Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 128.65K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 225

2021-10-03 13:58:56 •••☆《ኑረናል እንዴ》☆•••
ሚኪያስ እንዳለው
@mikiendialem


መርዶ ባናስነግር ሙሾ ባናወጣም በገዛ ራሳችን፤
እንደ እውር ቢያረገን ባይነዛ ፍሬው ድካም እትብታችን፤
ግና መጠየቅ አይጎዳ ከሽሽት ለራቀው ለኔ፤
በላዬ ላይ ቢጠምቅብኝ ፍርኸት ላጠቃው ወኔ፤
የመጠየቄን እውነት በመልስሽ ድጎ ብፍልግ፤
ለውሳኔዬ ረቂቅ መጠየቅ ከሆነ ፈለግ፤
እንጂ እኛ ኑረናል ብዬ መልስ ማሰስ ልፋቴ እንዲሆነኝ፤
ተራው ደርሶ ለኔ እናም እስክጠየቅ ላሁን ጠያቂ ነኝ።

ምነው ኑሮ ማለት?
ሞትን መፍራት!
ወይስ ከተፈጥሮ ጋር መጋባት፤
ብቻ መመለስ እንደ ህልም ሲያልሙት የሚያድር፤
በህልም እልም አለም ገብቶ የሚሰወር፤
በአንድ ቃና ፍቺ የማይደረደር፤
የአንዱ ህይወት ሰሙ
ለሌላው እንደወርቅ በላዩ ላይ ሚያምር፤
"ሁሉም በአካሄዱ ትርጉም ይሰጡታል
በዝብርቅርቅ አለም አንድ ከየት ይመጣል"
ንጹህ ያልናት አለም በሌላው ውሎ አዳር ቆሻሻ ይላታል።
ላንግባባ ከንቱ ልዩነቱ ነግሶ በላያችን ሲነድ፤
አንድነቱ ጠፍቶ የመተሳሰሪያው
ቃሉ ከአንደበት ፈርቶ እንደጉድ ሲርድ፤
መጠየቁ አይከፋም ለመስማት አንዳንዴ፤
ምላሹ ካላችሁ ግን ኑረናል እንዴ!።


19-06-2013

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsAbela, 10:58
Open / Comment
2021-10-03 09:34:08 ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!! (ርዕስ ነው!!)

"ቦታችን በተለመደው ሰዓት እጠብቅሃለሁ:: አፈቅርሃለሁ!" የሚል መልዕክት ነው እንዲህ ያስቦረቀኝ!!

እሱ ጏዳ ቁርስ እያበሰለ የሚያማስለው የመጥበሻ ድምፅ ይሰማኛል:: ስልኩ መልእክት ሲቀበል ድምፅ አሰማ ያለወትሮዬ እጅ ጥሎኝ ስልኩን አነሳሁት::

አንደኛ የራሳቸው ቦታ አላቸው! እኔና እሱ የኛ የምንለው ቦታ ኖሮን አያውቅም!! ከቤታችን ውጪ

ሁለተኛ የተለመደ ሰዓት አላቸው:: እኔና እሱ ለምንም የተለመደም የተመደበም ሰዓት የለንም:: የልደት ቀኖቻችንን እንኳን እረስተነው አልፎ ... 'ለካ ትላንት ነበር' የምንባባልበት ጊዜ አለ::

ሶስተኛና ዋነኛው ታፈቅረዋለች::

ይሄ ሲሰላ ቀመሩ እሱም ከኔ በላይ ያፈቅራታል ማለት ነው!

ደስ ሲል .....

"ምን ተገኘ?" ይለኛል አስሬ የሰራልኝን ቁርስ እያጎረሰኝ

"ምነው?"

"በጣም ደስ ብሎሻል! ይሄን ፈገግታ ካየሁት የማላስታውሰውን ያህል የጊዜ ርዝመት ያህል ዘመን ሆኖ ነበርኮ!" አለኝ የተለመደ የተመጠነ ፈገግታውን እየፈገገ... ዝም አልኩ

እያመነዘርክብኝ እንደሆነ ሳውቅ ነው ደስ ያለኝ! ይባላል? አይባልማ!!
.
.
.
ሊወጣ ይለባብስ ጀመር::

"እሱን ሸሚዝ ቀይረው:: ቅዳሜ አይደል? ፈካ ያለ ነገር ልበስ.. ቆይ እኔ ልምረጥልህ!" ብዬው ቄንጠኛ ሸሚዝ እፈልግ ጀመር ... ተዝረክርኮ ሄዶ የባሌ አፍቃሪ ፍቅሯ እንዲቀንስ አልፈልግማ! ተውቦ ነው መሄድ ያለበት!!

