🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.90K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 589

2021-02-07 20:20:52 https://p.dw.com/p/3p1Sp?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.3K viewsDW Amharic, 17:20
Open / Comment
2021-02-07 20:20:28 አዲስ አበባ-የኢትዮጵያና የዓለም ምግብ ድርጅት ስምምነት

የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ለመሰጠት ተስማሙ። የዓለም ምግብ ድርጅት የበላይ ዴቪድ ቤስሌይ የትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ከጎበኙ በኋላ ትናንት እንዳሉት ድርጅታቸዉ ሠብአዊ ርዳታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር «በተጨባጭ ርምጃዎች» ላይ ተስማምቷል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የቤስሌይን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሌለባቸዉ አካባቢዎችን ጨምሮ ለችግር ለተጋለጠዉ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ርዳታ እንዲያደርስ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበዉን ጥያቄ ለማሟላት ተስማምቷል።ቤስሌይ ትናንት በቲዊተር ባሰራጩት መግለጫ ትግራይ ዉስጥ 3 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ «የኛን ርዳታ እየጠበቀ ነዉ» ብለዋል።«የምናጠፋዉ ጊዜ የለም።» አከሉ ኃላፊዉ።
2.2K viewsDW Amharic, 17:20
Open / Comment
2021-02-07 20:20:14 https://p.dw.com/p/3p1PL?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.2K viewsDW Amharic, 17:20
Open / Comment
2021-02-07 20:19:48 ካርቱም-የሱዳን የዉኃ ሚንስትር ማስጠንቀቂያ

የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያን በሰበብ-አስባቡ መጎነታተላቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ። የሱዳን ጦር ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ግዛት ይዟል መባሉ አወዛግቦ ሳያበቃ ሠሞኑን፣ የካርቱም ባለስልጣናት የሕዳሴዉ ግድብ የዉኃ አሞላልን የአዲስ ማስጠነቀቂያ ሰበብ አድርገዉታል። የሱዳኑ የመስኖና የዉኃ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድን በተናጥል ዉኃ ከሞላች ለሱዳን ብሔራዊ ደሕንነት ቀጥተኛ ስጋት ትጭራለች። ሚንስትር ያሲር አባስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በመጪዉ ሐምሌ ግድቡን ከሞላች ሱዳን ከሁለት ግድቦችዋ የምታመነጨዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ይታወካል፤ የ20 ሚሊዮን ሱዳናዉያን ኑሮም ይቃወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈዉ ዓመት ክረምት ግድቡን መሙላት ጀመራለች። ግብፅና ሱዳን የኢትዮጵያን ርምጃ አልፈቀዱትም። ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እንዳሉት የዉኃ ሙሌቱ ይቀጥላል። ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የሱዳኑን ሚንስትር ጠቅሶ እንደዘገበዉ የ3ቱን ሐገራት ዉዝግብ ለማስወገድ ዩናይትድ ስቴትስ፣የአዉሮጳ ሕብረት፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና እንዲገቡ ካርቱም ሐሳብ አቅርባለች።
2.3K viewsDW Amharic, 17:19
Open / Comment
2021-02-07 20:19:34 https://p.dw.com/p/3oxlR?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.3K viewsDW Amharic, 17:19
Open / Comment
2021-02-07 20:01:20 ጥር 30፣2013
አርዕስተ ዜና
-ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስገነባችዉን ግድብ፣ ሱዳንና ግብፅን ሳታማክር ዉኃ እንዳትሞላ ሱዳን አስጠነቀቀች።የሱዳኑ የዉኃ ሚንስትር እንደሚሉት ኢትዮጵያ በመጪዉ ኃምሌ በተናጥል የሕዳሴ ግድብን ዉኃ ከሞላች ለሱዳን ብሔራዊ ደሕንነት ቀጥተኛ ሥጋት ትጭራለች።የሶስቱን ሐገራት ዉዝግብ ለማስወገድም የዓለም መንግስታትና ማሕበራት ጣልቃ እንዲገቡ ካርቱም ጠይቃለች።

-የዓለም ምግብ ድርጅት በጦርነት ለተጎዳዉ የትግራይ ሕዝብ ርዳታ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ።የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ እንደሚሉት ድርጅታቸዉ ትራንስፖርት በማይገኝበት አካባቢ ጨምሮ ለሚኖረዉ አንድ ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ ርዳታ ይሰጣል።

-የሶማሊያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተራዘመ።ነገ ይደረጋል ተብሎ የነበረዉ ምርጫ የተራዘመዉ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች በመራጮች ማንነትና በምርጫዉ ሒደት ባለመስማማታቸዉ ነዉ።የሶማሊያ ፖለቲከኞች ለስልጣን ሲሻኮቱ አክራሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ 12 የስለላ ባለሙያዎችን ገድሏል።
ዜናዉ በድምፅ ለማድመጥ፣ እዚሕ ይጫኑ https://p.dw.com/p/3p1bs
3.0K viewsDW Amharic, 17:01
Open / Comment
2021-02-06 20:00:49 አንድ ጎዳና ላይ ሰርከስ የሚያሳይ አርቲስት በፖሊስ መኮንን በተገደለባት ደቡብ አሜሪካዊት ሀገር ቺሊ ውስጥ ከፍተኛ አመጽ ተቀሰቀሰ። በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ዓርብ ማምሻውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁጣቸውን ለመግለፅ በደቡባዊ ቺሊ አደባባይ ወጥተዋል። እንደ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሰልፈኞች አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት እና መኖሪያ ቤቶችን በእሳት አጋይተዋል። ከዚህም ሌላ መንገዶችን በመዝጋት በፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ሰልፈኛውን ለመበተን የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስና ውኃ መጠቀማቸውም ተጠቁሟል። የሰርከስ አርቲስቱ የተገደለው በከተማ መሃል ቁጥጥር የሚያካሂዱትን ሁለት ፖሊሶች ትዕዛዝ ተላልፏል በሚል ነው። ፖሊስ የመኮንኑን ርምጃ ትክክል ነው በሚል የደገፈ ሲሆን ጉዳዮን ለማጣራት አቃቤ ሕግ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። የቺሊ ፖሊስ ብዙውን ጊዜ ጭካኔ በተሞላው ባህሪ ምክንያት በተደጋጋሚ ከፍተኛ ወቀሳ እንደሚቀርብበት የጀርመን የዜና ወኪል ዘግቧል።
6.0K viewsDW Amharic, 17:00
Open / Comment
2021-02-06 19:59:54 በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አፍሪካ ውስጥ በርካታ ልጃገረዶች ይበልጥ ለግርዛት መጋለጣቸውን የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስጠነቀቁ። ድርጅቶቹ ይህንን ያሉት የሴቶች ግርዛትን ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት ዛሬ ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ ዕለትን አስመልክተው ነው። የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት በአንዳንድ አገሮች ረዘም ላለ ጊዜ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው በመቆየታቸው ለዚህ ተጋላጭ የሆኑ ልጆችን የሚከታተሉ መምህራን አልነበሩም። ከዚህም ሌላ የእንቅስቃሴ እገዳው የፀረ-ግርዛት ሥራዎችን አስተጓጉሎ የጤና ድርጅቶችን ትኩረት በሙሉ ወደ COVID-19 ትግል ስቧል ባይ ናቸው። ወረርሽኙ ባባባሰው ድህነትም የተነሳ ተሟጋቾች ያነጋገሯቸው ወላጆች እንደሚሉት ሴት ልጆቻቸውን የጥሎሽ ክፍያ ለማግኘት እና ልጆቻቸውን በቶሎ ለመዳር ብለው እንዲገረዙ አድርገዋል። የተባበሩት መንግሥታት የኅብረተሰብ ድጋፍ መርሃግብር (UNFPA) እንደሚገምተው ከሆነ ጎጂ ልማዱን እስከ ጎርጎርዮሳዊው 2030 ሙሉ በሙሉ ለማስቆም ታስቦ ባለበት ወቅት የኮሮና ወረርሽኝ በፈጠረው ቀውስ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ተጨማሪ ሁለት ሚሊዮን ልጃገረዶች በቀጣይ አስር ዓመታት ውስጥ ለግርዛት ሊዳረጉ ይችላሉ። በዓለም ላይ 200 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናትና አዋቂ ሴቶች የዚህ ጎጂ ልማድ ሰለባ ሆነዋል ተብሎ ይገመታል።
5.9K viewsDW Amharic, 16:59
Open / Comment
2021-02-06 19:58:43 https://p.dw.com/p/3ozM7?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.6K viewsDW Amharic, 16:58
Open / Comment
2021-02-06 19:58:04 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ላይ ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ICC የጦር ወንጀል ምርመራ የሚከፍትበትን ውሳኔ «ግልፅ የሆነ ፀረ-ሴማዊነት» በማለት አወገዙ። ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫም ይህንን ለማስቆም እንደ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
« ናዚ በአይሁዳውያን ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ አይነት ጭካኔዎችን ለመከላከል የተቋቋመው ፍርድ ቤት አሁን በአንዱ የአይሁዳውያን ግዛት ላይ አነጣጥሯል። በመጀመሪያ አይሁዳውያን በትውልድ አገራቸው ሲኖሩ ይሄ የጦር ወንጀል ነው ይባላል፣ ሁለተኛ ዲሞክራሲያዊቷ እስራኤል ልጆቻችንን የሚገደሉ እና ከተሞቻችንን የሚደበድቡ ሽብርተኞችን ስትከላከል የጦር ወንጀል እንደፈፀምን ይቆጠራል። »
ኔታንያሁ አክለውም ይልቁንም «የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በየዕለቱ በሚባል ደረጃ ኢራን እና ሶሪያ የሚፈፅሙትን ወንጀሎች ለመመርመር ችላ ብሏል» ሲሉ ተችተዋል። የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ICC ትናንት ነበር የተያዙትን የፍልስጤም ግዛቶች ጉዳይ ለማጣራት ሥልጣን እንዳለው በመግለጽ ፍርድ ቤቱ የጦር ወንጀል ምርመራ እንዲሚከፍት በአብላጫ ድምፅ መወሰኑን ያስታወቀው። ምርመራውም እስራኤል ከጎርጎርዮሳዊው 1967 አንስቶ የተቆጣጠረቻቸው ጋዛ፣ ምሥራቅ ኢየሩሳሌምን እና የምዕራብ ዮርዳኖስን አካባቢዎች ያጠቃልላል ተብሏል።
4.3K viewsDW Amharic, 16:58
Open / Comment