Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 128.65K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 223

2021-10-06 11:32:32
2.5K viewsAbela, 08:32
Open / Comment
2021-10-06 09:58:26 የብብቷ ነገር

''የቆጡን አወርደዉ ብላ የብብቷን ጣለች''
ይላል የሀገሬ ሰዉ

እኔን የገረመኝ ይልቅ ያሳሰበኝ
በብብቷ መሀል ምን ነበረ ያለዉ

ምናልባት የማይጠቅም ነገር
ቢኖርም ቢጠፋም እርባን ያጣ ነገር።

እሱን አስባ ይሁን የቆጡን የሻተች
እድሏን ልትሞክር እጇን የሰደደች

ቆጡ ላይ ምን ነበር
የብብቷስ ነገር

አንዳንዴ ሳስበዉ
በብብቷ ያለዉ
ሸክሙ በዝቶባት
እጇን አዝሎባት

ታርፍበት ጥግ አጥታ
ትለቀዉ ዘንድ ሰበብ ሽታ

ጭንቀት ፍርሀቷን ችግሯን አምቃ
ድካም ዝለት ቁስሏን ከሰዎች ደብቃ

ድንገቴ ከቆጡ አንድ ነገር ብታይ
ለቀቀችዉ መሰል የብብቷን ስቃይ።

ታዲያ አሁን እቺ ሴት ጥፋቷ ምንድን ነዉ
ቆጡ አይሻልም ወይ አንዳችም ባይኖረዉ

ስለዉ የሀገሬን ሰዉ እሱ መልስ መች ያጣል
ከማያዉቁት መልአክ የሚያዉቁት ሰይጣን ብሎ ይተርታል
ደሞ ቤቱ ዘመን ሴጣን ተሽሎ ያዉቃል።

ተዋት የብብቷን እሷ ታዉቀዋለች
ይልቅ ከቆጡ ላይ ምን ነበረ ያየች።

ተፃፈ በትዝታ ወልዴ

@TIZITA21

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
765 viewsAbela, 06:58
Open / Comment
2021-10-06 08:28:23 •••☆《እነ አድር ባይ ቤቱ》☆•••

ሚኪያስ እንዳለው
@mikiendialem


እጣረሰው ትዕዛዝ
አሻፈረኝ ስለው ጌታው ቁጣ አስነሳ፤
ጭራሽ ዱላ አንስቶ
እኔን ሊደበድብ በንዴት አገሳ፤

.
ይቅርታ ይቅርታ
መማፀን አበዛሁ፤
እሱን ጌታ አክብሬ
ሎሌነትን ገዛሁ፤
ድል መንሳቱ ህልሜን
በሽንፈት ነሳው፤

.
ሲፈጠር ከሀረጉ
ለገዢነት ብቻ የተፈጠረ አለ፤
እንደኔ አይነት ደሞ
ከቅባቱ ስለ'ት ሎሌ የሆነ አለ፤
ብቻ በየፊናው
ጀብደኛ እና አሽቃባጭ ፈር እየጠረገ፤
እድሜውን ይኖራል
ለሌላው አሲይዞ ጥግ እየፈለገ፤

.
መረታት ተፅፎ
ለሞቀለት ሁሉ የሚያሸረግደው፤
ለይምሰሉ ውጦት
ሰው መሆኑን ካደው።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
480 viewsAbela, 05:28
Open / Comment
2021-10-05 23:15:51 ምርጥ የግጥም ቻናል
389 viewsAbela, 20:15
Open / Comment
2021-10-05 18:21:15 ና የሚሰማኝን ብታውቂው? እኔኮ በዓይኔ ነው ያየሁሽ። የምጠይቅሽ ጥያቄ አልነበረኝም። ራስሽን ይቅር ያላልሽው አንቺ ነሽ። እኔ ገና ድሮ ይቅር ብዬሽ አልፌዋለሁ።"

"ምን ያህል ጊዜያችሁ ነው?"

