Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.70K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 12

2023-05-11 12:25:55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኬንያው ሳፋሪ ኮም ኤምፔሳ ኩባንያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ። ባንኩ ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2015 በፌስቡክ ገጹ እንዳሳወቀው ለሳፋሪ ኮም የተሰጠው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለውጭ ኩባንያ የተሰጠ የመጀመሪያው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ ፈቃድ ነው።ባንኩ እንዳለው በጥሬ ገንዘብ የሚደረግን ግብይት በዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለመተካት የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ይደግፋል። የተለያዩ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን ስራ የማዋል ፍላጎት እንዳለው የጠቀሰው ባንኩ፣በሚቀጥሉት ዓመታት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት በማዘመን፣ ዜጎች ገንዘብ እንዲያስተላልፉ፣ እንዲቆጥቡ እንዲበደሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያግዝ መሳሪያ ይሆናል ብሏል። ለሳፋሪኮም የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ መሰጠቱ ምን ጥቅም አለው ትላላችሁ? ምንስ ትጠብቃላችሁ?ሃባችሁን አካፍሉን፣ ተወያዩበት
3.6K viewsDW Amharic, 09:25
Open / Comment
2023-05-11 12:16:21
በሊቢያ፤ በቱንዚያ ወይም በየመን በኩል አድርገው ባገኙት አጋጣሚ ወደ አውሮጳ ለመሰደድ ሲሞክሩ ያልተሳካላቸው እና በእነዚህ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማናገር እየሞከርን ነው። የሚገኙበትን ስልክ ቁጥር ብትተባበሩን ደስ ይለናል። ለትብብራችሁም በቅድሚያ እናመሰግናለን።
3.2K viewsDW Amharic, 09:16
Open / Comment
2023-05-10 20:05:28 የረቡዕ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና

የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ፣ መንግሥትን ለመገልበጥ በማሴርና በአሸባሪነት የጠረጠራቸው ታዋቂው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው አሁን ከሚገኙበት ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አስታወቁ። በፈቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የቀረበባቸውን ውንጀላ በፍርድ ቤት ለመከራከር ዝግጁ መሆናቸውን በተለይ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የተናገሩት አቶ ልደቱ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ጅዲ ሳዑዲ አረብያ ውስጥ የተኩስ አቁምና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያካሂዱት ንግግር በቀጠለበት በዛሬ እለት በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል በዋና ከተማይቱ ኻርቱም የሚካሄደው ውጊያ መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናገሩ። ለንግግሩ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማቶች እንዳሉት፣ ሁለቱ ወገኖች ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በጅዳ በሚያካሂዱት ንግግር የተጨበጠ ውጤት ላይ አልደረሱም።

