Get Mystery Box with random crypto!

ቅኔ ያለው ትውልድ

Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Channel address: @keney_serezoch
Categories: Literature
Language: English
Subscribers: 1.33K
Description from channel

ለነፋሳቹ ነፋስ የሚሆኑ ነገሮችን ዝሩለት . . !
ቤቴን ቤቶ ስላረጉ አመሰግናለው!
. .

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 7

2021-06-08 18:42:54
………………
…………… ለማምሻ



┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
@keney_serezoch
@keney_serezoch
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄

……… ፍቅር ……… አሁን………
90 views15:42
Open / Comment
2021-06-08 07:00:12
ህዝቤ ጠይም ሳለ፣
ሩህሩህ ነበረ ።

ቀለም ገባው መሰል፣
'ይቀላ' ጀመረ።
{አማኑኤል}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
134 views04:00
Open / Comment
2021-06-07 19:13:22
………………
…………… ለማምሻ

……… "አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ በጣም ብዙ የፈጣሪ ትናንሽ ጓደኞች አሉ ደስታም ለነሱ የተቸረ እሚመስለን፣ አልፎ ተርፎም ቀዝቃዛ እና ረሀብ መኖራቸውን ሲያውቁ እንኳን በጣም ደስተኛ እና ፍስሃ ማድረጋቸው ስህተት መስሎ ሊታይ ይችላል ፣ ግን እነዚህ መጥፎ አጋጣሚዎች ደስታችንን ከልባችን እንዲያስወግዱት ከፈቀድንላቸው ደስተኛ መሆን አንችልም ፣ ስለሆነም እኛ የምንችለውን ያህል ደስተኛ መሆን ትክክል እንደሆነ እና በተቻለ መጠን ትንሽም ቢሆን ፣ በዙሪያችን ያሉትን ደስተኞች ለማድረግ እና አስደሳች ጊዜን ለመፍጠር እንጣር ፡፡

በሐዘንም ለተደቆሰ ሰው ሁሉ ደስታን አምጡ።"

{ሄሌን ኬለር}


┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
@keney_serezoch
@keney_serezoch
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄

……… ፍቅር ……… አሁን………
156 views16:13
Open / Comment
2021-06-07 08:13:07

ሙኒባ ማዛሪ በ18 ዓመቷ ነበር በቤተሰቧ አስገዳጀነት ትዳር የመሰረተችው።ትዳር በመሰረተች በሁለተኛ ዓመቱ ከባለቤቷ ጋር ስትጓዝ የመኪና አደጋ ገጠማት ። በደረሰባት አደጋም የከፋ የጀርባ አጥንት ስብራትን ጨምሮ ውስብስብ የጤና እክል ገጠማት።

በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ቢደረግላትም ዳግም በእግሮቿ መራመድ ግን አልቻለችም። ይሄን በሰማች ጊዜም ለመቀበል ከበዳት።ይባስ ብሎ መውለድ እንደማትችል ሲነገራት ደግሞ የበለጠ ሃዘኗን ጨመረው ።ተስፋ
ቆረጠች።በርካታ የፈተና እና የመከራ ጊዚያትን በሆስፒታል ቆይታዋ አሳለፈች።

ነገር ግን መከራዋ እና ፈተናዋ አብሮት አልዘለቀም። ከለታት አንድ ቀን በጥዋት ተነስታ "ተስፋ መቁራጥ አማራጭ አይደለም !ተስፋ መቁራጥ ደስታን ነጣቂ ክፉ በሽታ ነው!" የሚለውን ደጋግማ ለራሷ ነገረች።ከዛም ፍርሃቷን አንድ በአንድ በመፃፍ አቃጠለችው።በሆስፒታሉ
ግድግዳ ተስፈዋን የሚያለመልም እና ከፍታዋን የተሸከሙ ስዕሎችን መሳል ጀመረች።

ሙኒባ የከፋ አደጋ በህይዎቷ አሰናክሏት የአካል ጉዳተኛ በመሆኗ "አበባዋ ረገፈ !" ሲሏት ተስፋ" ባለመቁረጥ ያሳየችው የመንፈስ ጥንካሬዋ ለስኬት አበቃት። ሙኒባ ከምትፈልገው እና
ከምታስበው በላይ ትልቅ ደረጃ፤ የላቀ ቦታ
ላይ ደርሰች። ተስፋ ሳትቆርጥ ባደረገችው ግስጋሴ ዛሬ ላይ ሙኒባ ማዛሪ በአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉት እንስቶች
መካከል አንዷ ሆናለች።

የተባበሩት መንግስታት የመልካም ሰው ክቡር አንባሳደር ተብላ አለም በስኬት ክብር ከሚያወድሷቸው ጥቂት አንደበተ ርቱዕ ታዋቂ ሰዎች መካከል አንዷ ሙኒባ ሆናለች ።

