Get Mystery Box with random crypto!

ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

Logo of telegram channel geezlibrary — ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ
Logo of telegram channel geezlibrary — ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ
Channel address: @geezlibrary
Categories: Literature
Language: English
Country: Not set
Subscribers: 8.73K
Description from channel

በኢትዮጵያውያን ደራስያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ሚተረኩበት ድንቅ ሀገራዊ ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 4

2021-02-25 07:34:24
#ብርጭቆ_መሆንህን_አቁምና_ሃይቅ ሁን!

አንድ ደስታውን ያጣ ወጣት ወደ አንድ ሽማግሌ መምህር መጣ። ለመምህሩም በየዕለቱ ስለሚኖረው የሚያሳዝን ሕይወቱ ነግሯቸው መፍትሄውን ጠየቃቸው።

መምህሩም ደስታ ለራቀው ወጣት እፍኝ ሙሉ ጨው፣ ውሃ የተሞላ ብርጭቆ ውስጥ እንዲጨምር አዘዙት። በብርጭቆ ያለውንም ውሃ ‘ጠጣው’ አሉት። ወጣቱም ከውሃው ተጎነጨ።

“ጣዕሙ እንዴት ነው?” ሽማግሌው ጠየቁ

“በጣም መጥፎ ነው” ወጣቱ ፊቱን አጨፍግጎ መለሰ

ሽማግሌውም ፈገግ አሉና አሁንም እፍኝ ሙሉ ጨው ሃይቅ ውስጥ እንዲጨምር አዘዙት። ሁለቱም በጸጥታ ውስጥ አቅራቢያቸው ወዳለ ሃይቅ አመሩ። እዛም ሲደርሱ ወጣቱ በእጁ የያዘውን ጨው ሃይቁ ላይ በተነው።

ሽማግሌውም “አሁን፣ ከሃይቁ ውሃ ጠጣ” አሉት

የተጎነጨውንም ውሃ በጉሮሮው እያወረደ ሳለ፣ ሽማግሌው መምህር “ጣዕሙ እንዴት ነው?” ብለው በድጋሜ ጠየቁት።

“በጣም ጥሩ ነው!” አለ በፈገግታ

“የጨው ጣዕም አለው?” መምህሩ ጠየቁት

“አይ” አለ ወጣቱ፡፡

መምህሩ ከተቸገረው ወጣት አጠገብ ተቀምጠው እጁን ያዙት፡፡ “ህመሞችህ ልክ እጅህ ላይ እንዳሉት እፍኝ ጨው ቅንጣቶች ናቸው፤ አያንሱም አይበዙም። ሕይወትህ ላይ ያለው ስቃይም አይጨምርም አይቀንስምም። ሆኖም ህመሙን የምንቀምስበት መንገድ እና ስቃዩን የምናስቀምጥበት እቃ ይለያያል። ህመም ውስጥ ስንሆንም ልናደርገው የምንችለው ነገር ቢኖር፣ ለነገሮች ያለንን እይታ መቀየር ብቻ ነው። ስለዚህ ብርጭቆ መሆንህን አቁምና ሃይቅ ሁን…”
@guramaylebooks
3.9K viewsedited  04:34
Open / Comment
2021-02-23 07:30:46 ………ከላይየቀጠለ

የዓድዋ ድል በዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ድብዳቤዎች

ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ የዓድዋን ድል አስመልክተው ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን የዛሬ 124 ዓመት የጻፉለት
የምሥራች ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር

“የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት
ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ››አጤ ምኒሊክ በመጋቢት 23 ቀን 1988 ዓ.ም.

ለፈረንሳዊው ሙሴ ሸፍኔ በላኩለት ደብዳቤ ያቸው እንዲህ ብለዋል

‹‹… ከአላጌ ጦርነት በኋላ፣ ጣሊያኖችን ጦርነት ይቅር፣ የክርስቲያንም ደም በከንቱ አይፍሰስ፣ እርቅ ይሻላል ብላቸው እምቢ ብለው መጥተው በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግ ተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድቁርናቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም፡፡ ነገር ግን በግፍ የመጡ ሰዎች ናቸውና እግዚአብሔር ግፉን አነጣጠረን…፡፡››

በማለት ያስታወቁ ሲሆን ምኒልክ ለሞስኮብ ንጉሥ ኒቆላዎስም መጋቢት 23 ቀን 1988 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤያቸውም

‹‹እንደ አውሮፓ ነገሥታት ሥራት
ሁሉ ጠብ መፈለጋቸውን ሳያስታውቀኝ፣ እንደ ወምበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሰግስ አድሮ ሲነጋ ግምባር ካደረው ዘበኛ ጋር ጦርነት ጀመረ፡፡ ጥንት ከአህዛብና ከአረመኔ አገራችን ጠብቋት የሚኖር አምላክ ከእኛ ባይለይ በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረግሁት…›› ብለው መጻፋቸው ይጠቀሳል ፡፡

አልፋና ኦሜጋ የማይረሳው መስዋዕትነት !
አልፋና ኦሜጋ በክብር ይዘከራል !

