Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.70K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 583

2021-02-11 19:58:24 በአውሮጳ የኮሮና ክትባት መጓተት

በአውሮጳ የኮሮና ክትባት ሂደት መጓተትና በሩሲያ አንጻር በሚወሰዱ አቋሞች ላይ የፓርላማ አባላትና አንዳንድ አባል መንግሥታት ጭምር በኮሚሽኑ ባለሥልጣናት ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ነው።
https://p.dw.com/p/3pERN?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
3.8K viewsDW Amharic, 16:58
Open / Comment
2021-02-11 19:57:13 የኢዜማ ወቅታዊ ማሰሳቢያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ በምህጻሩ ኢዜማ በትግራይ ሰብዓዊ ርዳታ ባስቸኳይ እንዲቀርብ አሳሰበ።
https://p.dw.com/p/3pE7g?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
3.7K viewsDW Amharic, 16:57
Open / Comment
2021-02-11 19:54:50 የቀይ መስቀል በስሙ ለቀረበው ዜና ማስተባበያ ሰጠ

የቀይ መስቀል 80 በመቶ የትግራይ ክልል የሰብዓዊ ርዳታ አይደርስም አለ በሚል በስሙ የቀረበውን ዜና አስተባበለ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ሆስፒታሎችንና የጤና ተቋማትን፣ የተፈናቀሉ ሰዎችንም መመልከቱን ገልፀ።
https://p.dw.com/p/3pE6P?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
3.7K viewsDW Amharic, 16:54
Open / Comment
2021-02-11 19:53:21 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ይቅርታ

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግሮች ምክንያት በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰው ሞት እና ከቤት ንብረት መፈናቀል አስመልክቶ ይቅርታ ጠይቋል።
https://p.dw.com/p/3pE55?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
2.3K viewsDW Amharic, 16:53
Open / Comment
2021-02-11 19:51:37 በትግራይ የተለያዩ ከተሞች አድማ

