🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 14

2021-04-19 15:11:11
#አጣዬና_አካባቢው

"የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲህ ያለ ግጭት ውስጥ ገብቷል ብለን አናምንም። እንዲህ ያለው ግጭት መከሰት የጀመረው ከቅርብ ዓመታት ጊዜ ጀምሮ ነው። በተለይ ከ2011 ጀምሮ በየዓመቱ እንደ ዓመታዊ ክብረ በዓል ችግሩ እየተከሰተ ነው ያለው በ2011፣ በ2012 አሁን በዚህ ዓመትም ነው።

ይሄን ግጭት በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የፈጠረው ነው ብለን አናምንም።

ስለዚህ ምንድነው የሚለውን፥ ለምን ይሄ ግጭት ሊሆን ቻለ የሚለውን እኛ የምናነሳቸው ሃሳቦች እንደተጠበቀ ሆኖ ተጎጂው ማህበረሰብ በሁለቱም በኩል ያለው ህዝብ በኦሮሞ ብሄረሰብ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ያሉ ህዝቦች ችግሩን እና ያጣላቸውን ሰው በደንብ ስለሚለዩ፣ ያጣላቸውን አካል ስለሚለዩ እዛ ላይ በደንብ ተወያይቶ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።

የህግ የበላይነት በቀጠናው ላይ መከበር አለበት ብለን እናምናለን፥ እንጂ እዛ አካባቢ ያለው ህዝብ በብዛት ሄዶ ቤት የሚያቃጥልበት፣ አረጋውያን የሚገልበት፣ ህፃናት የሚገድልበት ስነልቦና ፀባይም፣ ቁመናም የለውም።

ዘላቂ መፍትሄውን በተመለከተ በገለልተኛ ወገን ታይቶ ለግጭቱ አነሳሽ፣ አደራጅ፣ ቀስቃሽ እና ግብዓት አቅራቢዎች አካላት ያለ ምህረት መጠየቅ አለባቸው።"

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ

t.me/geradomedia
61 viewsGashu, 12:11
Open / Comment
2021-04-19 12:48:07 አጣዬ በታጣቂዎች ጥቃት ሙሉ በሙሉ መውደሟ ተገለፀ!

ከአንድ ወር በፊት በአማራ ክልል በሚገኙት የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት ተከስቶ ከ300 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም። በነዚሁ አካባቢዎች ካሳለፍነው ሐሙስ ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ምሽት አንስቶ ዳግም ግጭት አገርሽቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ስር የምትገኘው እና የኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ዋና መቀመጫ የሆነችው የአጣዬ ከተማ አስተዳደር፣ ታጣቂዎች ቀድመው ጥቃት የጀመሩባት ስፍራ ስትሆን፣ በታጣቂዎች በተፈጸመባት ጥቃት ሙሉ በሙሉ መውደሟ ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ telegra.ph/አጣዬ-04-19
336 viewsGashu, 09:48
Open / Comment
2021-04-19 11:11:17
778 ይደውሉ!

በመራጮች ምዝገባ ዙሪያ በነፃ የስልክ መስመር 778 በመደወል መጠየቅ ይቻላል። ይህ የነፃ ስልክ መስመር በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች ይሰራል።

መምረጥ መሰልጠን ነው፤ የመራጭነት ካርዶን ይውሰዱ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

t.me/geradomedia
599 viewsGashu, 08:11
Open / Comment
2021-04-19 11:11:00 ይህችን ምርጥ ቻናል ተቀላቀሏት! የፈለጋችሁትን ታገኙባታላችሁ!