ልክ የዛሬ 124 ኛ አመት እሁድ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓም ታላቁ የዓድዋ ድል በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ ተበሰረ !

ይህ የጥቁር ህዝብ በቅኝ ገዥዎች ከተቀዳጃቸው የዓድዋ ድል እውን እንዲሆን
አቀበት የወጡ ፣
ቁልቁለት የወረዱ ፣
እርጥብ የጨሰባቸው ፣
ደረቅ የነደደባቸው ፣
ከቤታ ቸው የተፈናቀሉ ፣
የቆሰሉ ፣
የሞቱ ፣
መዳረሻቸው የጠፋ ጀግኖቻችን አልፋና ኦሜጋ የማይረሳው መስዋዕትነት ነው።

ይህ አንጸባራቂ ድልም እነሆ አልፋና ኦሜጋ በክብር ይዘከራል !
የዛሬ 124 ዓመት ከዘመነው የፋሽሽት ጣሊያን ጦር እና ጦር ሰራዊት በላይ የጥቁር ህዝብ ብሔራዊ ክብርና ኩራት ልቀው የታዩበት የጦርነት አውድማ ነው !

ዓድዋ

ምንጮች :
* በታዋቂ የታሪክ አዋቂዎች ከተጻፉት የታሪክ መዛግብት፣
*ከአድዋው ጦርነት ዙሪያ ከቀረቡት የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት ፣
* ልዩልዩ

***
ሀገርን ከነድንበሩ፣
ታሪክን ከነባህሉ፣
ቋንቋን ከነፊደሉ ያቆዩልን፣
ለዛሬው ማንነታችን የአካል እና የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉልን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖችን እና አርበኞቻችንን እናመሰግናለን!
#ክብር_እነሱ_ወድቀው_ኢትዮጵያን_ከእነሙሉ_ክብሯ_ላስረከቡን_አርበኞቻችን_

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_125
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@yetarikdersan
3.0K views04:30
Open / Comment
2021-02-23 07:30:30 #የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_125
#ዝክረ_ዓድዋ

እቴጌ ጣይቱ ብጡል «እኔ ሴት ነኝ፣ጦርነት አልወድም፣ሆኖም ግን ኢትዮጵያን የጣሊያን ጥገኛ የሚያደርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ ፡፡ »

የጦርነቱ መነሻ ምክንያት

የዓድዋ ጦርነት መነሻ ምክንያት የሆነው የውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ሲሆን ይህ አንቀጽ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተን ሆኖ በመገኘቱ እንዲሰረዝ የተደረገው ሙከራም በጣሊያን እምቢተኝነት በመክሸፉ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

የጣሊያን ወረራ መሰማትና እቴጌ ጣይቱ

የጣልያንን እምቢተኝነት ተከትሎ ሚኒስትሮች፣ የጦር አለቆችና መኳንንቱ ባካሄዱት የምክክር ጉባኤ ላይ እቴጌ ጣይቱ ብጡል «እኔ ሴት ነኝ፣ጦርነት አልወድም፣ሆኖም ግን ኢትዮጵያን
የጣሊያን ጥገኛ የሚያደርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ ፡፡ » ሲሉ የሰጡት አስተያየት ነበር፡፡

የኢትዮጵያው ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አጤ ምኒሊክ የክተት አዋጅ

ጣሊያን ውል አፍርሶ ኢትዮጵያን ሲወርር በጉልበቱ የጀግኖችን ሃገር ሊፈታው እንደማይችል ያውቅ ነበር። ጣልያን በልዩነታችን ገብቶ ሊለያየን እቅድ አቅዶም ነበር ። ይህንንም
ለማሳካት በተለያየ አስተዳደር ግዛት ለይተው በሚቆራቆሱ የጦር አበጋዞችና በንጉሱ መካከል የነበረውን የከፋ ልዩነት መጠቀም ለድል እንደሚያበቃው አልሞ መነሳቱ እውነት ነበር ።

