Get Mystery Box with random crypto!

ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

Logo of telegram channel geezlibrary — ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ
Logo of telegram channel geezlibrary — ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ
Channel address: @geezlibrary
Categories: Literature
Language: English
Country: Not set
Subscribers: 8.73K
Description from channel

በኢትዮጵያውያን ደራስያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ሚተረኩበት ድንቅ ሀገራዊ ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 2

2021-05-20 21:17:21 ..................... ፪ ...............
የቀጠለ ....
...
ሌላው የደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ጥልቅ የፖለቲካ አረዳድ ችሎታ ሶቬት ህብረቱን ሊቀመንበር ሚካኤል ጎርቫቾቭ የሶሻሊስት ርዕዮተ አለም ትንታኔ ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አዛምዶ የሚያቀርብበት ስነዳ የደራሲው እምቅ የአረዳድ ችሎታ ሀሳቡን የሚሰማ ትውልድ ካለ ጠቃሚ ነጥቦችን በማሳረፍ ለውጥ ውሃ እንደጠማው የበረሃ ተጓዥ መንገደኛ ጥሟን የሚከላ ነው ብዬ አስባለሁ።
ደራሲው ሀብታሙ አለባቸው ስነፅሁፍንና አብዮት ነክ የታሪክ አተራረክ ፍሰትን የራሱ በሆነ ቀለም ለዘመናችን በሚመጥን ዘውግ አዲስ ነገር ፈጥሯል ብሎ ለማለት ቀደምት ስራውን የሱፍ አበባን እና የቄሳር እምባን ሁለት ድንቅ ልቦለዶች ማንበብ በቂ ሲሆን ረቂቁን አይቶ ጀርባው ላይ አስታየቱን ያሰፈረለት የአዲስ አድማሱ አምደኛ አቶ ደረጀ ይመር " ከአወዛጋቢው ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ በኃላ ስነ ፅሁፍንና ፖለቲካን " ድል ባለ ሰርግ" ያጋባ ደራሲ አቶ ሀብታሙ አለባቸው ይመስለኛል' እንዳለው እኔም በሀሳባቸው እስማማለሁ።
አብዮቱ ኢትዮጵያ ላይ ያሳረፈውን ጥቁር ጠባሳን በማሳየትም የልጅን አስክሬን ለመቅበር የጥይት ፍሬ ገንዘብ ከፍሎ ከማንሳት ወላጅን አለ ጧሪ ቀባሪ የማሳጣት እንዲሁም ሁለት ወንድማማች ሀገሮችን ለስልጣን ጥም ሲባል በፖለቲካ ደባ ህዝብ ማለያየት ፣ ንፁሃንን አለርህራሄ መግደል፣ ሀብት መዝረፍ፣ቤተሰብ ውበቷ ያማረ ልጅ ካለውም በሞት አስፈራርቶ መንጠቅና መድፈር ያሉትን የአብዮቱ ዘመን መገለጫ የነበሩ ትዕንቶች በአይነ ህሊናችን እንዲቀረፅ በብርቱ የተጋበት ፈርጅ ደራሲው የተዋጣለት የአተራረክ ዘውግን በመከተሉ ቆመን የምናጨበጭብለት ነው።
እንደመዝጊያ ይህን መሰል የአንድ ዘመንን አኗኗር ፣ የአስተሳሰብ ብስለት፣ የኑሮ ውጣ ውረድ፣ የመሪና የህዝብ ግንኙነት ስራን አበክሮ ለታሪክ ማቆየቱ አንባቢ ፊደላቱን መቁጠሩና መደርደሪያው ላይ ከመሰብሰቡ ባለፈ ከዘመን ተምረን የተሻልን እንድንሆን የሚያነቃ ትልቅ ማስተማሪያ ነው ብዬ አምናለሁ።
ባለንበት እየረገጥን ዘላለም በህዝብ እና በሀገር እየተማረርን ኑሯችን ከእጅ አይሻል ዶማ እንዳይሆን እነዚህን መሰል መፅሀፎች እንደትልቅ መስታወት ራስን መመልከቻ መንገዶች ናቸው ብዬ አምናለሁ።
የቱ ጋ ነኝ? ወደ የት ነው ጉዞዬ? መጨረሻዬስ? የሚሉ ብርቱ ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን በመፍታት በማህበረሰብ ንቃተ ህሊና አልያ በሀገር ላይ የሚነሳን ህዝባዊ አመፅ ለመግታት እንደ ሀብትሽ ያሉ ጀግና ደራሲያን ያስፈልጉናል ባይ ነኝ።
አሁንም አበክሬ የምናገረው የቄሳር እምባን የመሳሰሉ በብስለት የተፃፉ መፅሀፍት ለሀገር እድገት ከፍታ የሚውሉት ውለታ ይህ ነው የሚባል አይደለም።
አንባቢው ከመቶ አለቃ በላይ እና ሀምራዊት የከንፈር መሳሳምና የአልጋ ትይንት ባለፈ ወይም በኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም አስቂኝ ና አይረሴ ስድቦች ባሻገር እንደሀገር የሚለውጡን በርካታ ሀሳቦች ላይ ማተኮር ቢቻል ብዬ እያሳሰብኩ እንደመዝጊያ ከመቶ አለቃ በላይነህ " የልግመት ኢትዮጵያ " ጥናት ውስጥ የሚካኤል ጎርባቼቭን በዘመን መካከል ፀንታ የምትቆይ አባባል ላንሳና እንሰነባበት እነሆ፦