ለመቀላቀል t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
600 viewsGashu, edited  08:11
Open / Comment
2021-04-18 21:52:16 #ኮማንድ_ፖስት

"በሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን ወረዳዎች ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል!" - መከላከያ ሚኒስቴር

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዮ ዞን ወረዳዎች ከተከሰተው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ከክልል እና ከፌዴራል ፀጥታ ተቋማት ጨምሮ ሶስቱንም ዞኖች ያካተተ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አስታውቋል።

- በዚህም የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲባል የሚከተሉት ክልከላዎች የተደረጉ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል፡፡

1ኛ. ከደብረ ሲና እስከ ኮምቦልቻ አዋሳኝ ወረዳዎች መንገድ ላይ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ እስከ 20 ኪ/ሜ ውስጥ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ
የተከለከለ ነው፡፡

2ኛ. መንገድ መዝጋትን ጨምሮ አብያተ ክርስቲያናትን እና የመንግስት ተቋማትን የግለሰብ መኖርያ ቤትን እና ንብረት ማውደም ወይም ለዚህ ተግባር በተናጥልም ይሁን በቡድን መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ተጨማሪ telegra.ph/GM-04-18
659 viewsGashu, edited  18:52
Open / Comment
2021-04-18 19:50:53
#ንቃ

ትክክል ነገር ያደረግክ መስሎህ ሳይገባህና ምንም ባልተረጋገጠ መረጃ ተመርኩዘህ አገር የማፍረስ እንቅስቃሴው ተባባሪ ከመሆን ታቀብ። ማንም ሰው የሚነግርህን አልያም ከየትኛውም አቅጣጫ የአንተን የአዕምሮ እሳቤ ለመቆጣጠር የሚሰራጩ መረጃወችን ግራና ቀኙን ሳታይ በመቀበል በምትፈፅመው ድርጊት የአገር አፍራሽ ጠላቶችህ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነህ እንዳትገኝ ንቃ! #Copy

አዋ ንቃ! እምነት አለኝ፤ አምላኬ ፀሎቴን/ዱአየን ይቀበለኛል ትል የለ? በቃ ለሀገርህ ፀሎት/ዱዓ አድርግ! ንቁ ሆንክ ማለት ይህ ነው! ንቁ ካልሆንክ የሀገር አፍራሽ ጠላቶችህን ጉዳይ አስፈፃሚ ትሆናለህ ሲሉህ አትሰማም እንዴ! አዋ! አንተን ነው! አስተንትን! እስከመቼ ተኝተህ ግን?

ኧረ ንቃ!

t.me/geradomedia
569 viewsGashu, 16:50
Open / Comment
2021-04-18 19:50:46 ይህችን ምርጥ ቻናል ተቀላቀሏት! የፈለጋችሁትን ታገኙባታላችሁ!

ለመቀላቀል t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
523 viewsGashu, 16:50
Open / Comment
2021-04-18 12:53:43
#GERD

"ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ለልማቷ ስታውል፣ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት የማስከተል ፍላጎትም ዕቅድም የላትም። ባለፈው ዓመት የተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሕዳሴውን ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት እውን ያደረገ ሲሆን፣ የግድቡ መኖር በራሱ ጎረቤት ሀገራችን ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ በአስተማማኝ ሁኔታ ተከላክሎላታል።

ኢትዮጵያ ሁለተኛው የውኃ ሙሌት ከመቀጠሉ በፊት፣ አዲስ በተጠናቀቁት የውኃ መውረጃዎች አማካኝነት ባለፈው ዓመት ከተገደበው ተጨማሪ ውኃን የምትለቅቅ ሲሆን፣ መረጃንም ታጋራለች። ሁለተኛው ሙሌት የሚከናወነው ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚገኝባቸው የሐምሌ/ነሐሴ ወራት በመሆኑ፣ ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ ለመከላከል ይጠቅማታል።"

- ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር)

t.me/geradomedia
46 viewsGashu, 09:53
Open / Comment
2021-04-18 12:53:26 ይህችን ምርጥ ቻናል ተቀላቀሏት! የፈለጋችሁትን ታገኙባታላችሁ!

ለመቀላቀል t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
44 viewsGashu, edited  09:53
Open / Comment
2021-04-17 21:13:18 አጣዬ፣ ካራቆሬ፣ ማጀቴ፣ አንፆኪያ፣ መኮይና ሸዋሮቢት....