ያም ሆኖ የንጉሰ ነገስቱ መኳንንቱን ፣ ሹመኞችን እና የጦር አለቆችን ሰብስበው በመምከር ብሔራዊ ክብርን ማስጠበቁ ይቅደም አንድምታ ያለው ሃሳባቸው ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ በሰለጠነ መንገድ ከመግባባት ላይ ደረሱ። ይህም ምክክርና ስምምነት
ሁሉም በአንድነት ለነጻነትና ክብሩ ይተጋ ዘንድ ታላቅ አስተዋጽኦ ያደርግ ዘንድ ሁሉም በየስራ ድርሻው ተመድበው መስራት ጀመሩ።

መስከረም 1888 ዓ.ም ወር ላይ ንጉስ ምኒሊክ ጣሊያንን ለወረራ መዘጋጀቱን በስለላ ባለሟሎቻቸው በቅርብ አረጋገጡ።

በወረራ ዝግጅቱ የተቆጡት ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ የክተት አዋጅ
እንዲህ በማለት አስነገሩ …

‹‹እግዚአብሄር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፤ እኔም እስካሁን በእግዚአ ብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ ከእንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለእኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖትን የሚለውጥ፣ በፊት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት
ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ
ሰው ከአሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን
አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት
የሌለህ ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘንህ እርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፡፡ አልምርህም፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም…››

ዓድዋና የጦሩ ዝግጅት

የዓድዋው ጦርነት በጣልያኖች በኩል የቆየ የቀኝ ግዛት ጥማቸውን ለማሳካት ቀድሞ የተጠነሰሰ ነበር። በኢትዮጵያውያን ዘንድ ግን የጦርነት ዝግጅቱ እስከ ሰባት ወር የፈጀ እንደነበር ይነገራል። ዝግጅቱ ተጠናቆ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ጎህ
ቀዶ እስኪጠልቅ በቀድሞዋ ትግራይ ጠቅላይ ግዛት በዛሬዋ ክልል አንድ ትግራይ ውስጥ በምትገኘው በዓድዋ ከተማ ይገጥም ዘንድ ቀኑ ደረሰ ! በዓድዋው ዘመቻ በመቶ ሺሕዎች
ሆኖ የዘመተው የኢትዮጵያ ጦር ከጥቂቱ በስተቀር አብዛኛው ጦር፣ ሰይፍ፣ ጋሻና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ይዞ እንደ ነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

ጣሊያን በአስር ሽዎች የሰው ሃይል ፣
በዘመናዊ የጦር መሳሪያና በወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠነ አውሮፓዊ ጦር ነበርና ከፍ ባለ ስንቅና ትጥቅ ተደግፎ ወረራ
መጀመሩ ይጠቀሳል።

አንጸባራቂው የዓድዋ ድል !
የጥቁሮች ድል !

የጣሊያን ጦር በጄኔራል ባራቴሪ እየተመራ ባህር ተሻግረሮ ሲመጣ የተወረረችው የኢትዮጵያውያን ጦር
የሚመራው በንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ነበር። ጀግና ብልህና አርቆ አስተዋይዋ ባለቤታቸው እትየ ጣይቱ ብጡል በዚያ ባልሰለጠነ ዘመን ስልጡን ነበሩና በባለቤታች ከሚመራው የአርበኞች ግንባር እኩል ተሰልፈው ሃገሬውን ስንቅ ትጥቅ
በማስታጠቅና በማበረታታት የከፈሉት መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም።

ኢትዮጵያውያን በንጉሱ ብልህ አመራርና ክተት ብለው በህብረት ተነሱ ። ከሽኩቻና ዝብሪት ተዘፍቀው የባጁት
የየግዛቱ ሹሞች እና የጦር አበጋዞችም በንጉሰ ነገስት አጤ ምኒሊክ የክተት አዋጅ ልዩነታቸውን አስወግደው በህብረት ተመሙ !

የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ከ124 ዓመታት በፊት በዕለተ ሰንበት ክብሩ የተነካው አርበኛ ህዝብ ዓድዋ ላይ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ተንቀሳቅሶ ባካሔደው ውጊያ እብሪተኛውን
ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ የጣሊያን ጦር ጋር ገጠመ !

