🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ኢትዮጵ

Logo of telegram channel ethyoop — ኢትዮጵ
Logo of telegram channel ethyoop — ኢትዮጵ
Channel address: @ethyoop
Categories: Blogs
Language: Not set
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.56K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 2

2020-08-04 12:27:07 ኢትዮጵ pinned a photo
09:27
Open / Comment
2020-08-04 10:03:18
#ኢትዮጵ

#የኢትዮጵያ_አጠቃላይ_መረጃ

•መልክዓምድር

•አጠር ያለ ታሪክ

•የመንግስት አወቃቀር

•ቋንቋዎች እና ሌሎች መረጃዎችን





ነገ ማታ 1፡00 ይጠብቁን
ኢትዮጵ
3.3K views07:03
Open / Comment
2020-06-24 19:00:06 #የ1906_የበልጂየም_እና_የእንግሊዝ_ስምምነት

ይህ ስምምነት ግንቦት 09 ቀን 1906 እ.ኤ.አ በበልጂየም(ኮንጎን በመወከል) እና በእንግሊዝ መካከል የተከናወነ ሆኖ በዚሁ ስምምነት በአንቀፅ 3 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው የኮንጎ መንግስት ከሰምሊኪ ወይም ከልሳንጎ ወንዝ ወደ አልበርት ሀይቅ የሚወርደውን ውሀ ከሱዳን መንግስት ጋር አስቀድሞ ሳይስማማ የውሀውን ይዘት የሚቀንስ ስራ እንዳይሰራ ወይም ውሀውን የሚቀንስ ስራ ለመስራት ለማንም ፈቃድ እንዳይሰጥ በዚህ ውል አድርገዋል የሚል ነበር፡፡ ይህ ስምምነት የኮንጎ ህዝብ ከናይል ወንዝ ላይ የመጠቀም መብቱን የሚከለክል፤የሀገሪቱ ብሄራዊ ጥቅምን የሚጎዳ በበልጅየም ፍላጎት ብቻ የተፈረመ ሲሆን የታችኞች ተፋሰስ ሀገራትን ብቻ የሚጠቅም ኢ-ፍትሀዊ ስምምነት በመሆኑ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም፡፡

#የ1906_የእንግሊዝ_የጣልያንና_የፈረንሳይ_ስምምነት

ይህ ስምምነት በእንግሊዝ፣ ጣልያንና ፈረንሳይ መካከል በሎንደን የተከናወነ የሶስትዮሽ ስምምነት(Tripartite Agreement) ሲሆን በዚሁ ስምምነት አንቀፅ 4(a)ላይ እንደተመለከተው ፍፁም ግዛታዊ አንድነት ላይ በመመስረት የኢትዮጵያ መብትን ገታ በማድረግ በአንድ በኩል፤ጣልያን በሶማሊያና በኤርትራ ላይ ያላትን የቆየ ጥቅምን በማስጠበቅ በሌላ በኩል፤የእንግሊዝና የግብጽ ጥቅም በናይል ወንዝ ለማረጋገጥ ሶስቱም ሀገራት የተስማሙበት ነው፡፡ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በልአላዊ ግዛቷ ላይ በሚገኝ የውሀ ኃብት እንዳትጠቀም ሙሉ ለሙሉ ያገለላት በመሆኑ በውሀዋ ላይ እንድትገለገል ሊያሰቆማት የሚችል የውጭ ሃይል እንደሌለና ስምምነቱንም በኢትዮጵያ ተቀባይነት እንደማይኖረው በግልፅ ለሀገራቱ አሳውቃለች፡፡

#የ1925_የእንግሊዝና_የጣልያን_ስምምነት
በ1919 እ.ኤ.አ እንግሊዝ በጣና ሀይቅ ላይ ግድብ እንድትሰራ የኢትዮጵያ ይሁንታ እንድታገኝ ጣልያን ድጋፏን የምትሰጥ መሆኗን የሚገልፅ የስምምነት ማእቀፍ በእንግሊዝና በጣልያን መካከል ተከናወነ፡፡ ይህን ስምምነትን ተከትሎ በ1925 እ.ኤ.አ.ግብፅና ሱዳን በነጭና ሰማያዊ ናይል (ጥቁር አባይ) እንዲሁም በሌሎች የናይል ገባሪ ወንዞች ላይ የውሀ ስራዎችን ለመስራት ቅድሚያ መብት እንዳላቸውና ሌሎች ሀገራት የወንዙን የውሀ ይዘት የሚቀንስ ማንኛውም አይነት ስራ እንደማይሰሩ በመግለፅ ጣልያንና እንግሊዝ የማስታወሻ ልውውጥ አደረጉ፡፡ ይህ የደብዳቤ ልውውጥን ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ተቋውሟን ገልፃለች፤ቅሬታዋን በወቅቱ ለነበረው የአለም መንግስታት ድርጅት (League of Nations) አስታውቃለች፡፡

#የ1929_የእንግሊዝ_እና_የግብፅ_ስምምነት

ይህ ስምምነት ሱዳንን እና ሌሎች በእንግሊዝ ስር የነበሩ ቅኝ ተገዢዎችን(ኡጋንዳ፣ ኬንያና ታንዛንያን)በመወከል በእንግሊዝ እና በግብፅ መካከል የተከናወነ ሆኖ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገራትን ሊጎናፀፉት የሚገባቸውን ተፈጥሮአዊና ፍትሀዊ የውኃ ኃብት ተጠቃሚነትን እውቅና የማይሰጥ ፍፁም የሁለትዮሽ ስምምነት ነበር፡፡ ይህ ስምምነት ሱዳንን የተወሰነ ድርሻ ብቻ እንዲሰጣት በማድረግ ግብጽና እንግሊዝ ብቻቸውን የናይል ወንዝ ተጠቃሚ እንደሆኑ በተለይም ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ በብቸኝነት የመወሰንና ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን(Veto Power)እንደላትና ይህ መብትም ካለምንም ጣልቃ ገብነት የሚቀጥል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የግብፅ ፈቃድ ሳይታከልበት በናይልን ሆነ ናይልን በሚገብሩ ወንዞች ላይ ምንም አይነት የመስኖ ሆነ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ለመስጠት የሚችል ግንባታ በሌሎች ተፋሰስ ሀገራት መከናወን እንደሌለበት ማእቀብ የሚጥል ነበር፡፡
የ1952 የእንግሊዝና የግብፅ ስምምነት(The Owen Falls Agreement)
የኡጋንዳ ቅኝ ገዥ በነበረችው በእንግሊዝና በግብፅ መካከል የተከናወነ ሆኖ የስምምነቱ ይዘትም በአንድ በኩል ኡጋንዳ ለኤሌክትሪክ ሃይል አመንጪነት የሚውል ግድብ ለመገንባት የሚያስችል ህጋዊ መእቀፍ ለማግኘት፤በሌላ በኩል ደግሞ ግብፅ በናይል ላይ የነበራትን የተቆጣጣሪነትና የአለቃነት ስልጣን አስጠብቆ ለማስቀጠል በማለም የተፈፀመ ነበር፡፡ ይኸውም ግብፅ ካልፈቀደች ምንም አይነት ስራ መስራት እንደማይቻል እውቅና ለመስጠት በማሰብ የተከናወነ ይመስላል፡፡

