2023-06-05 18:42:49
...ይህንንም አንድ ወር ባነሰ ግዜ ውስጥ ለማከናወን አቅደንል ወደ ሥራ እየገባን እንገኛለን “ ብለዋል፡፡
ዕዳውን የማስመለሱን ሂደት ሥኬታማ ለማድረግ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የኮማድ ፖስት ወይንም የዕዝ ሠንሰለት መዋቅር መዘርጋቱን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ተናግረዋል፡ከተጠያቂነት አንጻር ሂደቱን ለማስስተጓጎል የሚሞክር ማንኛውም አካል በህግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድበት ይሆናል ያሉት ኃላፊ “ ለዚህም ዕዳውን የማስፈጸሙ ሂደት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እና የክልሉን ፍትህ ቢሮ ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጣ ኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተደርጓል ፡፡ የኮማንድ ፖስቱ ዋና ዓላማ ገንዘቡን ማስመለስ ነው ፡፡ የሚፈለግባቸውን ገንዘብ በሚያሸሹ ወይም ራሳቸውን ሊያሸሹ በሚሞክሩ አካላት ላይም የተጠናከረ ክትትል ይደረጋል፡፡ ያለባቸውን ዕዳ ሲመልሱም እጃቸው ላይ ካቆዩበት የወለዱ መጠን ጋር የሚመልሱ ይሆናል ›› ብለዋል ፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ደገላ ኤርገኖ የደቡብ ክልልን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች በቅርበት ከሚከታተሉት የዘርፉ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ናቸው ፡፡ ክልሉ አሁን ላይ ከአፈር ማዳበሪያ ዕዳ አመላለስ ጋር በተያያዘ ባጋጠመው የበጀት መዛባት ዙሪያ በዶቼ ቬለ DW አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶክተር ደገላ የበጀት ክፍተቱ በቶሎ መፍትሄ ካላገኘ በክልሉ ላይ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡
በክልሉ መመለስ የነበረበት ዕዳ ወደ መንግሥት ቋት አለመግባቱ ክልሉ ጤናማ በሆነ የበጀት ሥረዓት ውስጥ እንዳይገኝ እንዳደረገው የጠቀሱት ዶክተር ደገላ “ ይህ ሁኔታ አይደልም አንገብጋቢ የድህንት ቅነሳ ሥራዎችን ለማከናወን ቀርቶ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርሰው ችሏል ፡፡ የበጀት ክፍተቱን በቶሎ ማስተካከል ካልተቻለ በክልሉ ላይ ተጨማሪ ፖለቲካዊ ተፅኖ ሊያሳድር ይችላል ፡፡ምክንያት ሁኔታው ግብር እየከፈሉ ልማት ያላገኙ ዜጎችን ቅሬታ ውስጥ የማስገባት ዕድሉ ሠፊ ነው ፡፡ ይህም በጊዜ ሂደት አስፈጻሚውን አካል ፖለቲካዊ ጫና ውስጥ ሊከተው ይችላል “ ማለታቸውን የሐዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘግቧል ፡፡
በቀጣይ የክልሉ ምክር ቤትና አስፈጻሚው አካል የተጣለባቸውን ሃላፊነት ሊወጡና ተጠያቂነትን ሊያሰፍኑ ይገባል ያሉት የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ደገላ በተለይ በዕዳ አመላለስ ሂደቶችም ሆነ ለወደፊቱ በሚኖረው የበጀት አስተዳደር ሥራ ላይ ክልሉ በፋይናንስ ህግና ደንብ ብቻ እንዲመራ በማድረግ ከችግሩ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል መኖሩንም ጠቁመዋል ፡፡
2.7K viewsDW Amharic Team, 15:42