አንዴ ፀጉሩን አንዴ ጫማውን ... ደሞ ኮሌታውን ሳስተካክልለት ግራ ተጋብቶ ያየኛል::

"ዛሬ በጣም ጥሩ ሙድ ላይ ነሽ!" ብሎኝ ከንፈሬን ስሞኝ ወጣ!!

ልፀልይ ሁሉ ቃጣኝ:: ግን እንዲህ ያለው ፀሎት ለእግዜር ነው ለሰይጣን የሚቀርበው?

"በምንዝርናው እንዲፀና አድርግልኝ! ደግሞ ደጋግሞ እንዲያመነዝር እርዳው!! "

እንዲህ ያለው ድርጊት አምላክን አይመለከትም! ለዲያቢሎስ የትብብር ውይም የድጋፍ ጥያቄ ላቅርብ? ያው እኔ ባልጠይቀውም ወጥሮ ማስመንዘር መደበኛ ስራው ነው ብዬ ነው::

የአስር ዓመት ትዳሬ ነውኮ..... የመጀመሪያው ትሁን? እንዳገባ ታውቅ ይሆን? ሄዶ ሲስማት የኔን ከንፈር ልቅላቂ እንደምትስም ታውቅ ይሆን? እቤቱ ሲገባ የሚያስኮንን አፍቃሪ መሆኑን ታውቅ ይሆን? ዛሬም ከ10 ዓመት በኃላ እያጎረሰኝ እንደምበላ ታውቅ ይሆን? ወይስ እሷምጋ ዝንፍ የማይል አስኮናኝ አፍቃሪ ይሆን?

"ውሎህ እንዴት ነበር?"

"ፍቅሬ ለ2 ሰዓት ብቻ ነውኮ የተለያየነው?" አለኝ ከሷጋ እንደመጣ

"እኮ ቢሆንስ "

" እሺ ቆንጆ ነበር!" አለኝ መገረም ሳይለየው

ተጣልተው ይሆን? ተጨቃጭቀው? ለምንድነው የተለየ ፊት የማያሳየው? ምን አይነቷ ናት? ለሁለት ሰዓት እያገኘችው እንዲስቅ ማድረግ ያቅታታል? ወይስ እሷም እንደኔ መፈቀር ደከማት?

ባጠገቡ ሳልፍ መቀመጫዬን ደለቅ አደረገኝ!! እህህህ በቀን ሁለት እሙሙ አይሰለቸውም? ወይስ እሷ አትሰጠውም? እሷ እንደእኔ ሚስት ስላልሆነች ግዴታ የለባትም ይሆን? ወይም እንደኔ በገዛ ሀጢያቷ ስላልታሰረች ካልመሰላት ታፆመዋለች?

እኔ ሳገባው ቄሱ በመከራውም በደስታውም ... በድህነቱም በሀብቱም ... ብለው ያስማሉኝ እንጂ መሳቢያው ውስጥ እንደሚያስቀምጠው ገንዘብ በፈለገ ጊዜ እየከፈተ የሚዘግነው ንብረት እንዲሆን እሙሙዬን ማስያዜን አላስታውስም! (መሀላው የማላውቀው ውስጠ ወይራ ይኖረው ይሆን? ታዲያ የሚስትነት ግዴታዬ እንደሆነ የማስበው ማን ምን ብሎኝ ነው? ዛሬ ይለፈኝ ካልኩት የበደልኩት የሚመስለኝ በየትኛው ህግ ነው?

አንድ ቀን .... ርቆ እንደህልም በሚታወሰኝ አንድ ቀን በሰራሁት በደል .... ራሴን በእዳ አስይዣለሁ!!

"ሁለተኛ ቂጤን እንዳትነካኝ!" አልኩት ኮስተር ብዬ

"እንዴ? ለምን?"

"የራሴው ቂጥ አይደል?"

"አዎ"

"እንደገና ደግሞ የራሴው ሰውነት ላይ አይደል ያለው? ራሴው አይደል የተሸከምኩት?"

