🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.90K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 582

2021-02-12 19:42:49 https://p.dw.com/p/3pGWx?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.7K viewsDW Amharic, 16:42
Open / Comment
2021-02-12 18:25:13
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በርካታ ሴቶች የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ። «በክልሉ በሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈጸሙን በስፍራው ካለው ግብረኃይላችን መረጃ አግኝንተናል» ሲሉ የሴቶች ሚንስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ ትናንት ሐሙስ ምሽት በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። የፌዴራሉ መንግስት « ህግ የማስከበር ዘመቻ» ባለው እና ሕወኃት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በሴቶች ላይ በተከታታይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሲደርስባቸው እንደነበር የአይን ምስክሮች ፣ የህክምና ባለሞያዎች እና የረዲኤት ሰራተኞች ሲያስታውቁ ቆይተዋል። በመንግስት በኩል ለደረሰው ጥቃት እውቅና ሲሰጥ የሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ የመጀመርያው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን እንዳስታወቀው በትግራይ 108 የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በክልሉ መዲና የመቀሌ ከተማ በሁለት ወር ውስጥ የተፈጸመ እንደነበር ገልጿል። ከፊሎቹ ተጠቂዎች ጥቃቱን ያደሩሳበቸው የፌዴራል መንግስቱ ወታደሮች እና አጋሮቻቸው እንደሆኑ ቢገልጹም የጥቃት አድራሾችን ብዛት ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አለመቻሉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንደሚለው የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሪፖርት ያልተደረገባቸው አካባቢዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክቷል።መንግስት ጾታዊ ጥቃትን እንደማይታገስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።
ፎቶ/የኢትዮጵያ ሴቶች ሚንስትር
4.9K viewsDW Amharic, 15:25
Open / Comment
2021-02-12 16:20:36
አጣሪ ጉባኤው ባለፉት 5 ዓመታት 14 ጉዳዮችን ብቻ ተመለክቷል!
ህብረተሰቡ የህገመንግስት ትርጉም የሚስፈልጋቸውን ጥያቄዎች ባግባቡ መገንዘብ ባለመቻሉ ባለፉት 5 ዓመታት የቀረቡ አቤቱታዎች በጣም ዝቅተኛ መሆናቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
የፍርድ ቤቱ ፕረዚደንትና የአማራ ክልል ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ አቶ አብዬ ካሳሁን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከ2008 ዓ ም ጀምሮ 14 ብቻ የህገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች ቀርበዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 4ቱ የህገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልጋቸው አቤቱታዎች ሆነው በመገኘታቸው በውሳኔ ሀሳብ በማስደገፍ ለመጨረሻ ውሳኔ ለአማራ ክልል ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን ተልከው የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል እንዲፀኑ መደረጉንም አቶ አብዬ ተናግረዋል፡፡
10ሩ ደግሞ እንደማያስፈልጋቸው የውሳኔ ሀሳብ እንደቀረበባቸውም አስረድተዋል፡፡ የአቤቱታዎቹ ቁጥር አናሳነት ችግር አለመኖሩን የሚያሳዩ እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕረዚደንቱ፣ በየደረጃው የህገመንግስት ትርጉም የሚሹ ኢ ህገመንግስታዊ ህጎች፣ የተዛቡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና የፍርድ ቤት ዳኝነቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ መብቱን ወደ ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አቤት ማለት አለባቸው ሲሉ አመልክተዋል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ ካለው የህዝብ ቁጥር አኳያ የህገመንግስት ትርጉም አቤቱታዎች በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘታቸው ህብረተሰቡ ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንደሌለው ማሳያ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዬ፣ የህግ አዋቂዎች፣ ብዙሀን መገናኛና የህግ ተቋማት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል፡፡
አማራ ክልል 11 አባላት ያሉት የህገ መንግስት አጣሪ ጉበኤ አሉት፡፡
5.1K viewsDW Amharic, 13:20
Open / Comment
2021-02-12 16:19:16
