2021-01-31 21:02:28
ማንነታችንን የምናሻሽልበት እና በእውቀት ላይ የታነጸ ህይወት ይኖረን ዘንድ ንባብ ለህይወታችን ወሳኝ ነው ።አንድ የእውቀት መአድ ልጠቁማችሁ ።
የውዱ ኡስታዛችንን ትምህርቶች መገኛ በፌስቡክ-እና በቴሌ ግራም።
ቴሌግራም ፦ http://t.me/abuhyder
ፌስ-ቡክ USTAZ ABU HYDER Offical Page
እና Sadiq Mohammed Ahmed በቴሌግራሙ ጆይን በማለት በፌስቡክ ገጹን ፎሎ በማድረግ ይጠቀሙ እውቀትን ይገብዩ።
ከእሥልምና ቀደምት ህግጋት መካከል በግንባር ቀደምትነት ከሚገኙ በርካታ ትእዛዛት ውስጥ ቀድሞ የምናገኘው የንባብ ጉዳይ ነው። አምላካችን አላህ (ሱወ) ነቢያችንን ﷺ እንዲህ ሲል አዟቸዋል ታላቁን መልእክት ኢቅራእ” አንብብ” ሲል ነበር ቅድሚያ ያዘዛቸው ።
اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ
(ሱረቱ አል-ዐለቅ - 1)
አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ
(ሱረቱ አል-ዐለቅ - 2)
ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ
(ሱረቱ አል-ዐለቅ - 3)
አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ
(ሱረቱ አል-ዐለቅ - 4)
ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ
(ሱረቱ አል-ዐለቅ - 5)
ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
ይህ የአንብብ መርሕ ደግሞ በእምነቱ ጉልህ መመሪያ እንዲሆንም አስችሎታል። ንባብ ለህይወት መሥተጋብር ሁሉ እጅግ ወሳኝ ነው።
አንብብ ማንበብ ምላስን ያገራል እውቀትን ያሰፋል
ጥበብን ያስተምራል ከሥራ ፈቶች ይነጥላል ከሃሳብ ያሳርፋል ስኬትን ይጠቁማል ድክመትን ያሳያል ክብርን ይጠብቃል ሰውን ሙሉ ያደርጋል ።
http://t.me/abuhyder
1.3K views ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ ያረሡልﷺ ናፋቂ , 18:02