ከማለዳ አንስቶ ጀንበር እስክታዘቀዝቅ ባለው ጊዜ የተካሄደው ጦርነት እልፍ አእላፍ መስዋዕት ሆነው በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት በዓድዋ ተደመደመ !
ጣሊያን ከአንባላጌ እስከ አድዋ ተጠራርጎ እንዲወጣ ያደረገው
” የጥቁሮች ድል!” በሚል አለም ባወደሰው የዓድዋ ድል የጣሊያን መንግስት የሃፍረት ማቅን በግዱ ተከናነበ።

የዓድዋ ድል በመላ በአለም ከተበሰረ በኋላ የወረራው መነሻ የሆነውን የውጫሌ ውል ፈርሶ የጣልያን መንግስት በውጫሌ ውል
የነበረውን አጉል ምኞቱን ይሰርዝ ዘንድ ግድ ሆነበት ።

ወራሪው በሽንፈቱ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙሉ ነፃነት አውቆ እና ተቀብሎ
የሰላም ስምምነት ያደርግ ዘንድ ተገደደ ! የስምምነት ውሉም ለአለም መንግስታት ተሰራጨ። ውሉ የደረሳቸው መንግስታት እና ሃገራት የኢትዮጵያን የተረጋገጠ ሉአላዊ መንግስትነት በውድም ሆነ በግድ ተቀብለው አረጋገጡት !

ይቀጥላል………
2.5K views04:30
Open / Comment
2021-02-22 12:05:09 አደዋ በጂጂ

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር ሰው ሰው ሞቶ
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆሙኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
በኩራት በክብር በደስታ በፍቅር በድል እኖራለሁ
ያው በቀን በቀን በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ …. አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ ሄ......ተናገሪ ተናገሪ
የድል ታሪክሽኝ አውሪ
ሄ.....ይ....ተናገሪ......ሄ.........ይ
2.3K views09:05
Open / Comment
2021-02-22 09:33:54 ዋ!…ያቺ ዓድዋ
ዋ!…
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትብያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ ለት
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ፅዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
አፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲልሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኝው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኝው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኝው
ያባበለው በለው ሲለው
በለው- በለው-በለው-በለው!
ዋ!…ዓድዋ…
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኝው
በለው ብሎ፥በለው-በለው!
ዋ!…ዓድዋ…
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና
…ዋ!…ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…
የካቲት(፲፱፻፷፬-ዓድዋ)
ከ ፀጋዬ ገብረ መድህን
2.5K views06:33
Open / Comment
2021-02-21 02:45:46
Atomic Habits

በውስጡ ኦዲዮ ሲዲ ከተካተተበት መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ።

ልምዶቹን ለመለወጥ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የግድ ማንበብ ያለበት መጽሐፍ (ደግሞስ ማን ነው የማይፈልግ?)። በውስጡም፣ ቀላል የሆኑ ጥቃቅን (አቶሚክ) ልምዶች እንዴት ትልቅ ውጤቶችን እንደሚፈጥሩ ይማራሉ።

አቶሚክ ልምዶች አንድ ትልቅ ውጤት የሚያስከትሉ ትናንሽ ለውጦች ናቸው። የህይወትዎን የተለያዩ ገጽታዎች በትናንሹ ሲያሻሽሉ የመጨረሻው ውጤት ትልቅ ለውጥ ሊሆን ይችላል።

እነዚህ ቀላል የአቶሚክ ልምዶች ትልቅ ውጤቶችን መፍጠር ብቻ ሳይሆን በማንኛውም የህይወትዎ ክፍል ላይ ሊተገበሩ የሚችሉ ናቸው። ብዙ ውሃ እንደመጠጣት፣ ስልክዎ ላይ የሚያባክኑትን ጊዜ እንደመቀነስ፣ ወይም በተፈጥሮ የተከበበ ቦታ ላይ የእግር ጉዞን እንደማድረግ ያሉ ቀላል ፍላጎቶችዎን ሊሆን ይችላል። ለስራ ልምዶችዎ እና ምርታማነትዎ እንዲሁም ለጤንነት ግቦችዎ እነዚህ ልምዶች ይጠቅምዎታል።

በጣም ከሚወዷቸው ጥቂት መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ይህ ነው።

ለመጀመር የሚፈልጓቸው ማንኛውም ጥሩ ልምዶች ወይም ማቋረጥ የሚፈልጓቸው ማንኛቸውም መጥፎ ልምዶች ካሉዎት፣ Atomic Habitsን ያንብቡ እና ለውጡን አሁን ይጀምሩ። ሕይወትዎን ይለውጠዋል።

በተጨማሪም ይህ መጽሀፍ ትረካው ስለተካተተበት፣ መኪናዎ ውስጥ፣ በኮምፒተርዎ፣ ወይም በሞባይልዎ ማድመጥ ይችላሉ።

ሶስተኛው ህትመት በብዛት በገበያ ላይ ስለ ዋለ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።
2.6K views23:45
Open / Comment