"ካወቅኳት?" በጭንቅላቴ ንቅናቄ 'አዎ' አልኩት

"ከተዋወቅን ስድስት ወር ገደማ። .......ስለፍቅር ማውራት ከጀመርን አንድ ወር .......ከሳምኳት ሁለት ሳምንት ......." ከዛስ የሚለውን አይኔን አፍጥጬ እጠብቀዋለሁ።

"አድርገን አናውቅም። ታምኚኛለሽ?"
'አዎን' አልኩት በጭንቅላቴ ንቅናቄ:: ..... ዝም ተባባልን!! ..... ወርጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ:: .... ምን እያሰበ እንደሆነ ልጠይቀው እፈልጋለሁ:: ግን ከአፌ አይወጣልኝም:: አቅፎ ትከሻው ላይ አስደገፈኝ:: ዝም ተባብለን ብዙ ከቆየን በኃላ ... .... አቅጣጫውን ቀይሮ ከፊቴ ተቀመጠ:: በጣቶቹ አገጬን ደግፎ ቀና አድርጎኝ አይኖቹን አይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ

"ፍቅሬ እኔ ስላበድኩልሽ ያላንቺ ፍላጎት የራሴ አድርጌ ላቆይሽ እንደማልችል አውቃለሁ:: ምንድነው የምትፈልጊው? መለያየት ከሆነ የምትፈልጊው am ready now. ቢከብደኝም ልለቅሽ ዝግጁ ነኝ!! ምንድነው የምትፈልጊው? እንደገና መሞከር ነው የምትፈልጊው? Am ready ... አሁን ግን እኔን ወይም ቤተሰብሽን ሳይሆን ራስሽን ሰምተሽ ራስሽ ወስኚ .. .... የፈለግሽውን ጊዜ ያህል ውሰጂ የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ የለብኝም::" አለኝ

"እሷስ?" (ኤጭ ዛሬ ምንድነው ችግሬ የማስበውን የማወራው?)

"(ሳቅ አለ) እሷ ስላንቺ ታውቃለች ጣጣዬን እስክጨርስ ላለመገናኘት ተስማምተናል::"

"ለመወሰን ብዙ ጊዜ ቢፈጅብኝስ?"

"10 ዓመት ጠብቄሽ የለ? እጠብቅሻለሁ::" አለኝ:: ከጀርባዬ መጥቶ እግሮቹ መሃከል አድርጎኝ ካቀፈኝ በኃላ "ያ የሚያስጠላሽንም ነገር አናደርግም (ድክም ብሎ እየሳቀ) ሆ ሰው ፍሰሃ ያስጠላዋል? (ቡፍ ካለ በኃላ) ራስሽ ፈልገሽ ያውም 'እባክህ ፍቅሬ' ካላልሽኝ አናደርግም" ብሎኝ እጁን በቱታዬ ስር ሰዶ ወገቤን አቀፈኝ::

ይሄ ሰውዬ ዛሬውኑ እባክህ ሊያስብለኝ ነው እንዴ?

#Meri feleke

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.8K viewsAbela, 15:21
Open / Comment
2021-10-05 18:20:06 ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የመጨረሻ ክፍል ሊሆን የሚችል)

"እናውራ? ማውራት አለብን!" አለኝ አምስት ለሊቶች ሳይነካካኝ አቅፎኝ ካደረ በኋላ። አምስት ጠዋቶች ከንፈሬን ሳይስመኝ ደህና ዋዪ ካለኝ በኋላ:: አምስት አመሻሾች ደረቱ ላይ አቅፎ ግንባሬን ሳይስመኝ እንዴት ዋልሽ ካለኝ በኋላ....

"Finally" አልኩኝ ይህን እንዲለኝ ስጠብቅ እንደነበር በደንብ እያሳበቅኩ

"እንዴ? እንድናወራ እየጠበቅሽ ነበር? ማውራት ፈልገሽ ከነበር ለምን እናውራ አላልሽኝም?" ዝም አልኩ። እንዲህ ነኝ! ራሴን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝ የማውቀው ከእናቴ ጋር ስሆን ብቻ ነው። እንዲህ ሲለኝ እንዲህ ብዬው በነበር የምለው ካለፈ በኋላ ነው። እንዲህ ማለት ነበረብኝ የምለው አለማለቴ መዘዝ ከመዘዘ በኋላ ነው። በተለይ ስናደድና ስከፋ ሰዎች የልባቸውን ብለውኝ ከሄዱ በኃላ ነው .... በራሴ ብስጭት እያልኩ 'እንዲህ ባልኩ ኖሮ' የምለው..

