Get Mystery Box with random crypto!

ቅኔ ያለው ትውልድ

Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Channel address: @keney_serezoch
Categories: Literature
Language: English
Subscribers: 1.33K
Description from channel

ለነፋሳቹ ነፋስ የሚሆኑ ነገሮችን ዝሩለት . . !
ቤቴን ቤቶ ስላረጉ አመሰግናለው!
. .

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 10

2021-05-23 10:14:38
ቀን / 15 9 2013 እሁድ

የሳምንቱ የቻናሉ ምስል ……………


•••••• ይናገራል ሚስጥር••••••


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
161 views07:14
Open / Comment
2021-05-22 22:03:42 እወዳታለው ፣ የምር.........

የጠወለገች አበባ የውሃ ጠብታ እንደምትናፍቅ ፣ በጨለማ የከረመ ሰው የብርሃን ቅንጣትን እንደሚናፍቅ ፣ የራበው ህፃን የእናቱን ጡት እንደሚናፍቅ ሁሉ የእኔም ልብ የሷን ፍቅር ይናፍቃል ......

እሷ ግን ይህንን እውነት አትውቅም ። ማነው ስሙ ? አላውቀውም ። እና የማታውቂውን ሰው ነው ወደሽ ነው የምትሰቃይው ?........ እኔን የያዘኝ እኮ የአይን ፍቅር ነው ፤ ከእሱ ምን አለኝ ። የት ነው የምታውቂው ? ........ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የምንማረው ።......ለምን ወደድሽው ? ................. እኔንጃ ፤ ዝምታው ፣ ምናልባትም ብቸኝነቱ ፤ አላውቅም ። .................

እንደማልጠላት ብቻ እንጂ እንደማፈቅራት አታውቅም ፈፅሞ አታውቅም እኒም አልነገርኳትም። ጓደኝነቷን ላለማጣት ስል ብቻ ፣ ካጠገቧ እንዳታሸሸኝ ስል ብቻ ፣ እንዳትጠላኝ ስል ብቻ እውነት እውነቱን ትቼ ዋዛ ፈዛዛውን አወጋታለው ። በቀልዶቼ ደስ ይላታል .... ትስቃለሽ ፤ ሳቋን ሳይ ልቤ በደስታ ትቦርቃለች ።

እስኪ የዛን የሚስኪን ሰው ደብዳቤ ላንብብልሽ ............

የሚስኪኑ ሰው ደብዳቤ ቁጥር 144 .

ውዴ አንድ ምስኪን የመንግስት ደሞስተኛ ጥሬ ስጋን ከሚናፍቀው በላይ ትናፍቂኛለሽ ፤ ከእስፔ ሻል ክትፎ በላይ ውድ ሆነሽብኛል ፤ ከእንግዲህ ይቅር ብለሽኝ ከቤቴ እንደማትመለሺ አውቃለው ምክንያቱም ከደረጃዬ በላይ ሆነሽብኛል ፣ ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለእኔ ኩንታል ጤፍ ማለት ነሽ። ክፉኛ የምመኝሽ ግን የማላገኝሽ ........ ውዴ አንቺ ማለት ለእኔ ጤፍ አለኝ ጎጃም በረንዳ ..... እንጀራዋንም አላይ አይነት ነገር ሆነሻል የእኔ ጤፍ ይቅርታ የእኔ ቆንጆ ትናፍቂኛለሽ ።

በሳግ ውስጥ ሆና ፈገግ አለችለትና ናቲ? ወዬ ..... ፍታኝ? ለምን አትፈታኝም እሺ አንድ እስቲክ ስጠኝ ? አልሰጥሽም ።

...... ናቲ ያለውበትን ጉድጓድ አንተ ትረዳኛለህ ብዬ አስቤ ነበር ግን አንተም ያው ነህ ከህቴ አትሻልም ያው ናቹ እሷም የመንደሩን ወሬ ፈርታ እንደዚህ ያሰረችኝ የዛች የሃሺሻም እህት እንዳትባል አይደል እንደዚህ ያሰረችኝ ....... ውጣልኝ !!!።

ለሚወዱት ሰው መዳኒት እንጂ መርዝ አይሰጥም ..... ግን መርዙ መዳኒት የሆነስ ጊዜስ ? እወዳታለው ስቃዩአን ማየት አልፈልግም ፤ ስለ ነገም አላውቅም ፣ ቢያንስ ዛሬን እፎይ ብላ ስትስቅ ማየት ልቤን ያደምቀዋል ........

