2023-05-04 11:38:06
በግቢው ጥበቃ የተመታችው ተማሪ በፍትህ ፋንታ ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሚገኝ ገለጸች።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ አመት Hotel and Tourism managment ተማሪ የሆነችው ኤደን ገብሩ በግቢው ተረኛ ጥበቃ በመመታቷ በደረሰባት ጉዳት ሆስፒታል ተኝታ እንደምትገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ጉዳዩን ከተጎጂ፣ ከዓይን እማኞችና ከግቢው አካላት ለማጣራት ሞክረናል።
ተማሪ ኤደን ባነጋገርንበት ወቅት ጥቃት የደረሰባት በቀን 21 ዕለተ ቅዳሜ ጠዋት ላይ ከጓደኛዋ ጋር ቤተክርስቲያን ሄደው ሲመለሱ እንደሆነ ገልጻለች። መታወቂያ(ID) ባለመያዟ በር ላይ የሚቆጣጠሩ ጥበቃዎች አላስገባ እንዳሏት፤ እሷም እንደጠፋባትና በሚል ካርድ (በመመገቢያ ካርድ) ለመግባት መጠየቋን፤ በዚህም መከልከሏን ትናግራለች።
በር ላይ ከነበሩት ጥበቃዎች ሴት ጥበቃ እንደነበረችና እሷን እያዋራች በነበረችበት ሰዓት አንዱ ጥበቃ "ዞር በይ" በማለት ትከሻዋን በተደጋጋሚ ሲገፈትራት "አትገፍትረኝ" እንዳለችውና ከዚያ በኋላ በጥፊ እንደመታት፤ ከእንብርቷ በታች እንደረገጣት ትገልጻለች።
ከዚህ በኋላ ሌላኛው ዘበኛ "እንዴት ትነጋገሪያለሽ ቢመታሽስ አባትሽ አይደል" በማለት አባብሎ ወደ ግቢ እንዳስገባት፤ ከዚያም ጓደኞቿ ደግፈዋት ወደ ዶርም እንዳስገቧት ታስታውሳለች።
ጉዳዩን በግቢው ባለ ሴቶችና ህጻናት በማምራት ጉዳይዋን ብታማክርም ሰኞ ዕለት ማመልከቻ ይዛ እንድትመጣና አሁን መስራት እንደማይችሉ ይነግሯታል። እዛው ቢሮ እንዳለች እራሷን ስታ መውደቋን የምታስታውሰው ተማሪ ኤደን፥ በመጀመሪያ ወደ ግቢው ሆስፒታል ቀጥሎም በሪፈር ወደ ከተማው ሆስፒታል ተወስዳለች።
በሆስፒታልም X-ray እና UltraSound ተነስታ በማኅጸን አከባቢ ደም መቋጠሩንና ለሦስት ቀን ክትትል ተደርጎ መድኃኒቱ ካልበተነው ቀዶ ጥገና እንደሚደረግላት እንደተነገራት ታስታውሳለች። ሆኖም ሰኞ ዕለት "ውጤትሽ ጤናማ መሆንሽን ነው ሚያሳየው ውጪ" እንደተባለችና ህመሙ ግን እንዳልተሻላት ባነጋገርናት ወቅት ነግራናለች።
ተማሪ ኤደን፥ የምርመራ ውጤቱን ለቤተሰብ መላክ እንደምትፈልግና ውጤቱን እንዲሰጣት ብትጠይቅም ከግቢ አጽፋ ካልመጣች ውጤቱን መስጠት እንደማይችሉ ከሆስፒታሉ እንደተነገራት ተናግራለች።
ይህንን ያደረገው ጥበቃ ምንም አይነት ህጋዊ እርምጃ እንዳልተወሰደበት የሰማን ሲሆን ከዩኒቨርስቲው አስተዳደር በኩል ማጣራት አልቻልንም።
"እስካሁን ድረስ በሚገባ ድጋፍና ክትትል ሳይደረግልኝ ተኝቼ ነው ያለውት፤ የአልጋ ወጪ ብቻ ነው የተቻለልኝ ሌላውን ሁሉንም ወጪ ከራሴ ነው የከፈልኩት፤ ነገሮች እየተሸፋፈኑ እየታለፉ ነው፤ የሚመለከተውም አካል ምላሽ እንዲሰጠኝ እማጸናለሁ" ስትል በእንባ የታጀበ ተማጽኖዋን አቅርባለች።
አሁን ላይ ጉዳዩን ለምን ወደ ሚዲያ አወጣችሁ በሚል የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እየደረሰባት እንደሆነ የገለጸችው ተማሪዋ ከየትኛው አካል እንደሆነ ገልጽ አላደረገችም። ከቀናት በኋላ የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች በሆስፒታል ተገኝተው እንደጠየቋት ቲክቫህ ሰምቷል።
የግቢው የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ምላሽ፦
"ለናንተ ልሰጥ የምችለው ምንም አይነት መረጃ የለኝም፤ ልክ እናንተ እንደሰማችሁት ነው እኔም የሰማውት፤ እጄ ላይ ምንም አይነት ማስረጃ የለም" የሚል አጭር ምላሽ አግኝተናል።
ከዚህ በተጨማሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሌሎች የዩኒቨርስቲው አመራሮችን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ስልክ ባለማንሳትና መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካ አልቻለም። በቀጣይ ዩኒቨርስቲው በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ተቀብለን የምናቀርብ ይሆናል።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
1.9K views08:38