..... " የልግመት ሶሻሊዝም ምልክቶች አንዱ የህዝብ ተስፋ መቁረጥ ነው። ያኔ ለመንግሥት ተቋማት አክብሮት አይኖረውም። ህግን የሚጋፋና ረብሻ ወዳድ ትውልድ ይፈጠራል።
ሱቅ ይገባል። ገንዘብ አይከፍልም። ያገኘውን ይዞ ይሮጣል።
በትንሽ አለመግባባት ግጭት ይቀሰቀሳል፣ ይደባደባል ፣ ይገዳደላል...። የትም ሶሻሊዝም ሀገር ሂዱ። ይህ ቀውስ መዋቅራዊ መልክ ይዞ ታገኙታላችሁ።"....
................. ገፅ 162 ..........
አንድ ያጣላልና አለፍ ብለን አንድ እንድገም ፦
...... " ሕዝብ አዲስ ነገር መፍጠር እንዳይችል እጁ ተጠፍሮ ሲያዝ መልሱ እምቢ ነው።
በዚህ ጊዜ በሶሻሊዝም ካባ የተጀቦነው መንግስት የግዳጅ መዶሻውን ያገሳል።..."
....................ገፅ 225 .........
የቄሳር እምባ ምንድነው?....ማነውስ ቄሳር?..... የጅማው አስተዳዳሪ የይማም ሚስት ሀምራዊትና የመንግስቱ አማችና አማካሪ የሆነው የሊቁ መቶ አለቃ በላይነህ የስውር የፍቅር ግንኙነትስ የት ድረስ ይዘልቃል?.... ይማም ለአመታት ከከረመበት ግዳጅ ሲመለስስ በሚስቱ በባላንጣውና በእሱ በኩል ምን ይፈጠራል?....መቶ አለቃ በላይነህን ትንፋሹ እስኪቆም ያስደነገጠው የጠፋው የግል ሚስጥራዊ ማስታወሻ ደብተሩስ ይገኝስ ይሆን..?...ማስታወሻው ላይ የተፃፉ አደገኛ ፅሁፎችንስ መንግስቱ ሀይለማሪያም ያነቡት ይሆን? ...የመንግስቱን የግል ጠባቂ መቶ አለቃ ምስጋናውንስ ማን ገደለው?......ይህንና መሰል ምስጢሮችን ለመፍታት የቄሳር እምባን ያንብቡ.... ደራሲውን በጥልቀት ለመተዋወቅም የሱፍ አበባን እና በቅርቡ ለህትመት የበቃውን ሕንፍሽፍሽ የተሰኘ መፅሀፉን ያንብቡ
አበቃሁ!
388 views18:17
Open / Comment
2021-05-20 21:16:53 .................... ፩ ......................
.... " ተመልሳ ስትሄድ ከጀርባዋ አይዋት። እንደሀረግ እጥፍጥፍ የሚል ወገብና ዛላ። ከሽከሽ ቀሚሷ ስር ባቶቿን ተመለከቱ።
እንደብዙዎቹ በአንቀልባ ታዝለው የሚያድጉ ሰሜነኛ ልጆች ባት አልቆጠረችም።
ይህቺ ብቻ ነበረች ቅሬታቸው። የደነገጠች ልባቸው ወደ ቦታዋ ለመመለስ ጊዜ ወሰደባት።
ጠጁን ደጋግመው ተጎንጭተው መመገብ ጀመሩ። አይኖቻቸው ግን ወደ ጀርባው በር እንደተተከሉ ቀሩ። ትንሽ ቆይተው ሴትየዋ ወደ ጀርባ ተጣሩ።
" ውባ.....ንች!..... ውባ...ንች!" አቤት ስትላቸው "ቡናውን አምጭ!"አሏት።
ሻንበል መንግስቱ ይሄኔ ደስ ብሏቸው ቁንጥንጥ አሉ።
........... የቄሳር እምባ ገፅ 37 ..........
#የቄሳር_እምባ
ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው
በ2007 ዓ.ም በ408 ገፆች ተሰንዶ ለሁለት እውቅ ኢትዮጵያዊ ደራሲያን ማለትም ለአቤ ጉበኛና በ ግርማ በማስታወሻነት ተበርክቶ ለአንባቢያን የቀረበው የደራሲ ሀብታሙ አለባቸው አብዮት ተኮር ታሪካዊ ረጅም ልቦለድን ተተርሰን በጥቂቱ ልንቃኝ ወደድን እነሆ ፦
እንደመንደርደሪያ በሰማያዊው የደርግ ካኪ ስለተቀለዱ ቀልዶች ከመፅሀፉ ላይ ከየገፁ አይተን ፈገግ ብለን እንሻገር እነሆ አንድ :-
........ "በዓሉ እንደምታውቀው ነው። የኢንግሊዝ ሱፍ የጣሊያን ሸማዝና የቱርክ ከረባት ይለብሳል።
የሚረጨውን ሽቶም ታስታውሳለህ።በብዙ ነገሩ ምዕራባዊ ነው።
ሱፍ መልበስን ለእሱ ብቻ የተፈቀደ አድርጎታል። እኛ ሱፍ ስንለብስ ግን ተሳለቀብን።
" አብዮቱ ተቀለበሰ እንዴ ? " ብሎ አላገጠ።
ዳዊት ካኪ እንልበስ የተባባልን ጊዜ ምን እንዳለ ታውቃለህ ? " ጉዳዩ ከልብሱ አይደለም! "ብሎ አሾፈብን።....
............... ገፅ 8 - 9 ...........
ይላል አንድ ያጣላል እንድገም እስኪ :-
....... " ጨፌ በቃ ይሄን የደንብ ልብስ አልሞክረውም ብለህ ቀረህ አይደል? "አሉ ሻለቃ ደመቀን ሽቅብ አንጋጠው እየተመለከቱ። ከተዋወቁ ጊዜ ጀምሮ በሚጠሩበት ቅፅል ስም ጠርተዋቸው ፈገግታ አሳይተዋቸው።
" ጓድ መንግስቱ ምን ላድርግ ብለህ ነው? ሞክሬው ነበር።
ግን እሱን ስለብስ ራቁቴን የምሄድ ነው የሚመስለኝ።
ሙታንታ ብቻ እንደለበስኩ ነገር....."
አነጋገራቸው ኮሎኔሉን ፈገግ አሰኛቸው።......

