Get Mystery Box with random crypto!

Hawhora Clinic-Hosanna

Logo of telegram channel haworaclinic — Hawhora Clinic-Hosanna H
Logo of telegram channel haworaclinic — Hawhora Clinic-Hosanna
Channel address: @haworaclinic
Categories: Health
Language: English
Subscribers: 195

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 3

2021-04-11 18:59:04 https://telegra.ph/የማይግሬን-ራስ-ሕመም-04-11
216 views15:59
Open / Comment
2021-04-11 18:50:07
ለልጆ ጤና የሕጻናት ሕክምና በስፔሻሊስት ሐኪም

ዶክተር ሙሉዓለም
የሕፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም

መደበኛ የስራ ሠዐት
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዐርብ ከ11:00-2:30*
ቅዳሜና እሑድ ከ8:00-2:30

በቀጠሮ ለመታከም በ 0996237111 ይደውሉልን።


በ0932609203 በመደወል ሐኪሙን ያናግሩ።

@haworaclinic ይቀላቀሉ።

#child #pediatrics #health

*ከ2:30-11:00 በጠቅላላ ሐኪም ሕክምና ማግኘት ይችላሉ።
155 viewsedited  15:50
Open / Comment
2021-04-09 07:43:46 ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ
Recurrent pregnancy loss(RPL)

ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ምንድነው?

የፅንስ መጨንገፍ አንዲት ነፍሰጡር ሴት እርግዝናው 20 ሳምንት ሳይሞላው በራሱ ጊዜ ሲቋረጥ ነው።

ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ የሕክምና ቃል ሲሆን አንዲት ሴት 3 ወይም ከዚያ በላይ በተከታታይ የጽንስ መጨናገፍ ሲያጋጥማት ነው።

ለተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ምንድነው?

አንዳንድ ሁኔታዎች ለጽንስ መጨናገፍ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ

● የጽንሱ የክሮሞሶም ችግር

ክሮሞሶም በሺዎች የሚቆጠሩ ጂኖችን የያዙ ሴሎች ናቸዉ። የክሮሞሶም ችግሮች አብዛኛውን ጊዜ በአጋጣሚ የሚከሰቱ ናቸው ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ የሚከሰቱት የእናት ወይም አባት የክሮሞዞም ችግር ስላላቸው ሊሆን ይችላል። ይህ ሁኔታ በአብዛኛው በዕድሜ የገፉ እናቶች ላይ ይከሰታል።

● ከእናትየው የበሽታ መከላከል ስርአት ጋር የተያያዙ ችግሮች

● የእናትየው የውስጥ ደዌ በሽታዎች መኖር። ለምሳሌ የስኳር እና የታይሮይድ በሽታዎች

● የማህጸን የውስጥ ቅርጽ የሚቀይሩ አንዳንድ የተፈጥሮ ወይም ከጊዜ በኋላ የሚከሰቱ ችግሮች

ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ጊዜ ዶክተሮች የተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ሊያውቁት አይችሉም።

ለፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ለማወቅ ሐኪሜ ምን አይነት ምርመራ ያደርጋል?

የፅንስ መጨንገፍ ለምን እንደነበረ ለማወቅ ዶክተርዎ

● ከእርስዎ ጋር እየተነጋገረ ስለ ቀደምት እርግዝናዎ፣ ስለ የወር አበባዎና የጤና ሁኔታዎትን ይጠይቃል

● የማህጸን ምርመራን ጨምሮ አጠቃላይ የአካል ምርመራ ያደርጋል

● የደም ምርመራዎች እንዲያደርጉ ያዝዛል

እነዚህ የሚያጠቃልሉት በሽታ የመከላከያ ስርኣትን፤ የደም መርጋት ስርዓትን እና የሆርሞን ደረጃ ምርመራዎች ነው። በተጨማሪም እንደ ታይሮይድ በሽታ ወይም የስኳር በሽታ የመሳሰሉ አንዳንድ የጤና ሁኔታዎችን ምርመራ ያካትታል።

● አልትራሳውንድ

● ሂስተሮስኮፒ

ይህ ካሜራ ያለው ቀጭን ቱቦ ወደ ማሕፀን ውስጥ አስገብቶ የማህጸን የውስጥ ክፍል ምርመራ ነው።

● የክሮሞዞም ምርመራ

ይህ በዘረ-መል (genetic) ላይ ችግር ካለ ለማወቅ የሚደረግ ምርመራነው።የእርስዎ እና የባለቤትዎ የክሮሞዞም ምርመራ ከመደረጉ በፊት ከጂን ምርመራ አማካሪ ጋር እንዲወያዩ ይደረጋል።

የተደጋጋሚ የፅንስ መጨናገፍ ህክምናው ምንድን ነው ?