"ይሄ እኮ ነው ችግርሽ ምንም ሳታወሪ እንዳዳምጥሽ ትፈልጊያለሽ። ምንም ሳትጠይቂኝ መልስ ትጠብቂያለሽ። ለግምት እንኳን የራቀ ስሜት እያሳየሽኝ በልብሽ ያመቅሽውን ስሜት እንድረዳሽ ትጠብቂያለሽ::" እንዲህ ድምፁን ጮክ አድርጎ አውርቶ አያውቅም። መናደድ ይችላል ለካ! አሁንም ዝም አልኩ። በረዥሙ ተነፈሰ እና ደግሞ በራሱ ድምፅ ማውራት ጀመረ።

"እ የምነግርሽ ነገር አለ ......" እያለ እንዴት እንደሚነግረኝ ይታሽ ጀመር።

'አውቃለሁ' ልለው አስባለሁ ግን አፌ አያወጣውም። ሊነግረኝ ሲጨነቅ አየዋለሁ። እንደማውቅ ልነግረው እጨነቃለሁ። በመጨረሻ ከአፉ የወጣው ሊናገር የፈለገው እንዳልሆነ በሚያስታውቅ ሁኔታ 'ቆይ ሌላው ይቆይና ...' የሚል ለዛ ባለው ድምፅ

"ወደሽኝ ታውቂያለሽ ግን? በፍቅር? " አለኝ።

ደነገጥኩ። ምንድነው ያስደነገጠኝ? እንለያይ ወይም ከሌላ ሴትጋ ግንኙነት አለኝ እንዲለኝ ስጠብቅ ወድጄው እንደነበር ስለጠየቀኝ? ዝም አልኩ። አሁን ግን ያለመናገር አባዜዬ ሳይሆን መልሱን ስለማላውቀው ነው። ወድጄው የማውቅበትን ጊዜ ለማስታወስ ወደኋላ ተጓዝኩ። እሩቅቅቅቅቅቅ ነው።

"ይመስለኛል!" የሚል ቃል ነው ከአፌ የወጣው።

አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ። መሬት መሬቱን እያየሁ እንባው መሬቱ ላይ ጠብ ሲል አየሁት። ለማረጋገጥ ቀና አልኩ። በአስር አመት ውስጥ እህቱ የሞተች ጊዜ ካልሆነ ሲያለቅስ አይቼው አላውቅም። ዘልዬ ላቅፈው ፈልግያለሁ። እንባው መሬቱ ላይ ከመድረሱ በፊት በጣቶቼ ከጉንጩ ላይ ልጠርግለት። አታልቅስ ብዬ ልለምነውም እፈልጋለሁ። ከአፌ አይወጣልኝም። አስለቃሽዋ ራሴ ሆኜ ማባበል ትርጉም የሚሰጥ ነገርም አልመስል አለኝ። ለሰራሁትም ላልሰራሁትም ሀጢያት ይቅርታ ጠይቄው ለቅሶውን ላስቆመው እመኛለሁ። ውስጤ ሲታመስብኝ ይታወቀኛል።

"ስራ አልቆ መጥተህ እስክትወስደኝ በናፍቆት የምታመም የሚመስለኝ ጊዜ ነበር፣ ስትስመኝ ከመሳሳቴ መቼም የማልጠግብህ የሚመስለኝ ጊዜ ነበረ ፣ልታገባኝ ሽማግሌ የላክህ ቀን በዓለም ላይ የደስታ መጨረሻው ያ መስሎኝ ነበር ፣ መጀመሪያ ቢሮዬ መጥተህ ያየሁህ ቀን ልቤ በአፌ የምትወጣ መስሎኝ ነበር ፣ እራት ልጋብዝሽ ያልከኝ ቀን ምን ብለብስ ልትወደኝ እንደምትችል ስለብስ ሳወልቅ....... ተቀብቼ የማላውቀውን ሊፒስቲክና ኩል ስቀባ አንድ ሰአት ነበር የፈጀብኝ ፣ የሰርጋችን ቀን ማታ መቼም ከእቅፍህ እራሴን እንደማላርቅ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር ፣ ከልክ በላይ ስታቀብጠኝ በምድር እንደእኔ እድለኛ ሴት እንዳልተፈጠረች ያሰብኩባቸው ጊዜያት ብዙ ነበሩ ፣ ይሄ ሁሉ ፍቅር ከነበረ አዎ አፍቅሬህ አውቅ ነበር። ግን እውነተኛ ፍቅር ቢሆን ያልቅብኝ ነበር? ፍቅር ያልቃል?"

