Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 132.20K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 215

2021-10-12 16:01:46 አንች ከሌለሽ

አንች ከሌለሽ
ቀኑ ይደክማል
ለሊቱ ያማል
ሰማይ ይጠቁራል
ምድር ያድማል
አንች ከሌለሽ
ይበዛል ድብርት
ያይላል ፍርሀት
ይመጣል ጭንቀት
አንች ከሌለሽ
ይርቃል ደስታ
ጠፋ ጨዋታ
አንች ከሌለሽ
መኖር ያስጠላል
ሀሉ ይደብራል

essa arts

@essarim10

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.3K viewsAbela, 13:01
Open / Comment
2021-10-12 13:40:49 (........)

ህመሜ ተወለድ አይኔም አልቅስ እንባ
ይቀልህ እንደሆን፤
ልቤም ከሰው ራቅ ሰው አትውደድ ከቶ
መስሎህ አታፈንፍን፤
የራስህ ምሳሌ የራስህ እውነታን
ሰው ከሚቀድሰው፤
በራስህ ሀቂቃ እርግማንን ዘርተህ
በሰው አስወቅሰው።

ሚኪያስ እንዳለው
@mikiendialem

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsAbela, 10:40
Open / Comment
2021-10-12 11:35:47 ያ'ምላክ

[ቶማስ ትግስቱ]
.
.
እና እኔ
እና አንቺ
እንስሳት
እፅዋት
አዋፋት
እና አምላክ
።።።።።።።።።።።።።።
ከለታት አርብ ነው
ቀና ስል ጣሪያ አለ
ጭልጭል የሚል መብራት
ከሆዱ ያዘለ
መሃል ላይ አይመስልም
ዳርም ላይ አይደለም
ግን ደግሞ ተበስቷል
ወዲያ ጥግ ጥጉን
ሸረሪት ተኝቷል
(ከሸረሪቷ ጋር)
ብዙ ዝምባ ዝቦች
ቢምባ ቢምቦች
ትንኛ ትንኞች
ይተራረባሉ
ዝዝ ብዝ ጥዝ ምናምን እያሉ

(እኔስ?)
እኔ
ደክሞታል ወገቤ
አሞታል እራሴ
አላውቅም ጠግቤ
በስብሷል ትራሴ
ጀርባዬ ተኝቷል
እግሬም ተዘርግቷል
አጭር ነው ቁመቴ
አልጋው እረዝሞታል
ቀጭን ሰውነቴ
አልጋው ግን ጠቦታል
(እናም አልጋ ላይ ነኝ)

ግን አልጋው ጠቦኛል
አጥብቆ ገርሞኛል
(ማታ የጠጣሁት አለቀቀኝ ይሆን?)
አምቡላው
አተላው
ቅራሪው
(ዝቃጫም መጠጡ )
ሲደመር አስካሪው?
አይ አይ ለቆኛል
በርግጥም ጠቦኛል
ደግሞ በግራ ጎን
(በቀኝ ግርግዳ ነው)
ዳሰስኩ ጥግጥጓን

ሴት

አውዝቢላሂ ወ መንፈስ ቅዱስ
ማናባቷን ነው እጄ ሚዳብስ?

ግራ ጎኔ ጋር ሴት
ሊያውም እኔ ቤት
እኮ ማን ጠርቷት?
እኮ ማን ጋብዟት?
ደገምኩ ዳሰስኳት

ብዥ ይላል ጣሪያው
ማታን ሲያሳየኝ
ጥምብዝዝ ብዬ
እሷ ግን አዝላኝ
ከቤቴ ገብታ
ካልጋ ስጥለኝ
ልብስ አወላልቀን
ስላት ስትለኝ....

ሸረሪቷ እና....
ዝምባ ዝምቦቹ ፣
ቢምባ ቢምቦቹ ፣
ትንኛ ትንኞች
ይፋፌዛሉ
ይሳሳቃሉ
ዝዝ ብዝ ጥዝ ምናምን እያሉ
(<ድንቄም ባለ ሴት> ነገር)

ዞሬ አየሁሽ፤
ወፍራም ሰውነት
የ ቀይ ዳማ ፊት
ቡግራ ቡግር
ነጭና ጥቁር
ድብልቅ ጸጉር
ሽልጦ ከንፈር (የምር ትልቅ ነው)
ሌላውስ ይቅር

ሰው የጠላው እኔን
ያቀፈ ሰውነት
የሳመ ሴትነት
የሾመ አዳምነት

ሔዋኔ
ሔ....ዋ....ኔ
ሔ.....ዋ...... ኔ....ነሽ
በግራ ጎኔ አምላክ ያኖረሽ
እሱ የጠራሽ
እሱ የጋበዘሽ

ሰካራም
እድፋም
ቱሃናም
ፎከታም
ብሆንም
በስካር እንቅልፍ አምላክ ያመጣሽ
ካጥንቴ አጉሎ ላንቺ የሰጠሽ።
(እኔ ቀጭን እሷ ወፍራምም አይደለን?)