የአውሮጳ ህብረት ማዕቀብ የሚጥልባት ከሆነ ግንኙነቷን ልታቋርጥ እንደምትችል ሩስያ አስጠነቀቀች። ሩስያ ማስጠንቀቂያውን የሰጠችው ምዕራባውያኑ በአሌክስ ናቫልኒ መታሰር በሩስያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ ሩስያ ከሕብረቱ ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ልታቋርጥ እንደምትችል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ስርጌይ ላቭሮቭ ተናግረዋል። ላቭሮቭ ዛሬ በቴሌግራም በሚተላለፍ አንድ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ «ከሕብረቱ ጋር ግንኙነት ታቋርጡ ይሆን» ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ »ሕብረቱ የሩስያን ኢኮኖሚ ሊጎዳ የሚችል የማዕቀብ እርምጃ ከወሰደ ሩስያም በበኩሏ የራሷን እርምጃ ትወስዳለች » ሲሉ ተደምጠዋል። « ለዚያ ደግሞ ዝግጁ መሆናችንን እንቀጥላለን» ብለዋል ላቭሮቭ ፡፡ ከዓለማቀፍ ግንኙነት ራሳችንን መነጠል አንፈልግም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ «ነገር ግን ለዚያ ዝግጁ መሆን ይኖርብናል ፤ «ሰላም ከፈለክ ለጦርነት ተዘጋጅ» የሚል አባባል ለንግግራቸው ተጠቅመዋል፡፡የህብረቱ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን በበኩላቸው ሩስያ ለብቻዋ ለመነጠል እና ምዕራባውያንን ለመከፋፈል እየጣረች ነው ሲሉ ወቅሰዋል። በአውሮፓ ህብረት የሩሲያ ተወካይ ቭላድሚር ቺዝሆቭ ቀደም ሲል ዛሬ አርብ ጥዋት በኢዝቬሺያ ጋዜጣ ላይ በተለይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሩሲያ እና የአውሮፓ ህብረት ውይይቶች እንደሚቀጥሉ እና የቦረል ወደ ሞስኮ ለመጓዝ ፈቃደኛ መሆናቸው ነገሮች መስመር እንዳይለቁ ለማድረግ የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል ፡፡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ጀርመን እና ፈረንሳይ ይሁንታቸውን ከሰጡ በኋላ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አጋሮች ላይ የጉዞ እቀባ እና የንብረት እገዳ ለመጣል አቅዷል ፡፡
4.3K viewsDW Amharic, 13:19
Open / Comment
2021-02-12 16:18:36 በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ውጥረት በውይይት መፍታት እንደሚገባ የሁለቱ አገሮች ምሁራን ገለጡ፡፡ ከሱዳን የመጡና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በባሕር ዳር ባደረጉት ውይይት የተፈጠረውን የድንበር ጉዳይ በጦርነት መፍታት ዘላቂ መፍትሔ የለውም ብለዋል። ለመፍትሄው ውይይት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ታሪክ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አይቸግረው አደራ እንዳሉት የድንበር ጉዳይ የሁለቱ አገሮች ችግር ብቻ እንዳልሆነ አስታውሰዋል ። ቅኝ ገዥዎች የፈጠሩት ችግር የብዙ አፍሪካ አገሮች ተግዳሮትና የግጭት ምንጭ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ የሰሩት በወሎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር መምህር ዶ/ር ዓለማየሁ እርቅይሁን በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ችግር በውይይት መፈታት አለበት፣ ያ የሚሆነው ግን ሱዳን ወደነበረችበት ስትመለስ ብቻ ነው ብለዋል፡፡ በሱዳን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የስነጥበብ ፕሮፌሰር ዶ/ር ኡመር አላሚን በበኩላቸው ሁለቱም አገሮች ህዝቦቻቸውን ወዳልተገባ ሁኔታ የሚወስዱ ሽፍቶችን ማስወገድ አለባቸው ሲሉ ለዶይቼ ቬከ ገልፀዋል፡፡
4.2K viewsDW Amharic, 13:18
Open / Comment
2021-02-12 16:17:30
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተደረገው ጦርነት በርካታ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ማስከተሉ ሲነገር ቆይቷል። ጦርነቱን ተከትሎ ከደረሰው የህይወት እና የአካል ጉዳት ባሻገር የዜጎች ከመኖርያ ቄዬአቸው መፈናቀላቸው እና በርካታ ማሕበራዊ ችግሮች መፈጠራቸውም እንዲሁ በመንግስትም ሆነ በሌሎች አለማቀፍ የመገናኛ ብዙኃን እና ተቋማት በኩል መረጃዎች ሲወጡ ቆይቷል። በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ቀውስ ባሻገር በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱ ሰብአዊ እና ሌሎች ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸው አለመረጋጋቶችን በተመለከተ ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች አካላት የሚወጡ መረጃዎች ሚዛናቸውን ያልጠበቁ ስለመሆኑ ሲነገር ይሰማል። በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስንም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚደርሱ ሰብአዊ ችግሮች በመንግስት ፣ በሌሎች የአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የረድኤት ድርጅቶች የሚወጡ መረጃዎች ምን ያህል ሚዛናቸውን የጠበቁ ናቸው? እርስ በእርሳቸው የተጣረሱ መረጃዎች እንዲወጡ ምክንያቱ ምን ይሆን የዜጎች ትክክለኛ መረጃን ከማግኘት መብት እና ከወገንተኝነት የጸዳ እና ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት አንጻር ምን መደረግ አለበትስ ትላላችሁ? ሀሳባችሁን አካፍሉን።
7.1K viewsDW Amharic, 13:17
Open / Comment
2021-02-12 13:33:19 https://p.dw.com/p/3pGEt?maca=amh-Facebook-dw
5.3K viewsDW Amharic, 10:33
Open / Comment
2021-02-11 20:41:20 በአዲስ አበባ የእናቶች ሆስፒታል ምርቃት