አነቃቂ ንግግሮችን ለብዙ ሺዎች በማድረግ
የብዙዎችን ነፍስ ታለመልማለች እዲሁም
ድምፃዊ፣ሰዓሊ ስትሆን ፤ በጎ አድራጎቶችንም ታከናውናለች ።

ልጅ መወለድ ባትችልም እንኳን በማደጎ ልጅ አግኝታ ህይዎቷ ባጣችው የልጅ ፍቅር ታድሷል።
በሰው ልቦና ሊረሱ የማይችሉ ስራዎችንም እየሰራች ትገኛለች። በኑሮዋም ቅንጡ ሂወትንም
ትኖራለች።

መንገዷ ከባድ ቢሆንም መድረሻዋ ግን ስኬት ነው ምክንያቱም እሷ እንደምትለው ከመሞቷ
በፊት ስላልሞተች።

#ምንም ነገር ከማንችለው በላይ አልተሰጠንም!! መሆን የፈለግነውን ሁሉ መሆን ከፈለግን እንሆናለን!! እኛ በቃ እስካላልነው ድረስ የማያበቃ ስኬት እንገንባ !!


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
174 viewsedited  05:13
Open / Comment
2021-06-07 08:12:48
146 views05:12
Open / Comment
2021-06-06 16:39:00
"የፈጠርነው መንፈስና አካል 'ሰው' መሆኑን
በምን ይደርስበታል?" ስትል ጠየቀች

"የምንፈጥረው ሰው 'ሰዋዊነቱ ላይ የሚደርስበት ከሰው መንጋ ጋር ስንቀላቅለው አይደለም።"
(ከመፅሐፉ የተወሰደ)


••••• . . . ተጋበዙልኝ

ፀሐፊ ------- ዮናስ ዘውዴ ከበደ

ርዕስ ------- አልገባኝም

••••••• ነገ እቺን መፅሐፍማ በእጃቹ አስገቧት

{ ሄዶ መግዛት አይመቸኝም ካላቹ ደሞ @Guramaylebooks
@Guramayelie 0912319263 Free delivery ማዘዝ ትችላላቹ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
194 viewsedited  13:39
Open / Comment
2021-06-04 21:34:11
አሰቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ለወንድማችን !!
በቅንነት እና በመልምነት ሼር ሳያደርጉ እንዳያልፉ

የህይወት አድን ጥሪ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና

ውድ ኢትዮጵያውያን | ተማሪ ህፃን አቤኔዘር ቶሎሳ አድነው ይባላል የ10 ክፍል ተማሪ ነበር ሚማረውም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኝ ነበር ።

ይሁንና በደረሰበት ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ህመም ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል እና የኩላሊት የህመሙ ስሜት ሁለቱንም እግሮቹን እንደ ልብ እንዳይንቀሳቀስ አድርጎት በአልጋ ላይ እየተሰቃየ ይገኛል ።

ውድ ወገኖች በሃኪሞቹ በተነገረው የቀድሞ ጤን ነቱ እንዲመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት እጥበት እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ የኩላሊት ተከላ ለማድረግ ወደ ውጭ ሃገር ሄዶ መታከም ይኖርበታል ለህክምናም በጠቅላላ 1.500.000 ብር ያስፈልገዋል ቤተሰቦቹ ደግሞ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ ውድ ወገኖች ለጋስ እጆች አያጡምና የወንድማችንን ህይወት ለመታደግ የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉልን በፈጣሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ባትችሉ እንኩዋን ለሚረዱ ሰዎች ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን

ለበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር
09 67 92 14 67

እንዲውም ቤተሰቡ ጋር
09 22 95 94 60
09 13 56 02 42

በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ!!!በቅንነት ሼር ያድርጉ

ባንክ አካውንት
1000357725187 tolosa adinew bati
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

100089385079 aprhem tolosa adinew
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ለጋስ እጆች አያጡም !!!
353 views18:34
Open / Comment
2021-06-04 18:27:09 ………………

"ተረት . . ተረት


"በድሮ ጊዜ አንዲት ሴት ነበረች . . . ይቺ ሴት
ልጅ አልነበራትም . . ላልተሳለቹ ታቦት አልነበርም
ሆኖም ግን ልጆ ማግኘት አልቻለችም።

በመጨረሻ ለሴጣን ተሳለች ስለቷም ጋቢ ነበር። እናም እቺ ሴት ፀነሰች ፣ ወለድች ኃላም ስለቷን ለማድረስ ብፈልግም ሰይጣን የት እዳለ አታውቅምና ንሰሃ አባቷን ልጠይቅ ሄደች ። እሳቸውም እንዲህ አሏት፦