ራሴን ሳብራራ አገኘሁት። አውርቼ ስጨርስ ፈገግ እያለ እንደሆነ አየሁት። ከተናገርኩት ምኑ ነው ደስ የሚያሰኘው? ድንገት ተስፈንጥሮ አቀፈኝ። ግንባሬን ፀጉሬን አንገቴን እየሳመ

"ፍቅር አያልቅም! በጥላቻ ወይ በቂም ግን ይሸፈናል። " እያለኝ ደስ መሰኘቱን ቀጠለ።

ግራ ገባኝ። ምንድነው እየሆነ ያለው? አትሳቅ ተብሎ ሳቁን ለመቆጣጠር እንደሚታገል ሰው ያላለቀ ፈገግታ ፈገግ እያለ ተነስቶ መንጎራደድ ጀመረ። ዓይኖቼን አብሬ ከማንቀዥቀዥ ያለፈ ማድረግ የቻልኩት የለም።

"ጠይቂኝ እስኪ? ምንድነው እንዲህ የሚያስፈጥዝህ በይኝ? ለዛሬ እንኳን ደስታዬን ሙሉ አድርጊው! ለሚሰማኝ ስሜት ግድ አላት ልበል?" አለኝ

እያለ ያለው እንደገባኝ እርግጠኛ አይደለሁም። የቅድሙ እንባውን ከማይ ደስታውን ሙሉ የሚያደርገው የኔ መጠየቅ ከሆነ ሺህ ጊዜ ብጠይቀው ግድ አልነበረኝም።

"ምንድነው ደስ ያሰኘህ?"

"እነዚህን ቃላት ካንቺ አፍ ለመስማት ስንት ቀናት መናፈቄን ታውቂያለሽ? ፈጣሪዬን ለምኜው እንደማውቅ ታውቂያለሽ? ካንቺ አፍ የተሰማሽን ስሜት የሚገልፅ ቃል ፈልቅቆ ከማውጣት ....... "
አልጨረሰውም ቃል ጠፋው::

"ለምን አትጠይቀኝም ነበር? ዛሬ እንደጠየቅከኝ?ለምን ..."

"ለመልሱ ዝግጁ አልነበርኩም ነበር።" አለ ችኩል ብሎ!! ቀጥሎ

"ሁሌም እወድሻለሁ ስልሽ 'እኔም' ነበር መልስሽ። የዛሬ አራት ዓመት ህዳር 7 ጠዋት እወድሻለሁ ስልሽ 'እኔም' ማለቱ ሲያስምጥሽ አየሁ:: እያስጨነቅኩሽ እንደሆነ ስለገባኝ እወድሻለሁ ማለቱንም ተውኩት::"

ምን ልበለው ዝም አልኩ። ተቀምጦ ዝም አለ። እናቱ የሚወደውን ነገር ልትገዛለት ወጥታ መመለሷ እርቆበት በደስታና በጉጉት እንደሚቅበጠበጥ ህፃን እያደረገው ተቀመጠ።

"እኔኮ ግን ባትነግረኝም እንደምትወደኝ አውቃለሁ::" ብዬ ያሰብኩት ነው ያመለጠኝና ቃል ሆኖ የተናገርኩት

"(ፈገግ እንደማለት ብሎ) ቃሌን የሚተካልሽ ነገር አጊንተሽ አይደለም? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ስጦታ የገዛሽልኝ? የዛሬ ሰባት ዓመት የልደቴ ቀን...."

(ሰባት ዓመት ሙሉ ሲዘንጥ የሚያደርገውን ሰዓት እያሳየኝ:: እሱ ባለፈው ወር ጫማ ገዝቶልኝ ነበር::)

"መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ፈልገሽ የሳምሽኝ? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ባንቺ ተነሳሽነት ፍቅር የሰራ....." ቃሉን ሁላ ሳይጨርስ ተቀበልኩት

"ያስጠላኛል::" ዛሬ ምን ሆኜ ነው የማስበው የሚያመልጠኝ?

መጀመሪያ ደነገጠ:: ከዛ ከት ብሎ ሳቀ:: ከሶፋው ተነስቶ እግሬ ስር ቁጢጥ ብሎ .... እጆቹን እግሬ ላይ አድርጎ ወደ ላይ እያየኝ እየተንፈቀፈቀ ሳቀ.... ቡፍ ይላል እያረፈ....

"ምንም የሚያስቅ ነገርኮ አልተናገርኩም::"

"(ጭራሽ ከት ብሎ እየሳቀ) እንደሱ አድርገኝ ..... አዎ እሱጋ በለው ..... ብለሽኝ የነበረበት ዘመን እንደነበረ ትዝ ብሎኝ ነው::" ብሎኝ መንፈቅፈቁን ቀጠለ

"የቱጋ መቼ እንዳስጠላኝ አላውቅም::" አልኩት እንደማፈር እያደረገኝ

"ለኔ ያለሽ ስሜት የቀነሰብሽ ቀን" አለኝ ኮስተር ብሎ ቀጠል አድርጎ "ለምን በግልፅ አልነገርሽኝም? እያስጠላኝ ነው ማድረግ አልፈልግም ለምን አላልሽኝም?"