በአይነቱ ልዩ እና በርካታ መስፈርቶችን ያሟላ ነው የተባለ የእናቶችና የሕጻናት ሆስፒታል ዛሬ በአዲስ አበባ ተመረቀ። በክቡር ዶክተር አበበች ጎበና ስም የተሰየመው ሀኪም ቤት በአዲስ አበባ አያት ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ነው ለአገልግሎት ክፍት የሆነው።
https://p.dw.com/p/3pEQ3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
6.4K viewsDW Amharic, 17:41
Open / Comment
2021-02-11 20:38:58 *በሚያንማር ወታደራዊ የመንግሥት ግልበጣው ዐሥረኛ ቀኑን ካስቆጠረ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ብርቱ ርምጃ እንደምትወስድ ገለጠች። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ የተሳተፉ ጄኔራሎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ድርጅቶች ላይ አሜሪካ የማዕቀብ ቅጣት እንደምትፈጽም ዝታለች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን፦ በእስር ላይ የሚገኙት የኖቤል ተሸላማሚዋ አውንግ ሳን ሱ ኪ እንዲፈቱ፤ ሀገሪቱም ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንድትመለስ አሳስበዋል። በመላ ሀገሪቱ ወታደራዊ አመራሩን በመቃወም ዛሬም በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተዋል። ከሚናምማር ውጪም የተቃውሞ ሰልፎች ተከናውነዋል። ጃፓን ውስጥ በተደረገ ሰልፍ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰብ ለሳን ሱኪ እና ደጋፊዎቻቸው አለኝታነታቸውን ዐሳይተዋል። «የሚያንማር ጦር ሠራዊ አመራር ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ለዓለም እንነግራለን። ለሳስን ሱ ኪ መልእክቴ፦ በአንድነት ለመተባበር ተግተን እየሠራን ነው፤ ተስፋ እንዳይቆርጡ የሚል ነው። እሳቸውም ወታደራዊ አገዛዙን እስኪያሸንፉ በርቱ ተስፋ አትቊረጡ።» በሚያንማር መዲና ናይፒይዳው የጦር ሠራዊቱ ላይ ጫና ለማሳደር በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ መሐንዲሶችም ዛሬ የተቃውሞ ሰልፉን መቀላቀላቸው ተዘግቧል። በመላ ሀገሪቱ የተቃውሞ ሰልፉ ዛሬ ስድስተና ቀኑን አስቆጥሯል።

*የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የመከሰስ መብትን ለማንሳት ለሁለተኛ ጊዜ የተጀመረው ሒደት ሦስተኛ ቀኑን ዛሬ አስቆጥሯል። ዶናልድ ትራምፕ በመዲናዪቱ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ፓርላማ ሕንፃ ላይ ለደረሰው ኹከት ተጠያቂ ናቸው ለማለት ዴሞክራቶች ጫፍ መድረሳቸውም ተዘግቧል። ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ለኹከት እንዲነሳሱ ያደረጉበት የተባለ የቪዲዮ ምስል ትናንት በማስረጃነት ቀርቧል። የዶናልድ ትራምፕ ጠበቆች የቀድሞው ፕሬዚደንት ምርጫው ተጭበርብሯል ብለው ለማወጅ የመናገር ነጻነት አላቸው ሲሉ ተከራክረዋል። ዴሞክራቶቹ ዶናልድ ትራምፕን ለመክሰስ አጠቃላይ 50 ዴሞክራት ሴናተሮች እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፓርቲ የሪፐብሊካን አባላት ከሆኑት 50 ሴናተሮች የ17ቱ ድምፅ ያስፈልጋቸዋል።