#የ1959_የግብጽና_የሱዳን_ስምምነት
ይህ ስምምነት በዩናይትድ አራብ ሪፓብሊክ ግብጽና በሱዳን ሪፓብሊክ መካከል የተከናወነ ሲሆን የ1929 ስምምነት ተቀጥያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛው የናይል ውኃ የግብጽ እንደሆነ እውቅና የሚሰጥ ስምምነት ነበር፡፡ በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 4 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው 55.5 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ለግብጽ፣ 18.5 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ለሱዳን በመስጠት ቀሪው 10 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ደግሞ የአከባቢው የኢኮሎጂካዊ ሚዛን ለመጠበቅ ወደ ሰሃራ ምድረ በዳ እንዲተን በመስማማት ኢትዮጵያ በብርጭቆ እንኳን ውኃ የምትቀዳበት መብት ያላገኘችበት አስገራሚ ውል ነበር፡፡ ይህ ስምምነት ሌሎች ተፋሰስ ሀገራትን ያገለለና ፍፁም የሁለትዮሽ ውል ስለነበር በኢትዮጵያ ተቀባይነት እንደሌለው ተደጋግሞ ተገልጿል፡፡

ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።
5.2K views16:00
Open / Comment
2020-06-23 19:00:37 #ኢትዮጵ


#በናይል_ላይ_የተፈፀሙ_ስምምነቶች
በናይል ዙርያ ላይ የተከናወኑ ውሎችና ስምምነቶች በዋነኛነት በቅኝ ገዢዎች የተከናወኑ ሲሆን ግብጽን ማእከል ያደረጉና ሌሎች ተፋሰስ ሀገራትን የሚያገሉ ብሎም ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ የናይል ወንዝ የቅኝ ገዢዎች ቀልብና ፍላጎት መሳብ የጀመረው ከ19ኛ መክዘ ጀምሮ ነው፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ እንግሊዝ የናይል ወንዝን አጠቃቀምና አጠባበቅን በማስመልከት ስምንት ስምምነቶችን ተፈራርማለች፡፡ እንግሊዝ ለምን ይህን ያህል ስምምነት በናይል ወንዝ ላይ መዋዋል አስፈለጋት የሚለውን ጥያቄ ስናይ እንግሊዝ የግብፅ ቅኝ ገዥ ስለነበረች በአንድም በሌላ መንገድም የራሷን ጥቅም እያሰከበረች ነበር፡፡ ሌሎች የቅኝ ገዥ ሀገራትም በናይል ወንዝ ዙርያ ሲያከናውኑዋቸው የነበሩት ስምምነቶች የራሳቸውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ ይሁንና የእነዚህ ስምምነቶች ትሩፋቶች የግብፅ ብሄራዊ ጥቅም ብቻ የሚያስከብሩና የሌሎች ተፋሰስ ሀገራት ጥቅም ታሳቢ ያላደረጉ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ከ1891 እስከ 1959 ድረስ በናይል ወንዝና ገባሪዎቹ ላይ የተከናወኑ ስምምነቶች እንደሚከተለው እንያቸው፡፡

#የ1891_የጣልያንና_የእንግሊዝ_ስምምነት

ይህ ስምምነት የግብፅን ጥቅም ላለመንካት ሲባል ጣልያን በአትባራ ወይም ተከዜ ወንዝ ላይ ግድብ እንደማትሰራ ከእንግሊዝ ጋር የተዋዋለችበት ነው፡፡ በውሉ አንቀፅ 3 ላይ እንደሰፈረው ጣልያን የናይል ገባር ወንዝ የሆነውና ከአዲስቷ የቅኝ ተገዥ ኤርትራ ግዛት ላይ የሚነሳውን አትባራ ወንዝ ላይ የመስኖ ወይም የውኃውን ፍሰት የሚቀንስ ማንኛውም አይነት ስራ እንደማትሰራ ከእንግሊዝ ጋር ውል ማድረጓን ያሳያል፡፡ ጣልያን ከሃፀይ ዮውሀንስ መስዋእትነት በኃላ እ.ኤ.አ. ከ1890-1941 የኤርትራ ቅኝ ገዥ እንደነበረች የሚታወስ ሲሆን ይህ ውል ፍፁም ኢ-ፍትሀዊና በምን አገባኝ ስሜት የተፈፀመ መሆኑን መገመት የሚከብድ አይደለም፡፡

#የ1901_የእንግሊዝና_የጣልያን_ስምምነት

ይህ ስምምነት ከደቡባዊ አስመራ ተነስቶ አትባራ ወንዝን የሚገብርና በመጨረሻም ወደ ናይል የሚቀላቀል ጋሽ/መረብ ወንዝን በማስመልከት በእንግሊዝና በጣልያን መካከል የተከናወነ ሲሆን ይዘቱም ኤርትራ በመልካም የጉርብትና መርህ ላይ ተመስርታ በወንዙ ላይ የመጠቀም መብት እንዳላት እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ ከሌሎች የቅኝ ገዢዎች ስምምነቶች በተሻለ ሁኔታ ፍትሀዊና የአሁኗ ኤርትራን መብት የማይጎዳ ነው ይባላል፡፡

#የ1902_የእንግሊዝና_የኢትዮጵያ_ስምምነት

ይህ ስምምነት ግንቦት 15 ቀን 1902 እ.ኤ.አ የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው በእንግሊዝ እና በኢትዮጵያ መካከል የተከናወነ የአዲስ አበባ የድንበር ስምምነት ነበር፡፡ ይሁንና በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 3 ላይ መነሻቸው ከኢትዮጵያ ያደረጉ የናይል ገባሪ ወንዞችን የሚመለከት የውኃ ስምምነት ይዘትም ተካትቶበታል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ንጉስ ሚኒሊክ በግዛቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የእንግሊዝና የሱዳን መንግስታት ፈቃድ ሳያገኝ የአባይን ወንዝ ፍሰትን ማስቆም የሚችል ማንኛውም አይነት ስራ እንዲሰራ የማይፈቅድ መሆኑን የተስማማበት ውል ነበር፡፡ ይህ ውል የኢትዮጵያ መንግስት ሳይገደድና በራሱ ፍላጎት ስምምነቱን የፈረመበት በመሆኑ ኢትዮጵያ የምትገደድበት ውል ነው የሚል በግብፅ በኩል ክርክር ይነሳል፡፡
የስምምነቱ አንቀፅ 3 የእንግሊዝኛና የአማርኛ ቅጂዎች በተከታታይ እንደሚከተለው እንያቸው፡፡

“His Majesty the Emperor Menelik II, King of kings of Ethiopia, engages himself towards the Government of His Britannic Majesty not to construct or allow to be constructed, any works across the Blue Nile, Lake Tana or the Sobat, which would arrest the flow of their waters into the Nile except in agreement with his Britannic Majesty�s Government and the Government of the Sudan�.
ጃንሆይ ዳግማዊ ምንይልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ከጥቁር አባይና ከባህረ ፃና ከሰባት ወንዝ ወደ ነጭ ዐባይ የሚወርደውን ውሀ ከእንግሊዝ ጋር አስቀድመው ሳያስማሙ ወንዝ ተዳር እዳር የሚደፍን ስራ እንዳይሰሩ ወይም ወንዝ የሚደፍን ስራ ለመስራት ለማንም ፈቃድ እንዳይሰጡ በዚህ ውል አድርገዋል፡፡"

