ በመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሰጠት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

የቅበላ ሂደቱም ከዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሐምሌ18/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ስለፈተናው ሁኔታ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቶ ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ውቢቷ ወልድያ ከተማና ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ በማለት ዩኒቨርሲቲው መልካም ዕድል ተመኝቷል።

#አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.7K viewsedited  08:31
Open / Comment