Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.55K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 580

2021-02-15 20:18:48 ወደ መደበኛ ሕይወት የገቡት ወልቃይት ጠገዴና ሁመራ አካባቢዎች
በወልቃት ጠገዴና ሰቲት ሁመራ አካባቢዎች ህግ በማስከበር ዘመቻው ሥራ አቋርጠው የነበሩ አብዛኛዎቹ ተቋማት ወደ ስራ መግባታቸው ተነገረ። “በተለያዩ ምክንያቶች ፍርድ ቤቶች ግን ወደ ስራ አልገቡም” ፣ በአንዳንድ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች “ጠገዴ አካባቢ የፀጥታ ችግር አለ” እየተባለ የሚወራው ሀሰት መሆኑን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡https://p.dw.com/p/3pNPX?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.1K viewsDW Amharic, 17:18
Open / Comment
2021-02-15 20:15:03 ጊኒ ሦስት ሰዎች በኢቦላ በሽታ መሞታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ከህመምተኞቹ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች እያሰሰች ነው። በበሽታው ሊያዙ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችን እንዳገኘ በአካባቢው ክትባት የማዳረስ ሥራ እንደሚከናወን የሀገሪቱ ጤና ሚንስትር ሬሚ ላማህ ተናግረዋል። ጊኒ እጎአ ከ2013 - 2016 የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራትን ክፉኛ ያጠቃው የኢቦላ ወረርሽኝ ዳግም ተመሳሳይ ጥፋት እንዳያስከትል እና ለማስቆም ጥረት እያደረገች ነው። ቀደም ሲል በምዕራብ አፍሪቃ ለሦስት ዓመታት በቆየው እና በተለይ ጊኒን ያጠቃው ወረርሽኙ ሴራሊዮን እና ላይቤሪያን ጨምሮ ከ11,000 በላይ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል። ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተቀስቅሶ በርከት ያሉ ሰዎችን መግደሉ ተዘግቦ ነበር። ወረርሽኙ አሁን በድጋሚ በጊኒ መቀስቀሱ ስጋት ቢያሳድርም የሰለጠኑ የጤና ባለሞያዎች በአካባቢው በመሰማራታቸው «በሽታውን በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንችላለን » ሲሉ የጤና ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ነገርግን አሁን ከኢቦላ ታማሚ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ እና በመፈለግ ላይ የሚገኙ ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ የጤና ሚንስትሩ ያሉት ነገር የለም። ይህ ደግሞ በሽታው ወደ ጎረቤት ሃገራት ጭምር ሊዛመት የሚችልበት ዕድል እንዳለ ተነግሯል። ይህንኑ ተከትሎም ሴራሊዮንም በሽታው በቀላሉ ወደ ግዛቷ እንዳይዛመት ከጊኒ በምትዋሰንበት ድንበር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሯን አስታውቃለች።
4.0K viewsDW Amharic, 17:15
Open / Comment
2021-02-15 20:14:35 ማኅበረሰቡን የፈተነዉ የኑሮ ዉድነት
በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ያስከተለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የከተሜውን ሕይወት እየፈተነው ይገኛል። መንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እያደረገ ቢሆንም መቋሚያ ያጣው የሸቀጦች የዋጋ ማሻቀብ ከሥራ አጥነት ፣ ከወጪ ንግድ መቀዛቀዝ፣ ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ፣ ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ አናኗርን ፈተና ውስጥ እየጣለው ይገኛል። https://p.dw.com/p/3pNT7?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.1K viewsDW Amharic, 17:14
Open / Comment