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ኅብረተሰቡ ቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ላይ መሆኑ ተሰማ። ሱቆች መዘጋታቸው፤ የግልና የመንግሥት ቢሮዎች እንደማይሠሩ፤ የታክሲዎችም እንቅስቃሴ ማቆማቸውን ለመረዳት ችለናል።
https://p.dw.com/p/3pE4V?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
2.4K viewsDW Amharic, 16:51
Open / Comment
2021-02-11 18:56:47
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከሚገኙ ሆስፒታሎች አሰባሰብኩ ባለው መረጃ መሰረት ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ 108 የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መድረሱን አመልክቷል። ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው በትግራይ ክልል እየተፈጠረ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ለመከላከል የመሰረተ ልማት ፣ የማህበራዊ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ሊመለስ ይገባል ብሏል። በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ከሶስት ወራት ላለፈ ጊዜ ወደነበረበት ያልተመለሰው የማህበራዊ እና አስተዳደራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመሰረተ ልማቶች የአካባቢውን ነዋሪዎች እና ተፈናቃዮች ለተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰት አጋልጧቸዋል ብሏል። ኮሚሽኑ በአካል ተገኝቶ ክትትል ማድረግ ባልቻለባቸው በርካታ የክልሉ አካባቢዎች «የሰው ሕይወት አልፏል፣የአካል እና የስነልቦና ጉዳት ደርሷል፣ እንዲሁም ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት እና ዘረፋም ተፈጽሟል» ብሏል። ኮሚሽኑ በክልሉ ከሚገኙ አራት ሆስፒታሎች ከመቀሌ፣አይደር ፣ አዲግራት እና ውቅሮ ሆስፒታሎች አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 108 የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች ተፈጽመዋል ብሏል። ኮሚሽኑ አያይዞም በመቀሌ እና በሌሎች ተዘዋውሮ በተመለከታቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ የሚደረገው ጥረት መልካም መሆኑን በመግለጫው ጠቁሟል። ነገር ግን የአስቸኳይ እርዳታ ፍላጎቱ ገና እንዳልተሟላ ነው በመግለጫው የተመለከተው። በተጨማሪም በጦርነቱ ወቅት ተቀብረው የነበሩ እና በየሜዳው ተጥለው የነበሩ ፈንጂዎች በተለይ በሕጻናት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ኮሚሽኑ አያይዞ ገልጿል።‹‹እጅግ አሳዛኝና አሳሳቢው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጾታዊ ጥቃትና በሕጻናት ላይ የደረሰው ጥቃትና ጉዳቱ ከዚህ የበለጠ እንዳይስፋፋ ልዩ ትኩረትና ጥረት ይሻል›› ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።
6.3K viewsDW Amharic, 15:56
Open / Comment
2021-02-11 18:05:32
ሱዳን በሶስት ግዛቶቿ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሏን አስታወቀች። ሱዳን የሰዓት እላፊውን የደነገገችው በግዛቶቹ ህዝባዊ አመጽ እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ነው ተብሏል። የሰዓት እላፊ ገደቡ የተጣለባቸው ግዛቶች የሰሜን እና ደቡብ ዳርፉር እና የሰሜን ኮርዶፋን ግዛቶች ናቸው። ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ አልፋሽር በተባለች ከተማ እና አካባቢው በግመል አርቢዎች እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት በሱዳን አብዛኞቹ አካባቢዎች አመጽ እንዲባባሱ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ያመለክታል። በየአካባቢው እያየለ የሄደውን አመጽ ተከትሎም አመጾቹ አይለው በተስተዋሉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ምክንያት መሆኑም ተጠቁሟል። በግዛቶቹ የተቀሰቀሰው አመጽ እና ግጭት ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ የሚመሩትን አዲሱን የሱዳን የሽግግር መንግስት መፈታተኑም እየተነገረ ነው። የሰሜን ኮርዶፋን ግዛት አስተዳዳሪ ካሊድ ሙስጠፋ አደም በክልላቸው የሰአት ዕላፊ ገደብ መታወጁን ይፋ አድርገዋል። አስተዳዳሪው አዋጁን “የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ” የታወጀ ነው ብለዋል። ነገር ግን በግዛቶቹ የተላለፈው የሰዓት እላፊ ገደብ ያበሳጫቸው ሱዳናውያን አዋጁን እንደማያከብሩ የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በሱዳን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሀሰን ኦማር አልበሽርን ከስልጣን ያባረረው የኢኮኖሚ ውድቀት ሊስተካከል ቀርቶ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ ስለመምጣቱ በስፋት እየተዘገበ ነው። በአዲሱ መንግስት በቀላሉ ሊስተካከል የማይችል አስቸጋሪ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ቀውስ መከሰቱ በስፋት እየተዘገበ ነው፡፡
3.3K viewsDW Amharic, edited  15:05
Open / Comment
2021-02-11 16:32:05
