Get Mystery Box with random crypto!

ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

Logo of telegram channel geezlibrary — ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ
Logo of telegram channel geezlibrary — ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ
Channel address: @geezlibrary
Categories: Literature
Language: English
Country: Not set
Subscribers: 8.73K
Description from channel

በኢትዮጵያውያን ደራስያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ሚተረኩበት ድንቅ ሀገራዊ ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 3

2021-05-01 21:38:17 አምላክ ለእኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን
ለምን ከለከለች ፀሐይ ብርሃኗን?

ረቡኒ፣ በጎልጎታ ሲሰቀል ፀሐይ አሻፈረኝ ብላ ብርሃኗን ከልክላለች። ፀሐይ እምቢኝ እንዳለች ከአራቱ ወንጌላት ሦስቱ ዘግበውታል። በዚህ ቀን ሊፈጠር የሚችል የፀሐይ ግርዶሽ እንደሌለ ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል። ለደቂቃዎች እንጂ ለሰዓታት የሚቆይ የጨረቃ ግርዶሽም እንደሌለ እሙን ነው። ፀሐይ ብርሃኗን የነፈገችው በደመና ጉያ ተሸሽጋም አይደለም። ታዲያ ለሦስት ሰዓታት የቆየው የፀሐይ ዝምታ ለምንድነው? ደሙን ያፈሰሰው ለእኛ ሆኖ ሳለ ፀሐይ ምን ይሁን ብላ ነው የሸሸችው? ይኼ ምርምር የሚጠይቅ ሚስጥር ነው።

ጨለማ የእግዚአብሔር ሕልውና ያለመኖር ውክል ነው። ክርስቶስ የሰው ልጆችን ኃጢዓት በሙሉ የመሸከሙ የማረጋገጫ ሰነድም ጭምር ነው። በዚህም የክርስቶስን የሰቆቃውን ክብደት እናያለን። የእግዚአብሔር አብ አጠቃላይ ፍርድም ይንፀባረቃል።

የፀሐይ ግብዓቱ ከፈርዖን አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የተደረገውን ተዓምር ያስታውሰናል። እስራኤላዊያን ከግብፅ ባርነት ከመላቀቃቸው በፊት ሶስት ቀን በግብፅ ጨለማ እንደነበር መፅሐፍ ቅዱሳችን ያወሳል። እስራኤላውያን ከሶስቱ የጨለማዎቹ ቀናት በኋላ ከግብፅ ባርነት ነፃ እንደሆኑ ሁሉ፣ በዕለተ ስቅለት ከረበበው ፅልመት ማግስት የሰው ዘር በሙሉ ከኃጢዓት ባርነት ነፃ ወጥቷል። በስራ ከሚመጣ የፅድቅ ባርነት በፀጋ ወደ ሚገባበት የፅድቅ ነፃነት መልሶናል። በግብፅ ምድር የጨለመችው ፀሐይ ሙሴ እጁን አንስቶባት ሲሆን በዕለተ ስቅለት የጠለቀችው ፀሐይ ግን በገዛ ፍቃዷ ይመስላል።

የከበረው ስጋ የከበረው ደም
በመስቀል ላይ ዋለ ኢየሩሳሌም

የሰው ልጅ ራሱን ወደ መንፈሳዊ ረቂቅነት መቀየር ስለማይችል፥ ፈጣሪ ራሱን ወደ ተጨባጭ አካል መቀየር ነበረበት። የከበረው ስጋ የከበረው ደም ሲል መለኮት ራሱን ወደ ተጨባጭ አካልነት የቀየረ መንፈሳዊ ረቂቅ ሆኖ እናገኘዋለን። ወልድ መለኮታዊ ክብሩን ትቶ ስጋ መልበሱ ለፍጥረቱ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያመለክታል። ስለ ሰው ልጆች ኃጢዓት ሲል መስቀል ላይ የዋለበትን የፍቅር ውሃ ልክ የሚተካከል አይገኝም።

እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረው ብዙ ነው ሚስጥሩ

መስቀልና የመስቀል ውበት እርስ በራስ የሚቃረኑ ሐረጎች ናቸው። መስቀል በሰቀቀን የታጨቀ የሰቆቃ ጥቅል እንጅ አንዳች የውበት ዘለላን ያነገበ ነዶ አይደለም። መቸም መስቀል ስንል እንጨቱን አለመሆኑን ልብ ይሏል። በተለየ ሁኔታ የኢየሱስ መስቀልን እንዲያምር የሚያደርግ የስዕል ባለሙያ እንጅ የመፅሐፍ ቅዱስ ተረክ የለም። እንደውም እንደውም የመሲሑው መስቀል በየትኛውም ሰፊ ትከሻ የሚሸከሙት ሆኖ አናገኘውም። መስቀሉ ከገዛ ወገኖቹ ዘንድ ቅቡልነት ከማጣት የሚጀምር እንጅ ሰያፉን እንጨት ተሸክሞ ተራራ ከመውጣት አይደለም። ሌላው ሌላው ይቅርና ሐዋርያቱ እንኳን ብቻውን ትተውታል። ቁንጫ እንኳን ከፍራሹ ጋር አብሮ ይቃጠላል። ፎካሪው ጴጥሮስ እንኳን ከመስቀሉ ግዝፈት የተነሳ በአንድ የክህደት መለዮ ሶስቴ ቃለ-አባይ ሆኗል። ታዲያ ምኑ ጋር ነው የኢየሱስ መስቀል ማማሩ? የመስቀሉን ውበት ሚስጥር እሱው ይግለጥልን!

ቢመቱት ቢሰቅሉት ቢያላግጡበትም
ምንም አላገኙም ከሱ ዘንድ ስህተት
ፈጣሪ መሆኑን ሚስጥሩ ገብቷት
ጌታ ላይ ዝም አለች ግዑዟ መሬት

ትዕቢተኛ በቆሎ ከጤፍ ማኅፀን ዱቄት የሚወጣ አይመስላትም። ግዑዟ መሬት የገባትን እውነት፣ ሕያው ነኝ ባዮቹ የሰው ልጆች ሊያስተውሉ ዘንድ አልተቻላቸውም። ልሳነ-ሰቡ፣ ፈጣሪው ላይ እያላገጠ ሲያዋርደው፣ ምድር ግን በልሳነ-ተፈጥሯዊ አርምሞ፣ ፈጣሪዋን አከበረችው።

የአለማችን አብዛኛው ጦርነቶች የተካሄዱት በተራራዎችና በኮረብቶች ላይ ነው። ጦርነቱን ያሸነፈው ሐገር በኮረብታው አናት ላይ ትልቅ እንጨት በመትከል ባንድራውን ያውለበልባል። ኢየሱስ በቀራኒዮ ኮረብታ የተውለበለበ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰንደቅአላማ ነው።

በመጨረሻም

ይኼ ታላቅ ንጉስ ሲገለጥ በሰማይ
የናቁት የወጉት ይሉለታል ዋይ ዋይ
ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሲሸሹ
ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ


ከቢኒያም አቡራ
1.1K views18:38
Open / Comment
2021-05-01 21:14:43 እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን
1.1K views18:14
Open / Comment
2021-04-05 23:02:09 መፅሐፉ ደቡብ አፍሪካን ከኢትዮጵያ ለማነፃፀር ዕድል ሰቶኛል፤ ኢምባሲዎች ላይ ያለውን መጉላላት እዚህና እዚያ ብሎ የገለፀበት ሁኔታ በአገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚታየውን ችግር ፍንትው አድርጎ ያቀረበ ነው፡፡ ተቋማት እንዴት ይገንቡና ትውልዱስ እንዴት ይቀረፅ የሚለው ላይ ልናስብበት ይገባል ተብሏል በውይይቱ፡፡ በሀገራችን ከሁለት እስከ ሶስት ሚሊየን ወጣት በየአመቱ ወደ ስራ ዓለም ይገባል የስራ ዕድሉ ግን የለም ይህንን መሰል ችግሮችን ለማስተንፈስ መንግስታት ስደትን ባያበረታቱም እንኳን ዝምታን ሊመርጡ ይችላሉ፤ አመፅንም እንደ ማስተንፈሻ ይጠቀሙበታል የሚለው ሐሳብ በውይይት ወቅት የዳበረ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ በተነሱ ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝም ከመድረኩ ሀሳቦች የተሰነዘሩ ሲሆን መባከንን በተመለከተ የአንዲት ከስደት ተመላሽ ታሪክን በማቅረብ ሁኔታውን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ባለ-ታሪኳ ምንም አይነት እንግልት ባይደርስባትም ተብሰከሰካለች የሚያብሰከስካት ደግሞ ‹‹አስር ዓመታትን በሳውዲ አሳለፍኩ ምን ጠብ አለልኝ፤ ሀገሬ ላይ ብሆን አገባ፣ እማር፣ እወልድ ነበር›› የሚለው ቁጭት ነው፡፡
የደቡብ አፍሪካና የሰሜን ምስራቁ ስደት በንፅፅር ሲቀርብም፤ የደቡቡ በራስ የሚሰራ፣ የጉዞ ስቃይ የሚበዛበት እና ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚቻል ደረጃ በህገ-ወጥ መንገድ የሚከናወንና ሲሆን የአረቡ ዓለም ስደት ስፖንሰር ተብዬዎች የሚጠቀሙበት፣ በብዛት ሴቶች የሚሳተፉበትና ከጉዞ ይልቅ ስቃዩ እዛ ከደረሱ በኋላ የሚበረታበት ነው፡፡ ከስደትና ብሔራዊ የደህንነት ስጋት ጋር ተያይዞ የተነሳው ወሳኝ ነጥብ ነው ያሉት አወያይ ለምሳሌ በየመን የሚገኙ የሀውቲ አማፂያን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ይመለምሉ ነበር ያሉ ሲሆን ሀገራዊ ገፅታ ላይም ስደት ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ተያይዞም ከመድረኩ ለፀፊው ጥያቄ መሰል አስተያየት የተሰጠ ሲሆን የመጽሐፉ ውበት እንዳለ ሆኖ ውበቷ የሚያምር ሴትን ቆንጂት፣ የተከፋችና የተገፋችውን ራሄል እንዲሁም አርፋጁን ዘገየ ይለዋል ይህም ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል ተብሏል፡፡ ውይይቱ ከዚህም በሰፋ መልኩ እየበሰለ ቢሄድም ሰዓት ገደብ አለውና ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መሸጋገር ግድ ሆኗል፡፡
ክፍል ሶስት - የእላፊ ጸሐፊ
የማጠቃለያ ሐሳብና በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የበኩሉን እንዲል ለእላፊ መጸሐፍ ጸሐፊ ዮርዳኖስ መድረኩ የተተወ ሲሆን በርጋታ እያዋዛ ሃሳቦቹን አፍስሷል፡፡ የገፀ-ባህሪያቱ ስያሜ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ የቦታ ስሞችም ለባለታሪኮቹ ደህንነት ሲባል ተለውጠዋል ያለው ዮርዳኖስ ስማቸውም ከባህሪያቸው ጋር ተያይዞ እንደተሰጣቸው ተናግሯል፡፡
እላፊ የመንገደኛ ቀጣይ ስለሆነ መንገደኛ ላይ የተነሱ ነጥቦችና ሀሳቦች በዚህኛው መጽሐፍ እንዲካተቱ አልተደረገም፤ ለስደት እንደ መግፍዔ የተነሳው የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ላይ መጽሐፉ ያነጣጠረበት ምክንያትም ሌሎቹ ከዚህ በፊት ነስፋት በመንገደኛ ስለተዳሰሱ መሆኑን ለዕድምተኛው ተናግሯል፡፡
የዚህ መጽሐፍ መግቢያና መውጫው ‹‹መከባበር›› ነው ይህ መከባበር ደግሞ የበለጠ የሚገባን ከሀገር ስንወጣ ነው፤ ቅድሚያ ራስን ከዛም ሌላውን ማክበር ቢኖር በጾታ የሚነሳው አለመግባባትም ባልኖረ ነበር ያለው ዮርዳኖስ የግድ መዋደድ አይገባንም፤ ያ ሁለተኛ የሚመጣ ነገር ነው ግን ልንከባበር ይገባል ብሏል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የስራ ባህል የወረደ መሆኑን ተናግሮ ኢትዮጵያውያንን በስራ ባህል በደቡብ አፍሪካ ጥሩ ገፅታ እንዳላቸው ነግሮናል፡፡ የሀገሪቱ ፖለቲከኞች ግን ችግሮችን መቅረፍ ሲያቅታቸው ወደ በስደተኞች ላይ ያላክካሉ ይህም ነው ‹‹መጤ›› ጠልነት አመጾች እንዲነሱ ምክንያት የሆነው ብሎናል፡፡