በአማራ ክልል የተፈፀመውን ጥቃት ለማስቆም ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል መግባቱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። ትናንትና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን አጣዬ ከተማን የጸጥታ ኃይሉ መቆጣጠሩንም የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኀንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ አስታውቀዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ ጥቃት ንጹሐን ተገድለዋል፣ አካል ጎድሏል፣ ሀብትና ንብረት ወድሟል። ዜጎች ቀያቸውን ለቀው ራሳቸውን ለማዳን ሸሽተዋል። በአካባቢው ከአሁን በፊት የተከሰተው ችግር በመረጋጋት ላይ ባለበት ወቅት ነው ችግሩ በድጋሜ ነው የተነሳው። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንም (አሚኮ) ጉዳዩን እየተከታተለ ሲዘገብ መቆዬቱ ይታዎሳል።

በአማራ ክልል ስለተፈጠረው የጸጥታ ችግር የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደኀንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ ለአሚኮ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢ መጠነ ሰፊ የሆነ ችግር ተፈጥሯል ብለዋል። በአካባቢው ከአሁን በፊት ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮችን ከሕዝብ ጋር በመሆን ሲፈቱ እንደቆዬ ያመላከቱት ኃላፊው ችግሩ በድጋሜ ማገርሸቱን ነው የተናገሩት።

ትናንት በአጣዬና በአካባቢው የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም አመላክተዋል። በደረሰው ጉዳትም ንጹሐን ሞተዋል፣ አካል ጎድሏል፣ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትና ንብረትም ወድሟል ነው ያሉት።

በአጣዬ በማረሚያ ቤት የነበሩ ታራሚዎች ከእስር እንዲወጡ ተደርጓል። ከአጣዬ ባለፈ በካራቆሬ፣ በማጀቴ፣ በአንፆኪያ፣ በመኮይና በሸዋሮቢት ሕዝቡ በውጥረት ውስጥ ነው ያለው ብለዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ያለው ችግር እየከፋ የመጣና ሕፃናት፣ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር በግፍ የተገደሉበት መሆኑንም ተናግረዋል።

የኦነግ ሸኔ ቡድን በሸዋሮቢት የሚገኙ ታራሚዎችን ለማስለቀቅ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ያመላከቱት ኃላፊው በአካባቢው አሁንም የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ነው የተናገሩት።

የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአካባቢው የጸጥታ መዋቅርና የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።

የአማራ ክልል የጸጥታ መዋቅር ከፌዴራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። አካባቢውን ለማረጋጋት እና አጥፊውን ቡድን ለሕግ ለማቅረብ ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል ወደ ስፍራው መግባቱንም ተናግረዋል።

የአካባቢውን ሚሊሻ በማደራጀት ከሌላው የጸጥታ ኃይል ጋር እንዲገባ እያደርግን ነውም ብለዋል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን አጣዬ ከተማን የጸጥታ ኃይሉ መቆጣጠሩን አስታውቀዋል።

በሸዋሮቢት ያለውን ችግር ለመቅረፍ የመከላከያ ሠራዊት ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል።

የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን የአማራን ሕዝብና መንግሥት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ለመውሰድ እየሠራ መሆኑንም አመላክተዋል። ችግሩን የፈጠሩ፣ ያደራጁና የመሩ ለሕግ መቅረብ አለባቸው፤ ጽንፈኛውን ቡድን ከሕዝብ እየነጠሉ ለሕግ ማቅረብ ይገባልም ብለዋል።

በሌላ በኩል በጭልጋ አካባቢም የታጠቁ ኃይሎች በመከላከያ ሠራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ላይ ጥቃት በመፈፀም ችግር መፍጠራቸውን የተናገሩት ኃላፊው የክልሉና የፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ሰላምን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ሕዝብ የሚሰጡትን አጀንዳዎች በሰከነ መንገድ በማዬት ከመንግሥት ጎን በመቆም ችግሮችን በጋራ እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል።

Via አሚኮ

t.me/geradomedia
1.1K viewsGashu, edited  18:13
Open / Comment