Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.56K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 575

2021-02-19 20:08:11 በሶማሊያ የምርጫ መራዘምን በመቃወም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዛሬ መቃዲሾ ላይ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ በሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች በከፈቱት የሩምታ ተኩስ መበተኑ ተመለከተ። የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ መሰረት የሶማሊያ የፀጥታ ኃይላት ለሰልፍ በወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ላይ ተኩሰዋል። መዲና መቃዲሾ ላይ የመንግሥት ተቃዋሚዎች ሰልፍ የጠሩበት ቦታ መንገዶች ተዘጋግተዋል፤ በከፍተኛ የታጠቁ የፀጥታ ኃይላት ቦታዉን ተቆጣጥረዋል። በሶማሊያ መዲና መቃደሾ ላይ የታየው ከፍተኛ ውዝግብ ከመነሳቱ ከሰዓታት በፊት የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች እና የመንግሥት ተቃዋሚ መሪዎች መካከል በፕሬዚዳንቱ መኖርያ አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ተዘግቧል። በግጭቱ የሞተ ሰው ስለመኖር አለመኖሩ እስካሁን የተዘገበ ነገር የለም። ሶማሊያ የካቲት አንድ የምታካሂደውን ብሔራዊ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ ካራዘመች በኋላ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ሞዱላሂ ሞሃመድ በውጥረት ላይ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መቃዲሾ በሚገኘው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣብያ መግቢያ ላይ የነበረ ከፍተኛ ፍንዳታ የምግብ ቤቶች እና ሱቆችን ማውደሙን አንድ የዓይን እማኝ እና አንድ ፖሊስ መግለፃቸው ተዘግቧል። የሶማልያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ተቃዋሚዎችን እንጠብቃለን ያሉ የታጠቁ ኃይላት የመንግሥት የፀጥታ ኃይላት የሚቆጣጠሩ ቦታን አጥቅተው መቃዲሾን ለመቆጣጠር ጥረት አድርገዋል። መንግሥት የሰነዘረዘዉን ክስ ሃሰት ያሉት ተቃዋሚዎች በበኩላቸው መንግሥት በነበርንበት ሆቴል ላይ ጥቃት አድርሷል ሲሉ ይከሳሉ። «ትናንት ለዛሬ አጥብያ ሌሊት እና ዛሬ መቃዲሾ ውስጥ የታየው የተኩስ እሩምታ እንዳሳሰበው በትዊተር ገፁ መልክት ያስተላለፈው በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ኃይል ፤ በመቃድሾ በታየው ውዝግብ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲረጋጉ ውጥረቶችን ለመቀነስም የሚረዱ ክፍት የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
7.0K viewsDW Amharic, 17:08
Open / Comment
2021-02-19 20:08:01 በአፍሪቃ አህጉር በኮቪድ 19 በሽታ ባስከተለበት ሕመም የሞተው ሰው ቁጥር ከ 100 ሺህ መብለጡ ተነገረ። በአፍሪቃ ሃገራት የኮሮና ተኅዋሲን ስርጭት ለመግታት የሚታየው ጥንቃቄ ቸልተኝነት ታይቷል ተብሏል ከገመትነው በላይ ለተኅዋሲው ተጋላጭ ሆነናል፤ ይህ በጣም የሚያሳዝን ነው ሲሉ የአፍሪቃ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዳይሬክተር ጆን ክኔጋሲጋ ለአሶሽየትድ ፕሬስ መናገራቸው ተመልክቶአል። «በአህጉሪቱ የሕክምና ባለሞያዎች ከባድ የሥራ ጫና ላይ ናቸው ሞትን የተለመደ እንዳናደርገው እፈራለሁ» ሲሉም የአፍሪቃ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዳይሬክተር ተናግረዋል። በአህጉሪቱ የኮሮናን ጉዳይ የሚከታተለው እና በአፍሪቃ ኅብረት የተቋቋመው ግብረ ኃይል ዛሬ እንዳስታወቀው፤ ሩስያ 300 ሚሊዮን ስፑትኒክ V የተባለውን የኮሮና መከላከያ ክትባት ለአህጉሪቱ ግንቦት ወር ዉስጥ እንደምትሰጥ አስታዉቃለች። ኅብረቱ ከዚህ ቀደም ሲል 270 ሚሊዮን የኮሮና መከላከያ ክትባትን ከአስትራዜንካ፣ ፋይዘር እና ጆንሰን ኤን ጆንሰን ከሚባለው አምራች ኩባንያ አግኝቶአል።
6.1K viewsDW Amharic, 17:08
Open / Comment
