Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.55K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 579

2021-02-16 19:55:04 ጌዲኦ፣ የትምሕርት ቤት ምረቃ

በገደብ ወረዳ ባንኮዳዳቶ በተባለች የገጠር ቀበሌ የተሰራዉ ትምህርት ቤት ከ400 በላይ ተማሪዎችን ማስተማር ይችላል ተብሏል።
https://p.dw.com/p/3pRRU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
4.6K viewsDW Amharic, 16:55
Open / Comment
2021-02-16 19:39:21 https://www.facebook.com/dw.amharic/videos/434322681243207
4.9K viewsDW Amharic, 16:39
Open / Comment
2021-02-16 18:53:52
አድማጮች ስርጭታችንን ፦
በራዲዮ፤ በ11,830 ኪሎ ኸርዝ 25 ሜትር ባንድ እና በ 9,555 ኪሎ ኸርዝ፣ 31 ሜትር ባንድ ይደመጣል። በሳተላይት በበድር 4፣ በ12,111 ሜጋ ኽርዝ፣ ሆሪዞንታል፣ DWA2፤ በዩቴል-ሳት 8WB 11,137 ሜጋ ኸርዝ፣ ሆሪዞንታል፣ DWA2፤ በሆትበርድ 13 B፣ 11,727 ቨርቲካል፣ DW08፤ እንዲሁም በSES-5 በ12,034 ሜጋ ኼርዝ፤ ሆሪዞንታል DW08 ላይ እንገኛለን።
በዩቴልሳት ለማዳመጥ DVB-S2 ደረጃ ያለው ማለት የ HD ስርጭትን መቀበል የሚችል ቴሌቪዥን ያስፈልጋል። አንዳንድ ቴሌቪዥኖች DVB-52 ሊኖራቸው ስለሚችል በተመሳሳይ መስመር ፈልጉን።
እነዚህን አማራጮች መረጃው ለሌላቸው በማጋራት ተባበሩን።
5.5K viewsDW Amharic, 15:53
Open / Comment
2021-02-16 14:00:15
ካለፉት ሳምንታት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን እና የለውጡን አመራር የሚደግፉ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ናቸው። በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የጀመረው ይኸው የድጋፍ ሰልፍ በምዕራብ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያም የተደረገ ሲሆን በዛሬውም ዕለት እንደ ኮምቦልቻ ፣ ደሴ፣ ከሚሴ እና ባቲ ባሉ ከተሞች በመካሄድ ላይ ነው።
የምርጫ ቅስቀሳ ከትናንት የካቲት 8 ቀን 2013 አንስቶ በይፋ እንደሚጀመር የተገለጸ ቢሆን እስካሁን የተፎካካሪ ፓርቲዎች መሰል ሰልፍ መካሄዱ አልተሰማም። ተቺዎች ሰልፍ የሚፈቀደው ለብልፅግና ፓርቲ ወይም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋፊዎች ብቻ ነው ሲሉ ይደመጣል። ወቅቱ የኮቪድ 19 ተሐዋሲ እንዳይስፋፋ የሚሰጋበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምን ያህል ታስበዋል ማለት ይቻላል?https://www.facebook.com/dw.amharic/photos/a.507141705985597/4167865066579891
6.5K viewsDW Amharic, 11:00
Open / Comment
2021-02-15 20:22:55 የቱርኩ ፕሬዚዳንት ራስብ ጠይብ ኤርዶሃን ዩናይትድ ስቴትስ በኢራቅ የሚገኙ እና «አሸባሪ » ላሏቸው የኩርዲስታን ሚሊሻዎች ትወግናለች ሲሉ ከሰሱ። ፕሬዚዳንቱ ክሱን ያሰሙት የኩርዲስታን ሠራተኞች ፓርቲ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ፒኬኬ በሰሜናዊ ኢራቅ አብዛኞቹ ወታደሮች የሆኑ 13 ቱርኮችን ገድለዋል የሚል ስሞታ ከቀረበባቸው በኋላ ነው። የኩርዲስታን ሚሊሻዎች ከደቡባዊ ምሥራቅ ቱርክ አግተው የወሰዷቸውን አብዛኞቹ የመንግሥት ወታደሮች እና የፖሊስ መኮንኖችን በሰሜናዊ ኢራቅ ዋሻዎች ውስጥ ሸሽገዋቸው እንደነበር የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። ፒኬኬ እጎአ ከ1984 ዓ/ም ጀምሮ በቱርክ መንግሥት ላይ በጀመረው አመጽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ይታመናል። ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የቱርክ አጋር የሆኑት የተቀሩት ምዕራባውያን ፒኬኬን በአሸባሪነት ፈርጀው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ በተናጠል በሶርያ የሚገኙ ሌሎች ኩርዳውያን ሚሊሻዎችን ስትደግፍ መቆየቷ ቱርክን አላስደሰተም። ቱርክ 13ቱን ታጋቾች ለማስለቀቅ በዚህ ወር በሰሜናዊ ኢራቅ ወታደራዊ ዘመቻ አካሂዳ ነበር። ባይሳካም ቅሉ። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ትናንት እሁድ ባወጣው መግለጫ «በቱርካውያን ላይ የተፈጸመው ግድያ ያሳዝናል፤ ነገር ግን ስለዘገባው ትክክለኛነት ተጨማሪ ማረጋገጫ ያስፈልገኛል» ብላለች። ነገር ግን የኩርዲስታን ኃይሎች ግድያውን መፈጸማቸው ከተረጋገጠ ዩናይትድ ስቴትስ አጥብቃ እንደምትኮንነው ዘገባው አያይዞ አመልክቷል።
7.2K viewsDW Amharic, 17:22
Open / Comment
2021-02-15 20:22:25 የየካቲት 08 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ስፖርት ዘገባ
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ፒየር ኤመሪክ አውባሜያንግ ሔትትሪክ በመሥራት አርሰናልን ለድል አብቅቷል። እንደ ማንቸስተር ሲቲ ሌስተር ሲቲም ሊቨርፑል ላይ በግብ ተምነሽንሾበታል። በሻምፒዮንስ ሊጉ ሊቨርፑል ነገ ማታ ከጀርመኑ ላይፕትሲሽ ጋር ይጋጠማል። በተመሳሳይ ሰአት የስፔኑ ባርሴሎና የፈረንሳዩ ፓሪ ሳን ጃርሞን ይገጥማል።https://p.dw.com/p/3pOGw?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
6.3K viewsDW Amharic, 17:22
Open / Comment
2021-02-15 20:21:36 የእስራኤሏ የቴልአቪቭ ከተማ ነዋሪቿ የኮቪድ 19 ክትባት እንዲወስዱ ለማበረታታት ነጻ የምግብ ዕደላ መጀመሯን አስታወቀች። ከተማዋ የማበረታቻ እርምጃውን ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው አጎራባች የሆነችው የበናይ ብራክ ከተማ ተግባራዊ ማደግ ከጀመረች በኋላ መሆኑ ተነግሯል። በከተማዋ በተለይ የተሕዋሲው ስርጭት በርትቶ በታየባቸው እና ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኝነቱ ባልታየባቸው ሁለት አካባቢዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ነጻ የምግብ አቅርቦት እንደ ማበረታቻ ቀርቦላቸዋል ነው የተባለው። «ይህን በማድረግ የተሕዋሲውን ስርጭት በመቆጣጠር የትምሕርት፣ የንግድ እና የባህል ተቋማት ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ እና መደበኛው እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን በፍጥነት እንዲጀመር የተቻለንን እናደርጋለን» ሲሉ ከንቲባው ሮን ሁልዳይ ተናግረዋል። እስራኤል ከ9,3 ሚሊዮን ዜጎቿ አንድ አራተኛው የሚሆኑት ተከታትለው የሚሰጡትን ሁለቱን ክትባቶች መከተባቸውን የጀርመን ዜና ምንጭ ዘግቧል።
5.0K viewsDW Amharic, 17:21
Open / Comment
