🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

Beza International Church

Logo of telegram channel bezachurch — Beza International Church B
Logo of telegram channel bezachurch — Beza International Church
Channel address: @bezachurch
Categories: Religion
Language: English
Subscribers: 2.09K
Description from channel

Beza International Church is a nondenominational Christian fellowship located in Addis Ababa, Ethiopia. The church was founded with the vision "Redeeming Nations in Righteousness!"
To connect with us, please reach out - @bezaconnect
Linktr.ee/bezachurch

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


The latest Messages 163

2021-03-31 06:00:14 ሰላም የሞላው ህዝብ
 

የመጋቢት 22/ 2013 ዕለታዊ ቃል
ዮሐንስ 20: 19-21  ይነበብ


ከእግዚአብሔር ከምንቀበላቸው እጅግ ውድ ስጦታዎች መካከል አንዱ ሰላም ነው። ስለዚህ የማውቃቸው ሰዎች ድነትን ሲለማመዱ ብዙውን ጊዜ ከሚሰጡት የመጀመሪያ አስተያየት ውስጥ በልባቸው እና በአዕምሯቸው ስለሚሰማቸው ሰላም ነው። ከእግዚአብሔር የሚመጣ ሰላም ኃይለኛ ነው እናም ሁል ጊዜ ልንጣበቅበት የሚገባ ስጦታ ነው።
 
በዮሐንስ 20፡19 ውስጥ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በራቸውን ዘግተው ተቀምጠው እናገኛቸዋለን። ልክ በመስቀል ላይ በኢየሱስ ላይ የሆነውን አይተዋል እናም ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል አውቀዋል። ከዚያ ኢየሱስ ተገለጠላቸውና የተናገረው የመጀመሪያው ነገር “ሰላም ለእናንተ ይሁን” ነው። አትፍሩ አይልም፣ ፍቅር ከእናንተ ጋር ይሁን አይልም ይልቁንስ ስለ ሰላም ይናገራል። እሱ በሚሰጣቸው ሰላም ውስጥ እራሳቸውን የማግኘት ችሎታቸው እንቅስቃሴያቸውን እንደሚለውጠው ያውቃል። ከአሁን በኋላ ተደብቀው መቆየት አይኖርባቸውም፤ ነገር ግን ኢየሱስ እንዲንቀሳቀሱ በጠራቸው መንገዶች ወደፊት መሄድ ይችላሉ።
 
ሰላም እግዚአብሔር ለእኛ ባሰባቸው ነገሮች ወደፊት መጓዝ ከሚያስችሉን ቁልፍ ግብአቶች አንዱ ሰላም ነው። ተግዳሮቶች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጠሙን ከእግዚአብሔር ብቻ ሊመጣ የሚችለውን ሰላም መቀበል የምንችልበትን መንገድ መፈለግ አለብን። ከሁኔታዎች ያለፈ በቃላት ልናብራራው የማንችለው ዓይነት ሰላም።
 
ብዙውን ጊዜ   ስጋትና ጭንቀት በሚቆጣጠረው ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔር ሰላም የተለየ ሁኔታን ያሳያል። ዓለም ይህን የመሰለ ሰላም እየፈለገ ነው። እርሱን ተርበዋል። በዓለም ላይ በጣም ፈታኝ በሆነበት ወቅት ይህ ሰላማችን እኛ ማን እንደሆንን ለማሳየት ለእግዚአብሔር ህዝብ ቁልፍ ነገር ነው። እራሳችንን በምንገኝባቸው ሁኔታዎች መካከል ሁል ጊዜ እንደዚህ ዓይነቱን ሰላም  ለመቀበል  በሚያስችለን ስፍራ ላይ መሆናችንን ማረጋገጥ አለብን።
 
የሕይወት ተዛምዶ
በሕይወታችሁ  ውስጥ የእግዚአብሔርን ሰላም የማታገኙባቸው ስፍራዎች አሉ? በዚያ ስፍራ የእግዚአብሔርን ሰላም ለመቀበል እራችሁን እንዴት  ዝግጁ ማድረግ ትችላላችሁ?

ፀሎት
እግዚአብሔር  ሆይ፣ እኔ እራሴን በማገኝባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት በአንተ ሰላም መኖር እንደምችል አስተምሩኝ።  ከዚያ  የሰላም ስፍራ እንዴት እንደምኖር እናም አንተን መወከል/ማሳየት እንደምችል አሳየኝ።
346 views03:00
Open / Comment
2021-03-31 06:00:14
270 views03:00
Open / Comment
2021-03-31 06:00:14   Peace Filled People


A Daily Devotional for March 31, 2021
Read John 20:19-21

Peace is one of the most valuable gifts that we can receive from God. So many times when people I know have experienced salvation one of the first comments they often make is about the peace they feel in their heart and in their mind. Peace that comes from God is powerful and a gift we must continually tap into.
 