(በጭስ ተደብቄ)

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
192 views19:03
Open / Comment
2021-05-22 22:03:39
175 views19:03
Open / Comment
2021-05-22 09:18:56
………… ቅምሻ

የተረጋጋ ሰው ፍላጎቶቹ ጌታው ለሱ ከሚፈልግለት ጋር የሚጣጣሙ ናቸው። ማለትም ፈጣሪ የሚወደውና እሱም የሚደሰትባቸው ናቸው። ሆኖም መረጋጋትና ፍላጎትን በጭፍን መከተል በአንድ ሰው ልብ ውስጥ አብረው መኖር አይችሉም።አንድ ሰው ሁለቱም ባህሪ በውስጡ ካሉ ልቡ ጠንከር ባለው ይጠቃል !!


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
201 views06:18
Open / Comment
2021-05-21 20:18:20
አንቺን እንዲሰጠኝ ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ
ጧፍ መባ ገዛሁ ልሰጠው ከሰማኝ፡፡
አንቺዬ
ፀሎቴን ሳልጨርስ ብትይ እመጣለሁ
እኔ እኮ ሞኝ ነኝ
ፈጣሪዬን ትቼ እጠብቅሻለሁ፡፡
እጠብቅሻለሁ
በተገተርኩበት
እጠብቅሻለሁ
በተፈጠረኩበት፡፡
ጊዜ አይፈራረቅ አይጮኹም አእዋፍ
አንቺን ስጠብቅሽ
ለኮስኩት ጨክኜ ለስለት እንዲሆን የገዛሁት ጧፍ፡፡
ትመጫለሽ አይደል?

(ኤልያስ ሽታኹን)


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
102 views17:18
Open / Comment
2021-05-18 16:41:49 ማሰብ ምንድነው? ሰው በማሰቡ ከእንስሳት ይለያል ሲባልስ እንዴት ነው?...የሰው ልጅ ምንን ስላሰበ ነው ከእንስሳት የሚነጠለው? ወይስ እያሰበ መሆኑን(ማሰብ መቻሉን ማወቁ) ነው? ከእንስሳት ልዩ የሚያደርገው ። እንስሳት ወደ ማይሆን አቅጣጫ ሲጓዙ እረኛቸው እንደሚያግዳቸው ሁሉ ማሰብ እረኛችን ትሆን? እንዲህ ከሆነ የሰው ልጅ መች እረኛውን ሰማ? ከኔ ጀምሮ ።

ማሰብ ከእንስሳት የተለየንበት ሳይሆን ከአራዊት ይልቅ አውሬነታችን የተገለጠበት ከትንኝም በታች ቅንጣት ያከልንበት ሁኔታ ነው ። ማሰብ ነውራችንን አደባባይ ያሰጣብን ከእኔነታችን ያጣላን ከእንስሳት ዝቅ ያረገን ነገር ነው ።

" ዘሎ ገደል የገባ እንስሳ የትኛው ነው? የሰው ልጅ ብቻ ። መውደቅ አውቆ ማጥፋት አስቦ መጥፋት የሰው ልጅ ብቸኛ መለያ ነው...የማያስብ እንስሳ ጥፋት ከሚያስብ የሰው ልጅ አጥፊነት እናሳ ከሆነ የሚያስብ የሰው ልጅ ጥፋት በማያስብ እንስሳ ካልተደረገ ከሁለቱ አናሳው ማን ነው? ያሰበውስ? የደመ-ነፍስ እውቀት ከነፍሳዊ እውቀት ከተሻለ ሰው ክብሩን ለእንስሳ ሊለቅ ይገባዋል ። በእርሱ የተደረገው ጥፋት በእሪያዎች የለምና..."