የቄሳር እምባ
ከአጀማመሩ ጀምሮ የአንባቢን ልብ ሰቅዞ በማይንገጫገጭ ውብ ትውፊታዊ ፖለቲካ ቀመስ ታሪኮችን ሲያስዳስሰን እንመለከታለን ከደርግ ሊቀመንበር ጓድ መንግስቱ ሀይለማርያም የቤተመንግስት እንቅስቃሴ ባለቤታቸውን ወይዘሮ ውባንቺን እስካገኙበት ተራ የወታደርነት ሙያ ድረስ ወርዶ በማሰስ የመንግሰቱ ሀይለማሪያምን የግል ባህሪ ፣ የፖለቲካ አረዳድና ከባልደረቦቹ ጋር የሚግባባበትን ቋንቋ ታኮ በዚህ የልብ ወለድ ታሪክ ውስጥ እንደቅመም ከተጠቀመው ገፀባህርይ የመቶ አለቃ በላይነህ ጋር ያለውን የሞት ጥላ ያንጃበበበት ስውር የግንኙነት መስመርና ህዝብ ስለላን ጨምሮ በርካታ ነጥቦችን ልብ እንደሰቀለ እንደወራጅ ውሃ ሲወርድ በሌላ በኩልና የፈላጭ ቆራጩ የጅማው የደርግ ሹሙ ሚስት የአሰንዳቦው ቡና ነጋዴው ልጅ የሳቅ ንግስቷ የፈገግታ አድባሯ '
ሀምራዊትና የመንግስቱ ሀይለማርያም ስውር ሰላይና ባለ ብሩህ አእምሮው የፖለቲካ ተንታኝ የመቶ አለቃ በላይነህ ስውር ውሽምነት ድረስ ጠልቆ ሲመረምር መንግስቱ በአመራሩ ሰበብ በቤተሰቡ ላይ ምን አይነት ቀውስ እንዳስከተለ ለማሳየት የመንግስቱ የመጀመሪያ ልጅ ትምህርት መንግስቱ በገፅ _ ላይ እንዲህ ስትሆን እንመለከታለን:-_
..
.......ምን ሰምታ እንደተቆጧት ሲጠይቋት ነው ኮሎኔል ደመቀ ጋር ደጅ ቆመው የሰሟቸው።
"ይሄ የአሜሪካ ሬድዮ እያለ ምን ጤና አለ ብለህ ነው? ዳዊት ነው ማነው የሚባል ሰው አባቴን ሰደበው ብላ ስትቃጠል ነው አንተ የደረስከው።" ብለው ወይዘሮ ውባንቺ አገጫቸውን በእጃቸው ያዙ።
................... ገፅ 17.............
ሌላም አለፍ ብለን አንድ እንጨምርና ከዚህ ጉዳይ ወጣ እንበል
....." ትምህርት የወንድ ጓደኛ ይዛለች።ፈረንጅ ነው።ዜግነቱ ኖርዌይ ይሁን ኔዘርላንድ ትበለኝ አላውቅም ረስቼዋለሁ።
ለምን ፈረንጅ እንደመረጠች ጠየቅኳት። 'ታዲያ ሀበሻ አግብቼ አባቴን ሳሰድበው ልኑር?' ኢትዮጵያዊ አግብቼ ባኮረፈ ቁጥር አንች የነብሰ ገዳይ ልጅ ከሚለኝ ቆሜ ብቀር ይሻለኛል ' አለችኝ።
ትምህርት እንዲህ ስትለኝ እንባዬ መጣ ....በሷ ቦታ ሆነህ አስበው እስኪ..."
" ምን ታደርጊዋለሽ ፣ ሐምሪዬ... ውርስ እዳ ነው!!" ቅሬታዋ ወደ እሱም ተጋባበት።
................ ገፅ 250 - 251 .........
.....
ኮሎኔል መንግስቱ አይደለም ደፍሮ የተናገራቸውን ቀርቶ ሳት ብሎት ሀይለ ቃል ያመለጠውን ባለስልጣን በምን መንገድ እንደሚያስገድሉ የተኬደበትን መራር ግፍ ለማሳየት የእውቁ ደራሲ በዓሉ ግርማ እና የሌሎችንም ጀነራል ህይወት በከንቱ መንጥፋቱን ሲተርክልን መቶ አለቃ በላይነህ በገፅ 104 - 105 ከመቶ አለቃ ምስጋናው ጋር የሚያደርጉትን ትንፋሽ ቀጥ የሚያደርግ የሚስጥር ውይይት የመንግስቱ ሁለተኛዋ ሴት ልጅ ትዕግሥት መንግስቱ መጥታ እስካቋረጠችበት ድረስ እንዲህ......
...
...... " አዎ አንተ ከመጀመሪያው ድረስ አብረካቸው ነበርክ። ስንቱን መከራ አልፈሃል። ማዕረጉ ይገባሃል።