ይህ ውል የኢትዮጵያ ሉአላዊነትን የሚነካ አወዛጋቢ ይዘት ያለው ቢመስልም አሁንም ግን ህጋዊነቱን ውድቅ ለማድረግ የሚጠቅሙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑንም በብዙ የውሀ ሕግ ልሂቃኖች የሚታመንበት ነው፡፡ ለምሳሌ አንደኛ ውሉ በእንግሊዝም ሆነ በኢትዮጵያ አልፀደቀም ወይም Ratify አልተደረገም፡፡ ይሁንና ከዚህ ጋር ተያይዞ በወቅቱ የሁለትዮሽ ሆነ የባለብዙ ወገን ስምምነቶችን ማጽደቅ የሚችል የተለየ ተቋም ባልነበረበት ሁኔታ ስለ ውሎችን መፈረም እንጂ ስለማፅደቅ የሕግ ክርክር ሆኖ መነሳት የለበትም የሚል የመልሶ ማጥቃት ክርክርም ይነሳል፤ምክንያቱም እንደአሁኑ ዘመን የስልጣን ክፍፍል የሚደግፍ ህጋዊ መርህ ባልነበረበት በተለይም ደግሞ ሕግ አውጪ፣ ሕግ አጽዳቂና ሕግ ትርጓሚ ራሱ ንጉሱ በሆነበት ሁኔታ የሁለትዮሽ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልፀደቀ ተቀባይነት የለውም የሚለውን ክርክር ውሀ የሚያነሳ አይደለም በማለት ይከራከራሉ፡፡

ሁለተኛ በእንግሊዘኛውና በአማርኛው መካከል የቃላት አለመጣጣምና የትርጉም መጣረስ አለበት፤በአማርኛው ቅጂ የኢትዮጵያ መንግስት የማሳወቅ ግዴታ የገባው እንግሊዝን ብቻ ሲሆን በእንግሊዘኛው ቅጂ ላይ ግን ሱዳንም ተጨምራለች፡፡ ይህ የአማርኛ ቅጂ የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት መገለጫ ነው ተብሎ የሚታሰበው እንግሊዝ ሱዳንን ትታ እስክትሄድ ድረስ የሚቆይ ጊዚያዊ ግዴታ መግባቱን ነው፤ለዚሁ ማሳያም በውሉ አንቀፅ 4 ላይ “ለቅቆ እስኪሄዱ” የሚል የአማርኛ ቃልና “Removed” የሚል የእንግሊዘኛ ቃል እናገኛለን፡፡ በሌላ በኩል ውኃውን Arrest ወይም Block ማድረግን ወይም ሙሉ በሙሉ ማስቆምን እንጂ ማንኛውም አይነት ተጠቃሚነትን የሚከለክል ውል አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ የውሉ የአማርኛ ቅጂ ከእንግሊዘኛው በተሻለ ሁኔታ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር ቢሆንም የውሉ የእንግሊዘኛው ቅጂም ኢትዮጵያ ወንዟን ከመጠቀም የማይከለክላትና እንግሊዝ ሱዳንን ለቃ ከሄደች በኃላም የውሉ ተፈፃሚነትን የሚያበቃ በመሆኑ ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ ይህን ውል የምትቀበልበት የሕግ ምክንያት የለም፡፡ ግብፅም የውሉ 3ኛ ወገን እንጂ ፈራሚ ባለመሆኗ ይህን ውል በማንሳት መከራከር አትችልም፡፡

ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።
4.6K views16:00
Open / Comment
2020-06-21 19:00:35 #ኢትዮጵ
#በአባይ_ላይ_የተደረጉ_ውሎች

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ፀጋ የተከበበች ውብ ሀገር ብትሆንም በድህነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቃ የምትኖር፤ባደጉ ሀገራት ተረፈ ምርትና የአየር ብክለት ገፈት ቀማሽነት፤በሚጠጣ ንጹህ ውኃ እጥረት ተጠቂነት የምትነሳ ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ በመአድን፣ በለም መሬት፣ በእንስሳት፣ በውኃ ኃብት እንዲሁም በሌሎች አላቂና አላቂ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለፀጋ መሆኗን የሚካድ ባይሆንም በተፈጥሮ የታደለችውን ኃብት ጥቅም ላይ ከማዋል ረገድ ግን እምብዛም አይደለችም፡፡ ሜዳዋንና ተራሯን የሚሸፍን የተፈጥሮ ዝናብ እየተቀበለች ይህ ዝናብ አፈሯንና ወርቋን ጠራርጎ በመውሰድ ለጎረቤት ሀገራት ነፃ ስጦታና ችሮታ እንዲሆን ከመፍቀድ ውጪ የልማት መንገዱን አልተገለጠላትም፡፡ ወንዞች በደራሽ ውኃ ተጥለቅልቀው የገበሬ ማሳ የጎርፍ ሲሳይ ሲያደርጉ ማየት ክረምት በመጣ ቁጥር የምንገነዘበው መራራ እውነት ነው፡፡ አባይን የሚያክል ግዙፍ የውሀ ኃብት ከጉሮሮዋ እየፈለቀቁ የራሳቸው ከርሰ ምድር ሲሞሉ ኢትዮጵያ የበይ ተመልካች ሆና መኖሯን ግርምት ይፈጥራል፡፡

ናይል የሚባለው የአለም ረዥሙ ወንዝ ላይ ያለው ውኃ 85%ቱ የኢትዮጵያ ነው፡፡ ይሁንና ከ50% በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮውን በኩራዝ መብራት ይመራል፡፡ ይህ ክስተት ወገብን ይቆርጣል፡፡ ”ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” እንዲሉ ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ 5% እንኳን አስተዋፅኦ ሳታደርግ በምስራቅም በምእራብም የዚሁ ወንዝ ብቸኛ አለቃ ነኝ በማለት በሌሎች የናይል ተፋሰስ ሀገራት ላይ የምትሰነዝረው ዛቻና ማስፈራርያ የሚያስገርም ነው፡፡ የናይል ወንዝ ብቸኛ ባለቤት እንደሆነች በመግለፅ አሁናዊ ተጠቃሚነቷን የሚነካ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ የደም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነች በተለያዩ አጋጣሚዎች ስትገልፅ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ የግብፅ ሽለላና ቀረርቶ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በግዛታዊ ክልሏ ውስጥ በሚገኝ በጥቁር አባይ ላይ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጀምራ ከ70% በላይ ማድረሷን ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ይህ ግድብ ለግብፅ ራስ ምታት እንደሆነባት፤ኢትዮጵያ የያዘቸውን የልማት መንገድ ለማደናቀፍም ያልፈነቀለችው ድንጋይ እንደሌለ፤በቀጣይም የማትቆፍረው ጉድጓድ እንደማይኖር ኢትዮጵያውያን የምንገነዘበው እውነት ነው፡፡ የናይል ወንዝ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የፈጠረውን ውጥረት በተለያዩ ወቅቶች የውጭና የሀገር ውስጥ ሚድያዎች ርእሰ ዜና በመሆን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀልብ መሳብ የቻለ፤አሁንም ውጥረቱ በስምምነት ያልተቋጨ ክስተት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