In John 20:19 we find the disciples shut in, in fear of the Jews. They saw what had just happened to Jesus on the cross and they knew that their lives could be in danger. Then Jesus appears to them and the first thing he says is “Peace be with you.” He doesn’t say don’t be afraid, he doesn’t say love be with you, instead he talks about peace. He knows that their ability to find themselves in the peace He can give will change their trajectory. They no longer will have to remain in hiding but they can move forward in the ways that Jesus is calling them to move.
 
Peace is a key ingredient to being able to move forward in the things that God has for us. Challenges and tough circumstances are going to come and we have to find a way to align ourselves to receive the peace which can only come from God. The kind of peace that surpasses circumstances and often cannot be explained.
 
In a world often controlled by anxiety and worry, the peace of God tells a different story. The world is looking for this kind of peace. They are hungry for it. In times of great challenge in the world this is a key component to the people of God showing who we truly are. We must position ourselves to access and receive this kind of peace in the midst of the circumstances we find ourselves in.

Life Application
Are there areas in your life where you are not experiencing the peace of God? How can you realign yourself to receive God’s peace in that area?

Prayer
God, teach me how to remain in your peace despite the circumstances I find myself in. Show me how to live from that place so I can represent you well.
275 views03:00
Open / Comment
2021-03-31 06:00:14
267 views03:00
Open / Comment
2021-03-31 06:00:14 Good Morning Beza!

Here’s your Daily Devotional for today by Pastor Haley Millar፡

“Peace is a key ingredient to being able to move forward in the things that God has for us!”

“ሰላም እግዚአብሔር ለእኛ ባሰባቸው ነገሮች ወደፊት መጓዝ ከሚያስችሉን ቁልፍ ግብአቶች አንዱ ነው!”

Daily Devo 240 (March 31, 2021)
ዕለታዊ ቃል 240 (መጋቢት 22/ 2013)

http://bit.ly/DailyDevo240
***

For prayer, reach out
ለፀሎት በዚህ ያግኙን

@needprayer
298 views03:00
Open / Comment
2021-03-30 20:19:08 Beza International Ministries pinned «Dear Beza, We would like to announce that we have closely examined the Directive 30 issued by the government and Beza is complying with the requirements of wearing masks, using sanitizers and maintaining a seating that is 25% of hall capacity with 2 meters…»
17:19
Open / Comment
2021-03-30 20:19:03 Beza International Ministries pinned «ውድ ቤዛ፣ መንግስት ያወጣውን መመሪያ 30 በሚገባ ገምግመን እንደ ቤዛ ማስክ ማድረግ፣ ሳኒታይዘር መጠቀም፣ ከአዳራሹ አቅም 25% ሰው ብቻ ማስተናገድና በ2 ሜትር ርቀትን ወንበሮች እንዲቀመጡ የሚያስገድደውን እስካሁን እየፈጸምን እንገኛለን። ስለሆነም ሁሉም የአምልኮ ፕሮግራሞቻችን እንዲሁም የፀሎት መርሃ ግብሮች እንደተለመደው እንደሚቀጥሉ ለማሳወቅ እንወዳለን። እያንዳንዱ ሰው በእንቅስቃሴው ላይ ጥንቃቄ…»
17:19
Open / Comment
2021-03-30 14:16:30 ውድ ቤዛ፣

መንግስት ያወጣውን መመሪያ 30 በሚገባ ገምግመን እንደ ቤዛ ማስክ ማድረግ፣ ሳኒታይዘር መጠቀም፣ ከአዳራሹ አቅም 25% ሰው ብቻ ማስተናገድና በ2 ሜትር ርቀትን ወንበሮች እንዲቀመጡ የሚያስገድደውን እስካሁን እየፈጸምን እንገኛለን። ስለሆነም ሁሉም የአምልኮ ፕሮግራሞቻችን እንዲሁም የፀሎት መርሃ ግብሮች እንደተለመደው እንደሚቀጥሉ ለማሳወቅ እንወዳለን። እያንዳንዱ ሰው በእንቅስቃሴው ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የመንግስት መመሪያዎችን እንዲያከብር እናበረታታለን።

በሌላ ማስታወሻ ላይ ማንኛውም ሌሎች ስብሰባዎች፣ ሠርግ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቶች፣ ወዘተ በመመሪያው ቢበዛ እስከ 50 ሰዎች ተወስነዋል። ስለዚህ ቤተክርስቲያኗ በውስጧ ላሉት እንደዚህ ላሉት ፕሮግራሞች ይህንን መመሪያ ታከብራለች።