እነሱ በተጋጩ ቁጥር እርምጃ ወሳጅ መሆኑ በራሱ ከባድ ስራ ነው " ብሎ ወደ ትዕግሥት ገልመጥ አቀርቅራ እየሰራች አያት። በቀጥታ ወደ ነጥቡ ገባ " አንተ ሰባቱ ደርጎች ሲረሸኑ ጀምሮ ነበርክ አይደል? "
" ታዲያ! ጀነራል ተፈሪን ፣ ሻምበል አለማየሁ ና ሻምበል ሞገስን እኔ ነኝ የመታኃቸው።
ምን የመሰለ ድምፅ የሌለው ቶምሶን የሚባል የእስራኤል ጠበንጃ ነበረኝ መሰለህ። በእሱ ነው የመታኃቸው።
ኮሎኔል ኅሩይን ፣ ኮሎኔል አስራትን ፣ ሻምበል ተፈራንና አስር አለቃ ኃይሌን ደግሞ መቶ አለቃ ገብሩ ራሱ ነው የመታቸው።
እንዲያውም አስር አለቃ ሀይሌ በጀርባ ተገልብጠው በጫማ ጥፊ ሊመታቸው ሲታገሉ አየሁት።
እኔ የተመደቡልኝን ገድዬ ጨርሼ ነበር። ሄጄ ያዝኩለት። ማጅራቱ ላይ መታው። ሻለቃ አጥናፉንም እዛው ጋራዥ ውስጥ ምድር ቤት ነው የመታኃቸው።......
..
በሚል ተርኮ ሲያበቃ። ልክ በገፅ 138 ላይ ደሞ በሀምራዊት አንደበት ልብ የሚሰነጥቅ ጆሮን አቁሞ እንደሎጥ ሚስት የጨው አምድ ቀጥ የሚያደርግ ሽብርን ይነዛብናል እነሆ ከገፅ_ 138 ......
....... "በቀደም ለት አስመራ በሄድክ በሁለተኛው ቀን ሌሊት ..... ከቤቴ ጀርባ ድምፅ ሰማሁ። አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ይሆናል።
የሆነ ሰው ይጮሃል። 'በእግዜር ይዣችኃለሁ ተዉኝ ' እያለ ይለምናቸዋል። 'ምን ተፈጠረ ብዬ ደነገጥኩ።' ድምፁ እየራቀ እየራቀ ሄደ።
ትቼው ተመልሼ ጋደም አልኩ። ትንሽ ቆይቶ ሁለት ጥይት ተተኮሰ። ከርቀት በደንብ አይሰማም።
ከዚያ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ።
ጧት ስራ ገብቼ አንድ በመኪና አደጋ የቆሰለ ወታደር መጣ።
ሳየው እንደገና ትዝ አለኝ። ' ገና በሌሊት ሶስተኛ ግቢ የምን ተኩስ ነው የሰማሁት? ' ብዬ ሲያቀብጠኝ ጠየቅኩት።
ለማንም እንዳትናገሪ ብሎ ' የጓድ መንግስቱ አጃቢ መቶ አለቃ ምስጋናው ተረሸነ' አለኝ።
" ተረ.........ሸ........ነ?" በላይነህ ጭንቅላቱን ይዞ ጉንዳን እንደነደፈው አይነት ተስፈንጥሮ ተነሳ።.....
....
385 views18:16
Open / Comment
2021-05-18 22:19:12
"የተገናኘነው ከረዥም ጊዜ በኋላ ስለነበር በእዚያ ሁኔታ ላይ አገኘዋለሁ ብዬ ስላልጠበቅሁ በጣም አዝኜ ነበር። ነገር ግን ድንጋጤየን እንዲያይብኝ አላደረኩም። እሱ ላይ ያነበብኩት ስሜት ግንያለበት ሁኔታ ለህይወቱ አስጊ መሆኑን በትክክል የተረዳና ምንም ዓይነት ፍርሃት የማይታይበት ነበር። ... ለረዥም ጊዜ አብራኝ የቆየች የምወዳትን እና ደጋግሜ የማነባትን 'አስኮ ጌታሁንና ሌሎች' የምትል የጃርሶ ሞት ባይኖር አጫጭር ልቦለድ መጽሐፍ እንዲያነባት ሰጥቼው ምሳ በልተን ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገን ተለያየን።" ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