#የናይል_ወንዝ_የማን_ነው

ናይል የአለም ረዥሙ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ሆኖ 11 ተፋሰስ ሀገራትን የሚያቋርጥ ነው፡፡ የወንዙ ላዕላይ ተፋሰስ ሀገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳና ኬንያ፤የመሀል ተፋሰስ ሀገራት ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ሩዋንዳና ብሩንዲ፤የታሕታይ ተፋሰስ ሀገራት ደግሞ ሱዳን እና ግብጽ ናቸው፡፡ የናይል ገባር ወንዞች ነጭ ናይል፣ ሰማያዊ ናይል(አባይ) እና አትባራ ወንዞች ናቸው፡፡ ነጭ አባይ ከታንዛንያ፣ ኡጋንዳና ኬንያ ድንበሮች አካባቢ ከሚገኘው ከቪክቶርያ ሀይቅ ተነስቶ ወደ ናይል ወንዝ የሚቀላቀል ሆኖ 15% አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ሰማያዊ ናይል(አባይ) ደግሞ ከጣና ሀይቅ የሚነሳና 70% አካባቢ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን አትባራ የተባለው ወንዝ ደግሞ በተከዘና በሰቲት ወንዝ ገባሪነት ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ ተነስቶ በሱዳን በኩል አድርጎ ናይልን የሚቀላቀልና 15% አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው፡፡ ሰማያዊ ናይል(ጥቁር አባይና አትባራ)ከኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ተነስተው ኴርቱምን አቋርጠው ግብፅ የሚገቡና 85% የናይል የውሀ ይዘት የሚሽፍኑ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ሰማያዊና ነጭ ናይል በደቡባዊ የሱዳን ክፍል በሚገኘው ኳርቱም አካባቢ ይገናኙና ተያይዘው ወደ ግብፅ ሲና በረሀ በመክነፍ ሜዲትራንያን ባህርን ይቀላቀላሉ፡፡

(( ይቀጥላል))
ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።
3.5K views16:00
Open / Comment
2020-06-20 22:16:01
#በአባይ_ላይ_የተደረጉ_ውሎች

የስምምነቱ አንቀፅ 3 የእንግሊዝኛና የአማርኛ ቅጂዎች በተከታታይ እንደሚከተለው እንያቸው፡፡
“His Majesty the Emperor Menelik II, King of kings of Ethiopia, engages himself towards the Government of His Britannic Majesty not to construct or allow to be constructed, any works across the Blue Nile, Lake Tana or the Sobat, which would arrest the flow of their waters into the Nile except in agreement with his Britannic Majesty�s Government and the Government of the Sudan�.


ጃንሆይ ዳግማዊ ምንይልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ከጥቁር አባይና ከባህረ ፃና ከሰባት ወንዝ ወደ ነጭ ዐባይ የሚወርደውን ውሀ ከእንግሊዝ ጋር አስቀድመው ሳያስማሙ ወንዝ ተዳር እዳር የሚደፍን ስራ እንዳይሰሩ ወይም ወንዝ የሚደፍን ስራ ለመስራት ለማንም ፈቃድ እንዳይሰጡ በዚህ ውል አድርገዋል፡፡"

ነገ ማታ 1፡00 ሰዓት ይጠብቁን።
#ኢትዮጵ
3.5K viewsedited  19:16
Open / Comment
2020-06-06 19:01:00 ....አዲስ አበባ ላይ የሞተው የሕዝብ ቁጥር ዘጠኝ ሺህ ይኾናል ተብሎ ተገመተ።
የኅዳር በሽታ (ግሪፕ) በአዲስ አበባ ብቻ አልተወሰነም፤ ወደ ባላገርም ተላልፎ ብዙ ሰው ፈጅቷል። ኾኖም በባላገር የአዲስ አበባን ያኽል አልጠነከረም ይባላል። በዚህ በሽታ በመላ ኢትዮጵያ የሞተው ሕዝብ ቁጥር እስከ አርባ ሺህ ድረስ መገመቱን አስታዋለሁ።"
ምስሉ ፦አልጋ ወራሽ ተፈሪ ከበሽታው ካገገሙ በሁዋላ ከመኳንንቱ ጋር የተነሱት በ1911 ዓ/ም የአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት በሽታውን በተመለከተ የሚከተለውን ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር

የአዲስ ፡ አበባ ፡ ከተማ' ማዘጋጃ ቤት
=========================
ማስታወቂያ
1. ለዚህ ፡ ለዛሬ በሽታ ፡ ነጩን: የባሕር ፡ ዛፍ፡ ቅጠሉን: እየቀቀላችሁ ማታ ስትተኙ በላቦቱ ታጠኑ። ደግሞ ፡ የባሕሩን ዛፍና ቅጠል፡ እርጥቡን በብዙ ፡ አድርጋችሁ በቤታችሁም፡ ውስጥ ፡ በየደጃችሁም፡ እያነደዳችሁ አጭሱበት።
2. አይነ ምድራችሁን ሳትቆፍሩ አትቀመጡ ። እይነ ምድር፡ ተቀምጣችሁ ስትነሡ ፡ ባይነ ምድራችሁ ፡ ላይ ፡ የባሕር ፡ ዛፍ ፡ ቅጠል ጣሉበት። ያልጣላችሁበት እንደሆነ ከአይነ ምድራችሁ፡ ላይ ፡ እንደገና በሽታ ይነሣል።
3. ባትታመሙም፡ ብትታመሙም ፡ ውሀ ፡ እያፈላችሁ ፡ በውስጡ ጨው እየጨመራችሁ ፡ ጡዋትና፡ ማታ ፡ አፋችሁን ተጉመጥመጡ ።
4. ውሻ፣ ድመት፣ በቅሎና ፈረስ ሌላም ይህን የመሰለ፡ ሁሉ፡ በሞተባችሁ ጊዜ ሽታው በሽታ ያመጣል ና፡ ቅበሩት።
5. ሰው ፡ የሞተባችሁ፡ እንደህነ መቃብሩን ፡ በጣም ፡ አዝልቃችሁ ፡ ሳትቆፍሩ፡ አትቅበሩ ። በጣም ሳትቆፍሩ የቀበራችሁ ፡ እንደሆነ አውሬና ውሻ እያወጣ ይበላዋል። ሽታውም ከዛሪው የበለጠ በሽታ ያመጣብናልና።
6. በቤቱ፡ ሰው ፡ የታመመበት ሰው ፡ ወደ ፡ ማዘጋጃ ፡ ቤት፡ ድረስ፡ እየመጣ አለዋጋ መድኃኒቱን ይውሰድ። በማናቸውም ፡ ምክንያት፡ የሚያድን እግዚአብሔር፡ ነው ። ነገር፡ግን፡ የሚያድን ፡ እግዚአብሔር፡ ነው፡ ብሎ ፡ መድኃኒት አላደርግም ፡ ማለት እግዚአብሔርን መፈታተን ይሆናልና፡ መድኃኒት አናደርግም አትበሉ። መደኃኒትንም፡ የፈጠረልን፡ እግዚኣብሔር፡ ነው፡
7. ደግሞ ከመቃብር ላይ በሽታ እንዳይነሣ ብሎ መንግሥታችን በቸርነቱ፡ ብዙ፡ ኖራ በየቤተክርስቲያኑ አስቀምጥቶልናልና፥ በመቃብሩ ውስጥ ሬሳውን አግብታችሁ በላዩ ጥቂት አፈር ጨምራችሁ ባፈሩ፡ ላይ ኖራውን አልብሱና፡ከዚያ፡ በዋሁላ አፈር መልሱበት። ኖራው የሬሳውን ሽታ ያጠፋውና በሽታ፡ እንዳይነሣ ይሆናል።

