2021-02-08 16:03:50
You sent Today at 1:19 PM
በአማራ ክልል በወሊድ ወቅት የደም መፍሰስ ለእናቶች ሞት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ ተገልጧል:: ባለፉት 6 ወራት ከአንድ ሺህ 300 በላይ ህፃናት ከተወለዱ በኋላ ህይወታቸው እንዳለፈም ተመልክቷል:: አንዳንድ ባለሙያዎች የችግሮች ሁሉ መነሻ ለአዋላጅነት ሙያ የተሰጠው ትኩረትና ግንዛቤ አናሳ መሆንና በሙያው የመቆየት ፍላጎት አለመኖር እንዲሁም የግብዓት እጥረት ዋናዎቹ ምክንያቶች መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡
የኢትዮጵያ አዋላጅ ነርሶች ማህበር ሰሞኑን በባሕር ዳር ከተማ ባዘጋጀው ውይይት እንደተጠቀሰው የእናቶች እና የጨቅላ ህፃናት ሞት በተለያዩ ሁኔታዎች አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
በእለቱ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች ጤና አገልግሎት አስተባባሪ ሲሰተር አዲስዓለም ጫኔ እንዳሉት አሁንም በተለያዩ ምክንያቶች ከሚሞቱ እናቶች ውስጥ 43 ከመቶ የሚሆኑት ህይወታቸው የሚያልፈው በወሊድ ወቅት በሚፈጠር ደም መፍሰስ ነው፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት 74 ከመቶ የሚሆኑት ህፃናት ሆስፒታል ውስጥ የተወለዱ ቢሆንም ከሚሞቱት መካከል በርካቶቹ ደግሞ እዛው ሆስፒታል ውስጥ እንደሚሞቱ በቀረበው ፅሁፍ ቀርቧል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ሲሰተር አዲስዓከለምን በሰጡት ምላሽ የሆስፒታሎቹ የመሰረተ ልማት እጥረትና ሆስፒታሎች በርካታ ተገልጋዮችን ስለሚያስተናግዱ ከሚፈጠር ጫና ነው ብለዋል፡፡
በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥር አሁንም ወደ ተፈለገው ደረጃ እንዳልደረሰ ያመለከቱት ባለሙያዋ፣ 48 ከመቶዎቹ አሁንም ወደ ጤና ተቋማት አይመጡም፡፡
ችግሮቹ በርካታ መሆናቸውን የሚናገሩት ባለሙያዎቹ የግብዓት እጥረት ዋነኛው ነው፡፡
የክፍያና የትምህርት እድሎች አለመኖርና ለአዋላጅ ነርስነት የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን ሌላው ችግር መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያዎቹ ብዙዎቹ
4.1K viewsDW Amharic, 13:03