Get Mystery Box with random crypto!

ገበታ Recipes®

Logo of telegram channel gebeta_recipes — ገበታ Recipes®
Logo of telegram channel gebeta_recipes — ገበታ Recipes®
Channel address: @gebeta_recipes
Categories: Food
Language: English
Subscribers: 3.15K
Description from channel

Do you want to cook something different today ? Or do you want to give a spicy twist to your daily boring recipes? Then you are at right place .Enjoy our channel and learn the art of cooking foods and recipes.
Admin: [ @Tiletimothy @fasika_girma ]
አጣጥሙት

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


The latest Messages 3

2021-07-15 19:13:49
@Gebeta_Recipes
765 views16:13
Open / Comment
2021-07-07 19:08:13 ቤት የሚሰራ የእንጆሪ አይስክሬም

• ግብዓቶች
• 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• 200 ግራም እንጆሪ
• 3 እንቁላል
• 300 ሚሊ ሊትር ክሬም (6 የቡና ስኒ)
• 60 ግራም ስኳር (1 የቡና ስኒ እና 1 የሾርባ ማንኪያ)

• አሰራር
1. በትንንሽ ጎድጓዳ ሰሀን የእንቁላል አስኳል፣ ስካርና ቫኒላ ጨምሮ መምታት፤
2. በልላ ጎድጓዳ ሰሀን ክሬሙን ጨምሮ እስኪወፍር ድረስ መምታት፤
3. እንቁላሉን እና የተመታውን ክሬም በአንድ ላይ መቀላቀል እና ማዋሃድ፤
4. ሁለት ዕቃ አድርጎ ክሬሙን እኩል ለሁለት መክፈል፤
5. የሙዝ ኬክ መጋገሪያ ውስጥ የክሬሙን ግማሽ ጨምሮ ወደ ዲፕፍሪዝ ውስጥ አስገብቶ ለ1 ሰዓት ያህል ማቆየት፤
6. እንጆሪውን በጁስ መፍጫ ፈጭቶ የተፈጨውን እንጆሪ ወደ ክሬሙ ውስጥ መጨመር፤
7. በደንብ አደበላልቆ ከዲፐፍሪዘር አውጥቶ የእንጆሪ ክሬሙን መጨመር እና በደንብ አዳርሶ ለሌላ 2 ሰዓት ዲፕፍሪዝ ውስጥ ማድረግ፤
8. ማቅረብ ሲፈለግ ከዲፕፍሪዝ ውስጥ አውጥቶ በሰሀን ማቅረብ።

@Gebeta_Recipes
1.6K views16:08
Open / Comment
2021-07-07 19:07:58
@Gebeta_Recipes
1.4K views16:07
Open / Comment
2021-07-03 14:21:20 የካካዋ ብስኩት

• ግብዓቶች
• 200 ግራም የፍርኖ ዱቄት (4 የቡና ስኒ)
• 200 ግራም ስኳር (4 የቡና ስኒ)
• 200 ግራም የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን
• 1 እንቁላል
• 2 የሾርባ ማንኪያ ካካዋ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• (1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው

• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180° ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
2. በጎድጓዳ ሰሀን እንቁላል፣ ቫኒላ፣ የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን እና ስኳሩን ጨምሮ በደንብ መምታት፤
3. በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን ዱቄቱን፣ ካካዋ፣ ቤኪንግ ፓውደሩንና ጨው ጨምሮ በደንብ ማዋሃድ፤
4. እንቁላሉን ወደ ዱቄቱ አደባልቆ በእጅ ማሸት፤
5. ሊጡ ከወፈረ በኋላ ንጹህ ጠረጴዛ ላይ አድርጎ በመዳመጫ ወይም በጠርሙስ መዳመጥ፤
6. የብስኩት ቅርጽ ማውጫ ወይም የቡና ስኒ በመጠቀም በክብ በክብ አድርጎ ማውጣት፤
7. ዘይት የተቀባ የብስኩት መጋገሪያ ትሪ ላይ አድርጎ ለ20 ደቂቃ መጋገር፤
8. ዙሪያው ቡናማ እስኪሆን ማብሰል፤ አውጥቶ ማቀዝቀዝ።

@Gebeta_Recipes
1.9K views11:21
Open / Comment
2021-07-03 14:21:09
@Gebeta_Recipes
1.7K views11:21
Open / Comment
2021-06-24 12:35:04 ሐምበርገር

• ግብዓቶች
• ግማሽ መካከለኛ ጭልፋ ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
•1 የሾርባ ማንኪያ ደቆ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
•ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
•ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
•ግማሽ የቡና ሲኒ የፉርኖ ዱቄት
•ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ሮዝመሪኖ
• 300 ግራም የተፈጨ ቀይ ሥጋ
• 2 ዕንቁላል
• 4 የቡና ሲኒ (100 ግራም) የዳቦ ዱቄት
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ፐርስሊ
•1 የሻይ ማንኪያ በርበሬ
•2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
•2 ዝንጣፊ የሠላጣ ቅጠል
•3 ክብ የሐምበርገር ዳቦ ወይም 6 ተጠብሶ በቅቤ የወዛ ስስ ዳቦ
•3 በስሱ የተቆረጠ ክብ ቲማቲም