ሕዳር፡፩፡፲፱፻፲፩ (1911 ዓ/ም)
አዲስ ኣበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዲረክተር፡ ኅሩይ፡ ወ : ሥ
(ተፈፀመ)


ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።
5.4K views16:01
Open / Comment
2020-06-06 19:00:46 #ኢትዮጵ
#የወረርሽኝ_ታሪክ_በኢትዮጵያ
የመጨረሻ ክፍል

2500 ዓመታትን ያስቆጠረው ኢንፍሉዌንዛ የቀደሙትን ወረርሽኞች ያክል የከፋ ባይሆንም ኢንፍሉዌንዛ በኢትዮጵያ የብዙዎችን ህይወት ቀጥፏል።የላቲን አማርኛ መዝገበ ቃላትን ያዘጋጀው Iob Ludolf ኢንፍሉዌንዛን ጉንፋን ሲል ገልጾታል። የዚህ ዓይነቱ የመጀመሪያ ወረርሽኝ የተመዘገበው በ1706ዓ.ም በአጼ ኢያሱ ቀዳማዊ ዜና መዋዕል ነው።

በዜና መዋዕሉ እንደተጻፈው በጊዜው በወረርሽኙ ምክንያት የንጉሱ አልጋወራሽ የነበረው ልዑል ተክለሀይማኖት መኖሪያውን ጥሎ ሲሰደድ ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በሁለተኛው ማለትም በ1747ዓ.ም. በዳግማዊ ኢያሱ ዘመነ መንግስት በተከሰተው የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ የደረሰው ጉዳት ከመጀመሪያው የከፋ ነበር። በዚህ ግዜ የሟቹ ቁጥር በመብዛቱ ቀባሪ የታጣበት አጋጣሚ ሁሉ ተፈጥሮ እንደነበር በንጉሱ ዜና መዋዕል ተጽፎ ይገኛል።
የመጀመሪያው በኢትዮጵያ በኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ላይ የተጻፈ የባለሞያ ማስረጃ በ Dr. A. Petit በ1839ዓ.ም የተመዘገበው ነው። ይህ የፈረንሳይ የህክምና ቡድን ልዑክ አባል የሆነ ሰው እንደሚነግረን በአድዋ ወረርሽኙ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም ካለፈው ይልቅ እሱ ያየው ቀላሉን እንደነበር ያነጋገርኳቸው ሰዎች ነገሩኝ ይላል። በዚህም መሰረት ምናልባትም የ1833ቱ እና የ37ቱ ዓለም አቀፍ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በኢትዮጵያም ብዙ ጉዳት ሳያደርስ እንዳልቀረ ይገመታል። ምንም እንኳን የተጻፉና ተጨባጭ የሆኑ ማስረጃዎች ባይኖሩም። Petit እንደሚለው የ1839ኙ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በሁለት ዙር (two waves) የተከሰተ ነበር። የመጀመሪያው ሐምሌ ላይ የተቀሰቀሰው ሲሆን እንደገና መስከረም ላይ አገርሽቶ ብዙ ጉዳት አድርሷል።

ታላቁ ረሀብ
የኢትዮጵያ ህዝብ በረሀብ አለንጋ ክፉኛ በተገረፈበት በዚህ ዘመን ብዙ ወረርሽኞች ተፈራርቀውበታል። ከነዚህ ወረርሽኞች አንዱ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ነበር። ፈረንሳዊው የህክምና ባለሞያ በማስታወሻው በወቅቱ በዓለም አቅፍ ደረጃ ተከስቶ የነበረው ይህ ወረርሽኝ በኢትዮጵያም ብዙ ጉዳት ማድረሱ እንደተመለከተ ጽፎልናል። የዳግማዊ ምንሊክ አማካሪ የነበረው Alfred Ilg በበኩሉ በግዜው ወደ 20,000 የሚጠጋ ወታደር መታመሙንና ብዙዎቹም መሞታቸውን ይናገራል።
የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ
የዚህን ዘመን የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ታሪክ በአግባቡ መዝግቦ ካቆይልን ሰው አንዱና ዋነኛው ጆርጂያዊው ሀኪም Dr.Merab ነው። እንደ መረብ ዘገባ አዲስ አበባ ከ1908-1914 ዓ.ም. መካከል እየተመላለሰ በመታት የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ክፉኛ ተጎድታለች። እንደ መረብ ገለጻ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ኢንፍሉዌንዛን በጸሀይ ምክንያት እንደሚመጣ በሽታ ነበር የሚቆጥሩት። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም አንዳንዶች በሽታውን ምች ሲሉ ይጠሩት ነበር። አንዳንዶች ደሞ በቡዳ ተበልተን ነው ይሉ ነበር።

ኅዳር ሲታጠን (የኅዳር በሽታ)

ይህ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ከጠናቀቀ ብኋላ ዓለምን የመታው የስፓኒስ ፍሉ ወረርሽኝ ነው። ይህንን ወረርሽኝ በተለይም መርስዔ ኅዘን ወልደ ቂርቆስ "የሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ" በተሰኘ የታሪክ መጽሀፋቸው እንዲህ ዘግበውታል.....
"በ1911 ዓ.ም የበሽታ መቅሠፍት በኢትዮጵያ ላይ ወርዶ ብዙ ሰው አለቀ። በሽታው አዲስ አበባ ደርሶ በጣም የታወቀው በኅዳር ወር ስለኾነ በሕዝብ ቃል "የኅዳር በሽታ" የሚል ሥም ወጣለት። ፈረንጆች ግን የበሽታውን ስም 'ግሪፕ' ብለውታል። በሀገራችንም አንዳንድ ሰዋች "ቸነፈር " ብለውት ነበር። በሽታው ቀደም ብሎ አውሮጳ ላይ በዓለም ጦርነት ምክንያት ስለተነሳና ብዙ ሕዝብ ሰለፈጀ ይኼው ወሬ ከመስከረም ጀምሮ ተሠምቶ ነበር። ወደ ሀገራችንም በነፋስ ተዛምቶ መጣና ከጥቅምት ጀምሮ ጥቂት በጥቂት በአንዳንድ ሰው ቤት መግባትና መጣል ጀመረ። በኅዳር ወር ግን አብዛኛውን ሰው ስለነደፈው ከተማው ተጨነቀ ። በሽታው እንደ ሳል እና እንደ ጉንፋን አድርጎ ይጀምርና በሽተኛው ላይ ትኩሳት ያወርድበታል። ከዚያም ሌላ ያስለቅሳል፤ ነስር ነበረው። ተቅማጥና ውጋት ያስለትላል። አንዳንዱንም አዕምሮውን ያሳጣዋል። እንዲህ እያደረገ በሦስት፣ በአራት ቀን ይገድለዋል ። ከአራት ቀን ያለፈ በሽተኛ ግን ከሞት ማፋረሱ ነው። ኾኖም ግን ከግርሻ መጠንቀቅ ነበረበት። በአንዳንድ ሥፍራ ቤተሰብ በሙሉ ይታመም ስለነበር አስታማሚ በማጣት በረሐብና ውኃ ጥም ብዙ ሰው ተጎዳ። ስለዚህ በአዲስ አበባ ከተማ በየቀኑ ኹለት ፣ ሦስት መቶ ከዚያም በላይ ይሞት ጀመር። በአንድ መቃብርም ኹለቱን፣ ሦስቱን ሬሣ እስከ መቅበር ተደረሰ። አንዳንዶችንም ሰዎች ሬሣ ተሸካሚ በመታጣት በየግቢያቸው ውስጥ ቀበሯቸው።

