Get Mystery Box with random crypto!

ቅኔ ያለው ትውልድ

Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Channel address: @keney_serezoch
Categories: Literature
Language: English
Subscribers: 1.33K
Description from channel

ለነፋሳቹ ነፋስ የሚሆኑ ነገሮችን ዝሩለት . . !
ቤቴን ቤቶ ስላረጉ አመሰግናለው!
. .

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 6

2021-06-13 12:01:40
ቀን / 06 10 2013 እሁድ

የሳምንቱ የቻናሉ ምስል ……………


•••••• ይናገራል ሚስጥር••••••


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
161 views09:01
Open / Comment
2021-06-12 08:17:29
Take my crown away but not my books/ዘውዴን ውሰዱ መፅሀፎቼን ግን እንዳትነኩ
"The King's Speech " የተሰኘውን ፊልም ብዙዎቻችን ተመልክተነዋል። አንድ መስፍን ለፍቅር ሲል የእንግሊዝ ንጉስነትን ስልጣን እምቢ ብሎ ተራ ህይወትን ሲመርጥ በፊልሙ መጀመሪያ ላይ እናያለን።

በፊልሙ ላይ ያላየነው ተያያዥ ታሪክ ይህ አፍቃሪ ፣ መፅሀፍ አፍቃሪም ጭምር እንደሆነ ነው። ምንም እንኳን ለሚወዳት ሴት ሲል፣ የንጉሥነት ስልጣኑን እስከመተው ቢደርስም፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ካጠራቀማቸው 3000 ቅጾች ካሉት የመፅሀፍት ስብስቡ ጋር ለመለያየት ፍቃደኛ አልነበረም። ይህ የእውነተኛ መፅሀፍት አፍቃሪ ባህሪ ነው።እናም ከቤተ መንግሥቱ ወጥቶ ሲሄድ ይዞት የወጣው ንብረት 3000 መፅሀፍቱን ብቻ ነው።
"ጌታ ሆይ የምበላው ምግብ፣ የምወዳት ሴት፣ የማነበው መፅሀፍ አታሳጣኝ! ሌላው ትርፍ ነው!" ያለ ይመስለኛል!


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
203 views05:17
Open / Comment
2021-06-11 18:29:02
………………
…………… ለማምሻ

"ዓይናችንን መዝጋት ምንም ነገር አይለውጥም። ምን እየተካሄደ እንዳለ ስላልተመለከትን ብቻ ምንም ነገር አይጠፋም።በእውነቱ በሚቀጥለው ጊዜ ዓይኖቻችንን በምንከፍትበት ጊዜ ነገሮች እንኳን ከቀድሞ የከፋ ይሆናሉ ፡፡የምንኖርበት ዓለም መልኳ እንደዚህ ነው! ዓይናችንን በቻልነው ልክ ክፍት ይሁን ፡፡ዓይኖቹን የሚዘጋ ፈሪ ብቻ ነው………… ዐይንን መዝጋት እና ጆሮዎችን መጠቅጠቅ ጊዜ ቆሞ እንድናየው አያደርግም............... !"

{Haruki Murakami,Kafka on the Shore}


┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
@keney_serezoch
@keney_serezoch
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄

……… ፍቅር ……… አሁን………
76 views15:29
Open / Comment
2021-06-11 06:19:25
………………

እስከ ደርግ ስርአት ማብቂያ ድረስ በአቢዮት አደባባይ ተሰቅሎ የነበረውን የኮሎኔል መንግስቱ ሀ/ማሪያምን ግዙፍ ስዕል የሳሉት ሰአሊ ታደለ እጅጋየሁ ናቸው።ነገር ግን ከንፈሩን አነጣኸው አመድ የጎረሰ አስመሰልከው ተመልካች ሲመለከተው እንዲስቅበት አስበህ ነው የሳልከው በሚል ለእስር ተዳርገዋል።


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
114 views03:19
Open / Comment
2021-06-10 18:22:48
………………
…………… ለማምሻ


ሁላቹም ለውስጣቹ ይሄን ንገሩት!

"ነገሮች

ደህና

ይሆናሉ !!" እርግጥ ነው ደህና ይሆናሉ!!



┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
@keney_serezoch
@keney_serezoch
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄

……… ፍቅር ……… አሁን………
136 views15:22
Open / Comment
2021-06-10 06:44:55 ………………
………………

እስኪ ስለ General theory of relativity እናውራ።
ሁሉም ነገር አንፃራዊ እንደሆነ የሚያትተው ይህ መፅሐፍ የወጣው በ 1905 እ.ኤ.አ ነበር። በወቅቱ የጊዜን አንፃራዊነት አልበርት ሲያስረዳ " የጋለ ብረት ላይ ለአንድ ደቂቃ መቆም እና ከፍቅር ጓደኛህ ጋር አንድ ሰዓት ማሳለፍን ብታወዳድር የጋለ ብረት ላይ መቆም ረጅም ሆኖ ይሰማሃል" ይል ነበር ይባላል።

አልበርት አብዛኛውን የፊዚክስ ሃሳቦቹን የሚያመጣው በሚሰራቸው ሃሳባዊ ሙከራዎች (thought experiments) ነው። ከእነዚህ ሙከራዎች መካከል በ1905 እ.እ.አ የታተመው General theory of relativity ላይ ስለ ጊዜ (time dilation) የሰራው የሃሳብ ሙከራ (thought experiment) ለዛሬ እንመልከት።

እስኪ ሁለት ሰዎችን አስቡ፤ ሁለቱም ቁመቱ 1 ሜትር በመሆነ የመጓጓዣ አካል (መንኮራኩር) ውስጥ ናቸው እንበል።

የሁለቱም መንኮራኩር ጣራ ላይ መስታውት አለ፤ ሁለቱም የእጅ ባትሪ (ሌዘር) ይዘዋል።

በመቀጠል እነዚህ ሰዎች ወደ መስታውቱ ባትሪያቸውን አበሩ።

እንደሚጠበቀው ብርሃኑ መስታውቱ ላይ ተንፀባርቆ ይመለሳል። በዚህም ብርሃኑ ደርሶ መልስ 2 ሜትር ይጓዛል። ምስጋና ለ ጀምስ ማክስዌል ይሁን እና የብርሃን ፍጥነት ይታወቃል(300,000 ኪሜ በሰከንድ)።

ስለዚህ 2 ሜትሯን ለመጨረስ የሚፈጅበትን ጊዜ ማስላላት ይቻላል። በቀላሉ ርቀቱን ለብርሃን ፍጥነት በማካፈል ማወቅ ይቻላል።

t=2ሜትር÷300,000,000 ሜትርበሰከንድ= 6.6 ናኖሰከንድ

ይህ ሰዓት ለሁለቱም እኩል 6.6 ናኖ ሰከንድ ይሆናል።

ነገር ግን አንደኛው በፍጥነት ቢሄድ ( ለምሳሌ በብርሃን ፍጥነት ግማሽ) ቢጓዝ፤ ከቆመው መንኮራኩር ያለው ሰው የሚንቀሳቀሰው ውስጥ ያለውን ሰው ሲያይ፣ ብርሃን ከእጅ ባትሪው ተነስቶ 1 ሜትር ተጉዞ ጣራው ላይ ከመድረሱ በፊት 0.5 ሜትር ወደጎን ይጓዛል። በዚህም ምክንያት ቀጥ ብሎ ወደላይ ደርሶ መመለሱ ይቀርና ሰያፍ ይጓዛል።

ሰያፍ መሆኑ ደግሞ የሚጓዘውን ርቀን ይጨምረዋል። በትክክል ለማወቅ በፓይታጎረስ ቴረም ብንጠቀም

l=(x²+y²)½
x=ቁመት y=መንኮራኩሩ ወደ ጎን

የተጓዘው ርቀት
l=(1²+0.5²)½= 2.24ሜትር

ቅድም በተጠቀምነው መሰረት ጊዜን ብናሰላ፦
t=2.24ሜ÷300,000,000 ሜበሰከንድ
t=7.5 ናኖ ሰከንድ

ስለዚህ የቆመው ሰውየ የሚሄደውን ሰውን 7.5 ናኖ ሰከንድ እንደቆየ ያስባል፤ ይኸው የቆሞው ሰው የራሱን ሰዓት ግን 6.6 ናኖ ሰከንድ ነው ብሎ ያስባል።

ሰዎቹ መንታ ቢሆኑ እና በዚህ አይነት ሁኔታ ለ50 ዓመታት ቢቆዩ፤ አንዱ 50 ሌላኛው 56 ዓመት ከ10 ወር ይሆነዋል ማለት ነው (twin paradox).