መባከንን ቅጽበትን እንጂ ሁኔታን ከማይገልፁ ምስሎች ጋር ያያዘው ዮርዳኖስ፣ የክረምት በረዶን ጠብቆ የራሱ ካልሆነ መኪና ጋር ፎቶ ተነስቶ የሚልክ ዲያስፖራን በምሳሌነት አቅርቧል፤ የመጽሐፉ ዓላማም ነባራዊ ሁኔታን ማሳያት እንጂ ስደትን ደጋፊ ወይም ነቃፊ መሆን አይደለም ሲል ቋጭቷል፡፡
በርግጥ የተነሳው ሀሳብ ይህ ብቻ አይደለም በቦታው የነበረ ይህንን ይረዳል ግን ደግሞ በተለያዩ እክሎች ላልተገኛቹ ቤተሰቦቻችን ከተካፈልነው ጥቂቱን እናቃምሳቹ ብለን ነው፤ መልካም ሳምንት፡፡
(ምስጋና፡ በየ15 ቀኑ የመሰብሰቢያ አዳራሹን በነጻ ለሚቀፍድልን የጁፒተር ዓለምአቀፍ ሆቴል)
2.8K views20:02
Open / Comment
2021-04-05 23:02:09 ዕለተ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም
የብራና ቤተሰብ የመጽሐፍ ውይይት
በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል፤ ቦሌ ቅርንጫፍ
የመጽሐፉ ርዕስ፡ እላፊ፤በዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ
የገፅ ብዛት 524 (6 ምዕራፎችና ነፃ ገፆች)
አጋፋሪ፡ መኰንን መንገሻ
መወያያ ጽሑፍ አቅራቢዎች፡ ዶ/ር አበባው ማናዬ እና ሳራ ሞገስ
ማስታወሻ ከታቢ፡ ቢኒያም ተስፋዬ
ክፍል አንድ - ዳሰሳ እላፊ
ከቀኑ 10፡01 ሲል የዕለቱ አጋፋሪ የብራናን ባህል ተከትሎ የዕለቱን መርሃ-ግብር በማስተዋወቅ መድረኩን መፅሐፉን ከስደትና ከስነልቦና አንፃር ለቃኙት ዶ/ር አበባው ሰቷል፡፡ ዶ/ር አበባው በቅድሚያ እንደ ግለሰብ በመፅሐፉ ላይ ያላቸውን አስተያየት አጋርተዋል፡፡ ሰዎችን በማየት ብቻ መፈረጅና መፍረድ በበዛበት ሀገር ፀሐፊው ባህሉን ተገንዝቦ ነገር ግን ከፍርድና ከፍረጃ ነፃ የሆነ አቀራረብ መከተሉ የሚያስመሰግነው ነው፡፡ ባለፉት 12 ዓመታት በስደትና ተያያዥ ጉዳዮች ሰርቻለሁ በብዛት የሚቀርቡ የጥናት ፅሑፎች ደረቅ ሆነው ነው ያገኘኋቸው እላፊ ግን ህይወት ህይወት እንዲሸት ተደርጎ የቀረበ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከኢኮኖሚ እስከ ማህበራዊ ህይወት፤ ከፓለቲካ እስከ መንፈሳዊ ጉዳዮች ይዳስሳል መፅሐፉ፣ አልፎ አልፎ ወጣ ያሉ ሐሳቦችን ያስነብበናል (ለምሳሌ የማህበረሰብን አምባገነንነት)፡፡ በተጨማሪም የግርጌ ማስተወሻዎቹን እንደ ምክረ ሐሳብ ነው የወሰድኳቸው ያሉት ዶ/ር አበባው ተቃርኖዎችን የወሰደበት መንገድ በህይወታችን ያሉብንን ተቃርኖዎችና ያንንም እየመረመርነው እንዳልሆነ አሳይቶናል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሀገራዊ እሴቶቻችንን የቢራ ስሞች በዚህ ደረጃ እንደተቆጣጠሯቸው አላስተዋልኩም ነበር መፅሐፉ ያንን እንዳይ አድርጎኛል ብለዋል፡፡
በመቀጠል ምሁራዊ አስተያየታቸውን ያካፈሉት ዶ/ር አበባው የስደትን ምንነት በማስረዳት ጀምረዋል፡፡ ሰዎች ረዘም ላለ ጊዜ መኖሪያቸውን ለቀው ከአንድ ሀገር ወደሌላ ሀገር ወይም በሀገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ/ሲሄዱ ተሰደዱ እንላለን ካሉ በኋላ በማያያዝም ከአንድ ቢሊየን በላይ ስደተኛ በዓለማችን የተመዘገበ ሲሆን ከ273ሚሊየን በላይም ሀገሩን ትቶ የተሰደደ ነው ብለዋል፡፡ ስደት የምናጣጥለው አሊያም የምናንቆለጳጵሰው ጉዳይ አይደለም ነገር ግን የዓለምን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ፣ ስነ-ሕዛባዊ እና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ የቀረፀ ነው፡፡ ስደት ብሔርተኛ የሁኖ ኃይሎች አገንግነው እንዲወጡ ምክንያት ነው፣ ስደት አሜሪካን የመሰሉ ሀገሮች የተገነቡበትም ሂደት ነው ብለዋል ዶ/ር አበባው፡፡ እላፊ የደቡቡ የስደት መስመር ላይ ተመርኩዞ የተዘጋጀ ሲሆን የኔ የስራ ልምድ ደግሞ የሰሜን ምስራቁ ላይ ያተኮረ ነው ይሉና ስደት የባህልና የክህሎት ሽግግር ያመጣል በአንፃሩ ደግሞ ዜጎች ይጎዱበታል ይህንንም መፀሐፉ ቁልጭ አድርጎ አቅርቧል ሲሉ ሀሳባቸውን ከሰዓት ገደብ ጋር አጠናቀዋል፡፡
በመቀጠል የመፅሐፉን አጭር ዳሰሳና ወመያያ ሐሳብ ያቀረበችው ሳራ ሞገስ ከሽፋን ገፁ የተነሳች ሲሆን ጀንበርን፣ ድንበርን፣ ባህርን፣ በራሪ ወፎችን ቀረብ ሲሉት ግን የሽቦ አጥርን ያቀፈውን የመፅሐፉን ሽፋንና አቀራረብ ሳቢ ብላዋለች አያይዛም ፀሐፊው መሰል የሽፋን ስዕሎችን ጎላ የማድረግ ሁኔታ በመጀመሪያ መፅሐፉም መጠቀሙን አውስታለች፡፡ ሳራ ዳሰሳዋን ስትቀጥል የብዙ ሰዎችን ኑሮ ቀለል፣ ለዘብ ባለ አማርኛ ለማስረዳት ሞክሯል መፅሐፉ ትልና በስነ-ቃል፣ ዘፈን እና ቀልዶች ታጅቦ መቅረቡ ለማንበብ ሳቢ አድርጎታል ብላለች፡፡