"እንዴ ፍቅር ምን ሆነሻል?"

"ሌላ ደግሞ አንዳንድ አንዳንድ ጊዜ ተሸከምልኝ ብዬ አላስቸገርኩህም አይደል? ደሞም ቂጤን በማጣፍት የሚመለስ የተበደርኩት ብድርም የለብኝምኣ?"

"ምንድነው ጉዱ?"

"በነዚህ ከተስማማን በገዛ ቂጤ የማዘው እራሴው ነኝ! ደስ ባለህ ሰዓት እጅህን እየላክ በጥፊ እንድታላጋው አልፈቅድም!! አበቃሁ!!" ብዬው ማሳረጊያ የተለመደ ፈገግታ ፈገግ ብዬ ሄድኩ::

ይቀጥል ይሆናል!!

#Meri feleke

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K viewsAbela, 06:34
Open / Comment
2021-10-03 06:28:37 "ደመ ቀዝቃዛ ነኝ ጅንን ኩራተኛ
ቤተኛ ቢለወጥ ቢጠፋ ጓደኛ
እንኳን ሊናፍቁኝ ላስብ ይቅርና
ፈጠን ብለው ይምጡ መረሳት አለና!"
በማለት ራሴን እንዳላኮፈስኩት
በትቢት ማማ ላይ ከጫፍ እንዳልካብኩት
ሳምንት ብጠፊብኝ ከቦታው አጣሁት!
ወጤ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
766 viewsAbela, 03:28
Open / Comment
2021-10-02 19:23:01 ምኞት፥ ስለ ለመጪው አሮጌ ዐመት

አዲስ ሆኖ ይምጣ፤ መጪው አሮጌ ዐመት
ሰው በውድ ይገመት
እህልና ሲሳይ በርካሽ ይሸመት።
በጦም በፍስክም፥ ዱላ ለምንጠግብ
ጨቅላ ልጅ አስርበን፥ ጆፌ ለምንመግብ
ሰላም ይለግሰን
ከለታት አንድ ቀን ፥ የሰው ወግ ይድረሰን::
ያርሶ በሌ ልጆች
በእንግዳ ሰው እጆች
ሳናረጅ ከመጦር፥
ይሰውረን ከጦር
-ያስጥለን ከበቀል
እንደ ድንኳን ችካል
አመሻሽ ተተክሎ ፤ ጠዋት ከመነቀል ::
በእልህ ምትክ መላ
ልባችንን ይሙላ ::
ጉልበቱን ለሚያመልክ ፤ ጉልበቱን ያቅልጠው
ለደግ ሰው አክሊል
ለክፉ ልብ ይሰጠው::
ይፍለቅ ከየመስኩ
የርህራሄና የማስተዋል ጠበል
ቃል ምግባር ይወልዳል ፤ አሜን! ይሁን እንበል!

​​ከበእውቀቱ ስዩም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.6K viewsAbela, 16:23
Open / Comment
2021-10-01 21:00:20 ​​የሚከተለው ግጥም ከታች በሚታየው ታሪካዊ ፎቶግራፍ ንሸጣ የተፃፈ ነው፤በፎቶው ላይ ሻምበል አበበ ቢቂላ የልምምድ ሩጫ ሲሮጥ ይታያል፤ ከሁዋላው አህያ እየነዳ የሚያልፍ አላፊ ጠፊ ገበሬ አለ፤ ግጥሙን የጣፍኩት ለዚህ አህያ ነጂ ገበሬ ነው፤ )
ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ
(በእውቀቱ ስዩም)
ባሮጌው ጎዳና፤ በጮርቃው ማለዳ
ጋልቦ እንዳልደከመ፤ እንደ ጥቁር ፈርዳ
አቤ እየሠገረ
ከኋላው የሚሳብ፤ አህያ እየነዳ
ስሙ ማን ነበረ?
የመንደር ወፍጮ ቤት፤ ቅሪቱን ሲተፋ
ዱቄት የሚለብሰው
በዝነኞች ፊት ላይ፤ ካሜራ ሲያካፋ
ጠብታ ሚደርሰው
ማን ይሆን ይሄ ሰው?
እኛ የምናዘው፤ እሱ የሚሰማን
ሰው እያደረገን፤ ከሰው የማንቆጥረው
አህያ እየነዳ፤ አስፋልቱን ሲሻማን
የምንገፈትረው፤
በጥሩምባ እሩምታ፤ ምናስደነብረው፤
በኑሮው ምንቀልድ፤ በሞቱ ምንተርት
በፈረሰ ጎጆው፤ ፓርቲ ምንመሠርት፤
ፊቱ ቢልቦርድ ላይ፤ ወጥቶ ባይሰጣ
ጀግና የማይባል
ግና ለጀግኖቹ፤ ጉልበት የሚያዋጣ፡፡
ካበበ ሰሀን ላይ፤ በሶው እንዳይጠፋ
በተራ ክንዶቹ፤ ተራራ ሚገፋ
ለናቀችው ዓለም፤ ላቡን የገበረ
ስሙ ማን ነበረ?