ይሄን ሁሉ ላለማውራት መግቢያው ላይ ያለውን የፍቅረኛ እና የጋለ ብረት ላይ የመቆምን ተምሳሌት ይጠቀሙበታል።

ማጣቀሻ
¹ Concepts of modern physics Arthur Beiser et al
² Relativity : the special and the general theory Albert Einstein
³ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Time_dilation
https://steemit.com/physics/@procrastilearner/intuitive-special-relativity-time-dilation


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
164 views03:44
Open / Comment
2021-06-10 06:44:44
142 views03:44
Open / Comment
2021-06-09 18:37:59
………………
…………… ለማምሻ


“ሁላችንም እንፈጥረው ዘንድ የተፈጠርንለት ጥበብ አለ፡፡ እናም ደግሞ ጉዳዩ የሕይወታችን ማዕከላዊ ነጥብም ነው፡፡ ምንም ያህል ራሳችንን ለማታለል ብንሞክርም - ጉዳዩ ምን ያህል ለደስታችን ወሳኝ መሆኑን አናጣውም፡፡ ብዙውን ጊዜ ያ ጥበብ ለዓመታት በጫንንበት ፍርሃት፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና ወላዋይነት ሥር ተሸፍኗል፡፡ ግን ደግሞ ብቃታችንን ካልተጠራጠርን ግባችን ይሳካል ሕልማችንም እውን ይሆናል !!!አዎን … በዕርግጥም በክብር የመኖር ብቸኛው መንገድ ይህ ነው…”
{Paulo Coelho, The Pilgrimage}


┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
@keney_serezoch
@keney_serezoch
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄

……… ፍቅር ……… አሁን………
167 views15:37
Open / Comment
2021-06-09 08:26:34 …………………………………………
የማለዳ እንጉርጉሮ
…………………………

አንዳንዴ ደሞ ጎህ ቀዶ
አብሮኝ ያደረው ደወል ፤ ከራስጌየ ተጠምዶ
ከወፎች ቀድሞ ሲያመጣልኝ “ ነግቶብሃል” የሚል መርዶ
ብትት ብየ፤ ደንብሬ
ግማሸ ፊቴን ትራሴ ውስጥ ቀብሬ

“ እኮ ዛሬም እንደወትሮ
ካውቶብስ ወደ ቢሮ
ከኬላ ወደ ኬላ
ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ
አሺ ከዚያስ በሁዋላ?”

እያልሁ ልቤን ስሞግት ፤ መልሱን አያመለክተኝ
ይሄን ያህል ነው የታከተኝ፤

ጉዞየ፤ ካዋላጅ እቅፍ፤ እስከገናዦች አልጋ
ባራት አግር ተጀምሮ፤ ባራት ሰው ሸክም እስኪዘጋ
መንገዱ መንገድ እየሳበ
ትንንሹ ዳገት ፤ለትልልቁ እያሰረከበ
እንደ ሀረግ ስጎተት፤ እንደ ጥንቸል ስፈጥን
“ምን ሽልማት ታሰበልኝ? ይህ ልፋቴን የሚመጥን
እያልሁኝ ሳውጠነጥን፤

አንዳንዴ ደሞ ሲመረኝ
እንደ ለማዳ ፈረስ፤ ሞትን በፉጨት መጥራት ሲያምረኝ፥
ዛፉን የተቀማ አሞራ
በኮረንቲ ምሶሶ ላይ፥ ጎጆው ባዲስ መልክ ሲሰራ
ማርዋን የተዘረፈች ንብ ፤ በየአበባው ስትሰማራ
አይና
እንዲህ እንዲህ እላለሁ፤ ርስ በራሴን ሳጽናና፡ -

ሺህ ጊዜ ብትራቀቅ ፤ ቃላት መርጠህ ብትገጥም
ከዚህ አሞራ አታንስም ከዚች ንብም አትበልጥም
ተፈጥሮ ትግልን እንጂ፤ የድል ዋስትናን አትሰጥም
ቻለው! "


{በእውቀቱ ስዩም}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
186 views05:26
Open / Comment
2021-06-09 08:26:24
162 views05:26
Open / Comment