ህክምናው መንስኤውን መሰረት ያደረገ ነው። ለምሳሌ

● አንዳንድ ጊዜ በማህፀን ውስጥ ያለን ችግር በቀዶ ሕክምና ሊታከም ይችላል።

● አንዳንድ የበሽታ መከላከያ ወይም የሆርሞን ችግሮች በመድሃኒት ሊታከሙ ይችላሉ።

ድጋሚ የፅንስ መጨንገፍ እንዳይኖር በራሴ የማደርገው ነገር አለ?

የፅንስ መጨንገፍ በእርግጠኝነት እንዳይኖር ለማድረግ የሚያስችል መንገድ የለም። ይሁን እንጂ

● ሲጋራ ፣ የአልኮል መጠጥ፣ ኮኬይንና የመሳሰሉትን ነገሮችን በማቆም እና ክብደትዎን በመቆጣጠር የጽንስ መጨንገፍ እድሎዎን ሊቀንሱ ይችላሉ።

● ለመጸነስ ሲያስቡ ወይም መጸነስዎ እንዳወቁ ወድያውኑ ሃኪም ያማክሩ

ከተደጋጋሚ የጽንስ መጨናገፍ በኋላ መጨነቅና ማዘን የተለመደ ነው። አንዳንድ ሴቶች ግን በጭንቀት ይዋጣሉ። የመንፈስ ጭንቀትዎ የከፋ ከሆነ ግን ሀኪም ወይም ነርስ ያማክሩ።አንዳንድ ሕክምናዎችና የመቋቋሚያ ስልቶች አሉ። አንዳንድ ጊዜም ተመሳሳይ ችግር ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር ተገናኝቶ መወያየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ።

በክሊኒካችን የማህፀንና ፅንስ ህክምና ከተሟላ ምርመራ ጋር በማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም በ ዶ/ር ሎምባሞ ሊራንሶ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

@haworaclinic ይቀላቀሉ።
0911512338/ 0996237110 / 0996237111 ይደውሉ ።
366 viewsedited  04:43
Open / Comment
2021-04-08 15:38:09
#AvailableNow

*Cardiac Troponin I*
Safe way to Triage chest pain!


The diagmosis of cardiac emergencies is one of the most crucial tasks delegated to physicans. The broad differential diagnosis of chest pain must be narrowed to perform life-saving treatments.

- Cardiac Troponins are cardiac regulatory proteins that are found in the cytoplasm of cardiac myocytes.

- Cardiac Troponin I is found exclusively in cardiac muscles.

- Troponin levels start to elevate in circulation within 2-3 hours of the onset of chest pain. They reach peak between 12-48 hours and begin to fall over next 4-10 days down to normal.

- Troponin level greater than 0.6 ng/mL has 94% sensitivity and 81% specificity for the diagnosis of acute myocardial infarction.

#troponin #chestpain #heart #myocardiaInfarction #labtests
Subscribe to @haworaclinic
Like us on facebook.com/haworaclinic
160 views12:38
Open / Comment
2021-04-04 17:02:29
HaworaClinic

የስኳር መጠን መከታተያ ደብተር

- በቤቶ ወይም በአቅራቢያው ባለ የጤና አገልግሎት መስጫ የስኳር መጠኖን ሲለኩ ለመመዝገብ ያስችሎታል

- የ20 ሳምንታት ወይም የ140 ቀናት የስኳር መጠን ለመመዝገብ
- በቀን ስድስት ልኬቶችን መመዝገብ ይችላሉ

አውርደው ፕሪንት በማድረግ ይጠቀሙ።
ለሌሎች ያጋሩት

https://t.me/haworaclinic/161

@haworaclinic ይቀላቀሉ
ስለአጠቃቀሙ ለማወቅ በ 0996237111 ይደውሉ
234 viewsedited  14:02
Open / Comment
2021-04-04 16:55:27 Blood sugar log book
የስኳር መጠን መከታተያ ደብተር

የ20 ሳምንታት ወይም የ140 ቀናት የስኳር መጠን ለመመዝገብ

ለአጠቃቀም ቀላል በአማርኛ የተዘጋጀ

አውርደው ፕሪንት በማድረግ ይጠቀሙ።
ለሌሎች ያጋሩት

@haworaclinic ይቀላቀሉ
207 viewsedited  13:55
Open / Comment
2021-03-21 15:55:40 LAMFOORO'M TE'IM SIIRO'M AMMANENE HAKI'IM MINE WAAROO AMMO'INA ISSAMOO ABOOYYUWA.

1. Lamfoor ammo'o qarammena yoo ciilluwa danaamisa awwonimma.

2. Siiromine amaxxamaa waaroo jabbuwina qararissimma. kobi'llishina, pre-eclampsia

3. Siiro'm ammaninse illageen yoo jabbuwwa la'imaa eejabbuwwina qararissimma.

4. Aniimiya'i(anemia),shayyixi edanchine higoo jabbuwwi (kobi'llishina..chabara),HIV,horro'l jabb yoolas la'ima qararissimma.