በመቀጠል የመፅሐፉ ፋይዳ በሚል፤ መሰል ጥናታዊ ጽሁፎች ድርቅ ያሉ ጽሑፎችን የሚያቀርቡ ሲሆን እላፊ ግን በተዋዛ አቀራረቡ ስነ-ጽሑፋዊ አበርክቶው የጎላ ነው፣ ማጠቃለያ በሚለው ክፍል የቀረቡት ሐሳቦች ለፖሊሲ አውጪዎች እንደ ግብዐት የሚያገለግሉ ናቸው፣ መፅሐፉ አንባቢ የራሱን ድምዳሜ እንዲወስድ ዕድል ይሰጣል እንዲሁም እንደ ሀገር የወደቁ ስርዐቶቻችንን (ትምህርት፣ ጤና፣ የአገልግሎት ዘርፍ) ያወሳል በማለት የመፅሐፉ ፋይዳዎች ያለቻቸውን በአጭሩ ለታዳሚው አቅርባለች፡፡
በማጠቃለያዋም ለውይይት ቢሆኑን በማለት የመሚከተለሉትን ነጥቦችን ሰንዝራለች፡-
 መፅሐፉ Neo-classical የኢኮኖሚ ንድፈ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ይመስለኛል፤ ስለዚህም ሌሎች የስደትን መግፍኤ ምክንያቶችን ወደ ጎን በመተው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖችን ብቻ በሰፊው ያወሳል፤
 በስደት ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን/ ችግሮችን በሰፊው አላነሳም፤
 መጽሐፉ ሴቶች ከኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት ጋር በተያያዘ ውሳኔ ሰጪነታቸው ይጨምራል ቢልም ፆታ ተኮር ጥቃትን ግን በደደብዛዛው አልፎታል፤
 የተለያዩ ጽሑፎች መንግስት ስደትን የማመቻመች ሚና እንዳለው ያወሳሉ በእላፊ መጽሐፍ ግን ይህ ጉዳይ ሳይነሳ ታልፏል፤
 በመጽሐፉ የተገለፁ ገጸ-ብህርያት የጸሐፊውን ማንነት ባወቁበት ሁኔታ ተዐማኒነት ያለው መረጃ ይሰጡታል ብሎ ማሰብ ይቻላል ወይ ስትል ታጠይቃለች፡፡
ክፍል ሁለት - ውይይት በእላፊ
መድረኩ ለተሳታፊዎች ክፍት መሆኑን ተከትሎ በሁለት ዙር ከተሳታፊዎችና ከመድረክ ሀሳቦች እየተሰነዘሩ ውይይት በእላፊ መፅሐፍ ላይ ተደርጓል፤ በአጭሩ በምናብ ቦታው ላይ እንመለስማ፡-
መፅሀፉ ትልቅ ስራ ነው፣ ዘርፍ ብዙ ነው፣ አቀራረቡ ማራኪና ተነባቢ ነው የሚሉ ሐሳቦች በተደጋጋሚ ከተወያዮች የተሰጡ ሲሆን መፅሐፉን በሁለት መልኩ ከፍዬ አየዋለሁ ያለች ተሳታፊ ስነ-ጥበባዊና ጥናታዊ ያለቻቸውን ነጥቦች አውስታለች፡፡ በእላፊ ውስጥ ያሉ ስነ-ቃሎች፣ ግጥሞች፣ ተረኮች፣ ወጎች እና አስቂኝ ገጠመኞች ስነ-ጥበባዊ ጎናቸው የጎላ እኛንም ከዛኛው ዘመንና ከገጠሩ ህዝብ ጋር ያስተዋወቁን ናቸው ሰትል እንደ ጥናትም መጽሐፉ በገጸ-ባህሪያቱ ውስጥ ሀገሬን እንዳይ አስችሎኛል በማለት አጠቃላለች፡፡
በውይይቱ ወቅት ጎልተው ከተሰሙ የመጽሐፉ ጭብጦች መካከል ‹‹መፈናፈኛ› እና ‹‹ መባከን›› ዕለቱን ተቆጣጥረውት ውለዋል፡፡ እንደ ማህበረሰብ ልጆችን መፈናፈኛ ማሳጣት በብዙ አውድ የታየ ሲሆን ለፀሐፊውም እንዲያብራራው ጥያቄ ቀርቦበታል፤ በሌላ በኩልም የጠበቁትን አለማግኘትና ከሀገር ከወጡ በኋላ ባክኖ መቅረት ላይም ሀሳብ እንዲሰጥበት በተወያዮች ተጠይቋል፡፡
እላፊ ጆሀንስ በርግን ከአዲስ አበባ ጋር በማነፃፀር ያቀረበበት መንገድ ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ እየታዩ ካሉ ሁኔታዎች አንፃር (ለምሳሌ የዘረፈ ወንጀል መስፋፋት) እኛስ ወደዛ እየሄድን አይደለም ወይ በማለት ተወያዮቹ አጠይቀዋል፡፡ ስደት ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ያቀፈ፤ ትልቅ ዓለምአቀፍ መነጋገሪያም ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ጠላት›› ብለን የፈረጅናቸው ሀገራት ስደተኞችን ሊጠቀሙ አይችሉም ወይ ያለ ውይይቱ ተሳታፊ አያይዞም ለሀገር ደህንነትም ስጋት ስለሆነ የህግ ማዕቀፍ ሊበጅለት ይገባል ብሏል፡፡ ሌላ ተሳታፊ በበኩላቸው የውይይት አቅራቢው በሰሜን ምስራቁ ስደት ላይ ልምድ ያላቸው እንደ መሆኑ መጠን በመጽሐፉ ከተወሳው የደቡብ ስደት ጋር በማነፃፀር ቢያቀርቡልን ብለው ጠይቀዋል፡፡
2.1K views20:02
Open / Comment
2021-04-05 23:01:45
1.7K views20:01
Open / Comment
2021-03-30 19:05:10
ሀገራችን ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣት ተከትሎ ነው በ9 ነጥብ ወደአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የቻለው።
2.3K views16:05
Open / Comment
2021-03-28 20:44:28 ……………… …………………
ሃሳብ በሃሳብ ይረታል! ሃሳብም በውቀት ይጎለምሳል፣ የባለቅኔው ትውልድም በእውቀት ላይ ተመርኩዞ የሚሰራትን ሃገር አርቆ ይቃኛል. ኑ አብረን በእውቀት ውቅያኖስ እንስመጥ………!

