Get Mystery Box with random crypto!

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.70K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 587

2021-02-08 19:39:01 የሙስና ክስ ከተመሰረተባቸዉ ከዘጠኝ ወራት በኃላ ዛሬ የ71 ዓመቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ችሎ ፊት ቀረቡ። ኔታንያሁ ከሙስና ቅሌት ክስ ሌላ የማጭበርበርና የክህደት ክስም ተመስርቶባቸዋል ተብሎአል። ኔታንያሁ ለተከሰሱባቸዉ ወንጀሎች ሁሉ በግልፅ ይቅርታ መጠየቅን «አስቂኝ » ሲሉ መመለሳቸዉን የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቦአል። ይሁንና ፍርድ ቤቱ ያቀረበባቸዉን የማጭበርበር የክህደት እንዲሁም የሙስና ክሶች ሁሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃሰት ሲሉ አጣጥለዋል። «በፈጠራ» እኔ ላይ የተጣለዉ ክስ በፖሊስ እና በአቃቤ ሕግ የተቀነባበረ ነዉ ሲሉ ወቀሳን ሰንዝረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚዎች በበኩላቸዉ «ቤንያሚ ኔታንያሁ ይታሰሩ» ሲሉ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀረቡበት ፍርድ ቤት ፊት የተቃዉሞ ሰልፍም አካሂደዋል።
4.3K viewsDW Amharic, 16:39
Open / Comment
2021-02-08 19:38:46 የሶማልያ ተቃዋሚ መሪዎች ምርጫዉ መራዘሙን ይፋ ላደረጉት ለፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ -ፎርማጆ የስልጣን እዉቅና እንደማይሰጡ ገለፁ። የሶማልያ መንግሥት ተቃዋሚዎች እዚህ ዉሳኔ ላይ የደረሱት ፎርማጆን ለመተካት ሊካሄድ የነበረዉን ምርጫ ምንም ፖለቲካዊ ስምምነት ሳይኖር ስልጣናቸዉን በገዛ ፈቃዳቸዉ በማራዘማቸዉ ነዉ። የሶማልያ የተቃዋሚዎች ጥምረት ፕሬዚዳንታዊ እጩ ፤ በሶማልያ የሽግግር ብሔራዊ መንግሥት እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበዋል፤ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ ሕገ-መንግሥቱን እንዲያከብሩም አሳስበዋል። የሶማልያ ፕሬዝደንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ ትናንት ለሃገሪቱ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ እንደነገሩት ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ባለመስማማታቸዉ ምርጫዉ አሁን ማካሄድ አልተቻለም ብለዉ ነበር። በሌላ በኩል ከሶማልያ መዲና መቃዲሾ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ድሻምሪብ ከተማ ለደረሰዉ ፍንዳታ ኧልሸባብ ኃላፊነትን ወስዶአል። ትናንት አካባቢዉ ላይ በደረሰዉ ፍንዳታ ቢያንስ 13 የሶማልያ የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸዉ የሚታወስ ነዉ። ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ በነበረባት ወቅት ባለማካሄዷ የፖለቲካ ቀውስ ይገጥማታል የሚል ስጋት ተቀስቅሶአል።
4.0K viewsDW Amharic, 16:38
Open / Comment
2021-02-08 19:38:24 https://p.dw.com/p/3p4Dl?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
3.7K viewsDW Amharic, 16:38
Open / Comment
2021-02-08 19:37:58 የሱዳን መንግስት የቀድሞ የአማፅያንን በሚንስትርነት ሾሞ አዲስ ካቢኔዉን ይፋ እንደሚያደርግ ዛሬ አስታወቀ። የሱዳን መንግሥት እዚህ ዉሳኔ ላይ የደረሰዉ ባለፈዉ ጥቅምት ወር በሃገሪቱ ለአስርት ዓመታት የዘለቀዉን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም ያለመ የሰላም ስምምነት ካካሄደ በኋላ ነዉ። የሱዳንን አዲስ ካቢኔ ለመመስረት እንድያስችላቸዉ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ትናንት ምሽት ካቢኔያቸዉን መበተናቸዉ ተዘግቦአል። እንደ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ሃምዶክ አዲስ በሚመሰርቱት ካቢኔ ሰባት ሚኒስትሮች ከቀድሞዉ የአማጺ ቡድን የተመረጡ እንደሆነም ይገመታል። ሌሎች ሁለት ሚኒስትሮች ከወተዳራዊዉ ኃይል በኩል የመጡ ይሆናል ተብሎአል ። ቀሪዎቹ 17 ሚኒስትሮች ደግሞ በሱዳን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ቁልፍ ሚና ተጫዉተዋል ከሚባሉት የነፃነት እና የለውጥ ኃይሎች መካከል ይሆናል ተብሎአል። የሱዳን የነፃነት እና የለውጥ ኃይል ቡድን በጎርጎረሳዉያኑ 2019 ዓመት ሱዳንን ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በፈርጣማ ክርናቸዉ የገዙትን የቀድሞዉን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን የገረሰሰ ቡድን መሆኑ አይዘነጋም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አዲሱ ካቢኔያቸዉን ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
