Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.56K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 574

2021-02-20 19:57:02 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ምዕራባዊ ሀገራት አፍሪቃን በኮሮና ክትባት ዘመቻ እንዲደግፉ ጥሪ አቀረቡ። ማክሮ« የአውሮፓ ህብረት እና ዮናይትድ ስቴትስ ለአፍሪቃ አገሮች በተቻለ ፍጥነት 13 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦች መስጠት አለባቸው» ሲሉ ትናንት በኦንላይን በተካሄደ ውይይት ላይ ተናግረዋል። «በአህጉሪቷ 6.5 ሚሊዮን የጤና ባለሙያዎች ይገኛሉ» ያሉት ማክሮ ለእነሱ የሚውል 13 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦች ያስፈልጋሉ ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የምዕራብ ሀገራቱ ርምጃ የሚወስዱት ግን ገና ከስድስት ወራት በኋላ ከሆነ የአፍሪካ ሀገሮች ክትባቱን ከቻይና ወይም ከሩሲያ ያገኛሉ ሲሉ አሳስበዋል። ማክሮ ይህ የምራባዊያን ተሳትፎ «የተዓማኒነት» ጥያቄም ነው ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈረንሳይን ጨምሮ ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሃገራት መንግስታት መሪዎች በኦንላይን ባደረጉት ጉባኤ ላይ ለዓለም አቀፍ የክትባት ዘመቻ የሚውል የ 7,5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመለገስ ተስማምተዋል።
6.8K viewsDW Amharic, 16:57
Open / Comment
2021-02-20 19:56:45 https://p.dw.com/p/3pdhF?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
6.6K viewsDW Amharic, 16:56
Open / Comment
2021-02-20 19:55:47 ትናንት ፈረንሳይ ውስጥ አንድ ሱዳናዊ ስደተኛ የፈፀመው ግድያ ከሽብር ጥቃት ጋር የተያያዘ አይደለም ሲል የሀገሪቱ አቃቢ ህግ ዛሬ አስታወቀ። ሱዳናዊው ስደተኛ ትናንት ደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ በምትገኘው ፓዎ ከተማ አንድ የስደተኞች ጣቢያ ኃላፊን በተደጋጋሚ በስለት ወግቶ ከገደለ በኋላ በሁለት የጣቢያው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። የ 38 ዓመቱ ሱዳንያዊ ፈረንሳይ የገባው እጎአ በ 2015 ዓም ሲሆን ጥቃቱን በፈፀመበት የስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ለተወሰነ ያህል ጊዜ ይኖር እንደነበር አቃቢ ህግ ዛሬ አክሎ አስታውቋል። ከዚህም ሌላ ተጠርጣሪው ጥቃት ፈፃሚ በ 2017 እና በ2019 ዓም በወንጀል ተሳታፊ ሆኖ እስር ቤት ስለገባ የስደት ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ ተነግሮት ነበር። ሱዳናዊው ስደተኛ ግን ለሚመለከተው የስደተኞች ባለስልጣን ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል። ይልቁንስ ተጠርጣሪው የመቆያ ጊዜውን ለማራዘም ይረዳኝ ይሆናል ያለውን ማስረጃዎች ለማግኘት ጥቃቱን ወደ ፈፀመበት የስደተኞች ጣቢያ ባለፉት ቀናት ተመላልሶ እንደነበር አቃቢ ህግ ማረጋገጥ መቻሉን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ AFP ዘግቧል።
5.3K viewsDW Amharic, 16:55
Open / Comment
2021-02-20 19:55:30 https://p.dw.com/p/3pdsp
5.0K viewsDW Amharic, 16:55
Open / Comment
2021-02-20 19:55:00 ከ 20 በላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸውን የጀርመን ዜና ምንጭ DPA ዘገበ። የፅህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ አንቴኒ ዌክ አንቴኒ ለዜና ምንጩ በስልክ እንዳረጋገጡት በጠቅላላው ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሚሰሩ 27 ሰዎች በትህዋሲው ተይዘው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ። በሽታው የተረጋገጠባቸው ሰራተኞች በዋናነት የፕሬዚዳንቱ የጥበቃ ሰራተኞች፤ ምግብ አብሳዮች ፤ ሹፌሮች እና ራሳቸው ቃል አቀባዩም በተህዋሲው መያዛቸውን ገልጸዋል። «ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ» ያሉት ቃል አቀባያቸው ፕሬዚዳንቱ ከሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በከፍተኛ መጠን እንደቀነሱ እና ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ደቡብ ሱዳን ውስጥ እስካሁን በይፋ 6,417 ሰዎች በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን 83 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሞተዋል።
