🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.22K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 14

2023-05-03 14:46:15
በታንዛኒያው ድርድር ስምምነት ላይ አለመደረሱ ተገለጠ
የኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ብሎ በሚጠራው መንግሥት «ሸኔ» በሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል ታንዛኒያ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ድርድር «የመጀመሪያ ምእራፍ» ያለስምምነት መጠናቀቁ ተገለጸ ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በይፋዊ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ላይ ባወጣው ቁጥብ መግለጫ «ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው ምእራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም» ብሏል ። አወንታዊ የተባሉትም ሆነ ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች የትኞቹ እንደሆኑ ግን በግልጽ አልተቀመጠም ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት «የሰላም» ያለው ውይይት ታንዛኒያ ውስጥ መከናወኑን ከመግለጽ ባሻገር ግን ውይይቱ በማን እና በማን መካከል እንዲሁም በየትኞቹ ጉዳዮች መኪያሄዱን አልጠቀሰም ። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፦ (OLF-OLA press Release በሚል) ከሳምንት በፊት ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ መጠሪያ «የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት» እንደሆነ እና ከዚህ ሌላ ማንኛውንም ስያሜ እንደማይቀበል በመግለጫው አስታውቆ ነበር ። በዛሬው መግለጫው መንግስት አንዳችም ስያሜ አልጠተቀመም ።
ይህ ጽሑፍ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በታጣቂ ቡድኑ በኩል ስለድርድሩ በይፋ የወጣ መረጃ የለም ። ለቡድኑ ቅርበት ያላቸው የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ግን ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መስማማት አለመቻላቸውን ዘግበዋል ።
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid0245pnragAzXExxbYfcPZwDz7fteKzF8QKJYxdDxdP1Mnpe5AS9LHJtQeQHRrSMtfl
4.3K viewsDW Amharic, 11:46
Open / Comment
2023-05-03 13:54:05 https://p.dw.com/p/4QpwY?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
4.0K viewsDW Amharic, 10:54
Open / Comment
2023-05-03 13:34:59
ታጣቂዎች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትጥቅ አስረከቡ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በመተከል ዞን ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ 72 የሚደርሱት የታጠቁ እና ሌሎች ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የነበሩ 18 በድምሩ 90 የታጣቂ ቡድኑ አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በሚል ትጥቃቸውን ለመንግስት ማስረከባቸውን ዐስታወቀ ። ታጣቂዎቹ በዞኑ ጉባ እና ዳንጉር ወረዳዎች ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆን፤ የሰላም ጥሪ ተቀብለው ተመለሱ የተባለው ትናንት ማምሻውን እንደሆነም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሩን ኡመር ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል ። በጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሥር የሚንቀሳቀሱ ናቸው ተብሏል ።

የመተከል ዞን ለረጅም ጊዜ በጊዜያዊ አስተዳደር ወይንም ኮማንድ ፖስት ሲተዳደር የቆየ ሲሆን፤ በታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና የተለያዩ ጥቃቶች ምክንያት በዞኑ ብቻ ከ2 መቶ 60 ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው ቆይተዋል ። በዞኑ በእጀባ ይሰጥ የነበረው የመጓጓዣ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተከፍተው አገልግሎቱ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሱንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል ።

የጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ ከክልሉ መንግስት ጋር ስምምነት ከተደረገ ጥቅምት 9 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ወዲህ በድርጅቱ ስም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችት ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል ። የሰላም ጥሪውን የማይቀበሉ ታጣቂዎች ድርጅቱን እንደማይወክሉ እና ኃላፊነትም እንደማይስዱ ተናግረዋል ።

ዘገባ፦ ነጋሣ ደሳለኝ ከአሶሳ፤ ዶይቸ ቬለ (DW)
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid033uKsmRw2yCN9ABQqwEkoPyTD2Y19LyjBazRwareKymXUzEjkBo6LqWTV2Du6nkzql
4.1K viewsDW Amharic, edited  10:34
Open / Comment
2023-05-03 13:05:46
ሱዳን የተኩስ አቁም ቢኖርም ብርቱ ውጊያው ቀጥሏል