*ቲክቶክ የተሰኘው የቪዲዮ ምስሎች ማጋሪያ የማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ የቀጣዩ የአውሮጳ ዋንጫ ስፖንሰር እንደሆነ የአውሮጳ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት (UEFA) ይፋ አደረገ። ውድድሩን በገንዘብ በመደገፍ ቲክቶክ አራተኛው የቻይና ድርጅት ኾኗል። ቲክ ቶክ የአውሮጳ የእግር ኳስ ዋንጫን ለመደገፍ ምን ያህል ገንዘብ እንደበጀተ ግን አልተገለጠም። የ2020 አውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫ በኮሮና ተሐዋሲ ስርጭት ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወቃል።

የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ ማድመጥ እዚህ https://p.dw.com/p/3pEjw?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ይቻላል። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
5.5K viewsDW Amharic, 17:38
Open / Comment
2021-02-11 20:38:58 የየካቲት 4 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. የዓለም ዜና

*ሒውማን ራይትስ ዎች የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት፦ በትግራይ ገጠራማ አካባቢዎች ከሦስት ወር በፊት ከጦርነት ሕግ ውጪ የሆኑ የመድፍ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ዛሬ ገለጠ።ድርጅቱ በተዋጊ ኃይላት ተፈጸሙ የተባሉትን ጥሰቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲያጣራ ጠይቋል። ዓለም አቀፍ ድርጅቱ፦ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ 37 ምስክሮችን በስልክ በማነጋገር ባለፉት ሁለት ወራት አሰባሰብኩት ባለው መረጃ የኢትዮጵያ ጦር ያለ ጥንቃቄ ገጠራማ ቦታዎችን ደብድቧል ብሏል። ሕወሓት ከመቀሌ ወደ ባህርዳር እና ኤርትራ መዲና አስመራ ሮኬቶችን ሲያስወነጭፍ እንደነበር ግን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ አልዘገበም። የኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መኮንንኖች በውጊያው ወቅት የኢትዮጵያ ጦር ስነ ምግባርን የተከተለ ነበር፤ በውጊያ ወቅት የሚከሰተው ተጓዳኝ ጉዳትም አነስተኛ ነው ማለታቸውን ግን ጠቅሷል። የዓለም አቀፍ ድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ኃላፊ ላቲፋ ባደር፦ ጥንቃቄ ያልነበረው ባሉት ጥቃት «ሰላማዊ ሰዎች እና ንብረት» መጎዳታቸውንም ገልጠዋል። በያኔው ጥቃት ቢያንስ 83 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው እና 300 መቁሰላቸውንም መግለጫው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፦ «የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል፡ የመሰረታዊ ልማት፣ የማኅበራዊ እና የአስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ የመመለሱ ተግባር ልዩ ትኩረት ይሻል» ብሏል። ኮሚሽኑ ገና በአካል ተገኝቶ ክትትል ለማድረግ እንዳልቻለ በገለጠባቸው በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ስላለው ሁኔታም ገልጧል። «የሰው ሕይወት ማለፉን፣ የአካላዊ እና ሥነልቦናዊ ጉዳት መድረሱን፣ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት፣ ዘረፋ እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ስለመፈጸማቸው መረጃዎች» ደርሰውኛል ሲልም አክሏል።

*የአፋር ክልላዊ መንግሰት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ርዳታ ፈላጊዎች ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት እለታዊ ድጋፍ ማድረጉን ዐስታወቀ።ሌሎች ክልሎችም በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ የአፋር ክልላዊ መንግስት ጥሪ አድርጓል። የአፋር ክልል መንግስት የአደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ዛሬ ለዶይቼ ቬለ (DW)እንደገለፁት ክልሉ ድጋፉን የተለያዩ የመባእልት ድጋፍ አድርጓል። «የተደረገው ድጋፍ የተለያዩ የምግብ አይነቶች ናቸው። 1500ኩንታል ሩዝ አለበት፤ 900 ኩንታል ነጭ ዱቄት፤ እንዲሁም ፓስታ፣ ማካሮኒም አለ። ጨው ደግሞ 200 ኩንታል አለ። በአጠቃላይ 2700 ኩንታል ነው። በብር ሲተመን ከ9 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ርዳታ ነው የተደረገው።» አቶ መሐመድ ክልላቸው ለተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋልጦ እንደነበር በማስታወስ ዛሬ ያደረጉት ርዳታም ተርፏቸው ሳይሆን ወገንን ለማዳን የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። «እኛ ያቀረብነው በቂ ነው ማለት አይቻልም። እኛ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆነን ነው። እኛም የጎርፍ አደጋ፣ የአንበጣ እና ሌሎች ተዛማጅ አደጋዎች ነበሩብን።»