አፍላው በሽታ ከኅዳር 7 እስከ 20 ለ 14 ቀናት ያኽል ነበር። በተለይም ኅዳር 12 ቀን በኅዳር ሚካኤል ዕለት ብዙ ሰው ሞተ። ከመኳንንቱ ከንቲባ ወሰኔ ዛማኔል በዚህ ቀን ሞቶ አዲስ አበባ ሥላሴ ተቀበረ። ከካህናትም ሐዲስ አስተማሪው ዓለቃ ተገኝ ሞቶ አራዳ ጊዮርጊስ ተቀበረ። ይኽ ሰው የመምህር ወልደ- ጊዮርጊስ ደቀ-መዝሙር የነበረው ነው። በዚያ ሰሞን መቃብር የሚቆፍርና ሬሣ ተሽክሞ የሚወስድ ሰው ለማግኘት ችግር ኾነ። በቤተሰብ ውስጥ ከበሽታ ያመለጡ ሲገኙ ኹለት ሰዎች ሬሣ ተሸክመው እየወሰዱ ይቀብራሉ። ባል የሚስቱን፣ አባት የልጁን ሬሣ እየተሽከመ ወስዶ ቀበረ። ደግሞ አንዱ መቃብር ይቆፍርና ሬሣ ለማምጣት ወደ ቤቱ ሄዶ ሬሣ ይዞ ሲመለስ ሌላው ተቀብሮበት ያገኘዋል ።
ቤተሰብ በሙሉ በታመመበት ሥፍራ ብዙዎች በየቤታቸው እየታመሙ አውሬ በላቸው። ለጉዳይ ወደ አዲስ አበባ የመጣ እንግዳም እየታመመ መግቢያ ቤት አጥቶ በየመንገዱ እየወደቀ አውሬ በላው። በዚያ ወራት በአዲስ አበባ የነበረው ጭንቀት በሥፍራው ተገኝቼ ተመልክቼዋለሁ። የኔታ ወልደ-ጊዮርጊስ በሰፈራቸው በጉለሌ ክፍል በየቤቱ እየዞሩ ለበሽተኛቹና ለገመምተኛች እንጀራና ውኃ ሲያድሉ ሰነበቱ። በእግዚአብሔር ቸርነት ከበሽታው አምልጠን ነበርና እኔንና ጎጃሜ ኃይለ-ማርያምን ውኃ በገንቦ እያሽከሙ እርሳቸው ቁራሽ እንጀራ ይዘው ይሔዱና ከቤቱ ደጃፍ ሲደርሱ እኛን ውጭ አስቀርተው ውኃውንና ቁራሹን ይዘው ይገቡ ነበር። እኛን ማስቀረታቸው በሽታ እንዳይዘን ላሰቡልን ነው ።
በሌላም ሥፍራ የዚኽ ዓይነት ትሩፋት የሠሩ መንፈሳውያን ሰዎች ነበሩ። ለምሳሌ ሙሴ ሴደርኩዊስት የተባሉ ሽማግሌ (የስዊድን ሚሽን አስተማሪ ) በየሰፈሩ እየዞሩ ለበሽተኛች እሕልና ውኃ መድሃኒትም በመስጠት ትሩፋት መሥራታቸውን ስምቻለው። እኒኽ ሽማግሌ ሚሲዮናዊ ከጥቂት ቀናት በኋላ በዚሁ በሽታ ታመሙና ሞተው ጉለሌ ተቀብረዋል።”
በዚህ ወራት የተቆፈሩ መቃብሮች ጥልቀት ስላልነበራቸው እያንዳንዱን መቃብር አውሬ ያወጣው ጀመር። ከመቃብሮቹ የሚወጣውም "ሚክሮብ" እንደገና በሽታ ያስነሳል ተብሎ ስለተሠጋ ማዘጋጃ ቤት ኖራ እያስበጠበጠ በየመቃብሩ ላይ አስረጨበት........
4.5K views16:00
Open / Comment
2020-06-05 19:00:54 ​#ኢትዮጵ
#የወረርሽኝ_ታሪክ_በኢትዮጵያ
ታላቁ ረሀብ (1888_1892)

የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጨረሻው የኮሌራ ወረርሽኝ ታላቁን ረሀብ ታኮ የተቀሰቀሰ ነበር። በከባድ ረሀብ የተዳክመው ህዝብ ለማንኛውም ዓይነት በሽታ ተጋላጭ ስለነበር በቀላሉ ነበር የወረርሽኙ ሰለባ የሆነው። ወረርሽኙ እንዴት ባለ ሁኔታ እንደተቀሰቀሰ ግልጥ ያለ መረጃ ባይኖርም በወቅቱ ምጽዋ የነበረው ጣሊያናዊው ሀኪም Filippo Rho ከሀጂ ጉዞ ከመካ በተመለሱ ሙስሊሞች አማካኝነት ሳይመጣ አልቀረም ሲል ግምቱን አስቀምጧል።