የከተማው መናኝ ይነገር ጌታቸው
የገፅ ብዛት - 409 የተለጠፈበት ዋጋ - 270 ብር
መሸጫ ዋጋ - 230 ብር @Guramaylebooks
@Guramayelie 0912319263 Free delivery
208 views19:19
Open / Comment
2021-05-18 22:18:53
ግዕዝ የሚለውን ቃል ስንጽፍ በሁለት አይነት መንገድ ነው። አንድም 'ግዕዝ' ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ "ግእዝ" ብለን ነው። ወደ ትርጓሜው ስንመጣ "ግዕዝ" ስንል ዐጋዐዘ፤ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን፤ በቁሙ ነፃ የወጣ፤ ነፃ ያወጣ ብለን እንተረጉመዋለን። ይህም እንደምን ነው ቢሉ ከቋንቋ መርገም ነፃ የሆነ፤ ነፃ ቋንቋ መርገም ያልደረሰበት፤ የነፍስ ድምጽ፤ የነፃ ህዝን ልሳን እያልን ትርጓሜ እንሰጠዋለን። አንድም "ግእዝ" ማለት ቀዳማዊ፤ በኩር፤ መጀመሪያ ማለት ነው። ከቋንቋዎች በፊት የነበረ የቋንቋዎች አባት፤ የቋንቋ የዘር ግንድ፤ ልሳነ አዳም የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል።
ከገፅ 19 የተወሰደ።