"ባሌ አይደለህ? ሴክስ ማድረግ አልፈልግም ይባላል?"

"ባልሽ መሆኔኮ አንቺን የማስደሰት ሀላፊነትም አብሮ ይሰጠኛል:: abuse እያደረግኩሽ እንድደሰት መብት አይሰጠኝም::" አለኝ:: ምንጣፉ ላይ በቂጡ ተቀመጠና እንደመተከዝ እያለ....

"ልነግርሽ የሚገባ ነገር አለ!" አለኝ

"አውቃለሁ!" አልኩት። ግራ ገባው። እንዴት እንዳወቅኩ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሬ ነገርኩት።

"እንዴት አልጠየቅሽኝም? እንዴት አስቻለሽ?"

"አንተ ስንት ዘመን ሁሉ አስችሎህ ዝም ብለኸኝ የለ?"

"እንደዛ ነው የምታስቢው? ምናለ በይሆናል ራስሽን ከምትቀጪ ብትጠይቂኝ
2.6K viewsAbela, 15:20
Open / Comment
2021-10-05 13:50:06
20 viewsErmi , 10:50
Open / Comment
2021-10-05 11:22:39 ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
እንጦጦ ማርያም...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
እንዲህ እንዲያ እያለ
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!
እዘኝ አዛኝቱ!!
እዘኝ አዛኝቱ!!!
በላይ በቀለ ወያ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.2K viewsAbela, 08:22
Open / Comment
2021-10-05 07:38:27 ( ግብዣው ፤ ቅጽ 2)
(በእውቀቱ ስዩም)
ጓደኛየ ዘፈን መስራት ካቆመ አስር አመታት ያለፈው ድምጻዊ ነው:: ዋና ስሙ ፋኑኤል ሲሆን ለደህንነቱ ሲባል " ዘነመ" እያልሁ እጠራዋለሁ፤ ከቀናት ባንዱ ሰንበት “ወለላ “ ምግብ ቤት በረንዳ ተቀምጠን አስተናጋጅ እንጠብቃለን፤ አንዲት እንዲያው በደፈናው የአፈወርቅ ተክሌን ስእል የመሰለች ሴት ከፊታችን ብቅ አለች ::
“ አድናቂ ነኝ”
“ በጣም አመሰግናለሁ” አልኩ፤
“ ፈርምልኝ”
“ ምን ላይ ልፈርም?’
አንባቢያን ሆይ ! ባታምኑኝም ከመናዘዝ ወደ ሁዋላ አልልም፤ እየተሽኮረመመች “ ጡቴ ላይ “ አለችኝ :: እኔም ከኢትዮጵያ ባህል ጋር ላለመጋጨት፤ ከጡቷ ጋራ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ላለመቆራረጥ ፤ የጡት ማስያዣዋ ላይ ፈረምኩ::
“የት ነው እምትኖሪው?”
“ ሪችመንድ ነኝ! ከሁለት ሳምንት በሁዋላ አገር ቤት እሄዳለሁ”
“እቃ ይዘሽልኝ ትሄጃለሽ?”
‘ ኖ ፕሮብሌም! ይሄ ላንተ የማደረገው ትንሹ ነገር ነው “
“ለኔስ?” አለ ዘነመ፡:
‘ ቤቴ ራት እንድጋብዛችሁ ፍቀዱልኝ ! ቆንጆ ጭቅና ጥብስ መስራት እችላለሁ”
“ደስ ይለናል” አለ ጓደኛየ ተሽቀዳድሞ፤
ትንሽ ቆይቶ “ መጣሁ ! “ አለና ሹልክ ብሎ ወጣ፤
“አግብቷል ?” ስትል ጠየቀችኝ፤
“ አራት ጊዜ አግብቶ ፈቷል ”
“አንተም ፈት እንደሆንህ ሰምቻለሁ፤ ”
“ ልክ ነሽ! ስራ ፈት ነኝ”
“ ሸበላ ነገር ነው”
“ ጠባዩስ ብትይ ! ዘንዶ ያለምዳል”
