Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.34K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 2

2023-07-23 19:32:03 ፈተና ያቀጨጨው የኢትዮጵያ ፕረስ
"ጋዜጠኞች ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ ሆን ተብሎ ለመሆናቸው በቂ ጥርጣሬ ሊያሳድር በሚችል መልኩ ቢሮአቸው እየተሰበረ የስራ እቃዎቻቸውን እንዲዘረፉም እየተደረገ ነው።"https://p.dw.com/p/4UEHE?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
5.4K viewsDW Amharic Team, 16:32
Open / Comment
2023-07-23 19:30:41 የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እና የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት
የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለስድስት ኤጲስቆጶሳት ሹመት ሰጠች። የዛሬ ተሿሚዎች ትግራይ ክልል ውስጥ እና በውጭ ሀገር ቤተክርስቲያኒቱ እና ምእመናኑ የሚያገለግሉ ናቸው ተብሏል።https://p.dw.com/p/4UHma?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
5.1K viewsDW Amharic Team, 16:30
Open / Comment
2023-07-23 19:29:17 የሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓም የዓለም ዜና በድምጽ
የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለስድስት ኤጲስቆጶሳት ሹመት ሰጠች። የዛሬ ተሿሚዎች ትግራይ ውስጥ እና በውጭ ሀገር ቤተክርስቲያኒቱ እና ምእመናኑ የሚያገለግሉ ናቸው ተብሏል።

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምዕራባዊ ግዛት ናያኮቫ በተባለች መንደር አንድ ወታደር ለሃዘን በተቀመጡት ሰዎች ላይ በከፈተው የእሩምታ ተክስ ቢያንስ 13 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ። ከሞቱት ውስጥ ዘጠኙ ህጻናት ናቸው።

ሩስያ በኦዴሳ ከተማ ከተማ ዛሬ በፈጸመችው የሚሳይል ጥቃት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስና ትምህርት ማዕከል የተመዘገበውን ታሪካዊው የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ካቴድራል ማውደሟን ክየቭ አስታወቀች፤ ድርጊቱንም "የጦር ወንጀል" ብላዋለች።

ዩክሬይን በሩስያ በሃይል ከተያዙባት መሬቶች ግማሽ ያህሉ ማስመለሷን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ። https://p.dw.com/p/4UI2P?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.7K viewsDW Amharic Team, 16:29
Open / Comment
2023-07-23 18:52:23 Live stream started
15:52
Open / Comment
2023-07-22 20:09:19 ኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ በሚካሄደው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ሩቶ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማካሄድ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብቶችችን አለአግባብ በመጠቀም አመጽ በመቀስቀስ የህዝቦችን ደኅንነት እና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ ያሏቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መንግሥታቸው እንደማይታገስ አስጠንቅቀዋል። https://p.dw.com/p/4UGmQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
6.4K viewsDW Amharic Team, 17:09
Open / Comment
2023-07-22 20:08:53 የሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል «በሰላም የተመለሱ » ከ100 በላይ ታጣቂዎች አፈንግጠው ጫካ መግባታቸው ተገለጸ። ላለፉት ሁለት ወራት ያህል ከነትጥቃቸው በግልገል በሰለስ ከተማ አቅራቢያ የሰፈሩት ታጣቂዎቹ ተመልሰው ዱር መግባታቸውን የከተማዋ ከንቲባ አረጋግጠዋል።
• የግሪክ ድንበር ጠባቂዎች 100 ፍልሰተኞችን ከባሕር መስጠም መታደጋቸውን ዐስታወቁ። ፍልሰተኞቹን በማጓጓዝ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
• በአንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም ባለስልጣን ላይ ግድያ የፈጸመ ግለሰብ መለየታቸውን የየመን የጸጥታ ባላስልጣናት ዐስታወቁ ። ባለስልጣናቱ ገዳዩን ደረስንበት ይበሉ እንጂ ግለሰቡ ከጂሃዲስቶች ወገን ይሁን አይሁን በግልጽ ያሉት ነገር የለም።
• ሩስያ በጥቁር ባህር ከተደረሰው የእህል ዝውውር ስምምነት መውጣት «ሚሊዮኖችን ለረሃብ እና ለከፋ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል» የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኃላፊ አሳሰቡ።
• ዩክሬን ፤ ሩስያ በኃይል በያዘቻት የክሬሚያ ግዛት በአንድ የጥይት ማከማቻ መጋዘን ላይ ባደረሰችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በባለስልጣናት ታዘዙ ።
• ትናንት ዓርብ ሞናኮ ፈረንሳይ ውስጥ በተከናወነ የዳይመንድ ሊግ የሩጫ ውድድር በ5000 ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን ወንዶች ተከታታለው በመግባት ከ1ኛ እስከ3ኛ ያለውን ደረጃ ሲቆጣጠሩ ፤ በሴቶች አንድ ማይል ርቀት ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፒገን አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ ችምር አሸናፊ ሆናለች። https://p.dw.com/p/4UGm4?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
5.7K viewsDW Amharic Team, 17:08
Open / Comment
2023-07-22 20:08:05 በመተከል ዞን በግልገል በለስ ከተማ ካምፕ ውስጥ የነበሩ ታጣቂዎች ከነጦር መሳሪያቸው ወደ ጫካ መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ተናገሩ። የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ከትጥቅ ትግል ተመለሱ የተባሉት ታጣቂዎች ለተሐድሶ እየተዘጋጁ ነበር። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪ እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ መመለሳቸው ከተሰማ በኋላ በአካባቢው ሥጋት ሰፍኗል https://p.dw.com/p/4UGOE?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.8K viewsDW Amharic Team, 17:08
Open / Comment
2023-07-22 20:07:33 «የፕላስቲክ ጠንቅ» ፤ ክፍል 3 «በየቦታው ፕላስቲክ»
ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ በሚውሉ የፕላስቲክ መገልገያዎች ላይ የተጣለው እገዳ እስካሁን በሶንጋ ነጋዴዎች ዘንድ ቁም ነገር ተደርጎ አልተቆጠረም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የ16 ዓመቱ አካሉ እና ጓደኛው ተፈሪ ተጠያቂ እንዳይባሉ ስለፈሩ ስላዩት ነገር ለማንም ላለመንገር ወስነዋል። ታሪኩ እንዴት ይቀጥላል? https://p.dw.com/p/4SYJn?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
5.1K viewsDW Amharic Team, 17:07
Open / Comment
2023-07-22 20:07:06 https://p.dw.com/p/4UGAi?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
4.9K viewsDW Amharic Team, 17:07
Open / Comment
2023-07-22 20:03:09 Live stream finished (1 hour)
17:03
Open / Comment