የወርቅ ዘንግ መስፍን ሰለሞን
የገፅ ብዛት - 196 የተለጠፈበት ዋጋ - 170 ብር
መሸጫ ዋጋ - 150 ብር @Guramaylebooks
@Guramayelie 0912319263 Free delivery
216 views19:18
Open / Comment
2021-05-13 21:42:37
329 views18:42
Open / Comment
2021-05-12 23:12:09
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የረመዳን ኢድ አል ፈጥር አደረሳቹ!!!!
618 views20:12
Open / Comment
2021-05-12 22:04:23 ወራሪውን የጣሊያን ጦር ለመመከት አርበኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰባሰቡባት ስፍራ “አንዲትግራር”

“አንዲትግራር” በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ እንግዳ ዋሻ አንቀላፊኝ ሜዳ በተባለች ስፍራ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድ ተሰባስበው ወራሪውን የጣሊያን ጦር ለመዋጋት የጦር ስትራቴጂ ቀይሰው የመጀመሪያው የአርበኞች ማህበር የመሰረቱባት ታሪካዊ ስፍራ ነው።

ወደ አንዲትግራር ለማቅናት ከደብረሲና ተነስተው እስከ ታሪካዊው ስፍራ ለመድረስ የአካባቢው ፒስታ መሰል አቧራማ ወጣ ገባ መንገድ ማቆራረጥ የግድ ይላል።

አካባቢው ተፈጥሯዊ መስህብ ያለው በመሆኑ ወጣ ገባና ጠጠረማ
መንገዱን አንዳያስቡ ያደርጋል።

አንዲትግራር በአካባቢው የሚገኝ እድሜ ጠገብ ባለ ብዙ ቅርንጫፎች የግራር ዛፍ ሲሆን ስፍራው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር የተመሰረተባት ቦታ እንደሆነ
የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

ጥር 1 ቀን1931 ዓ.ም በባላንባራስ ባሻህ ኃይሌ ሰብሳቢነት
‹‹አንዲትግራር›› ስር ተገናኝተው አርበኞች ተወያዩ፡፡ ራስ አበበ
አረጋይ፣ልጅ ግዛው ኃይሌ፣ ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ፣ ፊታውራሪ ታደሰ በላይነህ፣ ልጅ ከፈለው ወልደፃዲቅ፣ አቶ ፀሃይ እንቁ ፃዲቅ፣ አቶ ፀኃይ እንቁ ስላሴ፣ ራስ መስፍን ሽመልስ እና
ሌሎችም የጦር አለቆች ጦራቸውን በመያዝ በግራሩ ስር መሰበሰባቸውን የአካባቢው አባቶች ይናገራሉ፡፡

የወረዳው ባህልና ቱሪዝም መረጃ እንደሚያመለክተው በአካባቢው አንዲት ግራር እንጂ ሌሎች ዛፎች አልነበሩም።

ግራሯ 200 ዓመት እድሜን ያስቆጠረች ስትሆን የአካባቢው
ማህበረሰብ የሽምግልና፣ የስብሰባ እና የሌሎችም ማህበራዊ ክንውኖች ማስፈጸሚያ ቦታ ነበረች።

ከኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ምስረታ በኋላም ቦታዋ አንዲትግራር በሚል በየአመቱ ጥር አንድ ቀን ታስቦ ይውላል።

ምንጭ ፦ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት
በጌትነት ተስፋማርያም
ፎቶሀዱሽአብርሃ

"ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለኢትዮጵያ ነፃነት ሰማዕታት"

@yetarikdersan
705 views19:04
Open / Comment
2021-05-02 10:39:42
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!
1.1K views07:39
Open / Comment
2021-05-01 22:48:34 ትንሿን ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ማንበብ ያለባችሁ ለምንድን ነው?