2021-02-15 20:13:46 ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ድንበሬን ተሻግሮ «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ከሰሰች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እሁድ እንዳስታወቀው ድርጊቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረውን የድንበር ውዝግብ የሚያባብስ ነው ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ የሱዳንን ድንበር ተሻግራ መግባቷ አሳዛኝ ነው ያለው መግለጫው ውጤቱ አደገኛ እና ተቀባይነት የሌለው እንዲሁም በቀጣናው ደህንነት እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሏል። በኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቃባይ በኩል በጉዳዩ ላይ ለጊዜው የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም ቀደም ሲል የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውቆ ነበር። የአሁኑ የሱዳን ክስ ከመሰማቱ በፊት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ቅዳሜ በፌስ ቡክ ገጹ እንዳስታወቀው ሱዳን ውስጥ ከጥቅምት ወር የመጨረሻ ቀናት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸሙ ዝርፍያ እና የማፈናቀል ተግባራት እንዲቆም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሱዳን መንግሥት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል። አምባሳደር ዲና አያይዘው «ኢትዮጵያ የሁለቱን ሃገራት የድንበር ይገባኛል ጥያቄን በሦስተኛ ወገን መሸማገል አትፈልግም፤ የሱዳን ጦር በኃይል የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች ለቆ መውጣት ይኖርበታል ።» ማለታቸውም ተዘግቧል። ሱዳን ባለፈው ወር « የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ድንበሬን ተሻግሮ ገብቷል » ስትል የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ድርጊቱን አስተባብሎ ነበር። እንደሮይተርስ ዘገባ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ባለው የለም መሬት ላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረው የድንበር ይገባኛል ጥያቄ አንድ ክፍለ ዘመን ተሻግሯል።
3.4K viewsDW Amharic, 17:13
Open / Comment
2021-02-15 20:13:26 ሕዝባዊ አገልግሎትን ለማስተካከል ያለመ ዉይይት በባህርዳር
በአገር ደረጃ የሚታየውን ቅሬታ የበዛበት አገልግሎት አሰጣጥ ማስተካከል የሚያስችል አገርአቀፍ ህዝባዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለው ባለው ውይይት 30 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ለመድረስ መታቀዱንም ሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡https://p.dw.com/p/3pODi?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.2K viewsDW Amharic, 17:13
Open / Comment
2021-02-15 20:12:00 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ በምህጻሩ ኢዜማ በቢሾፍቱ ከተማ የአንድ ምርጫ ክልል ሊቀመንበር የነበሩ አባሉ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን አስታወቀ። ፓርቲው ዛሬ በትዊተር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ እንዳለው አቶ ግርማ ሞገሥ የተባሉ አባሉ ትናንት እሁድ የካቲት 07/2013 ምሽት ላይ መገደላቸውን አመልክቷል። ፓርቲው በአባሉ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቆ፤ ግድያውን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን አሰባስቦ እንደጨረሰ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
4.2K viewsDW Amharic, 17:12
Open / Comment
2021-02-15 11:53:35
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በአንዳንድ የምዕራብ ኦሮሚያ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሲያስጀምሩ ፤ ተገንብተው የተጠናቀቁትን ደግሞ መርቀው ከፍተዋል። በኢትዮጵያ ቀደም ሲል በተለይ ምርጫ በሚካሄድበት ዓመት እንዲህ በስፋት የግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ እና የተገነቡትን ማስመረቅ የተለመደ ነበር። በምርጫ 2007 በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የበርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት ዓመት ነበር። ከክልል አስተዳዳሪዎች ጀምሮ እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች በያሉበት ተመሳሳይ ተግባራት ሲከወኑ ነበር። በወቅቱ በሀገሪቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች ለመገንባት የታቀዱ ሀገር አቋራጭ የባቡር መስመር ግንባታን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ታቅደው ነበር። በእርግጥ ነው በትላልቅ ከተሞች ለመገንባት ከታቀዱ የኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ አብዛኞቹ ተገንብተው ሥራ መጀመራቸው ሲገለጽ ቆይቷል። በዚያው ልክ የባቡር መስመርን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች በወቅቱ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠ በኋላ አሁንም ድረስ ግንባታቸው ያልተጀመረ እንዳሉ ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ ግንባታቸው ቢጀመርም በወቅቱ ያልተጠናቀቁ አልያም ግንባታቸው የተቋረጠ እንዳለም ይሰማል። መንግሥት በምርጫ ዋዜማ ከወትሮ በተለየ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን መንቀሳቀሱን ከምርጫ ጋር የሚያገናኙ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ መቼም ይሁን የሕዝቡን የመሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ የሚሠራ ሥራ ተቀባይነት አለው ብለው የሚከራከሩ ሰዎች አሉ። ለመሆኑ ምርጫ ሊደረግ በታቀደበት ዓመት በኢትዮጵያ በየአካባቢው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እርስዎ እንዴት ያዩታል? ሃሳብዎን ያጋሩን፤ ተወያዩበት።
6.0K viewsDW Amharic, 08:53
Open / Comment
2021-02-14 19:51:38 ትናንት በጃፓን ምስራቅ ዳርቻ ተከስቶ በነበረው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው እና ንብረት መውደሙ ተዘገበ። የሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ NHK እንደዘገበው በአደጋው ቢያንስ 150 ሰዎች ተጎድተዋል። ለደህንነት ሲባል አደጋው ወደደረሰበት አካባቢዎች ይደረጉ የነበሩ ፈጣን የባቡር አገልግሎቶችም መቋረጡ ተዘግቧል። ትናንት በተከሰተው ብርቱ የመሬት መንቀጥቀጥ መዲና ቶኪዮ የሚገኙ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሳይቀሩ ይንቀጠቀጡ እንደነበር ተገልጿል። አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ለሰዓታት ተቋርጦ ነበር። በሀገሪቱ የሰአት አቆጣጠር ቅዳሜ ሌሊት በፉኩሺማ አቅራቢያ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን በሬክተር መለኪያ 7,3 የነበረ ሲሆን ከዛም በኃላ ሌሊቱን በተደጋጋሚ መጠነኛ መንቀጥቀጦች ተከስተው ነበር ተብሏል።
6.5K viewsDW Amharic, 16:51
Open / Comment
2021-02-14 19:51:22 https://p.dw.com/p/3pLdM @dwamharicbot
6.3K viewsDW Amharic, 16:51
Open / Comment
2021-02-14 19:45:44 የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ያለ መከሰስ መብታቸውን ለማንሳት ተከፍቶ የነበረው ሂደት ውድቅ ሆነ። ይህም ሴኔቱ የሚያስፈልገውን ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ሳያገኝ በመቅረቱ ነው። በድምፅ አሰጣጡ ላይ ሰባት ሪፓብሊካን ከዲሞክራቶች ጎን በመሆን በጠቅላላው 57 የፓርላማው አባላት ትራምፕን ቢቃወሙም የሚያስፈልጉ ሌሎች 10 ተጨማሪ ድምፆች ጎድለዋል። ትራምፕ ላይ ዳግም ያለመከሰስ መብትን ለማንሳት ውሳኔ መስጠት የተጀመረው ትራምፕ በጎርጎሮሲያኑ ጥር 6 ቀን የምርጫውን ውጤት ለመቀልበስ ደጋፊዎቻቸውን ወደ ካፒቶል አዝምተዋል በሚል ነው። ፕራምፕ ውሳኔውን በመደገፍ ይህ ገና የፖለቲካ ንቅናቄያቸው ጅማሬ እንደሆነ ተናግረዋል። ትራምፕ ከጎናቸው ለቆሙት ሪፖብሊካኖች ምስጋናቸውን በመግለጽ ለደጋፊዎቻቸው ደግሞ በሚቀጥሉት ወራት ተጨማሪ አዲስ ነገር ይዘው ብቅ እንደሚሉ ተናግረዋል። አዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይድን በበኩላቸው የሴናቱን ውሳኔ ተከትሎ፤ የካፒቶልን ህንፃ ሲጠብቁ ህይወታቸን ያጡትን ሰዎች እንደሚያስቡ እና የዛን ዕለት የሆነው ነገር «ዲሞክራሲ ተፈረካካሽ መሆኑን የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው» ብለዋል።
5.3K viewsDW Amharic, 16:45
Open / Comment