Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.34K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 3

2023-07-05 19:51:03 ኢትዮጵያ ብሪክስን ብትቀላቀል ምን ጥቅም ታገኛለች?

ኢትዮጵያ ብሪክስን ብትቀላቀል ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ ያቋቋሙት ባንክ "አዲስ የብድር ምንጭ" ሊሆናት እንደሚችል አቶ አሌክሳንደር ደምሴ ያምናሉ። አቶ ያሬድ ሐይለመስቀል ግን "ከእነሱ ተርፎ የሚዘንብልን ነገር አይኖርም" ሲሉ ይሞግታሉ። ናይጄሪያ፣ ግብጽ እና ሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ በርካታ አገራት ወደ ብሪክስ አዘንብለዋል። https://p.dw.com/p/4TScU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.6K viewsDW Amharic Team, 16:51
Open / Comment
2023-07-05 19:49:54 በኦሮሚያ ክልል የጤናው ዘርፍ ችግር

በኦሮሚያ ግጭት በተራዘመባቸው አከባቢዎች በጤና ተቋማት ላይ በሚደርስ ውድመትና ዝርፍያ የአከባቢው ማኅበረሰብ ተገቢ አገልግሎት ለማግኘት መፈተኑ ተነገረ። ችግሩ ግጭት በተስፋፋባቸው የወለጋ አራት ዞኖች፣ በምዕራብ ሸዋ እና ጉጂ እንደሚሰፋም የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ ያስረዳል። https://p.dw.com/p/4TSVP?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.5K viewsDW Amharic Team, 16:49
Open / Comment
2023-07-05 19:48:26 ከችግር ያልተላቀቁት የአበርገሌ ወረዳ አካባቢዎች

ከሁለት ዓመት በላይ በጦርነት ውስጥ የነበሩ የአበርገሌ ወረዳ አካባቢዎች አሁንም አብዛኛዎቹ ነፃ ባለመውጣታቸው የግብርና ሥራዎችን ማገዝ እንዳልተቻለ የአካባቢዎቹ አስተዳዳሪዎች አመለከቱ። በ2014/15 የእርሻ ወቅት በአበርገሌና ፃግብጂ ወረዳዎች ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ አልታረሰም። https://p.dw.com/p/4TS8Y?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.1K viewsDW Amharic Team, 16:48
Open / Comment
2023-07-05 19:47:26 የደቡብ ክልል ሕዝበ ውሳኔ ውጤት በፌዴሬሽን ም/ቤት ጸደቀ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ያጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት አጸደቀ። በምክር ቤቱ የህዝበ ውሳኔ ውጤት መሠረት ስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ከደቡብ ክልል በመነጠል ለፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ የሆነ አዲስ ክልላዊ መንግሥት የሚመሠርቱ ይሆናል። https://p.dw.com/p/4TSGO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.0K viewsDW Amharic Team, 16:47
Open / Comment
2023-07-05 19:46:17 እገታዎች ፤ የተፈጠረው ሥጋት እና መፍትሔዎቹ

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ አካባቢ ሕፃናትን በማገት ለማስለቀቂያ የሚሆን ገንዘብ ወይም ቤዛ የሚጠይቁ ሰዎች መኖራቸው ተደጋግሞ ታይቷል። ለትምህርት የወጡ ሴቶችም በታጣቂዎች ታግተው አንደነበርም የማይዘነጋ የቅርብ ጊዜ ድርጊት ነው። https://p.dw.com/p/4TSc3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
1.8K viewsDW Amharic Team, 16:46
Open / Comment
2023-07-05 19:42:18 የሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
• የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የፌዴሬሽኑ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ወሰነ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በቅርቡ በተከናወነው ሕዝበ ውሳኔ መሰረት የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች የተካተቱበት «የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል» በሚል ስያሜ እንዲደራጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