፩. ስለ ጋብቻ በአበው ትምህርት የዳበረ ነገረ መለኮታዊ ትምህርት ታገኙበታላችሁ፡፡

፪. በየዘመናቱ በጋብቻ ዙሪያ የነበሩት የምንፍቅና ትምህርቶች ከእነ መልሶቻቸው ታውቁበታላችሁ፡፡

፫. ከልማዳዊ ጋብቻ (ትዳር) በተለየ ብልጫ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንድትኖሩ ይመራችኋል፡፡

፬. አንድ ወጣት ለማግባት እስከሚያስብ ድረስ ድንግልናውን ለምን መጠበቅ እንዳለበትና እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ትምህርት ይሰጣል፡፡

፭. የማግባት አሳቡ ሲመጣ ወጣቱ መጀመሪያ ምን ማድረግና ማወቅ እንዳለበት፣ የትዳር አጋሩን ለመፈለግ የትና ምን ምን ነገሮችን ማድረግ እንዳለበት፣ ከምን መጠንቀቅም እንደሚያስፈልገው ያሳያል፡፡

፮. የትዳር አጋር ያላገኙ ወጣቶች እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለው አሳብ ምን እንደ ኾነ አዲስ ምልከታና ምሪት ይሰጣል፡፡

፯. አጣማሪያቸውን ያገኙ ወጣቶች የዕጮኝነታቸውን ሕይወት እንዴት ማሳለፍ እንዳለባቸው ይመራል፡፡

፰. ሰርጋቸውን የትና እንዴት ማከናወን እንዳለባቸውና ከምን ዓይነት ቫይረስ ሊጠብቁት እንደሚኖርባቸው ያመለክታቸዋል፡፡

፱. ከሰርግ ማግስት ያለው ሕይወታቸው እንዴት ትንሿን ቤተ ክርስቲያን ማነፅ እንዳለባቸውና በዚያ ውስጥ ምንና እንዴት መጸለይ፣ መማር፣ መመጽወት፣ መፆም እንዳለባቸው፥ በአጠቃላይ እንዴት በቤታቸው ድኅነታቸውን መፈፀም እንዳለባቸው አርአያነት ባላቸው ቤተ ሰቦች ልምድ የዳበረ ትምህርትና ምሪት ያገኙበታል፡፡

፲. ባለ ትዳሮች በትዳር ሕይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች ምን ምን እንደ ኾኑና በምን ዓይነት አተያይ ሊፈቷቸው እንደሚችሉና እንደሚገባቸውም በዝርዝር መፍትሔ አሳቦች ይቀስሙበታል፡፡

፲፩. ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ እንደሚኖርባቸው፥ እስከ አሁን ከሰማናቸውና ካነበብናቸው በተለየ አቀራረብ ጥልቅና ዝርዝር የኾኑ ትምህርቶችንና ልምዶችን ያውቁበታል፡፡

፲፪. ይህ መጽሐፍ፥ አይኾንም እንጂ 10 ሚልዮን ቅጂ እንኳን ቢሸጥ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ምእመናን 10 ሚልዮን ስላልኾኑ፥ ወደ ሌሎቹ መድረስ የምንችለው በአሠራር ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ቀሪዎቹ እንዴት መድረስ እንደምንችልና ይህን ብናደርግ ምን ምን ጠቀሜታዎችን እንደምናገኝ ውጥን ምክረ አሳብን ይጠቁማል፡፡ በመጽሐፉ በጥቆማ መልኩ የቀረበ ቢኾንም፥ ዝርዝር አተገባበሩ በጸሐፊው እጅ ይገኛል፡፡

፲፫. በአጠቃላይ መጽሐፉን ማንበብ ያለብዎት እንዲሁ ከመቆጨት ባሻገር ለራስዎ፣ ለቤተ ክርስቲያንዎና ለሃገርዎ መሬት የረገጠ ሥራ ተቀናጅቶ ለመሥራት ነው፡፡
1.3K views19:48
Open / Comment
2021-05-01 22:48:26
865 views19:48
Open / Comment