2021-02-19 20:07:51 የእርስ በርስ ጦርነትን ለማቆም የሰላም ስምነት ከተፈፀመ ከአንድ ዓመት በኋላ ዛሬም በደቡብ ሱዳን ግጭትና ሁከት በሀገሪቱ ግዛቶች እንደተስፋፋ ነው ሲል የተመድ አስታወቀ። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫ፤ በጎርጎረሳውያኑ 2020 በደቡብ ሱዳን መንግሥት እና በመንግሥት ተቃዋሚ የሚታገዙ ታጣቂ ቡድኖች በሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ የፈፀሙት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል። የመንግሥታቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊ ያስሚን ሶካ የጥቃቱ መጠን በጎርጎረሳውያኑ 2013 እስከ 2019 ከነበረው መጨመሩን መናገራቸውን ሮይተርስ ዛሬ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣዉ የጽሑፍ መግለጫ በደቡብ ሱዳን በተለይ በማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ፣ በዎራፕ ፣ ጆንግሌይ እና በታላቁ ፒቦር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ ሕጻናት እና አዋቂ ሴቶች ታፍነዉ ተደፍረዋል፤ የፆታ ባርነት ደርሶባቸዋል፤ አስገድዶ ጋብቻም ተፈፅሞል ሲል አስነብቧል። በደቡብ ሱዳን የሚታየው ሁከት እና ግድያ ፤ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች በታጠቁዋቸው አዳዲስ የጦር መሣርያዎች ነው፤ ይህ ደግሞ ከመንግሥት በኩል አልያም የውጭ ኃይላት እጅ ያለበት ነው ሲሉ የኮሚሽኑ ባልደረባ አንድሬው ክላም መናገራቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል። በጎርጎረሳውያኑ 2011 ዓም ነጻነትዋን ያገኘችዉ ደቡብ ሱዳን፤ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ምክትላቸውን ሬክ ማቻርን ከሥልጣን ካነስወገድዋቸው በኋላ በሀገሪቱ በጎርጎረሳውያኑ 2013 ዓመት የእርስ በእርስ ጦርነት መቀስቀሱ ይታወቃል። በዚህ ጦርነት ከ 400 ሺህ በላይ ሕዝብ ተገድሏል። ባለፈው ዓመት ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ብሔራዊ ተጣማሪ መንግሥት መመስረታቸው አይዘነጋም።
5.4K viewsDW Amharic, 17:07
Open / Comment
2021-02-19 20:07:35 https://p.dw.com/p/3pbu7?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.9K viewsDW Amharic, 17:07
Open / Comment
2021-02-19 20:07:01 https://p.dw.com/p/3pc05?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.1K viewsDW Amharic, 17:07
Open / Comment
2021-02-19 20:06:33 https://p.dw.com/p/3pYyF?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.0K viewsDW Amharic, 17:06
Open / Comment
2021-02-19 20:05:49 እስራኤል የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ዘግታው የነበረውን ድንበር እና የዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣብያ ለተጨማሪ 14 ቀናት በዚሁ እንደምታራዝም አስታወቀች። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እና የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረጉት የጋራ መግለጫ ጥብቅ የዝውውር ሕጉ « በአስቸኳይ ምክንያት» እስከ የካቲት 27 ድረስ ይዘልቃል። የኮሮና ስርጭትን ለመግታት በሚል እስራኤል ከአለፈው ጥር 16 ጀምሮ የዓለም አቀፍ በረራዎችን ማስተናገድ ማቋረጧ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ሲል እስራኤል ከዮርዳኖስ እና ከግብፅ ጋር የሚያገናኛትን ድንበር ዘግታለች። እንድያም ሆኖ ከኢትዮጵያ፤ ከፈረንሳይ ከሩስያ ከዩክሬይን እና ከደቡብ አፍሪቃ የሚገቡ ይሁዶችን ለማጓጓዝ ስድስት የተለየ የዓለም አቀፍ በረራ መኖሩን የእስራኤል የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል። ወደ እስራኤል የሚጓዙት እነዚህ ዜጎች እስራኤል እንደገቡ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ወደ ተዘጋጀላቸው የተለየ ቦታ እንዲያርፉ እንደሚደረግ የእስራኤል የስደተኞች ጉዳይ መሥርያ ቤት አስታውቋል። የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ከፍተኛ ጥረት በሚደረግበት በአሁኑ ወቅት በእስራኤል በቀን በአማካኝ 4000 በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች መኖራቸው ተመዝግቧል። ይሁንና ይህ ቁጥር ከጥር ወር መጀመርያ ጋር ሲነፃፀር በ4000 የቀነሰ ነዉ። እስራኤል ውስጥ ባለፈው ጥር ወር በቀን 8000 ሰዎች በኮቪድ ይያዙ እንደነበር ተመዝግቧል። እስራኤል ውስጥ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት ካለፈው ታኅሣስ ወር ጀምሮ የወጣው ጥብቅ የዝውውር ሕግ ለአራተኛ ጊዜ መራዘሙ ተዘግቧል። እንደ እስራኤል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ 741 ሺህ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል፤ 5,501 ሰዎች ደግሞ የኮሮና ተህዋሲ ባስከተለባቸዉ ህመም ህይወታቸውን አጥተዋል።
4.0K viewsDW Amharic, 17:05
Open / Comment
2021-02-19 20:05:30 ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረዉን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር ማቋረጥዋ ከህዳሴ ግንባታ ጋር የነበረዉን የምክንያት ግንኙነት ሰረዘች። የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ህዳሴ ግድብ ያቀረቡትን የኢትዮጵያ መንግሥት አለዉ ባሉት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረዉን ከ 270 ሚሊዮን ዶላር በላይ አቋርጠዉ ነበር። አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር አሁን እንዳስታወቀዉ ግን ብድር ማቋረጡ ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ምክንያት መሆኑን ሰርዞአል። ይሁንና የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚ/ር እንዳለዉ የተቋረጠዉ ብድር አሁን ለኢትዮጵያ ይሰጣል ማለት አይደለም። ሚኒስትር መስርያ ቤቶ አክሎ እንዳስታወቀዉ ብድሩ የሚሰጠዉ አሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ሁኔታ ከመሻሻሉ ጋር በተያያዘ ነዉ። የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ሁኔታ ያለዉን በቀጥታ አልጠቀሰም ። ጋዜጠኞች ግን ትግራይ ዉስጥ የሚታየዉን ግጭት ሳይሆን እንዳልቀረ ገምተዋል። ሌላዉ የዩናይትድ ስቴትስ ሰብዓዊ ርዳታ በዚህ ብድር መያዝ ምክንያት እንደማይነካ መስርያቤቱ አስታዉቋል። ስለጉዳዩ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት መግለፁንም አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቦአል። ዶናልድ ትራምፕ ስለህዳሴ ግድብ ያቀረቡትን ሃሳብ ኢትዮጵያ ባለመቀበልዋ ምክንያት አሜሪካ የምትሰጠዉን ብድር በማቋረጣቸዉ በርካታ ኢትዮጵያዉያንን አስቆጥቶ ነበር።
3.9K viewsDW Amharic, 17:05
Open / Comment
2021-02-19 20:05:16 https://p.dw.com/p/3pbvV?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
3.9K viewsDW Amharic, 17:05
Open / Comment
2021-02-19 20:04:46 በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት ፖሊሲ ለውጥ እና መሻሻል ከተደረገ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ከሜክሲኮ ለሚመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎች ድንበር እንዲያቋርጡ በድጋሚ መፈቀድ መጀመሩ ተመለከተ። አዲሱ የጥገኝነት ረቂቅ ውሳኔ ከዛሬ ዓርብ ጀምሮ ከሚክሲኮ የሚመጡ የጥገኝነት አመልካቾች ያቀረቡትን ማመልከቻ በፍርድ ቤት ለመከታተል ወደ አሜሪካ እንዲገቡና እንዲከታተሉ ይፈቅዳል። ውሳኔው ከመተላለፉ ቀደም ሲል ተገን ጠያቂዎቹ ተቀባይነት ስለማግኘት አለማግኘታቸው በሀገራቸው ሆነው እንዲከታተሉ የሚደነግግ ብቻ ነበር። አዲሱን የጥገኝነት ማሻሻያ ረቂቅ የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራቶች ለፕሬዚዳንት ጆ ቢደን ኮንግረስ ውስጥ ለታሰበው የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ረቂቅ በማስተዋወቃቸው ውሳኔው መተላለፉ ተመልክቷል። ውሳኔው ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ አሜሪካ ውስጥ ለሚኖሩ 11 ሚሊዮን ስደተኞች የመኖርያ ፈቃድን ለማግኘት መንገድ የሚዘረጋ እንደሆነ ተመልክቷል።
3.9K viewsDW Amharic, 17:04
Open / Comment