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.6K viewsBewketu, 18:00
Open / Comment
2021-10-01 19:24:04 ​​የመፅሐፍ አጭር ዳሰሳ

ለውጥ

የመፅሐፉ ጭብጥ የለውጥ ሁሉ መሠረቱ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ብሎ እንደሚያስቀምጥ እገምታለሁ። ለዚያም ትኩረት አድርጎ መሠረታዊ የለውጥ ምሶሶዎችን በተለየ አቀራረብ ይተርካል።
እኛ ሰዎች ለመለወጥ ስናስብ እና እርምጃ ስንጀምርም ከምንም በፊት ነባር አሉታዊና ጎታች አስተሳሰቦችን በመተው በተቃና አስተሳሰብ መቃኘት እንዳለብን አመክሮ ይተነትናል።

በመፅሃፉ በምናብ ስለምናስባቸው አንድ ልሂቅ ስብዕና ይተርካል። የግለሰቡ ስብዕና ጣዕም ምስጢሮቹም በየምዕራፉ ተወስተዋል። ሕይወትን እንዴት እንደረዱት? ፣ የእስልምና እና ንባብን ወዳጅነት ፣ ተደራሲያንስ እንዴት ከእዚህ ግሩም ስብዕና ጋር መቆራኘት እንደሚችሉ ይተርካል።

መፅሐፉ ሲጀምር ትልቁን መሠረት የሚጥለው በኡስታዝ ሉቅማን ስብዕና ላይ ነው። እንዲሁም ከእርሳቸው ጋር ስላሉት ተማሪዎቻቸው እና ስለወሰዱት መሠረታዊ የህይወት መርሆዎች ያስቀምጣል።

ስለ ዕውቀት ፣ስለ አእምሮ አቅም ፣ ስለ ፍቅርና ተስፋ በኡስታዝ ሉቅማን መካሪነት ይቀሰማል።ሉቅማን ከመሠረቱም በእድሜ የገዘፉ በእውቀት የደረጁ በመሆናቸው ከእርሳቸው ብዙ እውቀቶችን ያገኛሉ።

እንዲሁም ስለቤተመፅሐፍት ፣ ንባብና ጥቅም ፣ የተለያዩ የንባብ ፕሮጀክቶችን በሚተገበር እና በተለየ መንገድ ያቀርባል። አክሎም በማሕበረሰቡ ውስጥ ለውጥ እንዴት እንደሚመጣ ብዙ ሐሳቦችን ይጠቁማል።

መፅሐፉ በልብወለድ መልኩ ቢቀርብም በገሃዱ ዓለም ለመሳል ጥረት እንድናደርግ የሚለፋ በርካታ እውነታዎችን ስሎ ያስቀምጣል።

ከመፅሐፉ ገፆች ውስጥ...

«የአካልን ምቾት ሊያስጠብቅ የሚማስነው የዘመናችን ስልጣኔ በመንፈሳዊነት ረሃብ ወድቆ መማቀቁ እሙን ነው ። በመጨረሻም ሊያረካው የሚለፋለትን አካሉን ከምድረ-ገፅ ሲያጠፋ ይስተዋላል። ከመንፈሳዊነት የተራቆተ ቁሳዊ ስልጣኔ ብቻውን ለሰው ልጅ ተስማሚ አይደለምና»
▯ለውጥ ▯

▯▯ኡስታዝ ኢንጂነር በድሩ ሁሴን ▯▯

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.0K viewsBewketu, 16:24
Open / Comment
2021-10-01 18:09:16 . ተስፋ.

