Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.56K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 577

2021-02-18 20:21:18 የአውሮጳ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ሩስያ ያሰረቻቸውን የሩስያ መንግሥት ተች አሌክሲ ናቫልኒን እንድትፈታ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ ሞስኮ ሕገ ወጥ ስትል ውድቅ አደረገች።የአውሮጳ ኅብረት ትናንት ባሳለፈው ውሳኔ ሩስያ ናቫልኒን በአስቸኳይ እንድትፈታ ጠይቋል። ይህን ካላደረገችም የአውሮጳ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌን እንደጣሰች ይቆጠራልም ብሏል ፍርድ ቤቱ ።የሩስያው ፕሬዝዳንት የቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፓስኮቭ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በሩስያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ሲሉ አውግዘውታል።
«የአውሮጳ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የሩስያው ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልኒ እንዲለቀቅ መጠየቁ ሕገ ወጥ ነው።ይህ በሩስያ የፍትህ ጉዳዮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ከባድ ሙከራ ነው።እኛ ማናቸውንም ግጭት አንፈልግም። በሌላ በኩል ግን እንደዚህ ዓይነት ውሳኔዎች እንቅስቃሴዎችና ፍረጃዎች ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳሉ»
ፓስኮቭ መጋጨት አንፈልግም ያሉት ምናልባት ሩስያ አባል ከሆነችበት ከአውሮጳ ካውንስል የመውጣት ሃሳብ እንዳላት ሲጠየቁ በሰጡት መልስ ነበር።ሩስያ ውስጥ የተመረዙት ናቫልኒ ጀርመን ታክመው ካገገሙ በኋላ ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ ነበር የታሰሩት።ከሁለት ሳምንት በፊትም ከዚህ ቀደም ተበይኖባቸው የነበረውን የእግድ እሥራት በመጣሳቸው የሁለት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶባቸዋል።
3.3K viewsDW Amharic, 17:21
Open / Comment
2021-02-18 20:19:41 https://p.dw.com/p/3pXal?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
3.3K viewsDW Amharic, 17:19
Open / Comment
2021-02-18 20:18:36 ባለፈው ጎርጎሮሳዊው 2020 ዓም በአውሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ተገን እንዲሰጣቸው ያመለከቱት ተሰዳጆች ቁጥር ከቀደመው ዓመት በ30 በመቶ ያነሰ እንደነበር ሕብረቱ አስታወቀ። ሕብረቱ እንዳለው የተገን ጠያቂዎች ቁጥር የቀነሰው በኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። ማልታ ዋና ከተማ ቫሌታ የሚገኘው የአውሮጳ የተገን አሰጣጥ ድጋፍ ሰጭ ቢሮ ዛሬ እንዳስታወቀው በጎርጎሮሳዊው 2020 በመላ አውሮጳ የተገን ማመልከቻ ያስገቡት ተሰዳጆች ቁጥር 461 ሺህ 300 ነበር። ይህም በቀደመው በ2019 ዓም ተገን ከጠየቁት 671 ሺህ 200 ጋር ሲነፃጸር በ30 በመቶ ያነሰ ነው። የ2020ው የተገን ጠያቂዎች ብዛት በአውሮጳ ከ2013 ወዲህ እጅግ ዝቀተኛው መሆኑ ነው የተነገረው። ድርጅቱ እንዳለው የተገን ጠያቂዎች ቁጥር የቀነሰበት ዋነኛው ምክንያት በኮሮና ሰበብ ሃገራት የጣሉት የጉዞ እገዳ ነው። የተገን ጠያቂዎች ቁጥር መቀነስም የተሰዳጆች ጉዳይ ከቀድሞ በተሻለ ፍጥነት እንዲታይ ረድቷል እንደ ድርጅቱ ።
3.8K viewsDW Amharic, 17:18
Open / Comment
2021-02-18 20:18:07 https://p.dw.com/p/3pZC2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
3.8K viewsDW Amharic, 17:18
Open / Comment
2021-02-18 14:36:32
አረብ ኤሚሬቶች ከአሰብ ወጣች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አሰብ-ኤርትራ ላይ የገነባችዉን ዘመናይ የጦር ሠፈር በከፊል ማፍረሷ ተዘገበ። ትንሺቱ የሰባት ተጫፋሪ ደሴቶች ስብስብ ኤሚሬትስ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር አብራ የየመን ሁቲዎችን ለመውጋት የሚረዳት የጦር ሠፈር አሰብ ውስጥ ገንብታ ነበር። እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ የተገነባው የጦር ሠፈር ዘመናይ ታንኮች፣ መድፎች፣ የጦር ጀልባዎች፣ ድሮኖችና ሌሎች ጦር መሣሪያዎችን የታጠቀ የራስዋ የአረብ ኤሚሬቶች፣ የየመንና የሱዳን ወታደሮች ሠፍረውበት ነበር። የአሜሪካው ዜና አገልግሎት አሶስየትድ ፕሬስ (AP) እንደዘገበው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ለጦር ሠራዊቱና ለጦር መሣሪያ ማከማቻ ዘመናይ ወደብና ጠንካራ ምሽግ ገንብታለች። አዋራማውን አውሮፕላን ማረፊያም አድሳው ነበር። የጦር ሠፈሩን ከኤርትራ ለ30 ዓመት ተኮናትራው እንደነበርም ተዘግቧል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ያፈሰሰችበትን ጦር ሠፈር ማፈራረስ የጀመረችበትን ምክንያት በይፋ አላስታወቀችም። AP እንደዘገበው የኤርትራ ባለሥልጣናትም ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡት ላቀረበው ጥያቄ የሰጡት መልስ የለም። የፖለቲካና የወታደራዊ ጉዳይ አዋቂዎች እንደሚሉት ግን የአቡዳቢ ገዢዎች የአሰቡን ጦር ሠፈር ያፈራረሱት የመን ውስጥ የሚያደርጉትን ውጊያ ካቆሙ በኋላ ነው። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስትር ጂም ማቲያስ ባንድ ወቅት «ትንሿ ስፓርታ» (በተዋጊነታቸው የምትታወቀው የቀድሞ የግሪግ ከፊል-ግዛት) በማለት ያንቆለጳጳሷት ሐገር ገዢዎች በተራዘመው የየመን ጦርነት መቀጠል የሚያስችል አቅም እንደሌላቸው በመገንዘባቸው ነው። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በፈራረሰው ጦር ሠፈር ተከማችቶ የነበረውን ጦር መሣሪያ በመርከብ ወደ ሐገራቸው እያጋዙ ነው።አሰብ ከየመን
5.4K viewsDW Amharic, 11:36
Open / Comment
2021-02-18 13:17:00
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በመጪዉ ሰኔ መጀመሪያ ለሚደረገው አካባቢያዊ ምርጫ ለመወዳደር እስካሁን ዕጩ ያስመዘገበ ተቀዋሚ ፓርቲ እንደሌለ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ዘንድሮ ሊደረግ በታቀደው ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እያስመዘገቡ ነው። የምረጡኝ ዘመቻም በይፋ ጀምረዋል። የድሬዳዋ የምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዚያድ -ያሲን እንደሚሉት ግን በከተማይቱ ሰኔ 5፣ 2013 ሊደረግ በታቀደው ምርጫ ለመወዳደር እስከ ዛሬ በይፋ የተመዘገበው ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ብቻ ነው። ኃላፊው እንደሚሉት በከተማይቱ ይወዳደራሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት አንዳድ ክልላዊ ፓርቲዎች የፖለቲካ ፓርቲነት መመዘኛዎችን አላሟሉም፣ ሌሎቹ ደግሞ ጽሕፈት ቤት እንዳላቸው ቢያስታውቁም አድራሻቸውን በትክክል ለምርጫ ጽሕፈት ቤቱ አላስታወቁም። ከብሔራዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስካሁን በከተማይቱ ጽሕፈት ቤት መክፈቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ብቻ ነው። ይሁንና ኢዜማም ቢሆን ዕጩዎቹን አላስመዘገበም፣ ቅስቀሳም አልጀመረም-እንደ ኃላፊው። የድሬዳዋ የምርጫ ጽሕፈት ቤት አራት የገጠር እና አራት የከተማ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አሉት። አቶ ዚያድ እንደሚሉት የየጽሕፈት ቤቶቹ ሠራተኞች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለምርጫው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ለማድረግ የመጓጓዣ ችግር እንዳጋጠማቸው አስታውቀዋል። የድሬዳዋው ወኪላችን መሳይ ተክሉ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የምትባለው ድሬዳዋ ከ600 ሺሕ በላይ ሕዝብ ይኖርባታል ተብሎ ይገመታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ከ1999 ወዲሕ የሕዝብ ቆጠራ ተደርጎ አያውቅም።
5.6K viewsDW Amharic, 10:17
Open / Comment
2021-02-17 21:00:19 አርዕስተ ዜና