5. Jabb qoccamoobe'isina awwaado qaraare uwwimma. Kobi'llishina-Gaangeer gudd kitibatta (tetanus vaccine) ,godaphphi daquura fissima (deworming),kachchis qaraaree kachchis bimbe'ii egaddoo agoberra uwwimma.

6. Ammo'i ixxuwwikaa ixxuwwi abaroosikaa fayya'omma hinkid egarim hassisoda'e losaan uwwimma. Kobi'llishina, abarooso qoodim bikkina, ciilluwa anuuna icisim bikkina, muccurooma egarim bikkina, xuuchi waaroo'n ilage Isakkam guddo Bikkinaa siiromine amaxxamaa waaroo Jorr mare bikkina annann anann soggitano uwokko.

GUDDISANCHI LIRANS DOCTOOR LOMBAMO
kii'n beshuwina
@haworaclinic sheer issimine hawoo'l killiniq abaroos isehe.

Kaani wooron yoo silk xigone aphisehe
0911512338

#healtheducation #pregnancy #obstetrics #dr_lombamo #health

****share****share****share****
354 viewsedited  12:55
Open / Comment
2021-03-21 15:55:33
LAMFOORO'M TE'IM SIIRO'M AMMANENE HAKI'IM MINE WAAROO AMMO'INA ISSAMOO ABOOYYUWA.

@haworaclinic
209 views12:55
Open / Comment
2021-03-19 08:36:35
የስኳር ሕክምና ይወስዳሉ?
በምን ያክል ደረጃ የስኳር መጠኖን እንደተቆጣጠሩት ያረጋግጡ!

የሔሞግሎቢን ኤ 1 ሲ ምርመራ

የሔሞግሎቢን ኤ 1 ሲ ምርመራ ባለፉት ሶስት ወራት በደማችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለማወቅ የሚጠቅም ምርመራ ነው።

የሔሞግሎቢን ኤ 1 ሲ ምርመራ የስኳር በሽታ ታካሚዎች በምን ያክል ደረጃ የስኳር መጠን መቆጣጠራቸውን ለማውቅ ከመጥቀሙ ባሻገር ከሌሎች የስኳር ምርመራዎች በተሻለ የስኳር በሽታን ለማረጋገጥ ያስችላል።

በክሊኒካችን የሔሞግሎቢን ኤ 1 ሲ ምርመራ ሳምንቱን በሙሉ ከውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም የማማከር አገልግሎት ጋር ያገኛሉ።

ስለ ስኳር ሕመሞ ጥያቄ ካሎት የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪማችንን ዶ/ር አቡበከርን በ 0913720545 ደውለው ይማክሩ።

@haworaclinic ይቀላቀሉ።
0996237110 / 0996237111 ይደውሉ ።

@haffadvert
232 viewsedited  05:36
Open / Comment
2021-03-13 18:35:06 ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ ከፍተኛውን የሞት ቁጥር አስመዘገበች

በኢትዮጵያ የመጀመርያው በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ሪፖርት ከተደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ ከፍተኛው የሞት ቁጥር መመዝገቡን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በዕለታዊው መረጃው ይፋ እንዳደረገው በመጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. 27 ግለሰቦች በአንድ ቀን በኮቪድ-19 ቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ እንደዚህ ዓይነት ከፍተኛ የሞት ቁጥር የተመዘገበው ከአስከሬን ላይ ናሙና ተወስዶ በሚመረምርበት ወቅት ነበር።
 በተጠቀሰው ዕለት፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 6,985 ሰዎች፣ ቫይረሱ የተገኘባቸው 1,361 ሲሆኑ፣ 454ቱ ደግሞ በጽኑ ታመዋል፡፡  

በኢትዮጵያ ባጠቃላይ 2,214,180 ተመርምረው፣ ቫይረሱ የተገኘባቸው 172,571፣  ያገገሙ 141,195 ሲሆኑ፣ ባሁን ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 28,864 ናቸው፡፡ በወረርሽኙ 2,510 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አሁናዊው መረጃ ያሳያል፡፡

መዘናጋቱ በዚሁ ከቀጠለ ነገ የእያንዳንዱን ቤት ማንኳኳቱን ሰለማይቀር አሁንም የመከላከያ መንገዶችን  ኅብረተሰቡ በአግባቡ እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

አራቱ የ‹‹መ›› ሕጎች
• መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
• መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
• መቆየት፡ አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
• መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር

@haworaclinic ይቀላቀሉ
#covid
272 views15:35
Open / Comment