እንደምን አመሻችው! እኔ ደህና ነኝ ክብሩ ይስፋ። ዛሬ ከወትሮው ወጣ ባለ መልኩ ስለ ተስፋ ላወራችው ፈለኩ። ይህንን ላወራችሁ የፈለኩበት ምክንያት ግሩፑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀዛቀዘ እንደመጣ እና ራሴ እፅፍላችው የነበሩትን ልብወለዶች ሳልጨርስላችው እየተቋረጡ እና እየቆሙ እንደሆነ ከብዙዎቻችው ቅሬታ እየሰማው ስለሆነ ነው። እውነት ነው ራሴ እየፃፍኩ አቀርብላችው የነበሩትን ልብወለዶች መቀጠል አልቻልኩም።

በህይወታችን ውስጥ በሚያጋጥሙን የተለያዩ ክስተቶች ምክንያት ሰላማችንን እንነጠቃለን አይደል ያው እኔም አንዳንዴ በሚያጋጥሙኝ ችግሮች ምክንያት የውስጥ ሰላሜን አጣለው እኔም ሰው ነኝና የሚያስጨንቁኝ የሚያሳስቡኝ ነገሮች ይኖራሉ። ለሰው መትረፍ የሚቻለው መጀመሪያ ራስን መግዛት ስንችል እንደሆነ አምናለው። 2013 ለኔ ትንሽ አስቸጋሪ አመት ነበረች በግል ህይወቴ ትንሽ ችግር አጋጥሞኝ ነበር። የጀመርኳቸውን መፅሃፎች እንኳን መጨረስ አልቻልኩም ነበር ያው ለናንተም አጫጭር ፅሁፎችን አልፎ አልፎ ሳቀርብ ነበር። ያው ከራስ ጋር ሳይሆኑ መፅሃፍ መፃፍ ቀላል አይደለም።
በባህሪዬ ስለግል ህይወቴ ማውራት አልወድም ግን አንዳንድ የእናንተም ቅሬታ ሲበዛ ያለሁበትን ሁኔታ በትንሹም ቢሆን ላስረዳችው ብዬ ነው።

የሰው ልጅ ደካማ ሆኖ ሳለ ያለው ትልቁ ሃብት እምነት እና ተስፋ ነው። እኔም በደካማ አቅሜ የምችለውን አድርጌ የቀረውን ለፈጣሪ ትቼ ነገሮች እንደሚስተካከሉ መልካም እንደሚሆኑ በፈጣሪዬ አምናለው ተስፋ አደርጋለው። በቅርቡ ወደበፊት አቋም ተመልሼ ሁሉንም እንደበፊቱ አስተካክለን እንደምንቀትል የተጀመሩትንም እንደምንጨርሰው ተስፋ አደርጋለው።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.0K viewsAbela, edited  15:09
Open / Comment
2021-10-01 12:05:46 መስኮት ቀዶ ገባ፣
ንፋስና ውርጩ፤
ለንጋት አዜሙ፣
ወፎቹ ተንጫጩ፡፡
ተነፋፍቀው የኖሩ፣
ተኳርፈው ያደሩ፤
ለወፎቹ ዜማ፣ ግጥም ያወርዳሉ፤
ለቀዘቀዘ ልብ፣ ሙቀት ይረጫሉ፤
ይተቃቀፋሉ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
.
ከጎረቤት ደጃፍ፣ቡና ይወቀጣል፤
‹‹ቡና ጠጡ›› እያለ፣
እንደመወርወሪያ፣
በመንደሩ መሀል፣ህጻን ልጅ ይሮጣል፡፡
እሱን ተከትለው፤
የመንደሩ ሴቶች፣
ሀሜት አንጠልጥለው፤
ይሽቀዳደማሉ፤
ለነጋው አዲስ ቀን
ንድፍ ያስቀምጣሉ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
.
ደግሞ ቀኑ ጋመ፣ . . . .
አዳሜ ተነሳ፣
ከትናንት ገንፍሎ፣
እንደልሙጥ ሽሮ፣
መግላሊቱን ጥሎ፤
ተስፋ አንጠልጥሎ፤
ሊረግም - ሊመርቅ
ሊጥል ወይ ሊወድቅ፤
ሊያለቅስ ወይም ሊስቅ፤
በናፍቆት - ሊተያይ፤
ተጣልቶ - ሊለያይ፣ . . . .
አሮጌ ትላንቱን፣ ጎጆው እየጣለ፤
አዲስ ቀኑን ሊያትም፣ አደባባይ ዋለ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
.
ደግሞ አመሻሽ ላይ፣ . . . .
ተራራው አናት ላይ፣
ሰአሊው ተፈጥሮ፣
አድማስን ወጥሮ፣
ቀለማት ደርድሮ፤
አንዳንዴ በተስፋ፣
ቢጫ እያበዛ፣ ቀይ እያሳነሰ፤
አንዳንዴ በምሬት፣
ቀዩን እያበዛ፣ ቢጫ እየቀነሰ፤
ተቅላሎት ሲሸምን፣ ፍም እያባዘተ፣
የደከመውን ቀን፣ አባብሎ ሲያስተኛ፣ ውበት እየጋተ፡፡
ደግሞ መለስ ብሎ፣
በልቤ የያዝኩትን፣ ማጣት አስተውሎ፣
በረዥም ቡሩሹ፣ ካድማስ ወዲያ በኩል፣ ጨለማን አጥቅሶ፤
ከሰል ሲያስመስለው፣ ሲሰራ ያዋለውን፣ ሲያፈርሰው መልሶ፤
ለጥበብ ምትሀት፣ ልባቸው የገበረ፤
ሰዎች ተሰብስበው፣ ያደንቁ ነበረ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
.
አንቺ የለሽበትም፡፡
አላገኘሁሽም፡፡
ቢሆንም አውቃለሁ፣ . . .
የለሽም አልልም እፈልግሻለሁ፡፡