አለማሰብ ባይቻልም ማሰብን መመኪያ ለማድረግ የሰው ልጅ እጅግ ብዙ ይቀረዋል ። ይህች ውብ ዓለም እናስባለን በሚሉ አደናቁርቶች ጠፍታለች ። ረሃብ የሰው ልጆች የተንኮል ቀመር ነው ። ጦርነት የሰው ልጆች ያለማሰብ ውጤት ነው በሽታ በሰው ልጆች ተቦክቶ ይጋገራል...የዋሆች ይመገቡታል ፈጥነው ይሞታሉ ። ይህ የሰው ልጅ የማሰብ ውጤት ነው ግን ይህ ዓይነት ጭካኔ በእንስሳት አልተደረገም ። ስለዚህ ከሚያስበው የሰው ልጅ እንስሳቶች በለጡ ። የተበለጠ ጎበዝ የሰው ልጅ ብቻ ነው ። ያሸነፈ ተሸናፊ ።

ማሰብ የመሆን ምክንያት አይደለም ። መሆን ግን አብዛኛውን ግዜ የማሰብ ሳይሆን የመፈለግ ውጤት ናት...አስበን አንፈልግም የፈለግነውን እናስባለን እንጂ ።

" የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች " ከገጽ 23-26 የተቀነጨበ


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
100 views13:41
Open / Comment
2021-05-18 16:41:41
93 views13:41
Open / Comment
2021-05-17 20:59:01
100 ጥቁር ጉንዳኖችን እና 100 ቀይ ጉንዳኖችን ሰብስበው በጠርሙስ ውስጥ ብናስቀምጠው ምንም ነገር አይከሰትም አይፈጠርም ሁሉም ሰላም ፣ ነገር ግን ጠርሙሱን ከነበረበት ቦታ አንስተን በኃይለኛ ብንበጠብጠው እና መልሰን ብናስቀምጠው ጉንዳኖቹ እርስ በእርስ መገደል እና መዋጋት ይጀምራሉ ፡፡ እውነተኛው ጠላት ጠርሙሱን ያናውጠው ሰው ቢሆንም ቀዮቹ ጥቁር ጠላት እንደሆነ ያምናሉ ጥቁር ደግሞ የጥቁሮቹ ጠላት ቀዮቹ እንደሆኑ ነው የሚያምኑት ፡፡ በሕብረተሰቡ ውስጥም ተመሳሳይ ነው ፡፡

ወንዶች እና ሴቶች
ግራ እና ቀኝ
ሀብታምና ድሃ
እምነት ከሳይንስ
ሐሜት ፣ ወሬ ፣ ወዘተ ...

እርስ በእርሳችን ከመዋጋታችን በፊት እራሳችንን መጠየቅ አለብን-ጠርሙሱን ያናወጠው ማነው?



╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
28 views17:59
Open / Comment
2021-05-16 09:47:36
ቀን / 8 9 2013 እሁድ

የሳምንቱ የቻናሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ……………


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
149 views06:47
Open / Comment
2021-05-16 07:17:34
ቀን / .8 9 2013 እሁድ

የሳምንቱ የቻናሉ የፊልም ግብዣ ………




Sweetness In The Belly :-

የፊልሙ ዘውግ ድራማ ሲሆን መነሻ ሃሳቡም Sweetness In The Belly ተብሎ ከተፃፈው የካሜላ ጊባ መፅሃፍ ነው።

የሃገራችን ታዋቂ አርቲስቶች እና በአለም አቀፍ ደረጃ በስራቸው ዝናን ያተረፉ እነ ዘሪቱ ከበደ ፣ እድልወርቅ ጣሰው ፣ አብራር አብዶ ፣ ዳኮታ ፋኒግ ፣ ኩናል ናያር የመሳሰሉ ተሳትፈውበታል

መቼቱ 1960 አካባቢ በኢትዮጵያ ፣ በሞሮኮ እና በእንግላንድ ያደረገ ፤ አንዲት ስደተኛ እንግሊዛዊ በአፍሪካውያን በማደጎ ባደገች እንስት ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን እድገቷን ፍቅሯን ፣ ተስፋዋን ፣ እምነቷን የምትፈተንበት እና ለማልፍ የምትታገልበትን ትይንት ያሳየናል ። በወቅቱ የነበረውን አብዮት እና አብዮተኞችንም እምነት እና ሃሳብ ያሳየናል።

ለእምነት መትጋትን ፣ ለፍቅር መኖርን ፣ ተስፈኝነትን ፣ ለህይወት ታጋይነትን በብዛት እንማርበታለን !!

ከሳውንድ ትራክ ጅምሮ በጥንቃቄ የተሰራ በመሆኑ በማየትዎ እሁድዎን ያሳምሩበታል............

እንደምትወዱት አልጠራጠርም !

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
160 views04:17
Open / Comment