እንደ De Lauribar የታሪክ ዘገባ ወረርሽኙ በወቅቱ የጣሊያን ቅኝ ግዛት በነበረችው ኤርትራ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ተስፋፍቶ ነበር። በየመንገዱም ብዙ ሰው ይሞት ስለነበር የጣሊያን ወታደሮችና ካራቢኔሪዎች እየዞሩ ሬሳ በማቃጠል ስራ ላይ ተጠምደው እንደነበር ይነገራል። በወቅቱ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው ነበር። የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት በማሰብ። እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ ያስቸግረኛል።
ስለወረርሽኙ ክፋት የዓይን ምስክርነቱን የሰጠው የብሪቲሹ ተጓዥ Theodore Bent በ1893 ዓ.ም. የሰሜኑን ክፍል ከጎበኘ ብኋላ.......
“የእርስ በርስ ጦርነት፣ ረሀብ እና የኮሌራ ወረርሽኝ ከባድ ውድመት አድርሰዋል። ቀዪዎች ወናቸውን ቀርተዋል፣ የእርሻ መሬቶች አረም ወርሷቸዋል። በቦታው ተገኝቶ የሆነውን በዓይኑ ላልተመለከተ በሀገሪቱ ላይ ደርሶ የነበረውን አሰቃቂ ስቃይ እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ ያስቸግረኛል። ለምሳሌ ደበርዋ በተባለች መንደር ሰው ሁሉ አልቆ ከድንጋይ ክምርና ከፈራረሰ ቤተክርስትያን በቀር ምንም አይታይም ነበር።”
..…ሲል በማስታወሻው አስፍሯል።
ደቡባዊው የኢትዮጵያ ክፍል
በ1892ዓ.ም. ኮሌራ በ ኤደን ባህረሰላጤ ተቀስቅሶ ብዙ ሰው አልቋል። እንደ ተጓዡ Drake Brockman ዘገባ በ ቡልሀር የነበረው ህዝብ ለወሬ ነጋሪም አልተረፈም ነበር። በዘይላ በበሽታው ከተጠቁ 369 ሰዎች 277 ሲሞቱ በበርበራ ደግሞ ከ 13 ታማሚዎች 11 እቺን ዓለም ተሰናብተዋል። በጅቡቲም እንዲሁ ብዙ ሰው ማለቁ ነው የሚነገረው።
በጅቡቲ ከሞቱት መካከል የቅኝ ግዛት አስተዳዳሪው Joseph Deloncle እና የወታደሮች ሀኪም የነበረው Dr. Aubrey ተጠቃሽ ናቸው።
ወደ መሀል ሀገር የተስፋፋው ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ካሉ የአምልኮ ማዕከላት አንዱ ከሆነው ድሬ ሼክ ሁሴን አናጂና መንደር ሲደርስ በወቅቱ ከነበረው ነዋሪ አራት አምስተኛውን አርግፏል። እንደ አጼ ምንሊክ ዜና መዋዕል ጸሀፊ ገብረሥላሴ ዘገባ በሀረር ከተማ ብዙ ሰው በወረርሽኙ ሲያልቅ ለተራበው ወገን ለመድረስ ከኦጋዴን ወደ መሀል ሀገር ከብቶች ሲነዱ የነበሩ ሰዎችም የበሽታው ሰለባ ሆነዋል።
ወረርሽኙ ንጉሱ ወዳለበት አንኮበር እንዳይደርስ እራሳቸውም በበሽታው ተጠቅተው የነበሩት አዛዥ ወልደ ጻድቅ ከብቶቹ በአዳል እንዲቆዩና መንገዶችም እንዲዘጉ አዘዙ። በወቅቱ ንጉሱ አጼ ምንሊክ ከአንኮበር ወረድ ብለው ዲቢ በተባለች ቦታ በጫካ ውስጥ ድንኳን ጥለው ይኖሩ ነበር።

20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
በዚህ ዘመን ዓለም ለኮሌራና ለሌሎች ብዙ በሽቶች መፍትሄ ማግኘት ጀመረች። የመጨረሻው ትልቁ የኮሌራ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው በ1902ዓ.ም. ሲሆን ኢትዮጵያ የደረሰው በ1906ዓ.ም. ነበር። ይሁንና ወረርሽኙ በወሎ ብቻ ነበር ሪፖርት የተደረገው። ከዚህ ብኋላ የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ላይ በወረርሽኝ ደረጃ ጥቁር ጥላውን አላጠላባትም።
ታይፈስ፤ የወታደሩ በሽታ እንደ ቀደሙት ሁለቱ ወረርሽኞች እንደ ፈንጣጣና ኮሌራ የከፋ ባይሆንም ታይፈስ በኢትዮጵያ ተቀስቅሰው ጉዳት ካደረሱ ወረርሽኞች አንዱ ነው። በብዛት ወታደሩን ያጠቃ ስለነበር ታይፈስ የወታደር በሽታ በመባል ነበር የሚታወቀው።
ምንም እንኳን James Bruce በ1771 ዓ.ም. በጌምድር ሳለ የተመለከተውና የዘገበው በሽታ ታይፈስ ቢሆንም ታይፈስ እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ በስም አይታወቅም ነበር። ሌላው ይህን በሽታ የዘገበው Arnauld d’Abbadie እንደሚለው በጎንደር በ1842 ዓ.ም. የንዳድ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ነበር። በዛው ዘመን ከሴናር የሚመጡ ሲራራ ነጋዴዎች በዚሁ በሽታ ሲሞቱ በኢናሪያም በሽታው ተቀስቅሶ ነበር። ይሁንና ይሄ d’Abbadie ንዳድ ሲል የገለጸው በሽታ ታይፈስ ይሁን ሌላ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። ታይፈስ ለሚለው ቃል ትክክለኛ የአማርኛ ስያሜው ባይታወቅም Isenberg ንዳድ ብሎ ሲተረጉመው d’Abbadie መጋኛ ወይም በደዶ ሲል ይጠቅሰዋል።
ይህ ወጥ ያልሆነ የስም አጠቃቀስ የታይፈስን ታሪክ በኢትዮጵያ ለማጥናት አስቸጋሪ አድርጎታል።

አጼ ቴዎድሮስ
በንጽጽር በሚገባ የተጻፈው የታይፈስ ታሪክ በሰኔ ወር 1866ዓ.ም. በአጼ ቴዎድሮስ ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰው ነው። በዚህ ወቅት ንጉሱ በጣና ሀይቅ አቅራቢያ ቆራጣ በተባለች ስፍራ ሰፍረው ነበር። በቀን ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እያለቁባቸው የተቸገሩት አጼ ቴዎድሮስ ወደ በጌምድር በመውጣት ራሳቸውንና ሰራዊታቸውን ከሞት ታድገዋል።
ሌላው የታይፈስ ወረርሽኝ በ1870ዎቹ ኢትዮጵያን ለመውረር በሱዳን በኩል በመጡት የግብጽ ወታደሮች አማካኝነት የመጣው ነው። ነሀሴ 9 ቀን እንደተጻፈው እንደ ኮማንደሩ Rateb Pasha ዘገባ ከወታደሮቹ 160 ያክሉ በበሽታው ሲጠቁ በቀን ውስጥ ከ አራት እስከ ስድስት ወታደሮች ይሞቱበት ነበር። ወረርሽኙ ተስፋፍቶ በመስከረም 19 ቀን 384 የሱዳንና 76 አረብ ወታደሮች ማለቃቸውንም ኮማንደሩ ዘግቧል። ይህ ወረርሽኝ ብኋላ ወደ ነዋሪው የተሰራጨ ሲሆን ምን ያክል ሰው እንደተጎዳ ግን የተጻፈ ማስረጃ ሊገኝ አልቻለም።

ታላቁን ረሀብ ተከትሎ ብዙ የበሽታ ወረርሽኞች ተቀስቅሰዋል። በዚህ ወቅት ከተቀሰቀሱ ወረርሽኞች አንዱ ታይፈስ ሲሆን በወቅቱ የአጼ ምንሊክ አማካሪ የነበረው አልፍሬድ ኢልግ (Alfred ilg) እንደሚነግረን ታይፈስ፣ ተቅማጥና ፈንጣጣን የመሳሰሉት ወረርሽኞች ተባብረው በ1890 ዓ.ም. ከትግራይ ዘመቻ ወደ ሸዋ ሲመለስ ከነበረው የንጉሱ ሰራዊት 15% የሚሆነውን መንገድ አስቀርተዉታል። ከዚህም ሌላ ወደ ደቡብ የዘመተውን ወታደር አብዛኛውን የፈጀው የታይፈስ ወረርሽኝ እንደነበር ይነገራል። በተለይም ወደ ከፋ የዘመተው በራስ ወልደ ጊዮርጊስ የተመራው ጦር በዚህ ወረርሽኝ እጅጉን መጎዳቱንና ወታደሮቹም ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ወረርሽኙን ይዘው እንደመጡ Carlo Annoratone እና Lincoln de Castro የተባሉ የህክምና ባለሞያዎች በጻፉት የታሪክ ማስታወሻ ጠቅሰዋል።
(ይቀጥላል)
[በቀጣይ በመጨረሻው ክፍልና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የወረርሽኝ ታሪክ በኢትዮጵያ እንገናኛለን።]
ምስል - ታላቁ ረሃብ
ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።
3.6K viewsedited  16:00
Open / Comment
2020-06-04 19:00:59 #ኢትዮጵ
#የወረርሽኝ_ታሪክ_በኢትዮጵያ
የገዳዩ ወረርሽኝ (ኮሌራ)