በሱዳን ውጊያ 550 ሰዎች መሞታቸው እና 5,000 ግድም መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚንሥቴር መሥሪያ ቤት ዐስታወቀ ። የሱዳን ጦር ሠራዊት እና ባላንጣው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ፓራሚሊታሪ (RSF)ለ7 ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ በመርኅ ደረጃ ቢስማሙም ዛሬም ውጊያው ቀጥሏል ። በስምምነቱ መሠረት ለአንድ ሳምንት ይዘልቃል የተባለው የተኩስ አቁም የሚጀምረው በነገው እለት ነው ... https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid02pGD2jJddrn3jYdNPiea1PWEZc5R7xzwZTkVkzFjLKhTiskXckbdxjWw5gEW8K7Tel
3.9K viewsDW Amharic, 10:05
Open / Comment
2023-05-03 12:07:18
የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ ወረርሽኝ 84 ሰዎች እስከ ሰኞ ሚያዝያ 23 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ድረስ መሞታቸው ተዘገበ ። ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ በላይ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸውም ተገለጿል ።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ(UN OCHA Ethiopia) በይፋዊ የትዊተር ገጹ እንዳወጣው ከሆነ፦ ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጀምሮ ከ5,500 በላይ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ ተጠቅተዋል ። የኢትዮጵያ መንግሥት «118 ከፍተኛ ተጠቂ አካባቢዎች» መለየቱን እንዲሁም «41 የኮሌራ ህክምና ማዕከላት» ማቋቋሙን ዓለም አቀፍ ድርጅቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል ።

በዋናነት ችግሩ የታየባቸው አካባቢዎች፦ የሶማሌ፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች፤ የኦሮሚያ፤ የአፋር፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ናቸው ብሏል ። አጣዳፊ ተቅማጥ የሚያስከትለው የኮሌራ ወረሽኝ የሚሰራጨው በተሐዋሲው የተበከለ ምግብ አለያም መጠጥ በመውሰድ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ኦቻ አሳስቧል ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በምኅጻሩ አተር (አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት) በተደጋጋሚ የጤና እክል ሆኖ እንደሚታይ ይዘገባል ። አተት የኮሌራ ሌላው የማለሳለሺያ ስም ነው የሚሉም አሉ ።

የምስል መረጃ፦ (የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ UN OCHA Ethiopia ይፋዊ የትዊተር ገጽ)
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid029Hn3SV8QU4YjKiu116f2n7X9pckFVZ5Bpdd2z99anS32DbvNCvRLcu791ntJeJkvl
4.5K viewsDW Amharic, 09:07
Open / Comment
2023-05-02 20:28:31 ዜና
-የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በኢትዮጵያ የዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ በማለት የወቀሱና ያስጠነቀቁት ኤርትራን ሳይሆን እንደማይቀር የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችና ተንታኞች እየተናገሩ ነዉ።የጠቅላይ ሚንስትሩን መልዕክትና መንግስታቸዉ ከኤርትራ ጋር ያለዉን ግንኙነት የሚተነትኑ ወገኖች እንደሚሉት መልዕክቱ በአስመራ ላይ ለማነጣጠሩ ብዙ ምልክቶች አሉ።


-የጀርመኑ መራሔ መንግስት ኦላፍ ሾልስ በኢትዮጵያና በኬንያ የሚያደርጉት ጉብኝት የጀርመንና የአፍሪቃ ሐገራትን ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚረዳ ተነገረ።ሾልስ ከመጪዉ ሐሙስ ጀምሮ በኢትዮጵያና በኬንያ በሚያደርጉት ጉብኝት ስለኢትዮጵያ ሰላም፣ስለሱዳን ጦርነትና ጀርመን ከኬንያ ጋር ስላላት የምጣኔ ሐብት ግንኙነት ከየባለስልጣናቱ ጋር ይነጋገራሉ።


የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት አዛዦች ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ለ7ቀን የሚፀና ተኩስ አቁም ለማድረግ በመርሕ ደረጃ ተስማሙ።የደቡብ ሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳለዉ ሁለቱ ጄኔራሎች ተደራዳሪ ለመሰየም በየፊናቸዉ ቃል ገብተዋልም።https://p.dw.com/p/4QoMt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
5.6K viewsDW Amharic, 17:28
Open / Comment
2023-04-30 19:30:03 ዉይይት፤ የሱዳን ጦርነት ጥፋቱና መዘዙ
ባለፈዉ ሚያዚያ 7፣ 2015 በተጀመረዉ ዉጊያ ከ520 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።4 ሺሕ 500 ቆስለዋል።አዉሮፕላን ማረፊያዎች፣የጦር ሠፈሮች፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች ሌሎችም ተቋማት ጋይተዋል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ወደ አጎራባች ሐገራት ተሰድዷል ወይም ተፈናቅሏል።መንግስታት በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎቻቸዉን ከሱዳን አስወጥተዋል። https://p.dw.com/p/4Qh1g?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
3.5K viewsDW Amharic, 16:30
Open / Comment
2023-04-30 19:29:10 የዓለም ዜና በድምጽ
የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎችንበቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።
የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ዛሬ በከባድ ቶክስ ስትናወጥ መዋሏን የአይን እማኞች ተናገሩ። የቀድሞው የሃገሪቱ ጠቅላይሚኒስትር በበኩላቸው ሱዳን ወደ ሙሉ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳትገባ አስጠንቅቀዋል።

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ ሃመኒ በኢራቅ አንድ አሜሪካዊ መኖሩ ብቻ እጅግ ብዙ ነው ሲሉ ለኢራቁ መሪ አሳሰቡ። ሃመኒ ይህን ያሳሰቡት ከኢራቁ ፕረዚደንት ዓብዱልለጢፍ ራሺድ በቴህራን ተገናኝተው ባደረጉት ንግግር መሆኑን ከጽሕፈት ቤታቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የሮማው ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ በሃንጋሪ ዛሬ ባካሄዱት ጉብኝት ለስደተኞች በራችሁን አትዝጉ ሲሉ አሳሰቡ። ይህ አባባላቸው ከሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የፍልሰት ፖሊሲ ጋር የሚጻረር ነው ተብሏል።

በህንድ ሰሜናዊ የፑንጃብ ግዛት ባፈተለከ ጋዝ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።
የኢንዱስትሪ መንደር በሆነችው ሉዲሂና ዞን በምትገኝ ጊስፖራ በተባለ አካባቢ ያጋጠመው አደጋ በምን ዓይነት ጋዝ እንደሆነ እና መንስኤው ምን እንደሆነ አለመረጋገጡን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያለፈለጉ ባለስልጣን ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ተናግረዋል። https://p.dw.com/p/4QjT3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.4K viewsDW Amharic, 16:29
Open / Comment
2023-04-29 20:06:58 «አውቄው ቢሆን ኖሮ» ፤ ክፍል 1 «የወንድ ልጅ ምኞት»

ቶማስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አንዲት ሴት በእርግዝናዎች መካከል ለምን ማገገሚያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋት ፈፅሞ አያውቅም ነበር። ስለሆነም እሱ እና ባለቤቱ በቶሎ ወንድ ልጅ እንዲወልዱ ግፊት ያደርግ ነበር። ዛሬ ታሪኩን በፀጸት መለስ ብሎ ያስቃኘናል። https://p.dw.com/p/4QHNe?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
5.2K viewsDW Amharic, 17:06
Open / Comment
2023-04-29 19:47:11 የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፊታችን ነሐሴ መገባደጃ ላይ በተፋጠነ የኤኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚገኙ አምስት ሃገራት በሚሳተፉበት ጉባዬ ላይ ለመገኘት ወደ ደቡብ አፍሪቃ እንደሚጓዙ ተገለፀ። ይህን ተከትሎ ደቡብ አፍሪቃ ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት እወጣለሁ አልወጣም መልስ ዉዥንብር ዉስጥ ከቷት ነዉ የሰነበተዉ። https://p.dw.com/p/4Qgjx?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
5.1K viewsDW Amharic, edited  16:47
Open / Comment