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ ብዙ ህልሞች አሉት ከብዙ በጥቂቱ
ተነጋግሮ መግባባት የሚችል አስተዋይ ማህበረሰብ መፍጠር
በተመረጡ መጽሐፍት ላይ ትንታኔ ማቅረብ
እንዲሁም በሙያቸው አንቱታን ያተረፉ ሰዎችን በመጋበዝ ከህይወት ተሞክሯቸው እንዲያካፍሉን ማድረግ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ተባብረን ብዙ ስራ መስራት እንችላለን እና እርሶም የግል አስተያየትዎን ይሰጡ ዘንድ ተጋብዘዋል።

@keneyalew @keneyalew
@keneyalew @keneyalew
2.8K views17:44
Open / Comment
2021-03-27 14:14:42
“ ከማይጨው እስከ ኦጋዴን “
የኢትዮጵያውያን የክፉ ቀን ታማኝ ወዳጅ የካርል ጉስታቭ ቮን ሮዘን እውነተኛ ታሪክ

በሁለተኛው የኢትየጵያና የጣሊያን ጦርነት ወቅት አባቶቻችን እናቶቻችን በማይነገር ጭካኔው በኩራት ከሚመካ እግዚአብሄርን ከማያቁ ልበ ድፍን ሠራዊት ጋር የተጋፈጡባቸዉን ክፋዎቹን የጦርነተን ወራት በዓይነ ህሊናችን የሚያሳየን የገዛ ራሳችን ታሪክ ነው።