ቱኒዝያ በሚገኝ አንድ ደሴት ውስጥ ባለ ሙክራብ አቅራቢያ ትናንት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ወደ አምስት ከፍ ማለቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ። በአንድ የቱኒዝያ ብሔራዊ ዘብ አባል፣ የሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የጀርባ አጥንት በሆነችው በጀርባ ደሴት ስለተፈጸመው የተኩስ ጥቃት መንስኤ የቱኒዝያ ባለሥልጣናት ያሉት ነገር የለም።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4RARg?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.4K viewsDW Amharic, 17:05
Open / Comment
2023-05-10 20:00:41 https://p.dw.com/p/4R9oB?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.7K viewsDW Amharic, 17:00
Open / Comment
2023-05-04 14:40:19
የጀርመን መራኄ መንግሥት አዲስ አበባ ገቡ
የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። መራኄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ርእሠ ብሔር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጋር በሁለትዮሽ ፣ አካባቢያዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ እንደዘገበው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ እና ጀርመን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸውና በብዙ የኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅቶች ጀርመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆየች አገር ናት ብለዋል። የኢትዮጵያ እና የጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ አንድ ምዕተ ዓመት ተሻግሯል። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ የንግድ ተቋማት ባለቤቶችን እና ኃላፊዎች አስከትለው ነበር።
ከጀርመን ሰፊ ቁጥር ያለው ባለሃብት የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስዓለም ጀርመን የኢትዮጵያ ሰፊ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰዋል። በትምህርት እና በስልጠና ከምታደርገው ሰፊ ድጋፍ ባለፈ አሁን የሰላም ስምምነት ሒደቱ በላቀ እንዲሳካ ፣ ለመልሶ ግንባታ ሥራዎችም ድጋፍ ያደርጋሉ ብለዋል። በሌላ በኩል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ላይ ችግር የሚፈጥር ነው የተባለው የሱዳን ቀውስ ክስተቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው ተብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም እንዳሉት እስካሁን 61 አገሮች 7726 ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል ከሰዳን ማስወጣታቸውንና ከነዚህም 3517ቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልፀዋል።
1.4K viewsDW Amharic, 11:40
Open / Comment
2023-05-04 13:10:11
ወደ ትግራይ የሚልከውን የምግብ እርዳታ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን የዩናይትድ ስቴትስ የእርዳታ ድርጅት USAID አስታወቀ። የUSAID አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ድርጅታቸው በምግብ እጦት ለረሀብ መሰል አደጋ ለተጋለጠው ለትግራይ ህዝብ የሚልከው የምግብ እርዳታ መዘረፉንና በአካባቢው ለሽያጭ መቅረቡን እንደደረሰበት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የምግብ እርዳታው መጥፋቱ ከደረሰበት በኋላ ድርጅቱ አዲስ አበባ ከሚገኘው የዩናይትድድ ስቴትስ ኤምባሲ እና ከአስፈጻሚ አጋሮች ጋር ለጊዜው የምግብ እርዳታውን ለማቋረጥ መወሰናቸውን ሳማንታ ፓወር ገልጸዋል።ሃላፊዋ እንዳሉት ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ለትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ነግረዋል። እንደ USAID ሁሉ የዓለም የምግብ ድርጅት በምህጻሩ WFPም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። WFP የምግብ እርዳታው ለህዝቡ እንደሚደርስ ዋስትና እስከሚሰጠው ድረስ እርዳታ ማቅረቡን አይቀጥልም። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰብዓዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን ወንጀል የሚያጣራና የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር ግብረ ኃይል መቋቋሙን ተናግረዋል።
2.2K viewsDW Amharic, 10:10
Open / Comment
2023-05-04 12:29:48
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የውጭ ባለሀብቶች በባንክ ዘርፍ መሰማራት የሚያስችላቸው ፈቃድ ለመስጠት እንዳቀደች አስታወቀች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰሎሞን ደስታ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የውጭ ወራቾች በሀገሪቱ የባንክ ዘርፍ እንዲሰማሩ የሚስችላቸው ከሦስት ከእስከ አምስት የሚደርስ ፈቃድ እንደምትሰጥ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አቶ ደስታ እንዳሉት እርምጃው የሀገሪቱን የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ ለውጭ ተፎካካሪዎች ክፍት ለማድረግ የተያዘው እቅድ አካል ነው።ከዚህ ሌላ ሀገሪቱ የውጭ ባለሀብቶች በኢዱስትሪው ዘርፍም ከሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በጋራ ወይም ለብቻቸው መወረት የሚያስችላቸው የተለያዩ አማራጮች ሊኖራቸው ይችላል ብለዋል። የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ባንክን ጨምሮ በቴሌኮም በትራንስፖርት እና በአቭየሽን ዘርፎች ላይ ለመወረት ዓይናቸው ከጣሉ ሰንብተዋል። ኢትዮጵያ ለውጭ ባለሀብቶች የባንክ ስራ ፈቃድ ለመስጠት የያዘችውን እቅድ እንዴት ታዩታላችሁ? የውጭ ዜጎች በዘርፉ መስማራታቸው ምን ጥቅም ይኖረዋል ትላላችሁ? አስተያየታችሁን አካፍሉን
2.4K viewsDW Amharic, 09:29
Open / Comment
2023-05-03 20:21:35 የሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ዐርዕስተ ዜና

በኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል ዛንዚባር ታንዛኒያ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ውይይት ዛሬ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥትና “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” አስታወቁ። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት እንዳለው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መስማማት አልቻሉም። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ባላቸው ላይ መስማማት አለመቻላቸውን ገልጿል።

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ቃል የገቡት የተኩስ አቁም እንዲጸና ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ዛሬም በተለያዩ የሱዳን ከተሞች ተኩስ ሲሰማ ነበር። ተፋላሚዎቹ ጀነራሎች ተኩስ ለማቆም የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸው ዓለም አቀፍ ትችት አስከትሏል።

በሰሜንና ምዕራብ ሩዋንዳ ፣ ጎርፍ ከ120 በላይ ሰዎችን ገደለ ። የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የፖል ካጋሜ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በሰሜንና ምዕራብ ሩዋንዳ ትናንት ለሊት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ቢያንስ 129 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። የሟቾቹ ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4QrHk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.2K viewsDW Amharic, 17:21
Open / Comment
2023-05-03 20:17:57 https://p.dw.com/p/4QqSQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.8K viewsDW Amharic, 17:17
Open / Comment
2023-05-03 20:16:01 https://p.dw.com/p/4QrF9?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.3K viewsDW Amharic, 17:16
Open / Comment