ወደ ፊልም ቢቀየር ሁለት ሲዝን የሚወጣው ወሬ ስናወራ ከቆየን በሁዋላ ፤
“ እኔ እምልህ እስቲ ስለ እቃው ንገረኝ” አለችኝ::
“ ጎን ለጎን ሆነን ስንሸና እንዳየሁት ከሆነ አስተማማኝ እቃ ነው ያለው “ አልኳት::
“ እኔ እንኳ የጠየኩህ አገር ቤት ትወስጅልኛለሽ ስላልከኝ እቃ ነበር ! ብቻ መረጃ አይናቅም”
ከማፈሬ የተነሳ የምመልሰው ቸግሮኝ ሳልጎመጉም ጓደኛየ ሁለት ኪሎ ስጋ እና አንድ ወይን ፤ ይዞ ተመለሰ;
እሳት ጎርሳ ፤ ጭስ ተፍታ ወቀሰችው፤
“ አፒታይት እና ስጋ ከኛ ነው፤ ካንቺ ሙያ ብቻ ነው እሚጠበቅብሽ ” ብሎ አለዘባት ::
ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ ወደ ቤትዋ መንዳት ጀምራለች፡: እኔና ዘነመ በርሱ መኪና ተከተልናት " ሸበላ " ነው ያለቺውን ስነግረው “ ባትለኝም፤ ልጂቱ እንደተዝለፈለፈችልኝ ገና ከመጀመርያም አውቄዋለሁ፤ ቤት ስንደርስ እንደፈረደብህ የሆነ ምክንያት ፈልገህ ዞር ትላላህ” አለኝ::
“ የት ነው ዞር የምለው ?” አልሁ ያለ የሌለ በሽቄ::
“ ወይ ሞቴል ትይዛለህ ! ካልሆነ የፈረንጅ ደጀሰላም ፈልገህ ትተኛለህ ”
ሁለት ሰአት ያክል ነድተናል:: የምትኖርበት ኮንደሚኒየም በር ላይ ስንደርስ መጥርያውን ተጫነቸው፤ በሩ ሲከፈት አንድ የጠወለገ ራስታ ሰውየ ከውስጥ ብቅ አለ:: ከወገቡ በላይ የተራቆተው ሰውነቱ በንቅሳት ተዥጎርጉሮ የጥምቀት ሽመል ይመስላል፤ ሰላምታ እንኳ ሳይመጸውተን ስጋውንና ወይኑን ተቀብሎን ወደ ውስጥ ገባ፤ ተከትለነው ስንዘልቅ የጫማ፤ የሀሺሽ እና የድህነት ጠረን ተቀበለን::
ሰጋውን ከምኔው ጠብሶ አደረሰው?! አበላሉን ስመለከት፤ ላለፉት ሶሰት ቀናት እህል እንዳልቀመሰ መገመት አላቃተኝም፤ እኛን እንደ እንግዳ ቀርቶ እንደ ፖስተኛ እንኳ አልቆጠረንም፤
ዘነመ ፤ጥግ ይዛ ወይናችንን እምትቀመቅመውን ጉደኛ እየተመለከተ “ ሸኚን” የሚል ምልክት አሳያት፤
ሶስታችን ድምጻችንን አጥፍተን አንድ አራት ደረጃ ወረድን፤
ከጠጉሬ እስከ ጥፍሬ የወጠረኝን ሳቄን ለመቆጣጠርና የወዳጄን ፊት ላለማየት መታገል ጀመርኩ፤
ብዙ አልራቅንም፤ ዘነመ ርምጃውን ገታ አድርጎ ፤ ለመላው የህንጻው ነዋሪ በሚሰማ ድምጽ
“ እናትሽ ትረዳና ባል እንዳለሽ ለምን አልነገርሽኝም?” ብሎ ጮኸባት!
ልጂቱ፤ዘና ፤ ረጋ ብላ የመለሰችውን ልጻፈውና ታሪክ ይፍረደው፤
“ አገሩ super busy ስለሚያደረግ ብዙ ነገር ትዘነጋለህ! ባል እንዳለኝ ራሱ ትዝ ያለኝ አሁን ነው”
"

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.1K viewsAbela, 04:38
Open / Comment
2021-10-04 22:36:42 ሴት ከሆንሽ እባክሽን ተጠንቀቂ!

ወንድ ከሆንክ ለምታውቃቸው የ ሴት ወዳጆችክ ሼር አድርግ እና የበኩልህን
ተወጣ... እባክዎ
:
ውሸት አይደለም ገብታቹ አንብቡት


OPEN



OPEN



PLAY



PLAY




OPEN



OPEN



PLAY



PLAY
1.2K viewsErmi , 19:36
Open / Comment