Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.70K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 584

2021-02-11 15:00:30
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ቢደርስም በሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ከማስመረቅ አላገዳቸውም::
ቫይረሱ ወደ ሀገሪቱ መግባቱ ከተረጋገጠበት ካለፈው አመት ጀምሮ ለወራት ያህል ትምህርት ተቋርጦ ነበር::
ቀደም ሲል በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የጸጥታ ስጋት ማንዣበቡን ተከትሎ የመማር ማስተማር ስራውን አቋርጠው ተማሪዎችን ወደየቤተሰቦቻቸው የመለሱ ነበሩ::
አሁን ከዚህ ሁሉ ውጣውረድ በኃላ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች እና የትምህርት ደረጃዎች እየተመረቁ ነው::
ቀጣዩ ጥያቄ ሀገሪቱ አሁን ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ የስራ እድል አለ ወይ የሚል ይሆናል:: የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥረው የነበሩ የጸጥታ ችግሮች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ መጉዳታቸውን መንግስት ሲያስታውቅ ቆይቷል::
ከዚህ በተጨማሪ የተማረው የሰው ሀይል በከተሞች አካባቢ ብቻ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለ በስፋት ሲነገር ቆይቷል:
ለመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች በመንግስት እና በግል ኩባንያዎች ተቀጥረው ለመስራት ከመዘጋጀት ባሻገር በግል ስራ የመፍጠር እድሉን ስንቶቹ ይኖራቸው ይሆን? ይህን ለማድረግስ ከማን ምን ይጠበቃል ትላላችሁ :: ሀሳባችሁን አጋሩን::
4.1K viewsDW Amharic, 12:00
Open / Comment
2021-02-10 20:13:14 ዋና ዋና ዜናዎቹ፤

የኢትዮጵያ መንግሥት የአውሮጳ ሕብረት «በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ነው» በማለት ያወጣውን መግለጫ ነቀፈ። የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በበርካታ የትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን መንግሥት እየሠራ ነውም ብሏል:: በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር 80 በመቶ በሚሆነው የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ርዳታ እየደረሰው አይደለም ማለቱ ተዘግቧል።

በደቡብ ሳውድ አረቢያ በአውሮፕላን ማፈሪያ ላይ በደረሰ ጥቃት የመንገደኞች አውሮፕላን በእሳተ መያያዙን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደው የሁቲ አማፅያን ቡድን ኢላማዬን አሳክቻለሁ ብሏል።

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ ፌደራል መንግሥትና የክልል መንግሥታት ባስቸኳይ በመነጋገር ምርጫ ለማካሄድ እንዲስማሙ አሳሰበ።

በዛሬው ዕለት በተለያዩ ደሴቶች በሚበዙባቸዉ ሃገራት ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን ተሰማ። በኢንዶኔዢያ፤ በአይስላንድ፤ እንዲሁም በኒውዚላንድ ከባሕር ስር የተነሳው የመሬት ነውጥ የሱናሚ ማዕበል እንዳያስከትል ተሰግቷል።
https://p.dw.com/p/3pBPv?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
5.6K viewsDW Amharic, 17:13
Open / Comment
2021-02-10 20:11:58 https://p.dw.com/p/3pAsu?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.8K viewsDW Amharic, 17:11
Open / Comment
2021-02-10 20:11:16 https://p.dw.com/p/3pBJS?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.3K viewsDW Amharic, 17:11
Open / Comment
2021-02-10 20:09:59 https://p.dw.com/p/3pB8Z?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.0K viewsDW Amharic, 17:09
Open / Comment
2021-02-10 20:09:05 https://p.dw.com/p/3pAAH?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
3.9K viewsDW Amharic, 17:09
Open / Comment
2021-02-10 20:07:53 https://p.dw.com/p/3pAYg?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.2K viewsDW Amharic, 17:07
Open / Comment
2021-02-10 20:06:55 https://p.dw.com/p/3pAa2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.3K viewsDW Amharic, 17:06
Open / Comment
2021-02-10 18:17:53 አድማጮቻችን ስጭታችንን በራዲዮ፤ በ11,830 ኪሎ ኸርዝ 25 ሜትር ባንድ እና 9555 ኪሎ ኸርዝ፣ 31 ሜትር ባንድ ላይ ይደመጣል። በሳተላይት በበድር 4፣ በ12,111 ሜጋ ኽርዝ፣ ሆሪዞንታል DWA2፤ በዩቴል-ሳት 8WB በ11,137 ሜጋኸርዝ፣ ሆሪዞንታል DWA2፤ በሆትበርድ 13 B፣ በ11,727 ቨርቲካል፣ DW08፤ እንዲሁም በSES-5 በ12,034 ሜጋ ኼርዝ፤ ሆሪዞንታል DW08 ላይም እንገኛለን።ዝግጅታችንን ከምናሰራጭባቸዉ የሳተላይት መስመሮቻችን አንዱ የነበረዉ ናይል ሳት ካለፈዉ ታሕሳስ 21 ጀምሮ አገልግሎት አስይሰጥም። በሌላ በኩል ሥርጭታችንን በዩቴልሳት ለማዳመጥ DVB-S2 ደረጃ ያለው ማለት የHD ሥርጭትን መቀበል የሚችል ቴሌቪዥን ያስፈልጋል። ሆኖም አንዳንድ ቴሌቪዥኖች ዩቴልሳት ሊኖራቸው ስለሚችል በተመሳሳይ መስመር መፈለግ ይቻላል።
3.1K viewsDW Amharic, 15:17
Open / Comment
2021-02-10 18:16:54
ኬንያ ከሶማልያ በምትዋሰንበት ሰሜናዊ ክፍል የአሸባብ ታጣቂዎች እያደረሱ ነው የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ነው:: በእካባቢው ማንዴራ የተባለች ግዛት እስተዳዳሪዎች እንዳስታውቁት የታጣቂዎቹን ጥቃት በመስጋት 126 ት/ቤቶች አሁንም ድረስ አልተከፈቱም:: በአካባቢው ታጣቂዎች በመንገድ ዳር እያደረሱ ያለውን የቦምብ ጥቃትን በመስጋት መምህራን እና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት መሄድ አለመቻላቸው ተገልጿል:: በግዛቲቱ የሚገኙ ጎዳናዎች በታጣቂዎቹ እጅ መውደቃቸው ለጥቃቱ መባባስ አስተዋጽዖ ማበርከቱም ተነግሯል:: ታጣቂዎቹ መንገደኞችን ያስጨንቃሉ :: የመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ዋነኛ ትኩረታቸው መሆኑ ተገልጿል:: በተጨማሪም ታጣቂዎቹ ለእጅ ስልኮች ኔትወርክ የሚያቀርቡ ማማዎችን ማውደማቸው ችግሩን እንዳባባሰው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል:: ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት አሸባብ ኬንያ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ሀይሉን እያጠናከረ መምጣቱ ተዝግቧል::
3.1K viewsDW Amharic, 15:16
Open / Comment