በሰሜኑ ክፍል እየቀነሰ መሄድ
ከምስራቅ የተነሳው የኮሌራ ወረርሽኝ በጥቅምት ወር 1865ዓ.ም. የወደብ ከተማ ከሆነችው ምጽዋ ደረሰ። የብሪቲሹ የመንግስት መልዕክተኛ Henry Blanc እንደሚለው ወረርሽኙ በምጽዋ ብዙ ጉዳት አድርሷል። በተለይም በቂ የሆነ ምግብ መመገብ የማይችሉትን ምስኪን ደሀዎች ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ ነበር ያጠቃቸው። በምጽዋ በወረርሽኙ ከተጠቁት አገግመው በህይወት የመትረፍ እድል ያገኙት ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። የአከባቢው አስተዳዳሪ የነበረው ፓሻ ሳይቀር በወረርሽኙ ብዙ ግዜ የሞትን ደጃፍ ከረገጠ ተመልሷል። ፈረንሳዊው የታሪክ ጸሀፊ Donin እንደሚነግረን ከሆነ በወቅቱ የኮሌራ ወረርሽኝ በጥቂቱ 300 የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
የምጽዋ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ከወሰዱት እርምጃ አንዱ የንግድ እንቅስቃሴን ማቋረጥ ነበር። በዚህም መሰረት ወደ አከባቢው ለንግድ የሚንቀሳቀሱትን ነጋዴዎች ወደ ከተማው እንዳይገቡ እገዳ ጣሉ። ይህን ያድርጉ እንጂ ጥንቃቄው የወረርሽኙን ስርጭት ሳይገታው ወደ ትግሬና ወደ ሌሎች አውራጃዎች ሊስፋፋ ችሏል። እንደ Blanc ማስታወሻ በተለይም በትግራይ የከፋ ጉዳት ነበር ያስከተለው። እንደ እንግሊዛዊው Shepherd ዘገባ ከሆነ ደግሞ በእንጣሎ እና አከባቢው ወረርሽኙ የፈጀውን ፈጅቶ የቀረውም ሰው ቀዬውን ጥሎ በመሰደዱ አከባቢው ወና ቀርቶ ነበር። በዚህ ያልቆመው የኮሌራ ወረርሽኝ ወደ ደናኪል በመውረድ ብዙ ጥፋት እንዳደረሰ ከስዊዙ ተጓዥ Muzinger ማስታወሻ መረዳት ይቻላል።
አጼ ቴዎድሮስ
በግንቦት 1886ዓ.ም. በደቡብ ምስራቅ ጣና ሀይቅ ዳርቻ በምትገኘው ቆራጣ የኮሌራ ወረርሽኝ መቀስቀሱ ተሰማ። Blank እንደሚለው አጼ ቴዎድሮስ ይህን ወሬ እንደሰማ ወደ በጌምድር ደጋማ ስፍራ ለመጓዝ ወሰነና ወደዛው ከመንቀሳቀሱ በፊት የወረርሽኙን መጠን ለመገምገም ቆራጣ ቢሄድ በቀናት ውስጥ ወረርሽኙ የንጉሱን ካምፕ አጥለቀለቀው። በቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መርገፍ ጀመሩ። ጉዳዩ ያሳሰበው ቴዎድሮስ ወደ አክባቢው ተራራማ ስፍራ ወታደሮቹን ቢያንቀሳቅስም ወረርሽኙ ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ ሰው መጣሉን ተያያዘው። አብያተ-ክርስቲያናት በሰው ሬሳ ተሞሉ፣ ወደ ቤተክርስቲያን የሚወስዱ ጎዳናዎች ተኝተው የመጨረሻ የሞት ጣር ባነቃቸው የመላዕከ ሞት እጩዎችና ሞተው በወደቁ አስክሬኖች ተዘጉ። ከዚህ መዓት ጥቂቶች ቢተርፉ ፈንጣጣና ታይፈስ እየተፈራረቁ ተቀራጯቸው።

በጌምድር - ጎንደር
ከዚህ ብኋላ አጼ ቴዎድሮስ ወደ በጌምድር የመጓዙን ጉዳይ ስለወሰኑ ወታደሩና የተቀረው ሰው ወደ በጌምድር ጉዞውን ጀመረ። የጉዞውን ሁኔታ ለታሪክ በማስታወሻው ከትቦ ለታሪክ ያቆየልን Waldmeir እንደሚለው ጉዞው እጅግ አድካሚ ነበር። ወደ 100,000 የሚጠጉ ወታደሮች፣ ሴቶችና ህጻናት ነበሩ አንድ ላይ ታጭቀው የሚሄዱት። አንዳንዱ ህመምተኛ ነው፣ በመንገድ ላይ የሚሞተውም መዓት ነበር። የሞተውን የሚያነሳው ስለሌለ ያሁሉ ህዝብ ተረማምዶበት ሲያልፍ የሚወጣውን ጠረን፣ ለሞተ ዘመዳቸው ሰዎች የሚያለቅሱትን ለቅሶ መቋቋም እጅግ ሲበዛ ፈታኝና አሰቃቂ ነበር።

የንጉሱ ምርመራ (Inquiry)

አጼ ቴዎድሮስ አብረዋቸው የነበሩትን የውጭ ሀገር እስረኞች መላ አምጡ ማለት ጀመሩ። እንዲህ ዓይነት ወረርሽኝ ሲያጋጥማቹ በሀገራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ሲሉ ጠየቋቸው። Henry Blanc ለዚህ ለንጉሱ ጥያቄ ወደ በጌምድር ተራራማ ቦታዎች መንቀሳቀስ እና በተቻለ መጠን ወታደሩን መበተን የተሻለ እንደሆነ ሀሳብ አቀረብን ይላል። አጼ ቴዎድሮስም የተባሉትን ምክር በመቀበል እንደታባሉት አደረጉ።
በግዜው በአጼ ቴዎድሮስ እስር ላይ የነበረው Henry Blanc ከእስር ተፈቶ ብዙዎችን ማከሙና ማዳኑ ይነገራል። ወታደሮቹን የመበተኑና ወደ ደጋማው ስፍራ የመሸሹ ምክርም ውጤታማ ሆኖ ወረርሽኙ መቀነስ አሳይቷል። በግዜው የነበረውን ሁኔታ Blanc ወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ በመጥፋቱ ንጉሱ ደስተኛ ነበር ሲለን Waldmeir በበኩሉ ይህን የሚያጠናክር ሀሳብ በማስታወሻው አስፍሯል። እንደ ህክምና ታሪክ ጸሀፊው Hirsch ዘገባ ግን ወረርሽኙ የሰሜን ተልዕኮውን አጠናቆ ወደ ደቡባዊው የሀገሪቱ ክፍል ለማቅናት ያኮበኮበበት ግዜ ነበር።
ከዛስ ምን ተፈጠረ? በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን።

ይቀጥላል.....
3.1K viewsedited  16:00
Open / Comment