🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.90K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 585

2021-02-10 18:16:54
ኬንያ ከሶማልያ በምትዋሰንበት ሰሜናዊ ክፍል የአሸባብ ታጣቂዎች እያደረሱ ነው የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ነው:: በእካባቢው ማንዴራ የተባለች ግዛት እስተዳዳሪዎች እንዳስታውቁት የታጣቂዎቹን ጥቃት በመስጋት 126 ት/ቤቶች አሁንም ድረስ አልተከፈቱም:: በአካባቢው ታጣቂዎች በመንገድ ዳር እያደረሱ ያለውን የቦምብ ጥቃትን በመስጋት መምህራን እና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት መሄድ አለመቻላቸው ተገልጿል:: በግዛቲቱ የሚገኙ ጎዳናዎች በታጣቂዎቹ እጅ መውደቃቸው ለጥቃቱ መባባስ አስተዋጽዖ ማበርከቱም ተነግሯል:: ታጣቂዎቹ መንገደኞችን ያስጨንቃሉ :: የመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ዋነኛ ትኩረታቸው መሆኑ ተገልጿል:: በተጨማሪም ታጣቂዎቹ ለእጅ ስልኮች ኔትወርክ የሚያቀርቡ ማማዎችን ማውደማቸው ችግሩን እንዳባባሰው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል:: ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት አሸባብ ኬንያ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ሀይሉን እያጠናከረ መምጣቱ ተዝግቧል::
3.1K viewsDW Amharic, 15:16
Open / Comment
2021-02-10 18:15:30
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ መተከል ዞን ለተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ:: ፓርቲው ካለፈው እሁድ ጀምሮ ሲያካሂድ የነበረውን ኮንፈረስ ዛሬ ካጠናቀቀ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫው "በሠላምና መረጋጋት ዕጦት ስትጠቀስ ማስተዋል በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የደረሰው ሞትና መፈናቀል ልብ ሰባሪ መቼም እና የትም መደገም የሌለበት አሳዛኝ ድርጊት በመሆኑ መላ የክልላችንን ኗሪዎች ይቅርታ እየጠየቅን በተግባር ለመካስ መዘጋጀታችንን እናረጋግጣለን" ብሏል፡: ነገር ግን በክልሉ የደረሰው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ዝርዝርን በተመለከተ እንዲሁም ለተጎጂዎች ሊደረግ ስለሚገባ ዝርዝር የካሳ ሁኔታ ፓርቲው ያለው ነገር የለም:: ከዚህ ቀደም በዞኑ ለሚፈጠሩ ችግሮ የተለያዩ ምክንያቶች ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቋዋሚ ፓርቲዎችን እና ግብጽን ተጠያቂ ሲያደረጉ ነበር፡፡
3.0K viewsDW Amharic, 15:15
Open / Comment
2021-02-10 15:00:54
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1,500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዘገበች:: እትሌቷ በሀገሯ ልጅ ገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች በማሻሻል 3:53:09 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው:: በፈረንሳይዋ የሌቪን ከተማ ትናንት ማምሻውን በተደረገው የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ሌሎች ኢትዮጵያውያንም አሸናፊዎች ሆነዋል:: አትሌት ለምለም ሀይሉ በ3,000 ሜትር ርቀት አሸናፊ ስትሆን በወንዶች ተመሳሳይ ርቀት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት እሸናፊዎች ሆነዋል:: ውድድሩን ጌትነት ዋለ 1ኛ በመውጣት አሸንፏል::
3.9K viewsDW Amharic, 12:00
Open / Comment
2021-02-10 15:00:01
የኢትዮጵያ መንግስት የአውሮጳ ሕብረት «በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ነው» በማለት ያወጣውን መግለጫ ነቀፈዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር እንደሚለዉ የሕብረቱ መግለጫ መንግሥት በክልሉ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ርዳታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው።የአውሮጳ ሕብረት ትናንት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ዉስጥ መግባት እና በክልሉ እየተፈጠረ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦኛል ብሎ ነበር።የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ለሕብረቱ መግለጫ በሰጠዉ መልስ "መንግሥት በአካባቢው የሕግ ማስከበር ስራን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሕብረቱ የሚያወጣው መግለጫ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ እና ተገቢነት የሌለው ነው" ሲል ወቅሷል። የአውሮጳ ሕብረት ትናንት እውጥቶ በነበረው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢያዎች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ እና ለስደተኞችና ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቋል።የመንግስታቱ ድርጅት 25 የዕርዳታ አቅራቢ ሰራተኞች ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ማግኘቱን አስታዉቋል።የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር <<የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በበርካታ የትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን መንግሥት እየሰራ ነው>> ብሏል::
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ 4.5 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልገዋል :: ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ የተረጂዎችን ቁጥር ከ2.5 ሚልዮን እንደማያልፍ ሲገልፅ ቆይቷል::
3.9K viewsDW Amharic, 12:00
Open / Comment
2021-02-10 14:57:27
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ እንቅስቃሴ ሲደረጉ ብዙ አይስተዋልም። የምርጫ ቦርድ እስከ ምርጫ ክልል ድረስ በመውረድ ጽህፈት ቤቶችን የማዋቀር ስራ ከክልሎች ጋር በመተባበር እያከናወነ መሆኑን አስታውቆ ነበር። የምርጫ ቦርድ እያደረኩ ነው ከሚለው ዝግጅት አንጻር በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ እንደ የምርጫ ዓመት የጎላ እንቅስቃሴ እንደማይታይ በርካቶች ይናገራሉ። ሰሞኑን ገዢው የብልጽግና ፓርቲን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች በአብዛኞቹ የሀገሪቱ ክፍል እየተካሄዱ ነው። መንግስት« ህግ የማስከበር ዘመቻ » ካለዉ የትግራይ ጦርነት በኋላ ከትግራይ ክልል ውጭ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ምርጫው መደረጉ የማይቀር ይመስላል። ነገር ግን በሀገሪቱ አሁንም ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉ በስፋት ይነገራል። ከሱዳን ጋር የተፈጠረው ውጥረት ፣ታዋቂ ፖለቲከኞች መታሰር እና በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ሲደረጉ የነበሩ ግጭቶች መፍትሔ አለማግኘታቸዉ የምርጫዉን ዝግጅትና ሒደት ላለማወካቸዉ ዋስትና የለም የሚሉ አሉ።የናንተስ አስተያየት ምድነዉ? ምርጫውን በተመለከተ? በየአካባቢያችሁ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴስ ምን ይመስላል? ሀሳባችሁን አጋሩን።
3.9K viewsDW Amharic, 11:57
Open / Comment
2021-02-09 20:28:13 *በምያንማር የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እና የፕላስቲክ ጥይቶችን በመተኮስ ጉዳት ማድረሱ ተገለጠ። የምያንማር መንግሥት ቴሌቪዥን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን በተንቀሳቀሰበት ወቅት ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰልፈኞች ዛሬ ዘግቧል። የምያንማርን ሲቢላዊ መንግስት አስወግዶ ሥልጣን የያዘዉን ወታደራዊ ኹንታ የሰጠዉን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ተቃዋሚዎች የጀመሩት ሰልፍ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ዛሬ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች አደባባይ መውጣታቸው ተዘግቧል። ሰልፈኞች በወታደራዊ ኹንታው ከሥልጣናቸው የተወገደዉ የሐገሪቱ መንግሥት ወደ ሥልጣን እንዲመለስ እየጠየቊ ነው።

የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ በድምጽ እዚህ https://p.dw.com/p/3p8F6?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ማድመጥ ይቻላል።
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ደግሞ ይኽን ይጠቀሙ @dwamharicbot
5.6K viewsDW Amharic, edited  17:28
Open / Comment
2021-02-09 20:28:12 ዜናው በዝርዝር

*የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) 25 ተጨማሪ ሠራተኞቹ ትግራይ ክልል ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃድ ማግኘቱን ዐስታወቀ።ፈቃዱን አስመልክቶም፦ የዓለም አቀፍ ድርጅት ዋና ፀሐፊ የአንቶኒዮ ጉተሬሽ ቃል አቀባይ ሽቴፋን ዱዦሪክ፦ የርዳታ ሠራተኞች ትግራይ ክልል ውስጥ በተቀላጠፈ መልኩ ርዳታ ማቅረብ እንዲችሉ «የመጀመሪያው ርምጃ ነው» ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያከናወናቸውን ቀና ያሉትን ቊርጠኝነት ቃል አአቀባዩ በመግለጫቸው አውስተዋል። በአሁኑ ወቅት 60 የሚጠጉ የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ ሠራተኞች ወደ ትግራይ ለመንቀሳቀስ አዲስ አበባ ሆነው እንደሚጠብቊም ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል። የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP)የኢትዮጵያ መንግሥት፦ «ወደ ትግራይ የሚገቡ እና የሚሠራጩ የርዳታ ጭነቶችን» በተመለከተ «ባለሥልጣናቱን እና የርዳታ ድርጅቶቹን ለማገዝ» አቀረበ ያለውን ጥያቄም መቀበሉንም ዐስታውቀዋል። ከዚያም ባሻገር የዓለም ምግብ ድርጅቱ እስከ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች ትግራይ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ለማቅረብ መስማማቱንም ጠቊመዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተጨማሪ ሠራተኞች ፈቃድ መስጠቱን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፦ መንግሥት ቃሉን እንዲጠብቅ ጠይቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋሮቹ ቀደም ሲል 1,8 ሚሊዮን ለሚጠጋ ነዋሪ ትግራይ ውስጥ ርዳታ ማድረሳቸውን የዓለም ምግብ ድርጅት ኃላፊ ዳቪድ ቤያስሌይ ማወደሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር ዛሬ በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ገልጧል። በሁለት የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ 26,000 ኤርትራውያን ስደተኞችም የምግብ ርዳታ እና የአልሚ ምግብ እንደታደላቸው አክሎ ጠቅሷል።