ሮዶልፎ ግራዚያኒ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ሙሶሊኒ ዘንድ ቀርቦ ተናገረው የተባለው አባባል ዘወትር በህሊናችን ታትሞ የሚኖር ነው::

" ኢትዮጵያን የምትፈልጋት ከኢትዮጵያውያን ጋር ነው ወይስ ያለ
ኢትዮጵያውያን?"

ይህ መጽሐፍ በመጽሐፉ ደራሲ በሄሊ ቮን ሮዘን በወጉ የተደራጀ መረጃና ያገላለጽ ውበት በኢትዮጵያውያን ብርቱ የጦር ሜዳና የዲኘሎማሲ ተጋድሎ ነፃነት ተመለሰ ከተባለ በኋላ ንጉሡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በገቡበት አዲስ የፈተና ምዕራፍ ወስጥ ያሳልፈናል።

በዚህኛው ምዕራፍ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከጦርነቱ መልስ በጦርነቱ የፈራረሰውን የመንግስት ሥርዓት የደቀቀውን ኢኮኖሚና የተጎሳቆለውን ኢትዮጵያዊ ሞራል መልሰው ለማቀናት አቅማቸውና ዘመናቸው በፈቀደላቸው መጠን ያለፋበትን አድካሚ ጉዞ ገድላቸውን ሳያጋንን ፡ ጉድለታቸውን ሳይሸሽግ በነጻ ታዛቢ ሚዛናዊነት በየረድፉ ያስቃኘናል፡፡