"በሁለት ሰዎቾ መሃከል ፀብ ተፈጥሮ አልታረቅም አሻፈረኝ ብሎ ለይቅርታና ለይቅር የሸሸ ሰው ስታገኚ ይህን ጋቢ አልብሽው እሱ ሰይጣን ነው" አሏት።

እሷም በሌላኛው ጊዜ ከአንድ ሸንጎ ቦታ ስታልፍ አንድ አልታረቅም ብሎ እምቢ ያለ ሰው አየች ሄዳም ጋቢውን አለበሰችው። ሰውየውም በብስጭት እንዴት ጋቢ ታለብሽኛለሽ ብሎ ተቆጣ
እሷም ንሰሃ አባቷ ያሏትን ነገረችው "እኔ ስለቴ ሞልቻለውም "አለችው።

እሱም ጋቢውን ጥሎ ተታርቆ ሄደ ይባላል።

ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ።"

{የዛይ መሬት ከሚለው ፊልም ላይ የተወሰደ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
216 views15:27
Open / Comment
2021-06-03 06:13:47 ……


ሕፃን እንደነበርኩ አማርኛ አስተማሪያችን "ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?" ብለው ጠየቁኝ: "አላድግም አልኳቸው!!"፡፡

ንዝረቱ ሱዳን ድረስ በሚሰማ ኩርኩም አጋጩኝ፡፡ ገጭ !! በ'ሬክተር ስኬል' ምናምን ቁጥር የተመዘገበ ኩርኩም በሽመልስ ሀብቴ ትምህርት ቤት ሁለተኛ 'ዲ' ሰነፍ መደዳ ሶስተኛው ዴስክ ላይ...ጥቁር ሰሌዳው እያደገ እያደገ ሄዶ ግድግዳውን የሸፈነው እስኪመስለኝ ፊት ለፊቴ የሚታየኝ ነገር ሁሉ ጨለማ ሆነ፡፡የቀኔ ማብሪያና ማጥፊያ አናቴ ላይ ተገጥሞ በኩርኩም የሚበራና የሚጠፋ ዓይነት...'ገጭ' ሲል እልም!! ቀኑ ጨለመብኝ፡፡ ማክሰኞ ቀን ነበር...ማክሰኞ ጨለመ...!!

ይሄ ኩርኩም የሚገባው ለእማማ ዙርያሽ ነበር...(የሰው ሀቅ ነው የወሰድኩት )እሳቸው ናቸው የመስኮታቸውን መስታወት ለወፍ በወረወርኩት ድንጋይ የሰበርኩባቸው ቀን መንደሩ ሁሉ እየሰማ "ይሄ ያስታውቃል አያድግም"ያሉኝ፡፡ ደግም የባሕል መድሀኒት አዋቂ ናቸው፡፡ ትንቢት ቀመስ የሀኪም ትዕዛዝ ብናገር ይህን የሚያክል ኩርኩም...?

በኩርኩም የ'አታድግም!' ትንቢቱን አክሽፈውት ነው መሰል አደግኩ!! ፀረ ትንቢት ኩርኩም፡፡" ልጅህን በኩርኩም አጋጨው: ሲያድግ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ይመኛልና፡፡"

{አሌክስ አብርሀም ...ዶ/ር አሸብር ላይ የተቀነጨበች}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
118 views03:13
Open / Comment
2021-06-01 10:39:53
ይህች የ2 ልጆች እናት ሰልዋ_ሁሴን ትባላለች!! ባለ ፈገግታዋ ሴት የምትኖረው እንግሊዝ ዉስጥ ሲሆን በዓለም ላይ ያለልብ የምትኖር 2ተኛዋ ሴት ናት።

ልቧን ያሳጣትን ከባድ የቀዶ ጥገና ሕክምና ካደረገች በኋላ ህይወቷ ሙሉበሙሉ ተቀይሮ ጀሪካን የሚያህል ሰው ሠራሽ ልብ በጀርባዋ ተሸክማ ትዞራለች!

በእንግሊዝ ሀገር በዚህ መልኩ የምትኖር ብቸኛ ሴት ስትሆን ጀርባዋ ላይ ያለው ቦርሳ ዉስጥ 6.8ኪ.ግ የሚመዝን ባትሪ አለ!ልቧን ያንቀሳቅሳል:ደሟ ሰዉነቷ ዉስጥ ተሠራጭቶ ደረቷ ዉስጥ ካለው ልብ መሰል ፕላስቲክ ጋር ተገናኝቶ ይሄድ ይመጣ ዘንድ ያግዛል!!

# የተሰጡን ስጦታዎች እረቂቅ ናቸው እያመሰገነው ስጦታዎቹ እዲቆዩልን እየጠየቅነው አሁንን ጣፍጦን እንኑረው !

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
96 views07:39
Open / Comment