የቤት ሕብረቶችን (ሆም ኬር) በተመለከተ፣ የኮቪድ ታማሚዎች ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየቱ ላልተወሰነ ጊዜ በኦንላይን ላይ መገናኘት ቢቀየር የተሻለ እንደሚሆን ወስነናል። ስለሆነም ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ሁሉም ሆምኬሮች በኦንላይን እንዲገናኙ ወስነናል። ሆኖም በአካል ለመገናኘት ከፈለጉ በታበርናክል እና በቲኬ ሕንፃ ውስጥ ሆም ኬር የሚያደርጉበት ሰፊ የመሰብሰቢያ ቦታ ስላዘጋጀን እዚያ መጠቀም እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

ደህንነትዎን ይጠብቁ እና ተባረኩ!
424 views11:16
Open / Comment
2021-03-30 14:16:18 Dear Beza,

We would like to announce that we have closely examined the Directive 30 issued by the government and Beza is complying with the requirements of wearing masks, using sanitizers and maintaining a seating that is 25% of hall capacity with 2 meters distancing. Therefore, we would like to announce that all our worship services as well as prayer programs will continue as usual. We advise everyone to be cautious in your engagement and adhere to the government guidelines.

On another note, any other meetings, weddings, funerals, etc. are limited by the Directive to a maximum of 50 people. Thus, Beza will be adhering to this guideline for such events in the church.

Regarding homecares, given the high rise in COVID cases, we have decided that it would be best to revert to meeting online until further notice. Thus, effective immediately, we are instructing all homecares to meet online starting this week. However, if you would like to meet in person, we have arranged space in the Tabernacle and TK which has ample meeting space where you can meet for Homecare.

Stay safe and stay blessed!
415 views11:16
Open / Comment
2021-03-30 06:32:09 ሕሊና 5

የመጋቢት 21/2013 ዕለታዊ ቃል
1 ጢሞ.1: 19; ኢሳይያስ 6፡ 5-6  ይነበብ

አፍም በሕሊና ላይ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የጋራ-ዕውቀትን ያጸናል። ከሌላው ፍጥረት የሚለየን አንድ ነገር ቢኖር መናገር መቻላችን ነው። እግዚአብሔርን እጅግ የሚያንፀባርቀው አንዱ ክፍላችን ነው። 

ኢሳይያስ የእግዚአብሔርን ክብር ባየ ጊዜ እጅግ ፈራ። እርሱም ጮሆ፣   “ወዮልኝ፤ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው……. ” አለ። ኢሳይያስ ስለላለፈ ስራው፣ ስለ ጉድለቶቹ ወይም ስለ ባህሪው እንዳልተጨነቀ ልብ በሉ። ነገር ግን ስለ ከንፈሮቹ ተጨንቆ ነበር። ምላስ የአንድን ሰው ሕይወት በመቅረጽ ረገድ የሚጫወተውን ሚና ተረድቷል። ያዕቆብ 3:4 ላይ፣ “መርከቦችን ተመልከቱ፤ ምንም እንኳን  በጣም ትልቅና በሃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም የመርከቡ ነጂ  ትንሽ  በሆነ መሪ  ወደ ሚፈልገው አቀጣጫ ይመራቸዋል። እንዲሁም ምላስ…… ”

ለኢሳያስ ጩህት መልአኩ ከመሠዊያው የእሳት ፍም ወስዶ አፉን በመዳሰስ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፣ በደልህ ተወግዶልሃል ኃጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለው። ይህ የአዲስ ኪዳን አማኝን የሆነ ነገር ሊያስታውሰው ይገባል፡-መሠዊያው የሚቃጠለው መስዋዕት ሥፍራ ነበር፣ ይህም የክርስቶስ ስቅለት ምሳሌ ነበር። 

የኢሳይያስ ኃጢአት ከንፈሩን በነካው ነገር ምክንያት ተወስዶለታል። ለእኛም ከዚህ የተለየ አይደለም።በልባችን በማመንና በአፋችን በመመስከር ድነናል። (ሮሜ 10:9-10) በበጉ ደም እና በምስክርነታችን ቃል አሸንፈናል። (ራእይ 12፡10)

ሕይወታችን የሕሊናችን ውጤት ነው፤ ሕሊናችን የአንደበታችን ውጤት ነው።

የሕይወት ተዛምዶ
ይህንን የመዳን ስጦታ እስካሁን ካልተቀበላችሁ በሮሜ 10፡9-10 ላይ ያለውን መመሪያ ተከተሉ፡- “ ኢየሱስ ጌታ ነው ብለህ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ።” ይህንን ስጦታ ተቀብላችሁ ግን ከጥፋተኝነት ፀፀት ጋር እየታገላችሁ ከሆነ ተመሳሳዩን ሂደት ተግብሩ።

ፀሎት
አባት ሆይ፣ ዛሬ የተጠናቀቀው ሥራህ  ከንፈሮቼን እንዲነካ እፈቅዳለሁ!!
370 views03:32
Open / Comment