"ሄዋኔ ስሚኝ"
አንቺ እስካለሽኝ
አንቺ እስከኖርሽኝ
ፀሃይ አጠልቅም
ሃጣን አይወድቅም
ፃድቅ አይፀድቅም
ዝምብ አትስቅም
ቢምቢ አትንቅም
ትንኝ አላውቅም

አ..ላ..ው..ቅ...ም አላውቅም(34×)
ማንንም አላቅም

ድሮም ባ'ዳም አለም
ሄዋን እና እሱ እንጂ
የሰው ፍጡር የለም

እናም በዚች ምድር፤
እንስሳት
እፅዋት
አዋፋት
እና አምላክ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እና እኔ
እና አንቺ
ብቻ እንቅር ፍቅር

[ቶማስ ትግስቱ]

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
143 viewsAbela, 08:35
Open / Comment
2021-10-12 07:40:48
39 viewsMerry G, 04:40
Open / Comment
2021-10-12 06:50:15 የ ኪያ ቁጥር 2 ፊልም አዲሱ ማጀቢያ ሙዚቃ ዳውንሎድ ማድረግ ሳይጠበቅባቹ ከስር 'Play' ሚለው በመንካት ያዳምጡ

ኤሊያስ ተሾመ - ኪያዬ ቁ.2
Play ▷ ◉─────── 04:55
305 viewsMerry G, 03:50
Open / Comment
2021-10-12 06:33:47
ሴክስ ምናምን ብለን አንዋሽም ስሜትን የሚገልፁ አማርኛ ጥቅሶች የሚገኝበት ቻናል ነው እመኑኝ ትወዱታላችሁ JOIN ማለት ብቻ !
https://t.me/joinchat/AAAAAFH485JjGwqkgZm4pA
406 viewsMerry G, 03:33
Open / Comment
2021-10-12 06:33:46
✧አንቺ'ና ቁንጅናሽ እኔም ለኔ ስልሽ
ሌላም ሠው ስመኝሽ ተወዳድርኩ እኔም
የግሌ ላደርግሽ ግና ምን ያደርጋል
መስፈርትሽ ይከብዳል እንኩዋን እኔ ቀርቶ
እብዱም ደግሞ ያብዳል።•
240 viewsMerry G, 03:33
Open / Comment
2021-10-12 06:30:08 ሠሚ ያጣ ግጥም......

እስቲ ልግጠምልህ
ከመድረክ ወጥቼ ልንጎራደድልህ
መድረኩ ይሰየም
አንተም በዛ ክተም
ፍቅሬን ልግለፅልህ
ብዬ ብጠራህም....................

ግጥም የት አባቱ
ጠፋብኝ ዉበቱ
ቤት አንመታም ብለዉ
ቃላቶች ዘበቱ

ላንተ ሲሆን ጊዜ
ፊደላት ምቀኛ
ሀረጋት ፌዘኛ
ሆሄያት ሸረኛ
ሆነዉ አበሩብኝ

ፊደልን አስማምቶ
ሀሳብ አቀናጅቶ

ሆሄያት ሰድሮ
ሀሳብ አቀናጅቶ
ቀለማት መጥኖ
ካንተ አወዳድሮ.........

ቤት መምቻ ቤትመድፊያ
ቁጥብ ቅኔ ልፊያ
ሚስጥር ማካፈያ
ብዬ ያመንኩት ግጥም
ላንተ ሲሆን ጊዜ............

ሁሉም አሽቃበጡ
የማያዉቁኝ መስለዉ እርቃኔን ገለጡ

ግን ባክህ አዘጋጅ
መድረኩም አይፍረስ
ተደራሲዉ ይፍሰስ
አንተም አትቅርብኝ
ግጥሙም ያብርብኝ
ብዕሬም ይንጠፍጠፍ
የምለዉን ልጣ ከዛ ሁሉ መሀል
ፊቴም ቅልት ይበል ድምብርብሬ ይዉጣ

ያኔ ይገባሀል.............

ብዕሬም ቃላቴም
ቤት መምቻ ቤት መድፊያ
ቀለም ምጥን ምቴም
አንተ እንደነበርከኝ

ግጥሜ ሙዚቃ ነዉ
ከልቤ ሲመታ አንተ ጨፍርበት
እስክስታና ሬጌ ሂፓፕ ዉረድበት።

አንደበቴ ከድቶኝ ልሳኔ ቢዘጋም
ፊቴን አይተህ እወቀዉ ፍቅር ቤት አይመታም

ፍቅር ቤት አይደፋም
ቃላት አይፈልግም
ቀለምም አያሻም
ቅኔ ምስጢር ይሉት ከሱ አይስማማም።

ፍቅር ቤት አልባ ነዉ ተቀባይ አያሻም
ታዳሚ አይፈልግም
መድረክም አያዉቅም
ፍቅር መንገደኛ
ግጥምን አይደለ በቤት ተወስኖ ለአፍታም አይተኛ።

ጠፋባት ይላሉ ታዳሚያን ሁሉ
ሁሉም ሰዉ ይንጫጫል
መድረክ አዘጋጁም ከመድረክ እንድወርድ ባይኑ ይጣቀሳል
ትግስት ያጣዉ ወጣት በድፍረት ያፏጫል።

እኔ እኮ አልጨረስኩም እንዴት ብዬ ልዉረድ
አይንህን ከአይኔ ለአፍታም ሳላወርድ
ስገጥምልህ ነበር
አንዱ ክንዴን ጨምቆ ባያስወጣኝ ከበር።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
432 viewsAbela, 03:30
Open / Comment
2021-10-12 02:51:35
የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች
OPEN
70 viewsErmi , 23:51
Open / Comment
2021-10-12 02:49:06
እንደስሙ ሽንት አስጨራሽ
የዚህን ቻናል ኮሜንቶች አንብበህ ሽንትህ ካላመለጠህ እመነኝ አለም ላይ ጀግና አንተ ብቻ ነህ

አልሸናም ካልክ Join ብለህ ሞክረው
26 viewsErmi , 23:49
Open / Comment