Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.34K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 7

2023-06-06 12:21:56
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት 801 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባ "የሀገርን ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በሕግ ማስከበር ዘመቻ የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ" ረቂቅ በጀቱ ተቃኝቶ የቀረበ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ ቤት ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በጀቱ ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች 369.6 ቢሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.9 ቢሊየን ብር ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 214.07 ቢሊየን ብር ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 14 ቢሊየን ብር በጠቅላላው 801.65 ቢሊየን ብር ሆኖ ቀርቧል ተብሏል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ውሳኔውን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው መሆኑን የዘገበው ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ነው። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
1.6K viewsDW Amharic Team, 09:21
Open / Comment
2023-06-06 12:10:55
እርስዎ ምን ይላሉ?
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰዎች እገታና ጠለፋ መልክና አፈጻጸማቸውን እየተቀያየረ እንደቀጠለ ነዉ። በአንድ ወቅት ከሊብያ እስከ የመን በተዘረጋው «የአግቶ አደሮች» ቁልፍልፍ ሰንሰለት ሰዎችን እያሰቃዩ ቤተሰብ የተቆረጠለትን ገንዘብ ወደ ታዘዘለት የባንክ ሒሳብ እንዲያስገባ በመጠየቅ የብዙዎች ሕይወት ተመሰቃቅሏል። ለሚደርሰዉ ወንጀል የሃገሪቱ ባለስልጣኖች «ሕገወጥ ደላሎች» የሚል የዳቦ ስም በተሰጣቸው አካላት ላይ አሳብበው የዘመቻ ስራ ተሰርቶ ለሚድያ ፍጆታ ከዋለ ቦኋላ ነገሩ ረገብ ያለ ቢመስልም ተግባሩን ግን እስከ አሁን ማስቆም አልተቻለም።
በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ የከፍተኛ ባለስላጣን ጠባቂ የሆነ ግለሰብ የባንክ ሰራተኛ የሆነችውን ወይዘሪትን የመጥለፉ ዜና እያነጋገረ ነው። ብዙዎችን ያስገረመዉ ፖሊስ በጠላፊነት የሚጠረጠረዉን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ ከማቅረብ ይልቅ ግለሰቡ እንዳይያዝ መረጃ በማቀበልና ድርጊቱ እንዲፈጸም በማበርም የፖሊስ ባልደረቦች ተሳታፊዎች ነበሩ መባሉ ነዉ።
በሌላ ወገን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከብልጽግና አመራሮች ጋር ያደረጉት ውይይት ላይ የተናገሩት ተብሎ በመንግስት የመገናኛ ብዙሐን እንደቀረበው መንግስታቸው አገሪቱ አይታው በማታውቀው ሁኔታ የመከላከያና የፖሊስ ሐይልና ሥርዓት መገንባታቸውን ገልጸዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል የዜጎች ሕይወት በየቀኑ በሚቀጠፍበትና በሚታገትበት ወቅት በመሆኑ የእሳቸው ንግግር ክፉኛ እየተተቸ ነው።
በተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች እየተፈጸመ ስላለው እገታ እርስዎስ ምን ይላሉ? እውነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አገሪቱ አይታው የማታውቀውን የመከላከያና የፖሊስ ሥርዓት ተገንብቶ ከሆነስ መንግስት ለምን ድርጊቶቹ ከመፈጸማቸው በፊት አስቀድሞ አልተከላከለም? ሲፈጸሙስ ሕጋዊ እርምጃ አይወሰድም? ተወያዩበት።
1.5K viewsDW Amharic Team, 09:10
Open / Comment
2023-06-05 20:33:58 የሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ በብሔረ ብጹአን አፄ መልከዓ ሥላሴ ገዳም የታጠቀ ቡድን እየሰለጠነበት ነው በሚል ከጥር 22 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በንጹሀን ላይ ግድያና የአካል ጉዳት ደርሷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ኢሰመጉ አስታወቀ። ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የገዳማቱ መናኝ መነኮሳትም የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈጸሙባቸው የአካባቢው አርሶ አደሮችም የግብርና ስራቸውን መከወን እንደተቸገሩ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ገልጿል ።ኢሰመጉ ተኩሱን ሸሽተው የሚሄዱ ሰዎችም ተምቻ ተብሎ በሚጠራው በአካባቢው በሚገኝ ወንዝ ለጎርፍ አደጋ መጋለጣቸውንም ፣ መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ሃላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ በሚል ባወጣው በዚሁ መግለጫ ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣ ያለው ሰዎችን አስገድዶ መሰወር በአፋጣኝ ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ አሳሰበ። ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተለይ በአዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጥቆማዎችን መሰረት አድርጎ ባደረገው ክትትል «በርካታ የአስገድዶ መሰወር ድርጊቶች መከሰታቸውን» አረጋግጫለሁ ብሏል።
የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮጳ የብዙ ሰዎችን ሕይወት ያጠፋ ጦርነት መሆኑ ተዘገበ ። አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ መረጃ ሰነድ ከ354 ሺህ በላይ የሩስያና የዩክሬን ወታደሮች በጦርነቱ ተገድለዋል ወይም ደግሞ ቆስለዋል ይላል ።
ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4SDkR?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.6K viewsDW Amharic Team, 17:33
Open / Comment
2023-06-05 20:21:58 https://p.dw.com/p/4SDCU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.2K viewsDW Amharic Team, 17:21
Open / Comment
2023-06-05 20:19:47 https://p.dw.com/p/4SDi9?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.8K viewsDW Amharic Team, 17:19
Open / Comment
2023-06-05 20:17:56 https://p.dw.com/p/4SDUv?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.7K viewsDW Amharic Team, 17:17
Open / Comment
2023-06-05 20:09:02 https://p.dw.com/p/4SDXE?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.6K viewsDW Amharic Team, 17:09
Open / Comment
2023-06-05 20:06:33 https://p.dw.com/p/4SDC6?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.5K viewsDW Amharic Team, 17:06
Open / Comment
2023-06-05 20:04:39 https://p.dw.com/p/4SDH5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.4K viewsDW Amharic Team, 17:04
Open / Comment
2023-06-05 20:01:20 Live stream finished (54 minutes)
17:01
Open / Comment