ዶ/ር በድሉ ዋቅጂራ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.9K viewsAbela, edited  09:05
Open / Comment
2021-09-30 22:53:53
TWS BLUETOOTH HEADSEAT
Earphone + power bank
authomatic pairing
waterproof
3500mah charging box
LED digitar power display
portable phone charger
comfortable and easy te wear and painless
8 hours chaging per weak of workout
ባለ ሁለት ጆሮ ኤርፎን እንዲሁም
ሞባይል እና ሌሎች electronics ነክ ነገሮችን ቻረጅ ማድርግ የሚያስችል power bank ያለው
ለ አጠቃቀም ምቹ የሆነ እና ጆሮ ውስጥ ብቻ የሚቀመጥ ለ እይታ የማትጋለጥ small sized ነው በተጨማሪም 100% waterproof ነው
ተንቀሳቃሽ የሞባይል charger ያለው
የ ኤርፎኖቹን እንዲሁም የ mobile charging ፐርሰንት(በቁጥር) የሚያሳይ LED display የተገጠመለት
Free Delivery Available
1400 birr
Contact- 0911468394
@abela1987
5.0K viewsAbela, 19:53
Open / Comment
2021-09-30 20:18:21 ​​ሳጥናኤል ቀፈፈው

የመለእክት አለቃ ሳጥናኤል ሲባረር ፥
ሰው የመሆን ፈቃድ እምላክ ሰጥቶት ነበር ፥
ሳጥናኤል ግን ከፋው ፥
ሰው መሆን ቀፈፈው ፥
ጌታን ተማፀነ ፥
ሰው አንዳያደርገው አልቅሶ ለመነ ።

ከመንበሩ ቀርቦ ሞገተ ፈጣሪን ፥
ከፍጥረትህ ሁሉ ሰው በጣም ይከፈል ፤
ይሄንን አልችልም ሰውነት ይቀፋል ፤
ሞቶስ መቼ ያርፋል ?
የሃጥያቱ ዘር ዘመን ይሻገራል ፤
ፍጹም አይማርም አዳኙን ይክዳል ፣
ስሞ ይሸጠዋል ፣ ሰቅሎ ይገድለዋል ፤
ጥበብ አጥሮት እንጂ ሰይጣንን ያስንቃል ።

እባክህ አምላኬ ፥ እኔም ፍጥረትህ ነኝ ፥
ሃጥያቴ በዝቶ ምን ብዳፈርህም ፥
ሰው የመሆን ቅጣት አትጥልብኝም ፥
ብሎ ተቀመጠ ሳጥናኤል ቆረጠ ፥
ሰው መሆንን ጠልቶ ሰይጣንን መረጠ ።

ያሬድ ዘ. ካህን
መሰከረም -12 / 2014

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.8K viewsBewketu, 17:18
Open / Comment