2021-02-15 20:21:21 ናይጄሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ ልዌላ የዓለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር መሆናቸው ተረጋገጠ። ኦኮንጆ ልዌላ 164 አባል ሃገራትን ያቀፈውን ዓለም አቀፉን ተቋም በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ሹመታቸው ዛሬ ሲረጋገጥ ዓለም አቀፍ የንግድ አለመግባባቶችን መፍታት ተቀዳሚ ተግባራቸው እንደሚሆን ይጠበቃል። አዲሷ የዓለም የንግድ ድርጅት ተሿሚ ሹመታቸው የተረጋገጠው አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይሁንታን ካገኘ በኋላ ነው ተብሏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ቀርቦላቸው የነበረውን የኦኮንጆ ልዌላን ሹመት ወደ ጎን ገፍተውት ነበር። የባይደን ርምጃ ቀደም ሲል ዶናልድ ትራምፕ ዓለም አቀፍ የንግድ ትብብሮችን ለአደጋ አጋልጦ እንደነበር የሚነገርለት እና «አሜሪካ ትቅደም» አቀራረባቸውን በማስቀረት አንድ እርምጃ ወደ ፊት ያራመደ ነው እየተባለ ነው። የናይጄሪያ የገንዘብ ሚንስትር የነበሩት ኦኮንጆ ልዌላ ከ25 ዓመታት በላይ ያገለገሉበት እና እስከ ሁለተኛው የሥልጣን እርከን ያደረሳቸው የዓለም ባንክ አገልግሎታቸው እና ልምዳቸው ለአዲሱ የሥራ ኃላፊነት እንዳሳጫቸው የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ያሳያል። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም የንግድ ድርጅትን በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ አያያዝ ይከተላል በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱ ቆይተዋል።
4.6K viewsDW Amharic, 17:21
Open / Comment
2021-02-15 20:20:54 የትራምፕ ዳግም ድል፣ የአሜሪካ ክፍፍል
ትራምፕ ከቀዝቃዛዉ የዋሽግተን ዓየር፣ ከፖለቲካ ጥልፍልፍ፣ እሰጥ አገባ፣ ዉጣ ዉረዱ ብዙ ርቀዉ ከዚያ ምቹ፣ ዉብ፣ቅንጡ ደሴት፣ ፀጥ፣ ረጋ፣ ለብ-ሞቅ ያለዉን ዓየር እየማጉ በተመሰረተባቸዉ ክስ የሚደረገዉን ክርክር ይከታተላሉ።https://p.dw.com/p/3pONk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.3K viewsDW Amharic, 17:20
Open / Comment
2021-02-15 20:19:13 ቻድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሽብርተኞች ጥቃት ተጋላጭ የሆነውን የምዕራብ አፍሪቃ የሳህል ሃገራትን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረበች። ቻድ ጥሪውን ያቀረበችው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበይነ መረብ ተሳታፊ የሆኑበት እና አምስት የሳህል ሃገራት የተገኙበት ውይይት በመዲናዋ በንጃሜና በተጀመረበት ወቅት ነው። ቻድ ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ሞሪታንያ እና ኒጀር እየመከሩ ባሉበት በዚሁ መድረክ የሳህል ቀጣና ሃገራት ድህነትን አምርረው በሚታገሉበት በዚህ ወቅት «ሽብርተኞች እንቅፋት ሆነውብናል» ሲሉ የቻዱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ተናግረዋል። በዚህም ዓለም አቀፉ ማኅሕበረሰብ የአሸባሪዎችን የሽብር ምንጭ ለማድረቅ ለአካባቢው ሃገራት የሚያደርጉትን የልማት ገንዘብ ማሳደግ አለባቸው ብለዋል። የሳህል ሃገራት ስብሰባ ፈረንሳይ በቀጣናው ከአሸባሪዎች ጋር የሚደረገውን ውግያ ለማገዝ በአካባቢው ኃይሏን ማጠናከር ከጀመረች ከአንድ ዓመት በኋላ መካሄዱን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። ፈረንሳይ በሳህል ቀጣና አገሮች ቀደም ሲል 4,500 የነበረውን የወታደሮቿን ቁጥር ወደ 5,100 ከፍ አድርጋለች።
4.2K viewsDW Amharic, 17:19
Open / Comment