ይህን መጽሐፍ ስናነብ ንጉሱ በረጅም የግዛት ዘመናቸው በመንግስታቸው ውስጥ በነበሩ፡ በመሣፍንቱና በዘመናዊያኑ ልሂቃን መካከል የግራቀኙን ሚዛን ጠብቀው አገሪቱን ወደፊት ለማራመድ የተጓዙበትን የሠርከስ ገመድ ላይ ጉዞ የሚመስለውን የፓለቲካ ህይወታቸውን እያስተነተነ ለህሊና ዳኝነት ያቀርብልናል፡፡
መጽሐፉ የባለታሪኩ የካርል ጉስታቭ ቮን ሮዘን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኛ የኢትዮጵያውያን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ማህደር ጭምር ነው የምለው።
2.7K views11:14
Open / Comment
2021-03-16 00:19:38 ማረፊያ፣
ጥንካሬ ወይስ ድክመት?
አንዳንዴ ደካማ ጎናችን ጥንካሬያችን ይሆናል። ለምሳሌ ያህል የአንድ ህጻንን ታሪክ እንመልከት። ህጻኑ
የአስር አመት ልጅ ሲሆን በደረሰበት የመኪና አደጋ ግራ እጁን አጥቷል። እናም የአካል ጉዳት ቢኖርበትም
ጁዶ (የትግል ስፖርት አይነት) መሰልጠን ፈለገ።
ልጁም ወደ አንድ ጃፓናዊ የጁዶ አሰልጣኝ ሽማግሌ ዘንድ ሄደ። ስልጠናውንም ጀመረ። ልጁ ስልጠናውን
በሚገባ ቢያካሂድም፣ ለሶስት ወራት በተከታታይ መምህሩ የሚያስተምረው የጁዶ እንቅስቃሴ አንድ
አይነት ብቻ ነበር። ተማሪውም ይሄ ለምን እንደሆነ አልገባውም።
“ሰንሴ” አለ፣ ተማሪው በመጨረሻ “ሌላ እንቅስቃሴ መማር የለብኝም?”
“የምታውቀው ይህንን እንቅስቃሴ ነው፤ የሚያስፈልግህም ይሄ ብቻ ነው።” መምህሩ መለሰ፡፡
አልገባውም ሆኖም መምህሩን በማመን ስልጠናውን ቀጠለ።
ከጥቂት ወራት ስልጠናም በኋላ መምህሩ ተማሪውን ወደ መጀመሪያ ፍልሚያው ይዞት ሄደ።
የመጀመሪያዎቹን ሁለት ፍልሚያዎች ለእሱም እስኪገርመው ድረስ በቀላሉ አሸነፈ። ሶስተኛው
ፍልሚያው ፈታኝ እና አዳጋች ነበር፤ ሆኖም ተፋላሚው ትግስት በማጣቱ እና በመዳከሙ በሚያውቃት
አንድ እንቅስቃሴ ፍልሚያውን አሸነፈ። ስኬቱ ለእርሱም ደንቆታል፤ ወደ ፍጻሜም አለፈ።
አሁን ተፋላሚው እንደቀድሞዎቹ ተፋላሚዎች አልነበረም፤ ግዙፍ፣ ጠንካራ እና ልምድ ያለው ነው።
ለጥቂት ጊዜም ፍልሚያው ከልጁ ቁጥጥሩ ውጪ ሆነበት። ዳኛውም እረፍት እንዲወስዱ ጠየቃቸው።
“አይ” አለ መምህሩ፣ “ይቀጥል”
ፍልምያውም ቀጠለ፤ ተፋላሚው ድንገት ስህተት ሰራ፤ ልጁም የሚያውቃትን እንቅስቃሴ ተጠቅሞ
ተጋጣሚውን ዘረረው። ልጁም ፍልሚያውን እና ውድድሩን አሸነፈ። ዋንጫውንም አነሳ።
መምህሩ እና ልጁም ከውድድር ስፍራው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ሳለ፣ ሰለ እያንዳንዱ የፍልሚያ
ቅጽበቶች መወያየት ጀመሩ። በመሃልም ተማሪውም ድፍረቱን አሰባሰበና አንድ ጥያቄ ጠየቀ
“ሰንሴ፣ እንዴት በአንድ እንቅስቃሴ ብቻ ውድድሩን አሸነፍኩ?”
“ያሸነፍከው በሁለት ምክንያቶች ነው” መምህሩ መለሰ፣ “የመጀመሪያው፣ እጅግ ከባድ የሆነውን የጁዶ
እንቅስቃሴ በደንብ ለምደኸዋል። ሁለተኛው ምክንያት፣ ተፋላሚህም ይህንን እንቅስቃሴ መመከት
የሚችለው ግራ እጅህን በመያዝ ብቻ ነው።”
የልጁ ትልቁ ድክመቱ ጥንካሬው ሆነ።
በጸጋ መቀበልን ልመድ፣ ድክመትህንም ጥንካሬህ አድርገው።
ከጭንቅላትህን አፅዳ መጽሐፍ የተወሰደ
t.me/guramaylebooks
3.2K viewsedited  21:19
Open / Comment
2021-03-02 02:11:04
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት
...........

ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
3.4K viewsedited  23:11
Open / Comment