*ሦስት የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽነሮች ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ፦ ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት እያባባሱ የሚገኙ ያሏቸው የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ።ዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ከዚሕ ቀደም ያደረገችዉን ጥሪ ሕብረቱ እንደሚደግፍ ኮሚሽነሮቹ አስታዉቀዋል። የኤርትራ ወታደሮች ግፍ ይፈጽማሉ፣ ግጭት እና ኹከት እንዲባባስም ሰበብ ሆነዋል ብሏል የኅብረቱ ሦስት ኮሚሽነሮች የጋራ መግለጫ። መግለጫውን የሰጡት የኅብረቱ የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል፤ የአስቸኳይ ርዳታ ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች እና የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነሯ ጁታ ኡርፒላይነን ናቸው።ትግራይ ክልል ውስጥ እየታየ ያለው «አስከፊ» የሰብአዊ ቀውስ እና በአካባቢው ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ያሳሰባቸው መሆኑን አክለው ገልጠዋል። የሰብአዊ ርዳታው መዳረስ በትግራይ ክልል እና በአጎራባች አካባቢዎች የአፋር እና የአማራ ክልሎችም የሰብአዊነት መርኆችን፣ ገለልተኝነትን፣ ሰብአዊነትን፣ ለማንም ባልወገነ እና ነጻ በሆነ መልኩ ሊረጋገጥ እና ሊፈቀድ ይገባል ብለዋል።

*የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ሠርጌ ላቭሮቭ፦ የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ክልል ውስጥ የሰብአዊ ተግዳሮትን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት የሩስያ ፌዴሬሽን ዕውቅና እንደሚሰጥ ገለጡ። የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ይህን ያሉት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ እና ምክትል ሚንሥትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነው። በውይይቱ ወቅትም አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው መልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ለሠርጌ ላቭሮቭ ማብራራታቸው ተጠቊሟል። ትግራይ ውስጥ የሰብአዊ ድጋፍ ኹኔታ ስኬታማ በሆነ መልኩ መቀጠሉን ማብራራታቸውንም ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ገልጧል። ሠርጌ ላቭሮቭ የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን የሰብአዊ ተግዳሮትን በተመለከተ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚረዱ መንግሥታቸውም በዚህ ጉዳይ ኢትዮጵያን መርዳቱን ለመቀጠል ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ጠቊመዋል። ሩስያ አባል የሆነችበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በትግራይ ጉዳይ በዝግ መምከሩ የሚታወስ ነው።