4.6K viewsDW Amharic, 16:55
Open / Comment
2021-02-20 19:54:48 https://p.dw.com/p/3pdso?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.6K viewsDW Amharic, 16:54
Open / Comment
2021-02-20 19:54:13 የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፖርላሜንታዊ የምርምር ትስስር ተቋማት ጋር በምርምር የተደገፉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ይጠቅማል የተባለለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ምክር ቤቱ ከዚህ መግባባት ላይ የደረሰው ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት ጋር ከትናንት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሸ ሲያካሂድ በነበረው የመጀመሪያው ዓመታዊ የፓርላሜንታዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ነው።
የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ዋና ፀሃፊ ዶክተር ምስራቅ መኮንን የሃገሪቱ ህጎች ሲፀድቁ በመረጃና በምርምር የተደገፉ እንዲሆኑ የምርምር ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው የምርምር ስራው በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስኮች ዘላቂነት ያለው ስራ ለመስራት በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል። በስብሰባው የተካፈሉ ምሁራን« የመግባቢያ ሰነዱ ቀደም ብሎ ቢደርሰን የተሻለ ግብአት እናበረክት ነበር፤»« ተቋሙ እራሱን ችሎ ቢመራ የተሻለ ነው» የሚሉና ሌሎች አስተያየቶች ሰንዝረዋል ሲል በስፍራው የተገኘው ወኪላችን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል። @dwamharicbot
4.5K viewsDW Amharic, 16:54
Open / Comment
2021-02-20 19:53:46 https://p.dw.com/p/3pdQx
4.5K viewsDW Amharic, 16:53
Open / Comment
2021-02-20 19:53:15 ሱዳን ፤ ኢትዮጵያ ባወጣችው መግለጫ « ይቅር የማይባል ስድብ» ሰንዝራብኛለች ስትል ዛሬ ወቀሰች። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀሙስ ዕለት በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ውዝግብ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ «በሱዳን መንግሥት ወታደራዊ ክንፍ እየተናፈሰ ያለው የግጭት ወሬ በሱዳናዊያን ወጪ የሶስተኛ ወገን ፍላጎቶችን የሚጠቅም ነው» ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ያለው ከቀናት በፊት ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ድንበሬን ተሻግሮ «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ለከሰሰችበት መግለጫ ነበር። ዛሬ ደግሞ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተራው በሱዳን ላይ የተሰነዘረው « ስም ማጥፋት » እና ለሌላ ወገን ወኪል ናት የመባል ክስ « ይቅር የማይባል ስድብ ነው» ሲል ምላሽ ሰጥቷል። መግለጫው አክሎም « የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሊክደው የማይችለው ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር የሌላ ሶስተኛ ወገን ወታደሮች አብረው ወደ ሱዳን መሬት ዘልቀው መግባታቸውን ነው « ሲል መወንጀሉን ሮይተርስ ዜና ምንጭ ዘግቧል። ሮይተርስ አክሎም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዛሬው የሱዳን መግለጫ ላይ ምላሽ እንዲሰጡት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ አስታውቋል።
4.9K viewsDW Amharic, 16:53
Open / Comment
2021-02-20 19:52:55 https://www.dw.com/am/%E1%88%88%E1%88%85%E1%8A%AD%E1%88%9D%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%8C%89%E1%8B%9E-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%A9-%E1%88%B0%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%B3%E1%8C%88%E1%89%B1/a-56635939
5.5K viewsDW Amharic, 16:52
Open / Comment