Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.55K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 581

2021-02-14 19:44:12 https://p.dw.com/p/3pLgl
5.0K viewsDW Amharic, 16:44
Open / Comment
2021-02-14 19:42:40 ጀርመን በኮሮና ስጋት ለተወሰኑ ሀገራት ከዛሬ እኩለ ሌሊት አንስቶ ድንበሯን ዘጋች። በዚህም የተነሳ የጀርመን የፌደራል ፖሊስ ከኦስትሪያ እና ከቼክ ሪፐብሊክ ወደ ጀርመን የሚጓዙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርጋል። ለድንበሩ መዘጋት ምክንያት የተባለው በተለይ በእነዚህ አከባቢዎች በቀላሉ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ሰው የመተላለፍ ባህሪ አለው የተባለው ልውጡ የኮሮና ተህዋሲ ተስፋፍቶ ስለሚገኝ ነው። ስለሆነም በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ውሳኔ መሠረት ወደ ጀርመን መግባት የሚፈቀድላቸው ጀርመናውያን እና የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ዜጎች ብቻ ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎች ፣ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና የግብርና ሰራተኞች እንደየሁኔታው ወደ ጀርመን የሚገቡበት ፍቃድ ሊያገኙ ይችላሉ። እንደዛም ሆኖ ሁሉም ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሰዎች በኮሮና አለመያዛቸውን የሚያረጋግጥ የምርመራ ውጤት ማቅረብና እራሳቸውን ለይተው ማቆየት ይኖርባቸውል።
4.7K viewsDW Amharic, 16:42
Open / Comment
2021-02-14 19:42:13 የኮሮና ወረርሽኝ ምንጭን ለማጣራት ወደ ቻይና ውሃን ከተማ የተጓዘው የዓለም ጤና ድርጅት ልዑክ ኃላፊ ፒተር ቤን እምባሬክ ቡድኑ ጥሬ መረጃ ለማግኘት መቸገሩን በመግለፅ ቅሬታ አቀረቡ። «ኮሮና ቀደም ብሎም ተከስቶ እንደሆነ ለማጣራት ተጨማሪ መረጃ ያስፈልጋል» ያሉት የልዑኩ ኃላፊ ከቻይና ባለሥልጣናት የጠየቁዋቸውን መረጃዎች ያገኛሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ቡድኑ በግልፅ የጠየቀው መረጃ በጥቅምት እና ታህሳስ ወር 2019 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ በተለይ ውሃን ከተማ 72,000 ህመምተኞ ላይ ተከስቶ ስለነበረ እንደ የሳምባ ምች ፣ ጉንፋን እና ትኩሳት ያሉ በሽታዎችን የሚያሳይ መረጃ ነው። የቻይና ባለሞያዎች በሽታው ከተከሰተ በኋላ ወደኋላ መልሰው ያጣሩት የ 92 በሽተኞችን ጉዳይ ብቻ ሲሆን የሁሉም የምርመራ ውጤት በኮቪድ 19 አለመያዛቸውን የሚያረጋግጥ ነበር ተብሏል።
4.6K viewsDW Amharic, 16:42
Open / Comment
2021-02-14 19:41:56 https://p.dw.com/p/3pIVZ @dwamharicbot
4.5K viewsDW Amharic, 16:41
Open / Comment
2021-02-14 19:40:46 በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ጊኒ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኤቦላ በሽታ መከሰቱ በይፋ ከተረጋገጠ በኋላ ሀገራቱ ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኙ አስታወቁ። የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴሮች ይፋ እንዳደረጉት ጊኒ ውስጥ ሰባት ሰዎች ላይ ተህዋሲው መገኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን የሶስቱ ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ ዛሬ አራተኛ ሰው ላይ ተህዋሲው ሊረጋገጥ ችሏል። ይህንን ተከትሎም ሁለቱ ሀገራት የበሽታውን ደረጃ ዝቅተኛ በሚባለው የወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዛሬ አስታውቀዋል። ተላላፊ በሽታው የተከሰተው በሰሜናዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪቩ አውራጃ ሲሆን በጊኒ ደግሞ የላይቤሪያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ጎውኬ ከተማ ነው። በዚች ከተማ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደ አንድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የተሳተፉ ሰዎች « የማስመለስ፤ የተቅማጥ፣ ትኩሳት እና የመድማት የመሳሰሉ ምልዕክቶችን ማሳየት እንደጀመሩ ተገልጿል። በከተማዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ናሙና የተወሰደው ግን ዓርብ ዕለት መሆኑን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። ጎረቤት ሀገር ላይቤሪያ ይፋ ከሆነው ዜና በኋላ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንደሆነች የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የዓለም የጤና ድርጅት በበኩሉ ፈጣን ርዳታ ለመለገስ ማቀዱን ገልጿል።
ጊኒ ውስጥ ከጎርጎሮሲያኑ 2013 እስከ 2016 ባለው ጊዜ ተከስቶ በነበረው የኤቦላ በሽታ 2500 ገደማ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በጠቅላላ በአካባቢው ባሉ ሀገራት ደግሞ ከ 11, 300 በላይ ሰዎች ሞተዋል። የኤቦላ ተህዋሲ ለመጀመሪያ ጊዜ እጎአ በ 1976 ዓም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ የተረጋገጠ ሲሆን መጠሪያ ስሙንም ያገኘው በሀገሪቱ በሚገኝ አንድ የወንዝ ስም ነው።
4.2K viewsDW Amharic, 16:40
Open / Comment
2021-02-13 20:27:57 ዋና ዋና ዜናዎች
. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ ማከናወን በተራዘመባቸው ክልሎች ከየካቲት 15-26/2013 እንደሚካሄድ ገለፀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቦርዱ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮችን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ፣ጋምቤላ ፣ ኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች ለምርጫ ክልል እና ለዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሊያገለግሉ የሚችሉ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዳስታወቁ ገልጿል።
. የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) “ለሚጠፋ የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግስት ኃላፊነቱን ይወስዳል” ሲል አስጠነቀቀ፡፡ኦፌኮ የረሃብ አድማው በአባላቶቹ ህይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ እንዲያንዣብብ አድርጓል ነው ያለው ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፡፡ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ አባላቶቻቸው የጠየቁት ጥያቄ ተገቢ በመሆኑ የረሃብ አድማውን እንዲገቱ አፋጣኝ መፍትሄ ያሻዋል ብለዋል፡፡

. በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የቤተ መንግሥት አቅራቢያ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ሶስት ሰዎች ተገደሉ። የከተማዋ የደህንነት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በፍንዳታው ከተገደሉት በተጨማሪ በሌሎች ስምንት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

. በአፍጋኒስታን ባልክ ግዛት ቦምብ የመስራት ልምምድ ሲያደርጉ የነበሩ 30 የታሊባን ተዋጊዎች በፍንዳታ መገደላቸውን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳለው በፍንዳታው ከተገደሉት ውስጥ ስድስቱ የውጭ ዜግነት ያላቸው ናቸው ብሏል።

. ማሪዮ ድራጊ አዲሱ የጣልያን ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ ። የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ የበላይ የነበሩት ማርዮ ድራጊ «ለህዝቡ ታማኝ ለመሆን እምላለሁ» ብለዋል።ድራጊ ቃለመሃላውን የፈጸሙት በፕሬዚደንት ሰርጂዮ ማታሬላ ቤተመንግስት በተሰናዳ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ለህዝብ በተሰራጨ መርሃ ግብር ላይ እንደነበር የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል።https://p.dw.com/p/3pK7S
6.4K viewsDW Amharic, edited  17:27
Open / Comment
2021-02-13 20:13:35 የቻድ ምርጫና ኮቪድ -19 ያባባሰው የመብት ጥሰት በዚምባብዌ
በመካከለኛው አፍሪቃ ሰሜን ምዕራብ ክፍል የምትገኘው ቻድ በመጭው ሚያዚያ የምታካሂደው ምርጫና ችግሮቹ እንዲሁም በዚምባብዌ በኮሮና ወረርሽኝ ሰበብ የተቃውሞ ድምጾችን አፈናና የመብት ጥሰቶች እየጨመሩ መምጣት የዛሬው የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት የተመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው።https://p.dw.com/p/3pK5i?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
5.7K viewsDW Amharic, 17:13
Open / Comment
2021-02-13 20:12:57 የአድማጮች ማህደር
የየካቲት 6 ቀን 2013 ዓም የአድማጮች ማህደር ስርጭትhttps://p.dw.com/p/3pJxC?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
5.1K viewsDW Amharic, 17:12
Open / Comment
2021-02-13 19:55:20 የዓለም የራዲዮ ቀን
የዓለም የራዲዮ ቀን ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ “New World, New Radio” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው፡፡ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ዶይቼ ቬለ አንድ የጣቢያውን የረጅም ጊዜ ደንበኛ አነጋግሯል፣ ደንበኛው የቀድሞ ትዝታቸውንና ተሳትፏቸውን እያነሱ ያጫውቱናል፡፡ https://p.dw.com/p/3pK7F?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
5.3K viewsDW Amharic, 16:55
Open / Comment
2021-02-13 19:29:05 የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የግል ሃኪሞች ክትትል ማቆም
በርሀብ አድማ ላይ የሚገኙት የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን የሚከታተል የግል ሃኪሞቻቸው ቡድን ሲያደርግላቸው የቆየውን የህክምና ክትትል ማቆሙን አስታውቋል።https://p.dw.com/p/3pK3I?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
5.9K viewsDW Amharic, 16:29
Open / Comment