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ ዛሬ ሌሊት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳዋ ፖሊስ አስታወቀ። ፖሊስ እንዳለው በርካታ ሰዎችን ከሌላ ጭነት ጋር ደርቦ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በወረዳዋ ሀርአምባ ቀበሌ ልዩ ስሙ ልጄን አደራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በመገልበጡ የስድስት ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 30 ያህል ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል። የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘገባ እንዳመለከተው ተሽከርካሪው በጫነው 39 ኩንታል ጤፍ ላይ 87 ሰዎችን ደርቦ ጭኖ ይጓዝ ነበር።የአደጋው ምክንያትም ዳገት ላይ ደርሶ ወደ ኋላ በመንሸራተት ወንዝ ውስጥ በመግባቱ መሆኑን የወረዳዋ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጂን ዘነበ ወልዴ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በአደጋው የተጎዱት በጎረቤላ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ጣቢያው ኃላፊ አቶ ተዋበ አይችሉህም ገልጸዋል።
3.8K viewsDW Amharic, 13:32
Open / Comment
2021-02-11 15:12:23
’የረዳነው ተርፎን ሳይሆን ህይወትን ለማዳን ካለን በማካፈል ነው፡፡” አፋሮች!
የአፋር ክልላዊ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ እርዳታ ፈላጊዎች የሚሆን የእለት እርዳታ ማድረጉን አስታወቀ:: ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ በክልሉ የተከሰተውን ቀውስ እንዲታደጉ የክልሉ መንግስት ጥሪ አድርጓል፡፡
የአፋር ክልል መንግስት የአደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት ክልሉ ተርፎት ሳይሆን ካለው በማካፈል በትግራይ ክልል በችግር ለተጋለጡ ወገኖች የእለት እርዳታ የሚሆን 9 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 2ሺህ 700 ኩንታል ምግብ የእለት እርዳታ አቅርቧል፡፡
በአጠቃላይ ክልሉ ደረገው ድጋፍ 1500 ኩንታል ሩዝ፣ 900 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 200 ኩንታል ጨውና ሌሎችም ምግብ ነክ እርዳታዎች ይገኙበታል፡፡
አቶ መሐመድ እንዳሉት በክልላቸው ባለፉት የክረምት ወራት በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተፈጥረው በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው እንደነበር አስታውሰው፣ ዛሬ ያደረጉት እርዳታ ተርፏቸው ያደረጉት ሳይሆን ወገንን ለማዳን ካላቸው በማካፈል የተደረገ እርዳታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ በትግራይ ክልል ያንዣበበውን ሰብአዊ ቀውስ መታደግ እንደሚገባቸው ጠይቀዋል፡፡
በትግራይ ክልል አንዳንዶቹ 4 .5 ሚሊዮን ህዝብ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ መጋለጡን ሲያመለክቱ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ የተባለው ቁጥር በመረጃ ያልተደገፈ መሆኑና ትክክለኛ በክልሉ ያለው የተረጂ ቁጥር ከ2.5 ሚሊዮን እንደማይበልጥ በተደጋጋሚ አመልክቷል፡፡ የባህርዳሩ ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን እንደዘገበው ከትግራይ ክልል ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት ባለስልጣናቱ ስልክ ማንሳት ባለመቻላቸው አልተሳካም፡፡
4.1K viewsDW Amharic, 12:12
Open / Comment
2021-02-11 15:01:23
የጀርመን መንግስት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል የጣለዉን የመንቀሳቀስ ገደብ ለተጨማሪ ጊዜ አራዘመ።የጀርመን መራሒተ አንጌላ ሜርክልና የክፍለ-ግዛት አስተዳዳሪዎች ትናንት ባደረጉት ስብሰባ እገዳዉ ጥቂት መሻሻል ተደርጎበት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር እስከ መጋቢት 7 ድረስ እንዲራዘም ወስነዋል።ከዚሕ ቀደም ሁለቴ ተራዝሞ የነበረዉ እገዳ በመጪዉ ዕሁድ ያበቃል ተብሎ ነበር።አዲስ በተሻሻለዉ ደንብ መሠረት ሙሉ በሙሉ ተዘግተዉ የነበሩት የዉበት ሳሎኖች ከመጪዉ መጋቢት መጀመሪያ ጀምሮ ይከፈታሉ።የተዘጉ ትምሕርት ቤቶችን በተመለከተ የክፍለ ግዛት መስተዳድሮች እንደየአካባቢዎቻቸዉ ተጨባጭ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ፣ በኢንተርኔት (ኦንላይን)ብቻ አለያም ሁለቱንም ቀይጠዉ እንዲያስተምሩ እንዲወስኑ ተሰብሳቢዎቹ ወስነዋል።የእንቅስቃሴ ገደቡን አጠቃላይ ውጤት ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ አራት ቀናት አስቀድሞ በሚደረግ ተመሳሳይ ውይይት ከአንዳች ውሳኔ እንደሚደረስ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል አስታውቀዋል::ጀርመን ዉስጥ የተህዋሲው ስርጭት ቢቀንስም በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚሰራጭ የተነገረለት ልዉጥ ተሕዋሲ ስጋት አሳድሯል::የእንቅስቃሴ ገደቡ ሊላላ የሚችለው በአንድ ሳምንት ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች አሀዝ ከ100,000 ሰዎች ከ35 ሰዎች በታች ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ የሳክሶኒ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካኤል ክሬሸሜር ከትናንቱ ውይይት በኃላ ተናግረዋል::
3.7K viewsDW Amharic, edited  12:01
Open / Comment