• አሰራር
1. ከዘይት፣ ከሠላጣ፣ ከዳቦውና ከቲማቲሙ በስተቀር ሌሎቹን ጥሬ ዕቃዎች በሙሉ ቀላቅሎ በደንብ በእጅ ማሸት፤
2. ሦስት ቦታ ከፍሎ በክብ ማድቦልቦልና መጠፍጠፍ ፤
3. በግሪል ወይም መጥበሻ ለይ በጋለ ዘይት መጥበስ፤
4. የተጠቀሙት ክቡን ዳቦ ከሆነ ከጎኑ በመቁረጥ ሁለት ቦታ ከፍሎ በቅቤ ማውዛት፤
5. አንዱ ቁራጭ ላይ የተጠቀሰውን ሥጋ ፣ ቀጥሎ የሠላጣ ዝንጣፊ ከዚያም አንድ ቲማቲም ካደረጉ በኃላ ሌላ ቁራጭ ዳቦ ከላይ መደረብ፤
6. በዚህ መልኩ ቀሪዎቹን አዘጋጅቶ መጨረስ፤
7.ከድንች ጥብስና ካሮት ጋር ሊቀርብ ይችላል።

@Gebeta_Recipes
3.4K views09:35
Open / Comment
2021-06-24 12:34:11
@Gebeta_Recipes
2.7K views09:34
Open / Comment
2021-06-20 16:10:36 ካሮት ካፕ ኬክ

• ግብዓቶች
• 3 ካሮት (የተፈቀፈቀ)
• 250 ግራም ፍርኖ ዱቄት /5 የቡና ስኒ/
• (1/2) ሩብ የሾርባ ማንኪያ ጨው
• 50 ግራም ዘቢብ (1 የቡና ስኒ)
• 2 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 100 ሚሊ ሊትር ዘይት (2 የቡና ስኒ)
• 150 ግራም ስኳር (3 የቡና ስኒ)
• 1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ
• 4 እንቁላል

• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180°c ሴንቲ ግሬድ ማሞቅ፤
2. በትልቅ ጎድጓዳ ሰሀን ፍርኖ ዱቄት፣ ቤኪንግ ፓውደር፣ የተፈጨ ቀረፋ እና ጨው በደንብ ማደበላለቅ፤
3. በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ እንቁላል እና ስኳሩን በደንብ መምታት፤
4. ዘይቱን እንቁላል ውስጥ ጨምሮ በደንብ መምታት፤
5. ሶስቱን ካሮት ልጦ በመፈቅፈቂያ በደቃቁ መፈቅፈቅ፤
6. የተመታውን እንቁላል የፍርኖ ዱቄት ውህድ ውስጥ መቀላቀል፤
7. ካሮትና ዘቢቡን ጨምሮ በደንብ ማደበላለቅ፤
8. የካፕ ኬክ መስሪያውን ዘይትና ዱቄት ቀብቶ በጭልፋ እኩል እየከፈሉ እያንዳንዱ የካፕ ኬክ ዕቃ ውስጥ መጨመር፤
9. ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ኦቨን ውስጥ ጨምሮ መጋገር፤
10. ከኦቨን ውስጥ አውጥቶ 30 ደቂቃ ያህል ማቀዝቀዝ።

@Gebeta_Recipes
709 views13:10
Open / Comment
2021-06-20 16:10:27
@Gebeta_Recipes
700 views13:10
Open / Comment
2021-06-16 17:31:03 Banana cake
ባናና ኬክ

• ግብዓቶች

• 5 እንቁላል
• 3 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 100 ሚሊ ሊትር ወተት
• 50 ሚሊ ሊትር ዘይት
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
• 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• ግማሽ ኪሎ ግራም የፉርኖ ዱቄት
• 3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ስኳር
• ግማሽ ኪሎ ግራም ሙዝ

• አሰራር
1. ሙዙን ልጦና ከትፎ ከስኳሩ ጋር በዕንቁላል መምቻ እስኪወፍር ለረጅም ጊዜ መምታት፤
2. እንቁላሉን በዝግታ እየጨመሩ መምታት፤
3. ወተቱንና ዘይቱን ጨምሮ በደንብ ማዋሃድ፤
4. ጨዉን፣ ዱቄትና ቤኪንግ ፓውደር ጨምሮ ትንሽ ከመቱ በኳላ ቫኒላውን መጨመር፤
5. የኬክ መጋገሪያ ትሪ ላይ ቅቤ ቀብቶ ዱቄት በላዩ ከነሰነሱ በኋላ ዱቄቱን አራግፎ ውሁዱን መጨመር
6. የሞቀ የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ በ220°c ለ45 ደቂቀ መጋገር ፤
7. ሲቀዘቅዝ እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ።

@Gebeta_Recipes
762 viewsedited  14:31
Open / Comment