-በትግራይ ክልል ከትናንት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድርጅት ለዶይቼ ቬለ ገለፀ።የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን " የጁንታው ርዝራዥ " ባሏቸው ኃይሎች ትናንት ከቀትር በኋላ በተፈፀመ "ጥቃት" ከአላማጣ መሆኒ መቀሌ የተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት አቋርጧል

-የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ የሐገሪቱን አምባሳደር ወደ ካርቱም ጠራ።ምክንያት ሁለቱ ሐገራት በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ ስለገጠሙት ዉዝግብ «ለመመካከር» ከመባሉ ሌላ ዝርዝሩ አልተነገረም።የሁለቱ ሐገራት ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።

-ኢትዮጵያን ጨምሮ ጦርነት፣ ግጭትና አለመረጋጋት በሚያብጣቸዉ ሐገራት ለሚኖረዉ ሕዝብ የኮቪድ 19ኝ ክትባት ለመስጠት ተኩስ እንዲቆም ብሪታንያ ጠየቀች።የብሪታንያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንደሚሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ተፋላሚ ኃይላት ዉጊያ እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ደንብ ማፅደቅ አለበት።ዜናዉን በድምፅ ለመስማት፣-https://p.dw.com/p/3pVBX
6.9K viewsDW Amharic, 18:00
Open / Comment
2021-02-17 20:51:37 https://p.dw.com/p/3pVAd?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
6.1K viewsDW Amharic, 17:51
Open / Comment
2021-02-17 20:50:26 https://p.dw.com/p/3pVEU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
5.4K viewsDW Amharic, 17:50
Open / Comment
2021-02-17 20:49:05 https://p.dw.com/p/3pV9J?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
5.1K viewsDW Amharic, 17:49
Open / Comment