3.6K viewsDW Amharic, 16:37
Open / Comment
2021-02-08 19:37:31 የአገራችንን ሉዓላዊነት ተዳፍሮ የገባው የሱዳን ጦር ችግሩ የበለጠ ከመወሳሰቡ በፊት መንግስት እልባት እንዲፈለግ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት የተባለ ማህበር ጠየቀ፡፡ ማህበሩ ትናንት ማምሻውን ባህርዳር ላይ በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው የሱዳን ጦር የአገራችንን ድንበር ተሸግሮ ረጅም ኪሎሜትር ዘልቆ ገብቷል፡፡ በመሆኑም ችግሮቹ ከመወሳሰባቸው በፊት መንግሰት ለችግሩ እልባት መፈለግ እንዳለበት የህብረቱ ጽ/ ቤ ት ኃላፊ አቶ መሳፍንት መንግስቱ በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ጽ/ ቤ ት ኃላፊ አቶ መሳፍንት መንግስቱ በመግለጫቸው እንደጠቀሱት ባለፈው ዓመት ከደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎችን ጉዳይም መንግስት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ከወለጋ ዞኖች አካባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከመሄዳቸው በፊት መንግስት አስተማማኝ ዋስትና እንዲሰጣቸው ሲል ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት በመግለጫዉ አሳስቦአል፡፡
2.0K viewsDW Amharic, 16:37
Open / Comment
2021-02-08 19:37:02 https://p.dw.com/p/3p47x?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.0K viewsDW Amharic, 16:37
Open / Comment
2021-02-08 19:36:41 ዩናይትድ ስቴትስ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ወደ ነበራት የታዛቢነት ቦታዋ እንደምትመለስ አስታወቀች። በቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በትራምፕ የስልጣን ዘመን አሜሪካ በጎርጎረሳዉያኑ 2018 ሐምሌ ወር ላይ ከመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የታዛቢነት ቦታዋን ለቃ መዉጣትዋ የሚታወስ ነዉ። ትራምፕ የመንግሥታቱን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ምክር ቤትን ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ እስራኤልን በተደጋጋሚ በመተቸቱ ምክኒያት አድሏዊ አድርገው ቆጥረዉት ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ በዘረኝነት ዉንጀላ ምክንያቶች በምክር ቤቱ ዒላማ ስር ወድቃ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ወደ ተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ታዛቢነት ቦታ መመለስ ትራምፕ ከዓለም አቀፍ ግዴታዎች ለመላቀቅ ያሳለፉት ዉሳኔን በመቀልበስ በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር በጆ ባይደን የተወሰደ ተጨማሪ ርምጃ ነዉ።
2.0K viewsDW Amharic, 16:36
Open / Comment
2021-02-08 19:36:16 https://p.dw.com/p/3p49u?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.0K viewsDW Amharic, 16:36
Open / Comment
2021-02-08 19:35:54 በጀርመን ባለፉት አስርተ ዓመታት ያልታየ የተባለለት የክረምት ወራት በተለይ በሰሜናዊ ጀርመን የባቡር እና የተሽከርካሪን እንቅስቃሴን ገታ። በሰሜናዊ ጀርመን እንከ መካከለኛ ጀርመን በሚገኙ በተለያዩ ግዛቶች የሚጥለዉ የጥጥ ንድፍ የመሰለዉ በረዶ ለመጥረግ የመንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ ሰራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ነዉ። ከበረዶዉ ሌላ ጎዳናዉ እጅግ አሸራተች መሆናቸዉ ብሎም የባቡር ሃዲዲች በበረዶ ክምር በመሞላታቸዉ እና ከፍተኛ ንፋስ በመኖሩ የመንገድ መጥረጉን ስራ እጅግ እንዳከበደዉ ተነግሮአል። የራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በበቦን ከተማ እጅግም በረዶ አይታይም።
2.0K viewsDW Amharic, 16:35
Open / Comment
2021-02-08 19:35:28 https://p.dw.com/p/3p4a8?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
2.1K viewsDW Amharic, 16:35
Open / Comment