*ኢትዮጵያ እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ 9 ሚሊዮን የኮሮና ተሐዋሲ መከላከያ ክትባት ብልቃጦችን ለማስገባት ማቀዷ ተገለጠ። የትኞቹ አይነት ክትባቶች እንደሆኑ ግን አለመገለጡን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ክትባቶቹን ለማስገባት ግዢ የፈጸመችው በቀጥታ ሳይሆን ክትባቶችን ለሁሉም ሃገራት ለማዳረስ የዓለም ጤና ድርጅት እና አጋሮቹ በተቋቋመው ኮቫክስ ከተሰኘው ተቋም መሆኑም ተጠቅሷል። ኮቫክስ በጣምራ የሚመራው ደሃ ሃገራት ክትባቶች እንዲዳረሣቸው ይንቀሳቀሳል በተባለው ጋቪ ጥምረት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ከ142 ሺህ በላይ ሰዎች ተመርምረው 2,154 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የጤና ሚንሥትር መረጃ ይጠቊማል። ኮቫክስ ክትባት አቅራቢ ተቋም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቢያንስ 330 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን ለደሃ ሃገራት ለማቅረብ አቅዷል። ለደሃ ሃገራት ይቀርባሉ ከተባሉት የክትባት ብልቃጦች መካከል 240 ሚሊዮን የሚደርሰው የህንድ ተቋም ከሚያመርተው አስትራዜኔካ-ኦክስፎርድ የሚገኝ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ቀሪው 96 ሚሊዮን ከአስትራዜኔካ መሆኑ ተጠቊሟል። አውራፓውያን የሚረባረቡበት ፕፋይዘር ባዮንቴክ ክትባት ግን 1,2 ሚሊዮን ብቻ ነው ለድሃ ሃገራት ሊሰጥ የታሰበው። ደቡብ አፍሪቃ አስትራዜንካ ስተባለዉ የኮሮና መከላከያ ክትባት ዝርዝር መረጃ እስከምታገኝ ክትባቱን ጥቅም ላይ እንደማታዉል መግለጿ ትናንት ተዘግቧል።

*በደብረ ማርቆስ ከተማ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 10 የሚሆኑ የሉካንዳ ቤቶች መቃጠላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የፖሊስ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አጃናው አዲስ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከንጋቱ 12 ሠዓት ተኩል አካባቢ በከተማዋ ቀበሌ 01 በተነሳው ቃጠሎ 10 ሉካንዳ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ እሳቱ ወደሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የከተማው ወጣቶች ተቆጣጥረውታል ብለዋል፡፡ የጉዳቱ መጠን እየተጠና ሲሆን በቅርቡም በተመሳሳይ ሁኔታ በከተመው የሸቀጦች መሸጫ ላይ ቃጠሎ ተከስቶ ከ20 በላይ አነስተኛ ሱቆች ከነንብረታቸው መውደማቸውን አስታውሰዋል።

*ምሥራቅ አፍሪቃን ከዚህ ቀደም ከታየው የበረታ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ሊያጠቃት እንደሚችል ጀርመን አኸን ከተማ የሚገኘው ሚዜሬዎር የተሰኘው የርዳታ ተቋም አስጠነቀቀ። ከአንድ ዓመት በፊት ከታየው የባሰ ነው የተባለለት ሁለተኛ ዙሩ መጠነ ሰፊ የበረሃ አንበጣ መንጋ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ ውስጥ ከፍተኛ የሰብል ጥፋት ሊያደርስ መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል ርዳታ ድርጅቱ። መንጋው ከፍተኛ የሰብል ጥፋት አድርሶ ረሐብ ሊቀሰቅስም ይችላል ሲል ሚዜሬዎር አስጠንቅቋል። የኦለም ምግብ ድርጅት (FAO) በበኩሉ የበረሃ አንበጣ መንጋው ወደ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ ድረስ ሊሠራጭ ይችላልም ብሏል።
4.9K viewsDW Amharic, 17:28
Open / Comment
2021-02-09 20:13:01 ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና የኮሮና ወረርሽኝ

በየዓመቱ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር የካቲት 6 የሴት ልጅን ግርዛ ፈጽሞ ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት በዓለም ደረጃ ይታሰባል። ኢትዮጵያ እስከ 2025 ዓ,ም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱን ለማስቆም ብታቅድም ተግባራዊነቱ ግን እያነጋገረ ነው። በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያትም በአዳጊና አዋቂ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መባባሳቸው ተሰምቷል።
https://p.dw.com/p/3p8D2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
4.2K viewsDW Amharic, 17:13
Open / Comment
2021-02-09 20:12:04 ጀርመን ኢትዮጵያዉያንን መመለስዋን ቀጥላለች

ጀርመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ መጠረዝዋን ቀጥላለች። በጀርመን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የሰብዓዊ ጉዳይ አቀንቃኞች ይህን የጀርመን መንግሥትን ርምጃ እያወገዙ ነዉ።
https://p.dw.com/p/3p843?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
3.9K viewsDW Amharic, 17:12
Open / Comment
2021-02-09 20:10:27 የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ

ትናንት መቀሌ የገቡት የኢትዮጵያ የተለያዩ የኃይማኖት መሪዎችና የሐገር ሽማግሌዎችም እዚያዉ መቀሌ ዉስጥ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ባለሙያዎችና ከከተማዋ የተወሰኑ ነዋሪዎች ጋር ተነጋግረዋል።
https://p.dw.com/p/3p7s5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
3.7K viewsDW Amharic, 17:10
Open / Comment