• በአማራ ክልል የሸዋሮቢት ከተማ የሰላም እና ጸጥታ ኃላፊ የነበሩት አቶ አብዱ ሁሴን ትናንት ማክሰኞ በደረሰባቸው ጥቃት ተገደሉ ። ከትናንት በስትያ ማክሰኞ በተመሳሳይ ምስራቅ ጎጃም የደጀን ወረዳ ሁለት የፖሊስ ኃላፊዎች ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል።

• ግጭት በተንሳራፋበት የሱዳኗ ዳርፉር ግዛት የከፋ ሰብአዊ ቀውስ እንይከተል ማስጋቱን ኢንተርናሽናል ሪስክ ኮሚቴ አሳሰበ። ዓለማቀፉ የግብረሰናይ ድርጅት እንዳለው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከ36 ሺ በላይ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሀገር ቻድ ተሰደዋል።

• እስራኤል በኃይል በያዘችው የዮርዳኖስ ምዕራባዊ ዳርቻ ጄኒን ከተማ በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ግዙፍ ነበር የተባለለትን ወታደራዊ ዘመቻዋን ማጠናቀቋን ዐስታወቀች። በሁለቱ ቀናት የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ የተገደሉባቸውን 12 ሰዎች ለመቅበር በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን በጄኒን ከተማ ተሰባስበዋል።

• ሩስያ የጥቁር ባህር የእህል ዝውውር ስምምነት እንዲቀጥል የሀገሪቱ የግብርና ባንክ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ዝውውር ስረዓት ወይም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ SWIFT የክፍያ ስረዓት መመለስን በቅድመ ሁኔታ አስቀመጠች ።

https://p.dw.com/p/4TSuz?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
2.1K viewsDW Amharic Team, 16:42
Open / Comment
2023-07-05 19:03:07 Live stream finished (9 seconds)
16:03
Open / Comment
2023-07-05 19:02:58 Live stream started
16:02
Open / Comment
2023-07-05 16:07:07
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት አጸደቀ ፡፡ በምክር ቤቱ የዛሬው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብእሸት አየለ በዞኖቹና በልዩ ወረዳዎቹ የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ውጤት በንባብ አቅርበዋልበህዝበ ውሳኔው 2 ሚሊየን 396 ሺህ መራጮች በጋራ ክልል መደራጀትን የደገፉ ሲሆን 120 ሺህ 268 ያህሉ ደግሞ የጋራ አደረጃጀቱን በመቃውም ድምፅ መስጠታቸውን ቦርዱ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
በህዝበ ውሳኔው በአተገባበር ሂደት አጋጠሙ ያሏቸውን ችግሮችም በሪፖርታቸው የጠቀሱት ምክትል ሰብሳቢው “ በአንዳንድ አካባቢዎች የወረዳ አመራሮች በምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ ጫና ያደርጉ ነበር ፡፡ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ነዋሪዎች ምርጫው ተሳትፈው ተገኝተዋል “ ብለዋል ፡፡
የቦርዱን የህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም ያዳመጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በበኩሉ በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተወያየ በኋላ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት በሙሉ ደምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡ በዚህም መሠረት ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ በደቡብ ክልል ሥር ሲተዳደሩ የቆዩት የዎላይታ ፣ የጋሞ ፣ የጎፋ ፤ የኮንሶ ፣ የደቡብ ኦሞ ፣ የጌዲኦ ዞኖችና አንዲሁም የአማሮ ፣ ቡርጂ ፣ ደራሼ ፣ አሌ እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ ክልል ሆነው እንዲደራጁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በእንጻሩ የሃድያ ፣ የከንባታ ጠንባሮ ፣ የሀላባ ፣ ሥልጤ ፣ የጉራጌ ዞኖችና እና የየም ልዩ ወረዳ ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል ፡፡
ዘገባ ፦ ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ፎቶ ፡ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት
3.4K viewsDW Amharic Team, 13:07
Open / Comment
2023-07-05 12:18:38 https://p.dw.com/p/4TPP3?maca=amh-Red-WhatsApp
3.7K viewsDW Amharic Team, 09:18
Open / Comment