*በትግራይ ክልል አንዳንዶቹ 4 ሚሊዮን 500 ሺህ ህዝብ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገዉ የተለያዩ ወገኖች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የተባለው ቁጥር በመረጃ ያልተደገፈ መሆኑን በመግለጥ በክልሉ ያለው የተረጂ ቁጥር ከ2 ሚሊዮን 500 ሺህ እንደማይበልጥ በተደጋጋሚ አመልክቷል። የባህር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ከትግራይ ክልል ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት ባለስልጣናቱ ስልክ ባለማንሳታቸዉ አልተሳካም።
*የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፦«የትግራይ ክልል 80 በመቶው ከርዳታ አቅርቦት ተቋርጧል» ብሏል በማለት የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ) ያሰራጨዉን ዜና ማሕበሩ የተዛባ ነው በማለት ማዘኑን ገለጠ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፦ እስካሁን 400,000 ተረጂዎችን ማለትም ከአጠቃላዩ 20 በመቶውን መድረስ መቻሉን ገልጧል። ማኅበሩ ዛሬ ለሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ አውታሮች በሰጠው ጋጤጣዊ መግለጫ በትግራይ፣ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ተጨማሪ ሰዎች ርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ዐስታውቋል። በዛሬው መግለጫ፦ የቀይ መስቀል ማሕበር ዓለም አቀፍ ፕሬዚደንት ፍራንሴስኮ ሮካ እና የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ፕሬዚደንት አቶ አበራ ቶላ ከአዲስ አበባ እና ከጄኔቫ በኢንተርኔት መገናኘታቸውንም ተገልጧል። አቶ አበራ ቶላ፦ በእንግሊዝኛ የተናገሩት እና በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች የተሰራጨው አጠር ያለ ቪዲዮ «በአሁኑ ወቅት 80 በመቶው ትግራይ መድረስ የማይቻል ነው» ይላል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ቅሬታ ያቀረበበት የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዜናን በመጥቀስ፦ «ፕሬዚደንታችን በመግለጫቸው ወቅት መልከዓ-ምድራዊ ቦታዎችን አልጠቀሱም» ብሏል። ማኅበሩ ትግራይ ውስጥ ርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው ዜጎች ለመድረስ «መቼም ተከልክሎ ዐያውቅም» ሲል በመግለጫው አክሏል። አያይዞም የማኅበሩ ፕሬዚደንት «ትግራይ ውስጥ 80 በመቶ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ለመድረስ» በአሁኑ ወቅት ስላጋጠመው የአቅም እና የአቅርቦት እጥረት ነው የገለጡት ሲልም አስተባብሏል።

*ጀርመን የኮሮና ተሐዋሲ ሥርጭኅን ለመግታት የጣለችውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለተጨማሪ ሦስት ሳምንታት አራዘመች። የሀገሪቱ መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የተሐዋሲውን «አደገኘነት» በመጥቀስ «ብርቱ ጥንቃቄ» ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከክፍላተ ሃገራት መሪዎች ጋር ቀደም ሲል ባደረጉት ውይይት የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ የሚያበቃው የፊታችን እሁድ ነበር። ሆኖም እንደ ብሪታንያ እና ደቡብ አፍሪቃ ልውጥ የኮሮና ተሐዋሲ ጀርመን ውስጥ በመከሰቱም የሚያደርሰው ጉዳት ስለማይታወቅ ገደቡ መራዘም እንዳለበት ትናንት ማታ ተስማምተዋል። የኮሮና ተሐዋሲ ሥርጭት ግን ጀርመን ውስጥ በተወሰደው ጠንካራ ርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገልጧል። በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ የሆነው ምን ያህል ፍጥነት እና የጉዳት መጠን እንዳለው ያልታወቀው ልውጡ ተሐዋሲ ነው። ከ18 ቀናት በኋላ መዋዕለ ህጻናት እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱ፤ የጸጉር ቤቶችም በጥንቃቁ ሥራ መጀመር እንደሚችሉ ተገልጧል። ትምህርት ቤቶች መች ይጀምሩ ለሚለው ግን 16ቱ ክፍላተ ሃገራት መሪዎች በየግላቸው እንዲወስኑ ተብሏል። የጀርመን መሪዎች የእንቅስቃሴ ገደቡን ስለማንሳት ወይንም ስለማላላት፣ አለያም ስለማራዘም ለመወሰን የዛሬ ሦስት ሳምንት ቀጠሮ ይዘዋል።
4.1K viewsDW Amharic, 17:38
Open / Comment